Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

 • ከውል ውጪ በሆነ ግንኙነት አንድ ሰው በሌላ ሰው ንብረት ላይ ጉዳት ባደረሰ ጊዜ ጉዳት የደረሰበት ንብረት ባለቤት ለንብረቱ የመድን ዋስትና የገባ ሆኖ የመድን ተቋሙ በመድን ውሉ መሠረት ጉዳት ለደረሰበት ወገን የጉዳት ካሣ በመክፈል በጉዳት አድራሹ ንብረት ባለቤት ላይ ብቻ ክስ በመመስረትና ጉዳቱን በቀጥታ ያደረሰውን ሰው በመተው ጉዳቱ ለደረሰበት ሰው የከፈለውን የጉዳት ካሣ ክፍያውን እንዲከፍለው ለመጠየቅ ስለመቻሉ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1677, 1896, 2081, 18, 2156 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 36(2)

  Download Cassation Decision

 • የክርክሩ ገንዘብ መጠን ከአምስት ሺህ ብር በታች በመሆኑ ምክንያት ብቻ ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ጋር በተገናኘ የሚቀርብን ክርክር የቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤቶች አይተው ለመወሰን ስልጣን አላቸው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 138, 142 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 9(1), 231(1)(ለ), አዋጅ ቁ. 416/96 አንቀጽ 41(1),

  Download Cassation Decision

 • ከጉምሩክ ህግና አፈፃፀም ጋር በተያያዘ በኮንትሮየባንድ ወንጀል ተጠርጥሮ በጉምሩክ ተቋም በቁጥጥር ሥር እንዲውል የተደረገ የንግድ ተሽከርካሪን አስመልክቶ ለንብረቱ ባለቤት የተቋረጠ ጥቅም (ገቢ) እንዲከፈል ሲወሰን የካሣውን መጠን ለመወሰን የተሽከርካሪውን ዓመታዊ የተጣራ ገቢ በተመለከተ ባለንብረቱ ለሚመለከተው የመንግስት አካል በህጉ አግባብ ያሳወቀውን የገቢ መጠን ከሌሎች አግባብነት ካላቸው ማስረጃዎች ጋር በማገናዘብና መሠረት በማድረግ ሊወሰን የሚገባ ስለመሆኑ፣  በአንድ የመንግስት ባለስልጣን ተረጋግጦ የተሰጠ የሰነድ ማስረጃ በህጉ መሠረት ተቃውሞ ቀርቦበት ዋጋ የሌለው ስለመሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር ማስረጃው በማስረጃነት ዋጋ ሣይሰጠው ሊታለፍ የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2010, 2011, 2090, 2091, 2141, 2152, 2153 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 136, 138, 180 (1

  Download Cassation Decision

 • ከውርስ ሀብት ክፍፍል ጋር በተገናኘ የውርስ ሀብት ተጣርቶና ሪፖርት ቀርቦ በመጽደቁ መነሻነት ሀብቱ ተከፋፍሎ ከተፈፀመ በኋላ ወራሾቹ ዋጋ ያለው የወራሽነት ማስረጃ ሣይኖራቸው ውርሱን ወይም ከውርሱ አንዱን ክፍል በእጁ አድርጓል በሚል እውነተኛ ወራሽ ወራሽነቱ እንዲታወቅለትና የተወሰዱበት የውርስ ንብረቶች እንዲመለሱለት በሚል ለመጠየቅ የሚችለው ተገቢውን የዳኝነት ክፍያ በመክፈል አዲስ ክስ በመመስረት እንጂ ክፍፍሉ ተፈጽሞና ውሣኔ አግኝቶ የተዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 996(1), 998(1), 999

  Download Cassation Decision

 • አንድ ፍርድ ቤት ክርክርን በሚሰማበት ወቅት የሚሰጠው ጊዜያዊ አገልግሎት ያለው ትዕዛዝ (Interlocutory order) ላይ በመነጠል ክርክር የሚካሄድበት ዋናው ጉዳይ ላይ ውሣኔ ከመስጠቱ በፊት ይግባኝ ሊቀርብበት የሚችለው የተሰጠው ትእዛዝ በባህሪው የሰውን መታሰር ወይም የንብረት ማስተላለፍን ወይም ስም ማዞርን ጉዳይ በተመለከተ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 320(3)(4)

  Download Cassation Decision

 • ነፍሰጡር (እርጉዝ) የሆነች ሴትን ሆዷ ላይ በመምታት ጽንሱ እንዲሞት ማድረግ ድርጊቱን በፈፀመው ሰው ላይ በግድያ ሙከራ የወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትል ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 27(1), 581(ለ), 540

