137939 intellectual property/ invention
የ ኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት በህጉ አግባብ በሁለት ኢንዱስትሪዊ ንድፎች መካከል ተመሣሣይነት አለ ወይስ የለም የሚለውን ለመለየት የአከራካሪውን ንድፍ አዲስነት ለመወሰን የኢንዱስትሪያዊ ንድፉ ዋና ዋና ባህሪያት በመለየት በኢትዮጵያ ወይም በውጪ ከታወቁ ተመሳሳይ ንድፎች የተለየ ወይም ተመሳሳይነት ያለው ስለመሆኑ በዘርፉ ያለውን የዳበረ እውቀት እና ልምድ መሰረት በማድረግ ማጣራት አድርጎ ውሳኔ መስጠት ያለበት ስለመሆኑ የአነስተኛ ፈጠራና ኢንዱስትሪ ንድፍ አዋጅ ቁጥር 123/1987 አንቀጽ 46(1)፤ 48(1) ፤ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤትን ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ ቁጥር 320/1995
136024 contract law/ rent of business
የ አገልግሎት ድርጅት ያከራየ ወገን ያከራየው ድርጅት ተገቢውን አገልግሎት እንዳይሰጥና ታሽጎ እንዲቆይ ለፍርድ ቤት ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ እግድ የተሰጠ በሆነበት እና ተከራዩም ከድርጅቱ ገቢ ባላገኘበት ሁኔታ ድርጅቱ ታሽጎ ለቆየበት ጊዜ ተከራይ የኪራይ ክፍያ እንዲከፍል የማይገደድ ስለመሆኑ፡
127459 contract law/ administrative contract/arbitration
የ አስተዳደር መስሪያ ቤቶች ውልን የሚመለከቱ ጉዳዮች በግልግል ዳኝነት (አርቢትሬተር) እንዳይዳኙ የተጣለው ገደብ ወይም ክልከላ ገላጋይ ዳኛ (አድጁዲኬተር) ጋር በተያያዘም ተፈጻሚነት ያላቸው ስለመሆኑ፡- የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 315/2/፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1678/ለ፣3131 እና 3132/ለ/Download Cassation Decision
124725 contract law/ urban land lease/ unlawful object/ Tigray
በሊዝ አዋጅ ቁጥር 272/94 እና አዋጁን ለማስፈጸም በወጣዉ የትግራይ ክልል ደንብ መሰረት የአምልኮ ቦታዎች በመንግስት የሚሰጡ መሆናቸዉን ቢደነግጉም ከግለሰቦች እንዳይገዛ በግልጽ ክልከላ የማያደርግ ስለመሆኑ፡- አንድ ውል ህገወጥ ነው በሚል ምክንያት ፈራሽ ሊሆን የሚችለው የውሉ መሰረት የሆነው መብትና ግዴታ በህግ በተከለከለ ነገር ላይ መደረጉ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ፣ ሊዝ አዋጅ ቁጥር 272/94 እና አዋጁን ለማስፈጸም የወጣ የትግራይ ክልል ደንብ ቁጥር 62/2002 እና የፍትሐብሄር ህግ አንቀጽ 1716Download Cassation Decision
Ethiopian Law, Simplified
Access legislation, case law, legal articles, and practical resources in one place. LawEthiopia helps lawyers, judges, students, researchers, and citizens find reliable legal information quickly.