Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • በሥራ ላይ ንብረትንም ሆነ ህይወትን ለአደጋ የሚያጋልጥ ድርጊት መፈፀም ህገ ወጥ በመሆኑ ያለማስጠንቀቂያ ሊያሰናብት የሚችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 27(1)(ቀ) 14(2)(ሀ)

    Download Cassation Decision

  • በሥራ ላይ ንብረትንም ሆነ ህይወትን ለአደጋ የሚያጋልጥ ድርጊት መፈፀም ህገ ወጥ በመሆኑ ያለማስጠንቀቂያ ሊያሰናብት የሚችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 27(1)(ቀ) 14(2)(ሀ)

    Download Cassation Decision

  • የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ህግ ውስጥ ""እንደ ጥፋቱ ክብደት በሥራ ቦታው አምቧጓሮ ወይም ጠብ አጫሪነት ተጠያቂ መሆን..."" በሚል የተመለከተው ሀረግ ሊተረጐምና ተግባራዊ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ፣ ""የሥራ ቦታ"" የሚለው ሀረግ አሰሪው (ተቋሙ) ለሥራና ለመኖሪያ በሚል ለሰራተኞች የሚሰጠውን ቦታ እንዲሁም ተፈፀመ የተባለውን የአምባጓሮ ድርጊት ከሥራ ሰዓት ሙጪ መሆኑንም ጭምር የሚያካትት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 27(1)(ረ),97,4

    Download Cassation Decision

  • የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ህግ ውስጥ ""እንደ ጥፋቱ ክብደት በሥራ ቦታው አምቧጓሮ ወይም ጠብ አጫሪነት ተጠያቂ መሆን..."" በሚል የተመለከተው ሀረግ ሊተረጐምና ተግባራዊ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ፣ ""የሥራ ቦታ"" የሚለው ሀረግ አሰሪው (ተቋሙ) ለሥራና ለመኖሪያ በሚል ለሰራተኞች የሚሰጠውን ቦታ እንዲሁም ተፈፀመ የተባለውን የአምባጓሮ ድርጊት ከሥራ ሰዓት ሙጪ መሆኑንም ጭምር የሚያካትት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 27(1)(ረ),97,4

    Download Cassation Decision

  • ግብር የተጣለበትን የካፒታል ንብረት ዝውውር የመቀበል ወይም የመመዝገብ ወይም በማናቸውም መንገድ የማጽደቅ ስልጣን ያለው (የተሰጠው) የመንግስት አካል ግብሩ መከፈሉን ሣያረጋግጥ ዝውውሩን እንዲቀበል፣ እንዲመዘግብ ወይም እንዲያፀድቅ ሊገደድ የማይችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 37(7)

    Download Cassation Decision

  • ሥራና ሰራተኛን ከመምራት እና ከመቆጣጠር ባለፈ በሠራተኛ ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ ለመውሰድም ሆነ ከሥራ ለማሠናበት ስልጣን በሌለው የቅርብ አለቃ ሠራተኛው ሥራ እንዲለቅ የተነገረ መሆኑ የሥራ ውል ተቋርጧል ወደሚል ድምዳሜ የሚያደርስ ስላለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 3(2)(ሐ)

    Download Cassation Decision

  • በሌላ ሰው ጥቅም የሥራ አመራር ላይ ወንጀል ተፈጽሟል ለማለት ስለሚቻልበት አግባብ፣  በተከታታይ ለተፈፀመ ወንጀል ይርጋ ስለሚቆጠርበት አገባብ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ/፣702/3/፣219/2/

    Download Cassation Decision

  • የመሬት ባለ ይዞታ የሆነ አርሶ አደር ይዞታውን ላለበት እዳ ለ3ኛ ወገን በመያዣነት ለመስጠት ወይም በስጦታ የቤተሰብ አባል ላልሆነ ሰው ለማስተላለፍ መብት የሌለው ስለመሆኑ፣  በህግ እንዲደረግ ያልተፈቀደ እና/ወይም የህግ ክልከላ ባለበት ጉዳይ ላይ የተደረገ ውል ህገ ወጥ ውል በመሆኑ ከመነሻው ውጤት የሌለውና ፈራሽ ስለመሆኑ፣  የውሉ መሠረታዊ ዓላማ በህግ ያልተፈቀደና የተከለከለ ሆኖ ሲገኝ ዳኞች ህገ ወጥ የሆነው ውል በቀረበላቸው ማንኛውም ጊዜ ህጋዊ ውጤትና ተፈፃሚነት የለውም በማለት ለመወሰን የሚችሉና ህገ ወጥ የሆነውን ውል ውድቅ ለማድረግ በህጉ የተደነገገው የይርጋ ጊዜ ገደብ መቃወሚያ ሊሆን የማይችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 130/99 አዋጅ ቁ.89/89 አንቀጽ 2(3) አዋጅ ቁ. 456./97 አንቀጽ 8(2),1)