  Download Cassation Decision

 • ባለ አምስት ዳኞች የሚሰየሙባቸው የክልል ፍርድ ቤቶች ሰበር ሰሚ ችሎቶች በአጣሪው ችሎት ጉዳዩ ያስቀርባል በሚል በተመለከተው ነጥብ (ጭብጥ) ሳይገደብ ሌላ (ሌሎች) ጭብጦችን በመመስረት ክርክሩ እንዲሰማ በማድረግ ውሣኔ ለመስጠት ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ፣

  Download Cassation Decision

 • በሕግ ተለይቶ የተወሰነ የይርጋ ጊዜ የመቋረጥ እና ያለመቋረጥ ጉዳይ አከራካሪ ነጥብ ሆኖ ሊነሳ የሚችለው የይርጋውን መቆጠር ያቋርጠዋል የተባለው ምክንያት የተከሰተው የይርጋው ጊዜ ከመሙላቱ በፊት በሆነ ጊዜ እንጂ የይርጋው ጊዜ የሞላ ወይም ያለፈ በሆነ ጊዜ ጭምር ስላለመሆኑ ፡- የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.1851

  Download Cassation Decision

 • የሥራ ኃላፊነቱን ባለመወጣት ተገቢነት የሌላቸው ሰዎችን ወደ አሰሪው ድርጅት ውስጥ ዘልቀው እንዲገቡ በማድረግ ጥፋት የፈፀመ የጥበቃ ሰራተኛ ወደ ድርጅቱ በገቡት ሰዎች ምክንያት የተፈጠረ የፀጥታና የደህንነት ችግር አልተከሰተም በሚል ምክንያት ብቻ አሰሪው በሰራተኛው ላይ የፈፀመውን የስራ ውል ማቋረጥ ተግባር ህገ ወጥ ነው ሊያስብል የሚችል ስላለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 27(1)(ሸ), 17(1)(ሸ)(ቀ), 14(2)(ሀ)

  Download Cassation Decision

 • ለቼኩ መሰጠት መሰረት የሆነውን ውል እና ለጉዳዩ አወሳሰን ተገቢነት ያለውን ህግ ሳይመለከቱና በተገቢው የክርክር አመራር ስርዓት ፍሬ ነገሩን ሳያጣሩ የሚሰጥ ዳኝነት ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣

  Download Cassation Decision

 • በሌለበት የተሰጠ ውሣኔ እንዲነሣ በቀረበ አቤቱታ መነሻነት ፍ/ቤቱ አስቀድሞ የሰጠውን ውሣኔ ያነሳውና አቤቱታ አቅራቢው ክርክሩን እንዲያቀርብ በድጋሚ እድል ከተሰሠጠው በኋላ የጽሁፍ ክርክሩን ያላቀረበና ክሱ በሚሰማበት ቀጠሮ ያልቀረበ እንደሆነ ክርክሩን እንደገና ለመስማት በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት የከሣሽ ክስና ማስረጃ እንደገና ተመርምሮ ተገቢው ውሣኔ ከሚሰጥበት በቀር እንዲነሣ ትእዛዝ የተሰጠበት የቀድሞው ውሣኔ በቀጥታ ተመልሶ እንደገና እንዲፀና ሊደረግ የሚችልበት የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 78(2), 70(ሀ)

  Download Cassation Decision

 • ከውርስ ሀብት ክፍፍል ጋር በተገናኘ አንድ ሰው ሟች በተውት ኑዛዜ መሠረት የጥሬ ገንዘብ ክፍያ እንዲከፈለው ክስ አቅርቦ ገንዘቡ እንዲከፈል ዳኝነት ከተሰጠ በኋላ በሌላ ግዜ የሟቹ የውርስ ሀብት ይጣራልኝ በማለት የሚያቀርበው የዳኝነት ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣  ኑዛዜን መሠረት አድርጐ የሚቀርብ የኑዛዜ ተጠቃሚት መብት ይረጋገጥልን ጥያቄና የውርስ ይጣራልኝ ጥያቄዎች ተመሳሳይ የሆነ የፍሬ ነገርና የህግ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዬች ስለመሆናቸው፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5(2)

  Download Cassation Decision

 • አንድ ሠራተኛ በስራ ውሉ እና በስራ ደንቡ መሠረት በአሰሪ የተሰጠውን ትዕዛዝ የመፈፀም ግዴታን አለመወጣቱ ስለሚያስከትለው ውጤት፣ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ አንቀጽ 13(2)፣13(7)

