partition of common property

  • የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሠራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ የወሰነውን ጉዳይ በይግባኝ ሲያይ የህግ ስህተት መኖሩን እና አለመኖሩን ከማረጋገጥ ባለፈ የፍሬ ጉዳይ እና የማስረጃ ምዘናን በተመለከተ የማየት እና የማረም ስልጣን የሌለው ስለመሆኑ፣

     

    አንድ አሠሪ የሠራተኛ ቅነሳ በሚል ምክንያት ሠራተኞችን ከሥራ ሲያሰናብት በአዋጁ የሠራተኛን ቅነሳ በተመለከተ የተቀመጡትን

    ...
  • በጋብቻ ጊዜ የተፈራ የባልና ሚስት የጋራ የሆነ የአክስዮን ድርሻ በፍቺ ጊዜ በአይነት ሊከፋፈል የሚችል ስለመሆኑ፣

     

    የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ  91 እና 92

    ...

  • Civil procedure

    Execution of judgment

    Family law

    ...
  • የባልና ሚስት ጋብቻ ፈርሶ የጋራ የሆነ ንብረት  ክፍፍል በሚፈፀምበት ጊዜ በፍ/ሕጉ ላይ የተቀመጡት በቅድሚያ የመግዛት መብት ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት የሌላቸው ስለመሆኑ

     

    የፍ/ሕ.ቁ. 1386፣1388፣1391፣1392፣1393፣(1)፣1397

    ...

  • የዲፕሎማቲክ ግንኙነቶችን ስምምነት ልምድን ለማክበር ሲባል የውጭ ዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖችና ኢትዮጲያዊያን ሠራተኞቻቸው የሚያደርጉት የቅጥር ግንኙነት ላይ የአሠሪና ሠራተኛ ሕግ ተፈፃሚ የማይሆን ስለመሆኑ፡-

     

    የተባበሩት መንግስታት አካል የሆነ ድርጅት የተባበሩት መንግስታት ጥቅምና የተለየ ከለላን በተመለከተ በተደነገገ ሥምምነት በማንኛውም የመንግስት ፍ/ቤቶች ተከሶ

    ...
  • አንድ ጋብቻ ሲፈርስ ንብረት ክፍፍልን በሚመለከት በእርቅ ውል ስምምነት በሽማግሌ የተደረገው እርቅ በፍ/ቤት ተመዝግቦ ከተዘጋ በኋላ እንደገና እንደ ባልና ሚስት አብረን እየኖርን ስለነበር በድጋሚ የንብረት ክፍፍል ይደረግ የሚል ጥያቄ አግባብነት ያለው ስላለመሆኑ፣

     

    የሰ/መ/ቁ. 105054

    ታህሳስ 22 ቀን 2008ዓ/ም

    ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ

     

    ባልና ሚስት በጋብቻ ዉስጥ ያፈሩት ቤት ፍቺን ተከትሎ እንዲከፋፈሉ ዉሳኔ ተሰጥቶ በአፈጻጸም ሂደት አንደኛው ወገን ድርሻ ከፍሎ ለማስቀረት የጠየቀና የተወሰነ ገንዘብ ብቻ ይዞ ቀርቦ ቀሪዉን ለመክፈል ጊዜ ከመጠየቅ በቀር ግዥዉን ለመፈጸምና የቅድሚያ ግዥ መብቱን በጊዜው ሳይጠቀም ከቀረ የቅድሚያ ግዥ መብቱ ሊጠበቅ የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ
    በፍ/ብ/ሥ/ስ/ሕ/ቁ 430(1)

    Download here

  • ከንብረት ክፍፍል ጋር በተያያዘ በዋናው ጉዳይ አከራካሪ የሆነው ንብረት መካፈል ከተቻለ እንዲካፈል ካልሆነ ደግሞ በባለሙያ ተገምቶ እንዲካፈሉ በሚል የተሰጠን ፍርድ መነሻ በማድረግ የአፈፃፀም ችሎት /ፍ/ቤት/ ከተከራካሪ ወገኖች መካከል አንደኛው ግምቱን ከፍለው ንብረቱን እንዲያስቀሩ በሚል ትዕዛዝ ለመስጠት የማይችል ስለመሆኑ

    Cassation Decision no. 23733

  • አንድ ወንድ ሁለት ሚስቶች ጋር ተጋብቶ በሚገኝ ጊዜ የንብረት ክፍፍል ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የፌዴራል የተሻቫለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 102(1),86(1),62(1),63(1) የአማራ ብ/ክ/መ/የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 113(1),97(1),73(1),74(1)

    Download Cassation Decision

  • የጋብቻ ፍቺን በተመለከተ በፍ/ቤት የተሰጠ ውሣኔ ከሌለ በስተቀር የባልና ሚስት የጋራ ንብረትን አስመልክቶ የፍቺ ውጤት የሆነውን የክፍፍል ጥያቄ በፍ/ቤት ማቅረብ አይቻልም ለማለት የሚያስችል የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.213/92 አንቀፅ 76

    Download Cassation Decision

  • አንድን ተቋም ወክሎ ውል ለመዋዋል በህግ ስልጣን የተሰጠው ሥራ አስኪያጅ ስልጣኑን ለሌላ ሰው በህግ ተቀባይነት ባለው ሁኔታ አስተላልፎ ውል የተደረገ እንደሆነ ተቋሙ በሥራ አስኪያጁ በራሱ በመፈረም ውል አላደረገም በሚል ምክንያት ብቻ በውሉ አንገደድም ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1731 2274 2214(1 2215(3),2180)

    Download Cassation Decision

  • የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል ጋር በተገናኘ አንድን የጋራ ንብረት በዓይነት ለመካፈል ተጋቢዎቹ ከስምምነት ላይ ለመድረስ ያልቻሉ እንደሆነና ሁለቱም የቅድሚያ ግዢ መብት ጥያቄ ያቀረቡ እንደሆነ ንብረቱ ለጨረታ ቀርቦ እንዲሸጥ በማድረግ ገንዘቡን መካፈል ያለባቸው ስለመሆኑ፣ የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ብ/መ/ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 75/96 አንቀጽ 103(1)

    Download Cassation Decision

  • አንድን የማይንቀሳቀስ ንብረት በተመለከተ የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ነው በሚል ፍርድ ከተሰጠ በኋላ ክፍፍሉን በተመለከተ ጥያቄ የቀረበለት የአፈፃፀም ችሎት ንብረቱ ሰነድ አልባ ነው የሚል ምክንያትን ብቻ በመያዝ ለአፈፃፀም የቀረበውን መዝገብ በመዝጋት የሚሠጠው ትዕዛዝ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 225(2),423,392(1),371(1)

    Download Cassation Decision