Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • አሰሪ በግልፅ ባልፈቀደበት ሁኔታ በሁለት ቦታ በተመሳሳይ ጊዜ መስራት ሠራተኛውን የማታለል ተግባር እንደፈፀመ የሚያስቆጥረው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 27(1)(ሐ)

    Download Cassation Decision

  • Download Cassation Decision

    ቀድሞ ይሰራበት የነበረን የሥራ መደብ በመሰረዙ ምክንያት ሠራተኞችን በማሰናበት ፋንታ በክፍያ አነስተኛ ወደሆነ ሌላ የሥራ መደብ እንዲሰሩ ያደረገ አሠሪ ለሠራተኞቹ በቀድሞው ደመወዝ መሠረት እንዲከፍል የሚገደድበት የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ

  • Download Cassation Decision

    የጋራ የሆነን የውርስ ሀብት ከፍቃዱ ውጪ እንዲሸጥ የተደረገበት ወራሽ ከሽያጩ ዋጋ ድርሻውን ለማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1266 1ዐ6ዐ(1)
  • የስጦታ ውል ሊተረጐም የሚገባው በውሉ ውስጥ የሚገኝን አንድ ሃረግ ነጥሎ በማውጣት ሳይሆን የውሉን አጠቃላይ ይዘት በመመልከት ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • ጋብቻ ህጋዊ ውጤት የሚኖረው በህግ አግባብ ተፈፅሟል ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 28(3)

    Download Cassation Decision

  • Download Cassation Decision

    የኮንስትራክሽን ሥራ የሚሰራ ድርጅት የሥራው መጠን በቀነሰ ጊዜ ሠራተኞችን ለማሰናበት የማስጠንቀቂያና ሌሎች የቅነሳ ሥነ-ሥርዓቶችን ሳይከተል ቅነሳ ለማካሄድ የሚችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 3ዐ

  • ዕቃዎችን ለሚያጓጉዝ የጭነት መኪና የተገባ የመድን ዋስትና ጋር በተያያዘ በመኪናው ላይ ተሣፍሮ ሲሄድ ለነበረና አደጋ ለደረሰበት ሰው መድን ሰጪው የጉዳት ካሣ የመክፈል ኃላፊነት የሌለበት ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ከሚያስተዳድራቸው ቤቶች ጋር በተያያዘ በፍርድ ሃይል የኪራይ ውል እንዲዋዋል የሚደረግበት ህጋዊ ምክንያት የሌለ ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • የሕግ ክርክሮችን በሰበር ማየት /ማስተናገድ/ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠ ስልጣን (power) ስለመሆኑ በግልግል ዳኝነት (arbitration) የታየ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተዋዋይ ወገኖች የይግባኝ መብትን ለማስቀረት የሚያደርጉት ስምምነት ጉዳዩን በሰበር ችሎት ከመታየት የማያግድ ስለመሆኑ (ከዚሀ ቀደም በሰበር ችሎት የተሰጠው የሕግ ትርጉም የተለወጠ ስለመሆኑ፡፡) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80/3 (ሀ), አዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 (4), አዋጅ ቁጥር 25/88, የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 350(2) 351 እና 356

    Download Cassation Decision

  • አንድን የሥነ-ጥበብ(ኪነ-ጥበብ) ሥራ ያለባለቤቱ ፈቃድ ኦርጅናሉ ወይም ቅጅው ለህዝብ እንዲታይ ማድረግ የኮፒ ራይት ህግ ጥሰት የሚያስከትል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1791 1771(1) 1790 2090-2123 አዋጅ ቁ. 41ዐ/96 አንቀፅ 7

    Download Cassation Decision

  • Download Cassation Decision

    አንድ ሠራተኛ የአሠሪው ንብረት የሆነን ገንዘብ ማጉደሉ የተረጋገጠ እንደሆነ አሠሪው ሠራተኛውን በፍ/ብሔር ከሶ ገንዘቡን የማስመለሱ ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ የሥራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ ሊያቋርጥ የሚችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27(1)(መ)

  • ኢንሹራንስ ሰጪ በውሉ መሠረት ከፈፀመ በኋላ በተሸሸገ ወይም በሀሰት ቃል የቀረበ ጉዳይ አጋጥሟል በሚል የሚያቀርበው አቤቱታ የተሸሸገውን ወይም በሐሰት የቀረበውን ቃል ካወቀበት ቀን ጀምሮ ባለው ሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ካላቀረበ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ የንግድ ህግ 674(1) (2)

    Download Cassation Decision

  • የስጦታ ውል ገደብ ያለበት ወይም ግዴታ የተጣለበት እንደሆነ በውሉ ውስጥ የተመለከተው ግዴታ አልተፈፀመም በሚል ፈራሽ ሊሆን የሚችል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 244(1) ላይ የተመለከተው የይርጋ ድንጋጌ በስጦታ ውል ውስጥ የተመለከተ ግዴታ አልተፈፀመም በሚል ውሉ እንዲፈርስ ሲጠየቅ ተፈፃሚነት የሌለው ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅን መሠረት አድርጐ ከሚቀርብ ክርክር ጋር በተገናኘ በግልፅ ዳኝነት ተጠይቆበት ውሣኔ ሣይሰጥ ከተጠየቁት ዳኝነት መካከል ወደ ሥራ የመመለስ ጉዳይ ላይ ብቻ ውሣኔ ከተሠጠና ሠራተኛው ወደ ሥራ መመለስ ሳይፈልግ ቢቀር ቀድሞ ዳኝነት በጠየቀባቸው ነገር ግን ውሣኔ ባላረፈባቸው ነጥቦች ላይ ዳኝነት ሊጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 43(3)

    Download Cassation Decision

  • ኑዛዜ በፍ/ቤት መፅደቁ በንብረት ላይ ያለ የባለቤትነት መብትን የሚያረጋግጥ ስላለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • የማይንቀሳቀስ ንብረት የመፋለም ክስ ጋር በተያያዘ ክርክር ቀርቦ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ በክርክሩ ተሣታፊ የነበረ ወገን ንብረቱን አስመልክቶ ተሰጥቶ የነበረው የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት መክኗል በሚል የሚያቀርበው አዲስ ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑና በፍርዱ መሠረት የተጀመረው አፈፃፀም ሂደትን ለማስቆም የማይቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1195,1196 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 6,358,378 የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 78(1), 79(1)(4) , 37

    Download Cassation Decision

  • ወራሽ የሆኑ ወገኖች የሚያቀርቧቸውን ተገቢነት ያላቸው ማስረጃ በሙሉ አሰባስቦ በመስማት ያልተከናወነ የውርስ ማጣራት ሪፓርት በህግ አግባብ የተከናወነ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 241 27ዐ እና 345

    Download Cassation Decision

  • በተዘዋዋሪ መንገድ ተወላጅን ከውርስ ያለ በቂ ምክንያት መንቀል የማይቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 938,842,915

    Download Cassation Decision

  • ልጅነት ሊረጋገጥ የሚችልበት አግባብ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 156 168 158 169

    Download Cassation Decision

  • ልጅነትን በማረጋገጥ በፍ/ቤት የሚሰጥ ውሣኔ የህግ ግምት የሚፈጥር እንጂ አስገዳጅነት ያለው እና የመጨረሻ ማስረጃ ተደርጐ መወሰድ የሌለበት ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 154 155 156

    Download Cassation Decision