    Download Cassation Decision

  • በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.43 መሠረት ወደ ክርክር እንዲገባ የተደረገ 3ኛ ወገን በክርክሩ ሂደት ሊያነሣ ስለሚችለው የክርክር አይነትና አድማስ፣  3ኛው ወገን ሊያነሣ የሚችላቸው የክርክር ፈርጆች በአንድ በኩል ከተከሣሽ ጋር ሆኖ ድርሻ ክፍያ ወይም ስለተከሣሽ ሆኖ የካሣ ክፍያ የመክፈል ግዴታ ያለበት መሆኑን ተቀብሎ በተከሣሽ እግር ተተክቶ ተከሣሽ ለከሣሽ ኃላፊነት የማይኖርበት መሆኑን፣ ኃላፊነት አለበት የሚባል ቢሆን እንኳን ሊከፈል የሚገባው የካሣ ክፍያ መጠን ላይ ከከሣሽ ጋር ንጽጽር በማድረግ መሟገት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ድርሻ ወይም ካሣ ለመክፈል ለተከሣሽ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ግዴታ የለብኝም በማለት መከራከር ስለመሆናቸው፤  3ኛ ወገን ጣልቃ ገብ በክርክር ሂደቱ መሟገት የሚችለው ከተከሣሽ ጋር ብቻ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 43 አስፈላጊነት ተከታታይ ክስ ሳይኖር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች በአንድነት እንዲታዩ በማድረግ የኃላፊነት መጠኑን እንዲሁም ከፋዩን ወገን በመለየት የመጨረሻ እልባት ለመስጠት ስለመሆኑ፣  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 43 መሠረት ጣልቃ የሚገባ ወገን ከመነሻውም ከተከሳሹ ጋር የህግ ወይም የውል ግንኙነት የለኝም በማለት ክርክር ያቀረበ እንደሆነ በመካሄድ ላይ ባለው ክርክር ተሣታፊ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የማይኖር ስለመሆኑና ይህን መሰል ክርክር ራሱን በቻለ ሌላ መዝገብ ታይቶ ሊወስን የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 43(1),76 የፍ/ብ/ህ/ቁ.1896,1897,1908,1909 የንግድ ህግ ቁ.687,688,683

    Download

    ...
  • ከሥራ ጋር በተገናኘ እንዲከፈል በሚል የሚቀርቡ የደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓት እና ሌሎች ክፍያዎች ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው የይርጋ ጊዜ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው ሠራተኛው ክፍያዎቹን መጠየቅ ይችላል (ይገባዋል) ከሚባልበት ግዜ ጀምሮ እንጂ የሠራተኛው የሥራ ውል ከተቋረጠበት ግዜ ጀምሮ ነው ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 162(1-4)

    Download Cassation Decision

  • በህግ የሰውነት መብት የተሰጣቸው ተቋማት (ወገኖች) በድሀ ደንብ ዳኝነት ሳይከፍል በፍ/ቤት ለመስተናገድ የሚያቀርቡት ጥያቄ ተቋሙ ከሚገኝበት የገንዘብ አቋም አኳያ ተገናዝቦ መታየት ያለበት ስለመሆኑና ተቋሙ የሚገኝበትን የገንዘብ አቋም (Financial status) ለመለየት ተቀባይነት ስለሚኖረው የማስረጃ አይነት፣  ለዳኝነት የሚከፈለውን ገንዘብ ለመክፈል አልችልም በሚል በድሀ ደንብ ለመስተናገድ የህግ ሰውነት የተሰጠው ተቋም የሚያቀርበው አቤቱታ ሊስተናገድ ስለሚችልበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 467

    Download Cassation Decision

  •  የንግድ መደብር ኪራይ ከንግድ ቤት ኪራይ የተለየ ስለመሆኑ፣  የንግድ መደብር የተከራየ ሰው ያለአከራዩ እውቅና እና ፈቃድ መደብሩን ለ3ኛ ወገን በኪራይ አሳልፎ ለመስጠት ስለመቻሉ፣ የንግድ ህግ ቁ. 127 (ሐ),145(ለ),

