በሥራ ላይ ከሚደረስ አደጋ ጋር በተያያዘ አደጋው የደረሰው ከሥራ ሰዓትና ከሥራ ቦታ ውጪ ከሥራው ጋር ግንኙነት በሌለው አጋጣሚ እና ከአሰሪው ትዕዛዝ ሳይኖር እንደሆነ አሰሪው ለደረሰው ጉዳት ኃላፊነት የማይኖርበት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 95, 96, 97
Download Cassation Decision
በባል ወይም በሚስት ለጋራ መተዳደሪያቸው በሚል ከሚካሄድ የንግድ ሥራ ማስኬጃ ጋር በተያያዘ የተገባ ዕዳ የተጋቢዎች የጋራ እዳ እንደሆነ የሚቆጠር ስለመሆኑ የንግድ ህግ ቁ.19 የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.213/92, አንቀፅ 70
ከቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጋር በተያያዘ የመብቱ ተጠቃሚዎችና የመብቱ አድማስ የቅጅ መብት እንዲከበር ለመጠየቅ መሟላት ስለሚገባቸው ነገሮችና መብቱ እንደተጣሰ የሚቆጠርበት አግባብ አዋጅ ቁ. 410/96 አንቀፅ 7, 9-19, 2(6)
በወንጀል ጉዳይ የተከሰሰ ሰው የሚያነሳው የጤና ችግር ከዋስትና መብት አኳያ ሲታይ ስላለው ህጋዊ ጥበቃ
የተጨማሪ እሴት ታክስን ተግባራዊ ለማድረግ በወጣው አዋጅ ቁ.285/94 አንቀጽ 49 መሰረት በወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ተከሳሽ ላይ ቅጣት ሊጣል ስለሚችልበት ሁኔታ፣ አዋጅ ቁ.285/94 አንቀጽ 49,47,50(2) የወ/ህ/አ 2(2)
አንድን ተቋም ወክሎ ውል ለመዋዋል በህግ ስልጣን የተሰጠው ሥራ አስኪያጅ ስልጣኑን ለሌላ ሰው በህግ ተቀባይነት ባለው ሁኔታ አስተላልፎ ውል የተደረገ እንደሆነ ተቋሙ በሥራ አስኪያጁ በራሱ በመፈረም ውል አላደረገም በሚል ምክንያት ብቻ በውሉ አንገደድም ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1731 2274 2214(1 2215(3),2180)
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በአንድ ወቅት የሰጠውን የህግ ትርጉም በሌላ ጊዜ በተመሳሳይ ጭብጥ ላይ የተለየ የህግ ትርጉምና የተለየ አቋም መያዙ በቀደመው የህግ ትርጉም መሠረት ዳኝነት የተሰጠበት ጉዳይን እንደገና እንደ አዲስ እንዲስተናገድ ለማድረግ የማያስችል ስለመሆኑ፣
ብዙ ሰዎች በአንድ ጉዳይ ለደረሰ ጉዳት ካሣን እንዲከፍሉ የተገደዱ እንደሆነ እያንዳንዳቸው ለደረሰው አጠቃላይ ጉዳት ኃላፊ የሚሆኑ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2155(1)
በፎርክሎዠር ህግ መሰረት የሚከናወን ሐራጅ በፍ/ቤት የሚሰረዝበት አግባብ ስላለመኖሩና ሐራጁ በህግ አግባብ ያለመከናወኑ በባንኩ ላይ የጉዳት ካሣ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.97/90 አንቀፅ 7, አዋጅ ቁ.216/92 የፍ/ብ/ሥ/ሣ/ህ/ቁ 447(1), 423(2) የፍ/ብ/ህ/ቁ 2143(1), 2027, 2028, 2035
የአዲስ አበባ ከተማ ነክ ፍ/ቤቶች የከተማው አስተዳዳር የሚያስተዳድራቸውን የንግድ ቤቶች ባለቤትነትን በተመለከተ በግለሰቦች መካከል የሚነሱ ክርክሮችን ለማየት ስልጣን የሌላቸው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 361/95 አንቀጽ 41(1)(ረ) አዋጅ ቁ. 408/96 አንቀጽ
ህግ ስልጣን በተሰጠው የመንግስት አካል በግልጽ በተላለፈ መመሪያ መሰረት የሠራተኛን የሥራ ውል ያቋረጠ አሠሪ የሥንብትና የማስጠንቀቂያ ክፍያ እንዲከፍል የሚገደድበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 28, 12(1)(ሀ)
Page 90 of 114