constitution (cassation)

  • በወንጀል ተጠርጥሮ በህግ ከለላ ስር የሚገኝን ተጠርጣሪ በዋስትና የመለቀቅ ጥያቄ ባነሳ ጊዜ ተጠርጣሪው በከተማው ውስጥ ቋሚ የመኖሪያ /የመታወቂያ/ አድራሻ የለውም በማለት የዋስትና መብቱን መከልከል ህገ መንግስታዊ ስላለመሆኑ፣ አንቀጽ 19/6/፣ 25 እና የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 69/ሀ/

    Download Cassation Decision

  • በ ትምህርት ደረጃው ከፍተኛ የሆነና በባህሪው ለህብረተሰብ አርአያ ሊሆን የሚገቡ ሰዎች ፍፁም ነውረኛ በሆነና ጨካኝነት በተሞላበት ሁኔታ የፈፀሙት ከባድ የወንጀል ድርጊት የወንጀል አፈጻጸሙን ከባድነት እና የወንጀለኛውን አደገኛነት የሚያሳይ በሆነ ጊዜ ወንጀለኛው ላይ የቀረበ የቀደመ የወንጀል ሪከርድ ያለመኖር ወንጀለኛው ጥሩ ፀባይ ወይም መልካም ፀባይ ያለው ነው የሚል ግምት ለመውሰድ የማያበቃ ስለመሆኑ፣ -የወ/ህ/ቁ. 184/1/ሀ/ እና ለ ቁ. 539 ቁ. 671/1/0/ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ. 2/2006 የኢ.ፌ.ዲ.ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት በአንቀጽ 15 እና የወ/ህ/ቁ. 117

    Download Cassation Decision

  • በፍርድ ቤት የቀረበ ጉዳይ የክስ ምክንያት አለው ብሎ ለመወሰን የሚቻለው በክሱ ላይ የተገለፀው ነገር ቢረጋገጥ ከሳሹ የጠየቀውን ዳኝነት ለማግኘት ሕግ የሚፈቅድለት የሆነ እንደሆነ ስለመሆኑ፡- ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በህግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብ እና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ፡- የኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37(1)

    Download Cassation Decision

  • በ ከተማ አስተዳደር ወይም በቀበሌ ያላግባብ የተያዘን የምርጫ ቤት ለማስመለስ የሚቀርብን ክስ የማየት ስልጣን በህግ ለሌላ የመንግስት አካል ባልተሰጠበት ሁኔታ መደበኛ ፍርድ ቤቶች የማየት ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ፡- ኢ.ፊ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 37

    Download Cassation Decision

  • አንድ ተከሳሽ በሕግ አግባብ መጥሪያ የደረሰዉ እና እርሱ በሌለበት ዉሳኔ መሰጠቱን ማወቁን አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ባልተረጋገጠበት  ሁኔታ በሌለሁበት የተሰጠዉ ፍርድ ተነስቶ የመከላከያ መልስ ላቅርብ በማለት የሚያቀርበውን አቤቱታ በህግ በተቀመጠው አንድ ወር ጊዜ ዉስጥ አልቀረበም በሚል ምክንያት ብቻ መከላከያ መልስና ክርክር አቅርቦ የመሰማትና ፍትሕ የማግኘት ሕገ መንግስታዊ መብት መንፈግ ያልተገባና ህጋዊነት የሌለው ስለመሆኑ፡- 

    የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 37፣የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78፣95 /2/

    Download here

  • አንድ ተከሳሽ በሕግ አግባብ መጥሪያ የደረሰዉ እና እርሱ በሌለበት ዉሳኔ መሰጠቱን ማወቁን አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ባልተረጋገጠበት  ሁኔታ በሌለሁበት የተሰጠዉ ፍርድ ተነስቶ የመከላከያ መልስ ላቅርብ በማለት የሚያቀርበውን አቤቱታ በህግ በተቀመጠው አንድ ወር ጊዜ ዉስጥ አልቀረበም በሚል ምክንያት ብቻ መከላከያ መልስና ክርክር አቅርቦ የመሰማትና ፍትሕ የማግኘት ሕገ መንግስታዊ መብት መንፈግ ያልተገባና ህጋዊነት የሌለው ስለመሆኑ፡- 

    የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 37፣የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78፣95 /2/

    Download here

  • ባ ል እና ሚስት በጋራ ሲጠቀሙበት የነበረ መሬት ጋብቻው በአንደኛው ተጋቢ ሞት የተቋረጠ ቢሆንም ሌላኛው ተጋቢ በሌላ ህጋዊ ምክንያት መብቱ እስካልተቋረጠ ድረስ ይዞታው በስሙ ተመዝግቦ ደብተር ለማግኘት እና በይዞታው ለመጠቀም የሚችል ስለመሆኑ፣ ሴቶች መሬትን በመጠቀም፤በማስተላለፍ፤በማስተዳደርና በመቆጣጠር ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት ያላቸዉ ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕ/መ አንቀጽ 35/7/፣ የኦሮሚያ የገጠር መሬት አዋጅ ቁ. 130/99 አንቀጽ 6/3/ እና ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 15

