በወንጀል ጉዳይ በተሰጠ ውሣኔ ቅሬታ ያለው ወገን ይግባኙን ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ለማቅረብ በህጉ ተለይቶ ስለተመለከተ የጊዜ ገደብ፣ የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 187(2)
Download Cassation Decision
የፀና የውክልና ስልጣን ከሌለው ሰው ጋር የተደረገ ውል ከጅምሩ ፈራሽና ህጋዊ ውጤት የሌለው ስለመሆኑ ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2232(2),2015(ሀ),2005(2),1204
ተከሳሽ የቀረበበትን የወንጀል ክስ በተመለከተ በመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያነት ሊያቀርባቸው ስለሚችላቸው መከራከሪያዎች ተከሳሽ በመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያነት የሚያቀርባቸው መቃወሚያዎች በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 130 ላይ የተመለከተቱት ጉዳዬች ጋር ብቻ በተገናኘ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ ማንኛውም ሰው የወንጀል ክስ ሲቀርብበት የተከሰሰበት የወንጀል ድርጊት በተፈፀመበት ጊዜ ድርጊቱን መፈፀሙ ወይም አለመፈፀሙ ወንጀል መሆኑ ካልተደነገገ በስተቀር ሊቀጣ የማይችልና ወንጀሉ በተፈፀመበት ጊዜ ተፈፃሚ በነበረው ህግ ከተመለከተው የቅጣት ጣሪያ በላይ ሊቀጣ የማይችል ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ የማይሰራ ስለመሆኑና ዳኞች ወንጀሉ በተፈፀመበት ጊዜ ክስ የቀረበበት ድርጊት ወንጀል ስለመሆኑ የሚደነግገው ህግ ፀንቶ በሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት መሆኑን ከተረዱ በማናቸውም ጊዜ አንስተው ውሣኔ ለመስጠት የሚችሉ ስለመሆኑ፣ ፍ/ቤቶች በዐ/ህግ የቀረበ የወንጀል ክስ በህገ-መንግስቱና በወንጀል ህጉ የሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር የተቀመጡ መርሆዎችና ድንጋጌዎችን የሚያሟሉ መሆን አለመሆኑን በመመርመር የመወሰን ግዴታ ያለባቸው ስለመሆኑ፣ የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 5(2) ,13(1), 22(1 ) የወ/ህ/አ. (414/96)3,402,419,5(2) የወ/ህ/ቁ.(214/74) አለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን ስምምነት (ICCPR) አንቀጽ 15(1) የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 130(2)(1)
የፌዴራል መንግስት ተቋማት በአጠቃላይና የከፍተኛ ት/ት ተቋማት በተለይ የራሳቸው የሆነ የእድገት አሰጣጥ፣ የቅሬታ አፈታትና አጠቃላይ አስተዳደራዊ ሥራዎች የሚከናወንበት አግባብ ያለ በመሆኑ በቀጥታ ለመደበኛ ፍ/ቤቶች ጉዳዩ ቀርቦ ውሣኔ የሚሰጥበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 515/99
በወንጀል ጉዳይ የተከሰሰ ሰው የዋስትና መብቱ በፍ/ቤት ከተከበረለት በኋላ ህጋዊ ምክንያቶችን በማቅረብ የዋስትና መብቱን በመተው ያስያዘው ገንዘብ ተመልሶለት ጉዳዩን ማረሚያ ቤት ሆኖ ለመከታተል የሚያቀርበውን ጥያቄ ውድቅ ለማድረግ የሚያስችል የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣
በህጉ አግባብ ሊሟላ የሚገባው የዳኞች ቁጥር ባልተሟላበት ሁኔታ የሚሰጥ ትዕዛዝ ወይም ውሣኔእንደተሰጠ የማይቆጠርና ህጋዊ ውጤት ሊኖረው የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 73,337
ከስራ ክርክር ጋር በተገናኘ በዲሲፕሊን ተከስሶ በዲሲፕሊን ኮሚቴ ሠራተኛው በፈፀመው የማታለል ድርጊት ጥፋተኛ የተባለ መሆኑን መነሻ በማድረግ የተሰናበተ ሰራተኛ የዲስፕሊን ኮሚቴው አባላት በሥራ ክርክር ሰሚው አካል ፊት ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን ስላልሰጡ ስንብቱ ህገ ወጥ ነው በሚል የሚያቀርበው አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 27(1)(ሐ) እና (መ)
የትራፊክ ደንብ መተላለፍ ጋር በተያያዘ የክስ ቻርጅን ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆን በወ/ህ/አ.438 በየመንግስት ሥራን ማሰናከልና የመተባበር ግዴታን መጣስ ወንጀል ሊያስጠይቅ ስለመቻሉ፣ የወ/ህ/አ.348
አንድ ኢትዮጵያዊ የሆነ የበጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር ከውጭ ምንጭ በህጉ ከተመለከተው የገንዘብ መጠን በላይ እንዲሰበስብ ሊፈቀድ የማይችል ስለመሆኑ፡ አዋጅ ቁ. 621/2001 አንቀጽ 2(2),(3)(4),14(5), 14(2), 6, 90, 111(2), 112,108,110, ደንብ ቁጥር 168/2001 አንቀጽ 18(3),10(2),36
አንድ ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ በሚል ፍ/ቤት በሚሰጠው ብይን ላይ ይግባኝ ለማቅረብ የሚያስችል የህግ መሠረት የሌለ ስለመሆኑ የሙስና ክስ ከሚመራበት ሥርዓት ጋር በተገናኘ ተከሳሽ የሆነ ተከራካሪ ወገን ይግባኝ ለማቅረብ ስለሚችልባቸው ህጋዊ ጉዳዮች፣ ለሰበር ችሎት የሚቀርቡ ማናቸውም ጉዳዮች የይግባኝ አቅራረብ ሥርዓትን ያጠናቀቁና የመጨረሻ ፍርድ የተሠጠባቸው መሆን የሚገባቸው ስለመሆኑ፣ አዋጀ ቁ. 25/88 አንቀጽ 22 አዋጀ ቁ. 434/97 አንቀጽ 36(2) 40, 55 አዋጀ ቁ. 236/93
ከአሰሪና ሠራተኛ አገናኝ አገልግሎት ጋር በተገናኘ ሰዎችን ወደ ውጪ አገር የላከ ሰው በተላኩት ሰዎች ላይ ለሚደርስ ጉዳት ካሣ የመክፈል ግዴታ የሚኖርበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 632/2001
አሰሪ ሲሰራው የነበረው ሥራ በመቀነሱ ወይም በመቀዝቀዙ ምክንያት ካሉት ሠራተኞች መካከል ከአሥር ፐርሰንት በታች የሆኑትን የሥራ ውል ሟቋረጡ የግድ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሥራ ውላቸው የሚቋረጥና ሥራ የሚቀጥሉትን ሠራተኞች ለመለየት ሊከተለው ስለሚገባ አካሄድ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 28(8), 29(3)
Page 96 of 114