  Download Cassation Decision

 • ከህብረት ሥራ ማህበራት ጋር በተገናኘ የማህበር የሥራ ኃላፊዎችን በተመለከተ ገንዘብ አጉድለዋል በማለት ገንዘቡ እንዲከፈል ማህበሩ በኃላፊዎቹ ላይ የሚያቀርበው ክስ አስቀድሞ በእርቅ ካልተቻለ ደግሞ በሽምግልና ሊታይ የሚገባው እንጂ በቀጥታ በመደበኛ ፍ/ቤት ክስ ሊቀርብበት አይችልም ለማለት የማይቻል ስለመሆኑና መደበኛ ፍ/ቤቶች ጉዳዩን አይተው ለመወሰን ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 49(1-4), 47(1), 26(2), 39(1)(ለ)(ሐ), 152 አዋጅ ቁጥር 402/96 አንቀጽ 46 ደንብ ቁጥር 106/96 አንቀጽ 14(ሀ)(ሐ)(መ)

  Download Cassation Decision

 • አንድ ውል በቂ የሆነ እርግጠኛነት ያለውና ህጋዊ የሆነ ጉዳይ ለማከናወን ሊደረግ የሚገባ ስለመሆኑ፣  የመድን ዋስትና ሽፋን የተገባለት ተሽከርካሪ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሆኖ ከትራንስፖርት ጋር በተገናኘ በወጡ ህጐች ከተፈቀደው የመጫን አቅም በላይ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ አደጋ የደረሰበት እንደሆነ መድን ሰጪው የዋስትናውን ሽፋን ገንዘብ ለመድን ገቢው የመክፈል ኃላፊነት የማይኖርበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1678(ለ)

  Download Cassation Decision

 • በመያዣ ውል መነሻነት አንድን የማይንቀሳቀስ ንብረት ከነይዞታው የያዘ ሰው በይዞታው ላይ የንብረቱ ባለቤት ሳይቃወመው ግንባታ የፈፀመ ከሆነ ተጠቃሹ የመያዣ ውል አይፀናም በሚል ተዋዋዬቹ ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ሲደረግ የንብረቱ ባለቤት በመያዣው ይዞታ ላይ የወጣውን የግንባታ ወጪ ግንባታውን ላካሄደው ወገን ለመክፈል የሚገደድ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1818, 2162

  Download Cassation Decision

 • አንድን ክርክር በማስተናገድ ላይ ያለ የክልል ፍ/ቤት በፌዴራል መንግስት የተመዘገበ ተቋም (ድርጅት) አግባብነት ያለው የጣልቃ ገብ አቤቱታ በቀረበለት ጊዜ ጉዳዩን ጣልቃ ገቡን ወደ ክርክሩ በማስገባት አይቶ ለመወሰን ስልጣን የሌለው በመሆኑ ክርክሩ ጣልቃ ገብን ባካተተ መልኩ ለማየት ወደሚችለውና ስልጣን ላለው ፍ/ቤት ጉዳዩ ቀርቦ ሊታይ የሚገባ መሆኑን ገልፆ መዝገቡን መዝጋትና ተከራካሪዎችን ማሰናበት የሚገባ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 5(6),14 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(4) የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ህገ መንግስት አንቀጽ 64(4) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 9, 231(1)(ለ)

  Download Cassation Decision

 • በህግ ፊት የሚፀና ስጦታ ለማድረግ ሰጪው ስጦታ በተደረገበት ንብረት ላይ መብት ሊኖረው የሚገባ ስለመሆኑ፤የባልና የሚስት የጋራ በሆነ ንብረት ላይ አንደኛው ተጋቢ ብቻውን የሚያደርገው ስጦታ ዋጋ የሌለው ስለመሆኑ፣

  Download Cassation Decision

 •  ከወጪና ኪሣራ አወሣሠን ጋር በተገናኘ ከቅን ልቦና ውጪ ለክርክር የተዳረገ ወገን የክርከሩ ረቺ መሆኑ እስከታወቀ ድረስ ቅን ልቦና ከሌላው ወገን በክርክሩ ምክንያት ያወጣውን ወጪ እንዲተካለት በሚል ውሣኔ ሊሰጥ የሚገባ ስለመሆኑ፣  የወጪና ኪሣራ ጥያቄን አስመልክቶ ፍ/ቤቶች በመጠኑ ላይ ለመወሰን በህግ ስልጣን የተሰጣቸው ስለመሆኑና ረቺ የሆነ ወገን ሁል ግዜ ወጪና ኪሣራ እንዲተካለት ሊወሰን ይገባል ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 462-464

  Download Cassation Decision

 • አንድ ክስ ሲቀርብ በክስ ማመልከቻው ላይ መገለፅ ከሚገባቸው ነገሮች መካከል አንዱ የክሱ ምክንያት እና ለክሱ ምክንያት የሆኑት ነገሮችና እነዚሁ የተፈጠሩበት ጊዜና ስፍራ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ8ዐ(2)፣213(1)፣216(1)፣222(1)(ረ)

  Download Cassation Decision