Download Cassation Decision
በሠራተኛ እጅ የሚገኙ የአሠሪ ንብረቶች መመለስ ወይም አለመመለስ ጉዳይ ሠራተኛው የሥራ ውሉ በተቋረጠ ጊዜ የሚያነሣችውን ልዩ ልዩ ክፍያዎችን ለማስተናገድ ግምት ውስጥ መግባት ያለበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 36 38
በአሰሪና ሠራተኛ መካከል በሚካሄድ የሥራ ክርክር የሚያዘው ጭብጥ አሰሪው ገንዘብ ይከፈለኝ በሚል በሠራተኛው ላይ ክስ ባቀረበ ጊዜ ከሚያዘው ጭብጥ ጋር አንድ አይነት ነው ሊባል የማይችል ስለመሆኑ
በቀጥታ ክስ ወቅት የተገመተ የንብረት ግምት በአፈፃፀም ወቅት በአይነት ካልተገኘ እና የንብረቱ ዋጋ በልጦ ከተገኘ አፈፃፀሙ ሊሆን የሚገባው ንብረቱን በአይነት ለመተካት በሚያስችል የወቅቱ ዋጋ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 378 392
አስተዳደራዊ የሆኑ መስፈርቶች ባልተሟሉበት ሁኔታ ካርታ እንዲሰጥ የሚወሰን ውሣኔ ተገቢ ስላለመሆኑ
የይዞታ መብት ፍፁም ስላለመሆኑ እና በህግ አግባብ ይዞታው የተወሰደበት ሰው ተገቢ የሆነ ካሣ የመጠየቅ መብት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 114ዐ 1149(1) (2) አዋጅ ቁ. 7/1986 አንቀጽ 2(5) 21 22 24 23 በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ- መንግሥት አንቀጽ 4ዐ (8) አዋጅ ቁ. 455/1997
Cassation Decision no. 39540
በተጭበረበረ ማስረጃ ሥራ የተቀጠረ ሠራተኛ በሥራ ላይ እያለ የማጭበርበር ድርጊቱ የታወቀ/የተደረሰበት/ ከሆነ ማጭበርበሩ የተከሰተው ሥራውን በማከናወን ላይ እንዳለ ተቆጥሮ ሊያስናብተው የሚችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 27(1) (ሐ)
በውል ግንኙነት ውስጥ የራስን ግዴታ ሳይወጡ ሌላው ወገን ግዴታውን አልተወጣም በሚል የሚቀርብ ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1757
የንግድ ቤቶችን የማከራየት እንቅስቃሴ ከታክስ ነፃ ከሆኑ ግብይቶች የማይመደብ ስለመሆኑ የንግድ ቤት ኪራይ የመክፈል ግዴታ ያለበት ወገን የተጨማሪ እሴት ታክስ መክፈል ያለበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 285/94 አንቀፅ 8
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 28ዐ መሠረት መዝገብ ሊዘጋ የሚችልበት አግባብ ተከራካሪ ወገኖች በአቤቱታቸው ዳኝነት የሚጠይቁበትን ፍሬ ነገር በአግባቡ ከገለፁ ትክክለኛውን የህግ ድንጋጌ አለመጥቀሳቸው መብታቸውን የሚያስቀር ስላለመሆኑ
የጉዳት ኪሣራ የሚከፈለው ጉዳት ስለመድረሱ ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2ዐ9ዐ 2ዐ91
ኃላፊነቱ የተወሰነ የንግድ ማህበር ሥራ አስኪያጅ የሆኑ ሰዎች ማህበሩን ሲያስተዳድሩ በሰሩት ያልተገባ ስራ ምክንያት በኃላፊነት ሊጠየቁ የሚችሉበት አግባብ የንግድ ሕግ ቁጥር 580
በጥበቃ ሥራ የተቀጠረ ሠራተኛ እንዲጠብቅ የተሰጠው የአሰሪ ንብረት የጠፋ እንደሆነ ሰራተኛው ለንብረቱ መጥፋት አስተዋጽኦ ያለማድረጉን ማረጋገጥ ካልተቻለ በስተቀር በሃላፊነት ሊያስጠይቀው የሚችል ስለመሆኑ
በተወሰነበት ፍርድ ላይ ይግባኝ እንደሚል ፍላጐቱን አሳውቆ እያለ ፍርዱን በሰጠው ፍርድ ቤት በኩል በተከሰተ መጓተት የይግባኝ ጊዜው ያለፈበት ፍርደኛ የሚያቀርበው የማስፈቀጃ አቤቱታ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ
የማይንቀሣቀስ ንብረት ገዥ ውል እንዲፈፀምለት ሻጭን የመጠየቅ መብቱ በፍርድ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ በአስር ዓመት ጊዜ ውስጥ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 384(ሀ) የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2892(3)
የባለዕዳውን ዕዳ ለባለገንዘብ የከፈለ ወገን በባለገንዘቡ መብቶች ላይ በመዳረግ (subrogation) ባለገንዘቡ የነበረውን መያዣን መሰረት ያደረገ የቀዳሚነት መብት ሊሰራበት የሚችልበት አግባብ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1968 - 1974
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 43 ሊተረጐም የሚችልበት አግባብ
የማይንቀሣቀስ ንብረትን በተመለከተ የሚደረግ የስጦታ ውል የማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ያልተደረገ ቢሆንም በህግ የፀና ውል ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2443 881 1723(1)
የሥራ ውል አንደተቋረጠ የጡረታ አበል ለማግኘት መብት ያለው ሠራተኛ የሥራ ስንብት የማይከፈለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 39 አዋጅ ቁ. 494/98 አንቀጽ 2(2) (ሰ)
Page 61 of 114