Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • ከአሰሪና ሠራተኛ አገናኝ አገልግሎት ጋር በተገናኘ ሰዎችን ወደ ውጪ አገር የላከ ሰው በተላኩት ሰዎች ላይ ለሚደርስ ጉዳት ካሣ የመክፈል ግዴታ የሚኖርበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 632/2001

    Download Cassation Decision

  • አሰሪ ሲሰራው የነበረው ሥራ በመቀነሱ ወይም በመቀዝቀዙ ምክንያት ካሉት ሠራተኞች መካከል ከአሥር ፐርሰንት በታች የሆኑትን የሥራ ውል ሟቋረጡ የግድ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሥራ ውላቸው የሚቋረጥና ሥራ የሚቀጥሉትን ሠራተኞች ለመለየት ሊከተለው ስለሚገባ አካሄድ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 28(8), 29(3)

  • አንድ የንግድ ድርጅት (ማህበር) የተጨማሪ እሴት ታክስ ህግንና ማሻሻያውን ተላልፏል በሚል በወንጀል ጥፋተኛ ሊሰኝና ሊቀጣ ስለሚችልበት አግባብ፣  የህግ ሰውነት የተሰጠው (legal personality) ድርጅት የወንጀል ተካፋይ ሊሆን የሚችልበት አግባብ፣  የህግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት ወንጀል እንዳደረገ ተቆጥሮ የሚቀጣው ኃላፊዎቹ ወይም ከሰራተኞቹ አንዱ ከድርጅቱ ሥራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የድርጅቱን ጥቅም በህገ ወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ ወይም ህጋዊ ግዴታን በመጣስ ወይም ድርጅቱን በመሳሪያነት ያለአግባብ በመጠቀም በዋና ወንጀል አድራጊነት፣ በአነሳሽነት ወይም በአባሪነት ወንጀል ሲያደርግ ስለመሆኑና የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በወንጀል ተከስሶ የጥፋተኛነትና የቅጣት ወሣኔ እስከተሰጠበት ድርስ ድርጅቱ የወንጀሉ ተካፋይ እንደሆነ የሚቆጠር ስለሆነ ጥፋተኛ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ. 34(1),(2) አዋጅ ቁ. 285/95 አንቀጽ 56(1)

    Download Cassation Decision

  • ፍቺን በስምምነት ለመፈፀም ለፍ/ቤት አቤቱታ ያቀረቡ ባል እና ሚስት የፍቺ ውጤትን በተመለከተ ያደረጉትን ስምምነት ፍ/ቤት ለህግና ለሞራል የማይቃረን መሆኑን በማረጋገጥ ያፀደቀው እንደሆነ ስምምነቱ ተፈፃሚ መደረግ ያለበት ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 80,83(3) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 277(2)

  • አንድ ሠራተኛ በአሠሪው በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ የሚባለው ንብረቱ የአሰሪውን ወይም ከአሠሪው ድርጅት ሥራ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 27(ሸ)

  • የኮንዶሚኒየም ቤትን በጋብቻ ወቅት እያሉ የደረሳቸው ባልና ሚስት የቤቱ ቅድመ ክፍያ በጋብቻ ወቅት ከተፈራ የጋራ ሀብት የተከፈለ እንደሆነና ቤቱን ለማሳመርና ለሌሎች ተያያዥ ወጪዎች ከጋራ ሀብቱ ወጪ በማድረግ ጥቅም ላይ በዋለበት ሁኔታ ጋብቻው በፍቺ የፈረሰ እንደሆነ ቤቱ ለተጋቢዎቹ፣ ሊከፋፈል ስለሚችልበት አግባብ፣ እንዲሁም በፍቺ ጊዜ እኩል መብት የሚኖራቸው ስለመሆኑ፣ የኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 35(1)  በህገ መንግስቱ የተረጋገጠላቸውን ቤተሰብ የመመስረት መብት በመጠቀም ጋብቻ የፈፀሙ ወንዶች እና ሴቶች በጋብቻው አፈፃፀም፣ በጋብቻው ዘመን

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰው በወ/ህ/አ. 675(1) የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት ፈጽሟል በሚል ሊከሰስና ጥፋተኛ ተብሎ ሊቀጣ ስለሚችልበት አግባብ፣ የወ/ህ/አ.675(1),23

  • የውክልና ውል ሳይኖር ወኪል ነኝ በሚል የሚደረግ ውል ህጋዊ ውጤት አግኝቶ የሚፀናበት አግባብ ስላለመኖሩ፣ የውክልና ሥልጣኑ ከመሰጠቱ በፊት የተደረገ ውል ውክልና ከተሰጠ በኋላ ሊፀና ይችላል ለማለት የሚያስችል የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑና ወካይ የሆነ ሰው የወካዩን ድርጊት እንደተቀበለ ሊቆጠር የሚችለው በህግ የሚፀና የውክልና ውል ኖሮ ነገር ግን ወኪሉ ከተሰጠው ስልጣን በላይ ሰርቶ የተገኘ እንደሆነ ወይም የውክልና ስልጣኑ ካበቃ (ከተቋረጠ) በኋላ ወካዩን በመወከል የሰራቸውን ሥራዎች በተመለከተ ብቻ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2190, 1678 (ሐ),1719(2),1723

  • የሠራተኞች ስንብት ተከትሎ አሰሪ የሆነ አካል የከራካሪ የሆኑ ክፍያዎችን በተመለከተ ሊያዘገይ እንደሚችልና ክፍያ በማዘግየት በሚል ሊቀጣ የሚችለው ከቁጥጥር ውጪ በሆነ ምክንያት ሳይኖር ወይም የሚያከራክር ክፍያ ሳይኖር ያለአግባብ ያዘገየ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 37, 38, 36

  • በአንድ ቦታ ከተደረገ በኋላ በሌላ ጊዜ ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፊት ቀርቦ እንዲረጋገጥና ማህተም እንዲደረግበት የተደረገ የኑዛዜ ሰነድ በህጉ ዳኛ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት እንደተደረገ ኑዛዜ የማይቆጠር ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.881,882

    Download Cassation Decision

  • የተጨማሪ እሴት ታክስ የመክፈል ግዴታ መወጣት ጋር በተያያዘ ታክስ ከፋዮች የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያን የመጠቀም ግዴታ የሚኖርባቸው የንግድ ፈቃድ የሥራ ዘርፍ በግልፅ ተለይቶ በተመለከተባቸው ሽያጮች ጋር በተገናኘ ብቻ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.285/94 አንቀፅ 55 አዋጅ ቁ.609/201 አንቀፅ 50(መ)(2) ደንብ ቁ.139/99 አንቀፅ 5(1)(ለ) የወ/ህ/ቁ.23(2)

  • ግዜው ያለፈበት የይግባኝ አቤቱታን ማስፈቀጃ በመቀበል ፍርድ ከተሰጠ በኋላ በበላይ ፍ/ቤት በተካሄደ ክርክር የማስፈቀጃ አቤቱታው ተቀባይነት ማግኘቱ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ ወሣኔ የተሰጠ እንደሆነ የስር ፍ/ቤት በዋናው ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ፍርድ ተፈፃሚነት የማይኖረው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 325,326,349