    Download Cassation Decision

  •  ከውል አፈፃፀም ሂደት ጋር በተገናኘ በተዋዋይ ወገኖች ላይ ለሚደርስ ጉዳት ኪሣራ ሊሰላ ስለሚችልበት አግባብ፣  የኪሣራው ልክ ከውል ውጪ የሚደርስ ኃላፊነትን መሠረት በማድረግ በርትዕ ሊወሰን ስለሚችልበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1790, 1800, 2102(1)(2)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሠራተኛ በባህሪው ቀጣይነት ባለው ሥራ ላይ መቀጠሩ መረጋገጡ ብቻ ሠራተኛው ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠረ የሚያስቆጥረው ስላለመሆኑ፡ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 24(1)

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ጉዳይ የተከሰሰው ሰው ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦ ንብረቱ በቅጣት ለመንግስት እንዲወረስ በተወሰነ ጊዜ በአፈፃፀም ደረጃ ከአጥፊው (ወንጀለኛው) ንብረት ውስጥ ለቤተሰቡ ህይወትና መተዳደሪያ ሊውል የሚገባውን ድርሻ ለመወሰን ስለሚቻልበት አግባብ፣  በውርስ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ከተወሰነው የአጥፊው (የወንጀለኛው) ሀብትና ንብረት ውስጥ ለቤተሰቡ ህይወት መተዳደሪያ ሊውል የሚገባው ድርሻ ሊሸፍናቸው የሚገባው የወጪ አይነቶችና መጠናቸው፣  የአጥፊው (ወንጀለኛው) ጋር ጋብቻ የመሠረተ ሰው እንዲወረስ ከተወሰነው ንብረት ግማሽ ድርሻ የነበረው መሆኑን መሠረት በማድረግ በአፈፃፀም የሚያነሣው የቅድሚያ ግዢ መብት ጥያቄ የህግ መሠረት የሌለው በመሆኑ ጥያቄው እንደ መብት አቤቱታ ሊቀርብበት የማይችል ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 98(ለ)(መ), 98(3) (ለ)

    Download Cassation Decision

  • ወራሽነትን በማረጋገጥ በተሰጠ የወራሽነት ማስረጃ ላይ መብቴን ወይም ጥቅሜን ይነካል በሚል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 መሠረት የሚቀርብ የመቃወሚያ አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ሥለመሆኑ እና ተረጋግጦ የተሰጠውን ማስረጃ በሌላ ክርክር መቃወም የሚችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358

    Download Cassation Decision

  • ከዋስትና ውል ጋር በተገናኘ ዋስ የሆነ ወገን በውሉ ላይ የተመለከተውን ፊርማ የእርሱ አለመሆኑን ወይም የውሉን ቃል በተመለከተ በመካድ በግልጽ ባልተከራከረበት ሁኔታ ውሉ በሁለት ምስክር ፊት የተደረገ አይደለም በሚል የሚቀርብ ክርክር የዋሱን ግዴታ ተፈፀሚነት የሚያስቀር ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1727(2) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.83,235

    Download Cassation Decision

  • በአዋጅ ቁ. 515/1999 መሠረት የተቋቋመና የሚተዳደር የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤት ሠራተኞች የሚያቀርቡትን ክርክር በተመለከተ ተቋሙ በራሱ ገቢ የሚተዳደር በመሆኑ ምክንያት አዋጅ ቁ. 377/96 ን መሠረት በማድረግ ጉዳዩን የመደበኛ ፍ/ቤቶች ለማየት ስልጣን አላቸው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አዋጁ ቁ. 515/99 አዋጅ ቁ. 553/99 አንቀጽ 6(1), 14(2)(ለ) አዋጅ ቁ. 545/99

    Download Cassation Decision

  • የጡረታ መውጫ እድሜ ወሰንን በተመለከተ አሰሪው ከሠራተኛ ማህበር ጋር የሚያደርገው ስምምነት ተፈፃሚ ሊሆን የሚገባው በተመሣሣይ ጉዳይ ለሠራተኛ በህግ ከተደነገገው ይልቅ የህብረት ስምምነቱ የተሻለ (የበለጠ) ጥቅም የሚያስገኝ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 134(2),24(3) አዋጅ ቁ. 715/2003 አንቀጽ 17(1

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሠው የአራጣ ወንጀል ድርጊት ፈጽሟል በሚል በወንጀል ተጠያቂ ሊሆን ስለሚችልበት አግባብ፣  በወር 10% ወለድ ታስቦ እንዲከፈል በመስማማት ገንዘብ ማበደር በአራጣ የወንጀል ድርጊት የሚያስጠይቅ ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ 667(1)

    Download Cassation Decision