Federal Court Case Tracker

 • Civil procedure

  Execution of judgment

  Family law

  ...
 • Family law

  Rural land law

  Pecuniary effect of marriage

  ...
 •  

  ጋብቻ በአንደኛው ተጋቢ ሞት ምክንያት በፈረሰ ጊዜ የጋራም ሆነ የግል ንብረት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ መጠየቅ እንዳለበት በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1677 መሠረት በቁ. 1845 ላይ የተቀመጠው ይርጋ ተፈፃሚ ስለመሆኑ

  የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1768 1ዐዐ16771845

   

  Cassation 17937

 • በጋብቻ ውል ላይ የግል ተብሎ ያልተመለከተና ጋብቻ ከመፈፀሙ በፊት ግንባታው የተጀመረ ቤት ግንባታው የተጠናቀቀው በጋብቻ ወቅት ከሆነ የጋራ ንብረት ተደርጐ የሚወሰድ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 62(1) , 63(1)

  Cassation Decision no. 25005

 • የባልና ሚስት የጋራ ሃብት ነው በሚል የተወሰነ መኖሪያ ቤት ጋር በተያያዘ አንደኛው ተጋቢ ቤቱ የተሰራበትን መሬት (ቦታ) ከጋብቻው በፊት የተመራ በመሆኑ ሌላኛው ተጋቢ የቤቱን ግማሽ ዋጋ ተቀብሎ እንዲለቅ በሚል የሚሰጥ ውሣኔ የህግ መሠረት የሌለው ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 92

  Cassation Decision no. 25281

 • ጋብቻ ከመመስረቱ በፊት የግል የነበረ ሃብት ከጋብቻ በኃላ የጋራ ከሆነ ንብረት ጋር ተቀላቅሎ በተገኘ ጊዜ የግል የሆነው ንብረት ተለይቶ የግሉ ለሆነው ተጋቢ ሊሰጥ የሚገባ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 5786(1)

  Cassation Decision no. 26839

 • ጋብቻ ፀንቶ ባለበት ጊዜ የጋራ ንብረት የተሸጠ ቢሆንም የሽያጩ ገንዘብ በሙሉ ወይም በከፊል እንደሚገኝ ካልተረጋገጠ ለጋራ ትዳር ጥቅም እንደዋለ የህግ ግምት የሚወሰድበት ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 85 -93

  Cassation Decision no. 27697

 • ተጋቢዎች በጋብቻ ወቅት የተፈራ ቤታቸውን በትርፍነት ለመንግስት ያስረከቡ እንደሆነ የአንደኛው ተጋቢ የግል ንብረት የሆነን ቤት ያለምንም ተጨማሪ ስምምነት የጋራ የሚያደርገው ስለመሆኑ

  Cassation Decision no. 29343

 • ቤት የጋራ ሃብት ነው ከተባለ ቤቱ የተሰራበት መሬት ላይ የጋራ ባለሃብቶቹ እኩል የመጠቀም መብት የሚኖራቸው ስለመሆኑ

  Cassation Decision no. 29402

 • ተጋቢዎች ጋብቻቸው ፀንቶ ባለበት ወቅት የገዙት ንብረት በስማቸው ያልዞረ ቢሆንም እንኳን ንብረቱ የእኔ ነው በሚል የቀረበ የ3ኛ ወገን ተቃውሞ እስካልቀረበ ድረስ ንብረቱ የጋራ ሀብት ተደርጐ የሚወሰድና ሊከፋፈል የሚገባ ስለመሆኑ

  Cassation Decision no. 33411

 • ከጋብቻ በፊት የተፈራ ንብረት ላይ ያለን ዕዳ ለመወጣት ከጋብቻ በኃላ ከባልና ሚስት የጋራ ገንዘብ መከፈሉ ንብረቱን የጋራ ንብረት የማያደርገው ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 62(1) እና 7ዐ(1)

  Cassation Decision no. 35376

 • Family law

  Pecuniary effect of marriage

  Common property

  ...
 • ከጋብቻ በፊት በአንደኛው ተጋቢ ስም የነበረን የግል ንብረት በጋብቻ ወቅት በንብረቱ ላይ መሰረታዊ መሻሻል ቢደረግበትና ይሄው መሻሻል የተደረገው የባለንብረቱ የግል ገንዘብ መሆኑ እስካልተረጋገጠ ድረስ ህጉ ንብረቱ የጋራ ነው የሚል ግምት የሚወስድ ስለመሆኑ፣

  አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀፅ 63(1)

  የሰ/መ/ቁ. 94952

  በኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ መሠረት ባልና ሚስቱ በየግል ያገኟቸውን ንብረትም ሆነ ገንዘብ በግል ይዘው መቀጠል እንደሚችሉ  ሲደነገግ ይህ የግል የተባለው ንብረት የግል ሆኖ ሊቀጥል የሚችለው የግል ይባልልኝ ተብሎ በፍ/ቤት ሲፀድቅ ስለመሆኑ፣

  የኦሮሚያ ክልል የቤተሰብ ህግ ቁ.69/1995 አንቀፅ 741ዐ፣አንቀፅ 74/2

  የሰ/መ/ቁ. 95680

  ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል ሊባልባቸው ስለሚችሉባቸው ሁኔታዎች ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል ተብሎ ከሚታሰብበት ጊዜ አንስቶ በአስር ዓመት ጊዜ ውስጥ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ካልቀረበ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ

   

  የሰ/መ/ቁ.102662

  የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ/ም

  ዳኞች፡-አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ

  አመልካች፡- ወ/ሮ አልማዝ ለሼ- ጠበቃ ኤርሚያስ ደስታ ቀረቡ፡፡ ተጠሪ፡- አቶ በቀለ በላቸው- ወኪል 

  ...
 • በተሻሻለው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የቤተሰብ ህግ መሰረት ባልና ሚስት የጋራ ንብረታቸውን እኩል የማስተዳደር መብት ያላቸውና የጋራ ስምምነት ሳይኖር ንብረትን ለሌላ 3ኛ ወገን በአንደኛው ተጋቢ ፍቃድ ብቻ የተላለፈ ከሆነና ይህንን ስምምነቱን ያልሰጠው ተጋቢ በህጉ በተፈቀደለት ጊዜ ገደብ ውስጥ የይፍረስልኝ ጥያቄውን ካላቀረበ የተፈፀመው ተግባር እንደፀና የሚቆይ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.213/92 አንቀፅ 68፣69

   

  የሰ/መ/ቁ. 103721

  የካቲት 03 ቀን 2008 ዓ.ም

   

   

  አንድ ጋብቻ ሲፈርስ ንብረት ክፍፍልን በሚመለከት በእርቅ ውል ስምምነት በሽማግሌ የተደረገው እርቅ በፍ/ቤት ተመዝግቦ ከተዘጋ በኋላ እንደገና እንደ ባልና ሚስት አብረን እየኖርን ስለነበር በድጋሚ የንብረት ክፍፍል ይደረግ የሚል ጥያቄ አግባብነት ያለው ስላለመሆኑ፣

   

  የሰ/መ/ቁ. 105054

  ታህሳስ 22 ቀን 2008ዓ/ም

  ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ

   

  ባል ወይም ሚስት የጡረታ አበል ተጠቃሚ ሆነው ባሉበት ፍቺ ቢከሰት የጡረታ መብት ተጠቃሚ የሆነው ባል ወይም ሚስት የጡረታ አበል ለባል ወይም ለሚስት ሊያካፍል የሚገባ ስላለመሆኑ ፣ የመንግስት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 345/95 አንቀጽ 35

  Download Cassation Decision

 • የገጠር መሬት እንደሌላው ንብረት በመቁጠር ከቤተሰብ ህጉ አንጻር የሚታይ ስላለመሆኑ ፣ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በአንድ ተጋቢ ስም ተዘጋጅቶ ከተሰጠ በኋላ ጋብቻ ቢፈፀምና ተጋቢዎቹ መሬቱን የጋራ ለማድረግ ሊስማሙ የሚችሉ ስለመሆኑ፣ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 133/1999 አንቀጽ 24/3/ ደንብ ቁ. 151/1999 አንቀጽ 20/6/

  Download Cassation Decision

 • ባልና ሚስት የጋራ የሆነውን የንግድ ድርጅታቸውን መልካም ስም የማከራየት መብትና በቤቱ ውስጥ የሚገኘውን የንግድ ዕቃ የመከፋፈል መብት ያላቸው ስለመሆኑ፣ የን/ሕ/ቁ. 127

  Download Cassation Decision

Page 1 of 3