    Download Cassation Decision

  • ሰ በር ችሎቶች ሥነ ሥርዓታዊ የሆነ የህግ ጥያቄን ብቻ ለማየት ስልጣን እንዳላቸው ግንዛቤ በመውሰድ በአንድ ጉዳይ ላይ የተሰጠ ውሳኔ ስነ-ስርዓታዊ ሕጎችን መሰረት አድርጎ የተሰጠ መሆን ያለመሆኑን መመርመር አንጂ ከዚህ ውጪ መደበኛ ሕጎችን መሰረት አድርገው በሸሪዓ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ሊመረምሩ የሚችሉበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፡- በኢ.ፌ.ዲ.ሪፐብሊክ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ))፣ 80(3(ለ)) እና አዋጅ ቁጥር 53/94 እና አዋጅ ቁጥር 188/1992 አንቀጽ 6

    Download Cassation Decision

  • አ ንድ የመሬት ሽያጭ ውል ህገ ወጥ ውል መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ ገዥ ወገን በመሬቱ ላይ የሰራው ቤት በሻጭ ፈቃድ እንደተሰራ ተደርጎ የህግ ግምት የሚወሰድበት አግባብ የማይኖር ስለመሆኑ የኢፌድሪ ህ/መ አንቀፅ 40 (3) እና የፍ/ብ/ህ ቁጥር 1678 (ለ) እና 1716

    Download Cassation Decision

  • የከተማ ይዞታን የማስተዳደር ስልጣን በህግ አግባብ የተሰጠው አካል ስልጣንና ኃላፊነቱን በህግ አግባብ አልተወጣም የሚል ክርክር ያለው ወገን ጉዳዩን ለፍ/ቤት የማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ
    የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 37፣ 40(3)(4)፣79(1) እና 78(4)

    Download here

  • በወንጀል ጉዳይ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ አዲስ የወጣ ህግ ተከሳሹን የሚጠቅም በሆነ ጊዜ ተከሳሹ አዲሱ ህግ ተፈፃሚ እንዲሆን አቤቱታ ባቀረበ ጊዜ አዲስ የወጣው ህግ ተፈፃሚ እንዲሆን መደረግ ያለበት ስለመሆኑና በዚሁ ጉዳይ አቤቱታ የቀረበበት ጉዳይ በባህሪው እንደመደበኛ የክርክር ጉዳይ የሚታይ ሳይሆን በቀረበ ጊዜ ሊስተናገድ የሚችል በመሆኑ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የቀረበ አቤቱታ ነው በማለት ተቀባይነት የለውም የማይባል ስለመሆኑ 

    የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 22(2)፣ የወ/ሕ/አንቀጽ 6 እና 9(1)፤ ዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት አንቀጽ15/1/ 

    Download here

  • አንድ ተከሳሽ የቀረበበትን ክስና ማስረጃ በመመርመር ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ መልሱን አዘጋጅቶ እንዲያቀርብ የታዘዘው እና ቀጠሮ የተሰጠው ከ10 ቀን ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከሆነ የተከሳሹን የመከላከልና የመከራከር የመሰማት መብቱን የሚነፍግ በመሆኑ በቂ ጊዜ ተሰጥቶት የመከላከያ መልሱን እና ክርክሩን እንዲያቀርብ መደረግ ያለበት ስለመሆኑ
    ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37፣
    የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.240[2] 

    Download here

  • አንድ ተከሳሽ ጥፋተኛ ቢባል በቀላል እሥራት፤ ከ12 ዓመት በታች በሆነ ጽኑ እሥራት ወይም ከአሥራ ሁለት ዓመት በላይ በሆነ ጽኑ እሥራት ሊቀጣ የሚችል በመሆኑ ተመራጭ የሚሆነው የፍርድ ሂደት ተከሳሹ በተከሰሰበት ድንጋጌ የተቀመጠው ከፍተኛ ቅጣት ሊቀጣ ይችላል ብሎ ከወዲሁ በማሰብ ጉዳዩን በሌለበት እንዲታይ ማድረግ ሳይሆን የተከሳሽ በችሎት ተገኝቶ የመከራከር መብት ከሚጣስ ይልቅ ተከሳሽ እስኪገኝ ድረስ የፍርድ ሂደቱ እንዳይካሄድ በማድረግ ስለመሆኑ
    የኢፌዲሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 20/4፣ ዓለም ዓቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት አንቀጽ 14፣የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 162(2) 

    Download

  • የአስተዳደር አካል በክርክር ሂደት በፍርድ አደባባይ ከተረታ በኋላ ተከራካሪው ወገን መብት ያገኘበትን ካርታ በማምከን አስቀድሞ የተሰጠው ውሳኔ እንዲለወጥለት የሚያቀርበው አቤቱታ ውድቅ ሊደረግ የሚገባው ስለመሆኑ 
    የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 9(1) (2)፤ 12/1 እና 40/1 ድንጋጌዎች እና የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1195 እና 1196 

    Download

  • በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 78 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ ነፃ እና ገለልተኛ የዳኝነት አካል በየደረጃው ማቋቋም ያስፈለገው ሰዎች ነፃና ገለልተኛ በሆነ አካል ፊት ቀርበው መብታቸውን በማስከበር ዳኝነታዊ መፍትሄ ማግኘት እንዲችሉ፣ በህግ ፊት እኩል ጥበቃ እና ፍትህ የማግኘት መብታቸውን ለማስከበር እንዲሁም ሌሎች የሰዎችን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ለማስከበር በመሆኑ የክልል ፍርድ ቤቶች በህግ በታወቀ ምክንያት በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን የውክልና ሥልጣን መጠቀምና ለዜጎች ፍትህ መስጠት በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ሲሆኑ እና ጉዳዩም የፌደራል ጉዳይ ሲሆን የሰዎችን ፍትህ የማግኘት መብት፣ እኩል የሕግ ጥበቃ የማግኘት መብት እና ሌሎች መብቶችን ለማስከበር የፌደራል ፍርድ ቤቶች በቀጥታ ጉዳዩን ተቀብለው የመዳኘት ሥልጣን የሚኖራቸው ስለመሆኑ

    የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 25፣ 37/1፣ እና አንቀጽ 78 እና ተከታዮቹ፤ የተባበሩት መንግስታት የሰበዓዊ መብቶች መግለጫ (Universal Declaration of Human Rights) አንቀጽ 7፣8 እና 10 እንዲሁም የዓለም አቀፍ የሲቪልና ፓለቲካ መብቶች ቃልኪዳን (International Covenant on Civil and Political Rights/ICCPR) አንቀጽ 2(3/ሀ እና ለ)፣ 26  

    Download

  • በፍ/ብ/ህጉ ውስጥ “ከዘር የወረደ ርስት” በሚል የተቀረበው አገላለጽ በህገ-መንግስቱ የተሻረ ወይም ተፈፃሚነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1000/2/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 40

    Cassation Decision no. 30158

  • የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ በሰበር ችሎት የተሻረ ሲሆን በውሣኔው መብቱ የተነካ ወገን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 358 መሰረት ለሰበር ችሎት መቃወሚያ ማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ፣ መብታቸው የተነካ ወገኖች ሊስተናገዱ ስለሚችሉበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 35ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ) አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 1

    Download Cassation Decision

  • አንድን ጉዳይ ተመልክቶ ዳኝነት ለመስጠት ሥልጣን የተሰጠው ለሌላ የዳኝነት አካል ከሆነ ፍ/ቤቶች ጉዳዮን የማየት ስልጣን የማይኖራቸው ስለመሆኑ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ስልጣን ሥር የሚወድቅ አይደለም በሚል በኤጀንሲው የተረጋገጠ ጉዳይን ጉዳዩን የማየት ስልጣን ለሌላ የዳኝነት አካል የተሰጠ ነው በሚል ክርክር እስካልቀረበ ድረስ ፍ/ቤቶች ተቀብለው ማስተናገድ የሚችሉ ስለመሆናቸው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 231/1//ለ/, 9/2/, 244/3/ እና 328/3/ አዋጅ ቁ. 110/87 አዋጅ ቁ. 47/67

    Download Cassation Decision

  • ከዘር የወረደ ርስት ነው በሚል የመሬት ባለቤት ለመሆን የሚቀርብ ክስ ህገ-መንግስታዊ ያልሆነና ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • ከፌዴራል መንግስት የልማት ድርጅት ሠራተኞች የሚሰበሰብ የሥራ ግብር ምንም እንኳን ሥራው የሚካሄደው በክልሎች ቢሆንም ወይም ሠራተኞቹ የክልል ነዋሪዎች ቢሆኑም ገቢ የሚደረገው ለፌዴራሉ መንግስት ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 96(3) አዋጅ ቁ. 33/85 አንቀጽ5(2)(ሐ) ደንብ ቁ. 109/96

    Download Cassation Decision

Page 2 of 4