Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • ፍርድ ከተሰጠ በኋላ አዲስ ማስረጃ ተገኝቷል በሚል የተሰጠው ፍርድ በድጋሚ ሊታይ የሚችልበት አግባብ ውሣኔ ያልተሰጠበት ጉዳይ በድጋሚ ዳኝነት እንዲታይ አቤቱታ ሊቀርብበት የማይቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 6

    Cassation Decision no. 08751

  • አንድ ፍ/ቤት ክስ ቀርቦለት ጉዳዩን የማየት ሥረ ነገር ስልጣን የለኝም በማለት መዝገቡን የዘጋው እንደሆነ ዋናውን ክርክር እንዳላየ የሚያስቆጥር ሲሆን የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.5፣9 እና 231 በመዝገቡ ላይ የሰጣቸው ማናቸውም ትእዛዞች በማናቸውም ወገን ላይ ህጋዊ የሆነ አስገዳጅነት ውጤት የሌለውና በዚሁ ጉዳይ ለሚመለከተው ፍ/ቤት መዝገቡ ቢቀርብ ከዚህ ቀደም በፍርድ ያለቀ ነው ሊያስብል የማይችል ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • የማይንቀሳቀስ ንብረት የሸጠ ሰው ንብረቱን ከሌሎች ሰዎች ቁጥጥር ይዞታ ሥር ነፃ አድርጎ ፣የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ባለሀብትነት ለማስተላለፍ የሚያስችሉ አስፈላጊ ሰነዶች ለገዢ የማስረከብና የማይንቀሳቀሰዉን ንብረት የማይነካ የባለሀብትነት መብት ለገዥ ለማስተላለፍ አስፈላጊ የሆነ ተግባራትን የመፈጸም ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2875፣ 2879(1)፣2281

    Download Cassation Decision

  • በክስ ማሻሻል ሥርዓትና ዓላማ ቀድሞ ዳኝነት ከተጠየቀበት ጉዳይ ፈጽሞ የተለየ ጥያቄ ለማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ፣

    ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91

    ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 342

    አንድ ሰው በህግ ወይም የሚፀና ውል የሚሰጠው አንዳች መብት እንደሌለ እያወቀ የሌላ ሰው የሆነን ንብረት በእጁ ባደረገ ጊዜ ንብረቱ ሊያፈራ የሚችለውን የገንዘብ ግምት እንዲመልስ ሊወሰን የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ.2178

     

    የሰ/መ/ቁ. 100651

     

    መሰከረም 27 ቀን 2008 ዓ/ም

     

    ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ

    ...
  • የRTD ችሎት መከላከያ የማቅረብ መብትን የማያስነፍግ ስለመሆኑ

     

     

    ዳኞች

    የRTD ችሎት መከላከያ የማቅረብ መብትን የማያስነፍግ ስለመሆኑ

     

     

    ዳኞች

    እብደቱ በግልጽ ያልታወቀ ሰው ወራሾች ወይም ባለገንዘቦች ይህ ሰው የፈጸመው ውል ጉድለት የሌለበት ፈቃድ አልሰጠበትምና ውሉ ሊፈርስ ይገባል ሲሉ እብደቱን ምክንያት በማድረግ የውሉን መፍረስ መጠየቅ የማይችሉ ስለመሆኑ፡- የማይንቀሳቅስ ንብረት ሽያጭ ውልን ዋጋ ተጎዳሁ በሚል ምክንያት ሊፈርስ የማይችል ስለመሆኑ፡- የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ሕ/ቁ. 348፣347/1//2/፣349፣350፣341፣342 የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2887

     

    የሰ/መ/ቁ. 100931 ታህሳስ 18 ቀን 2008ዓ.ም

    ዳኞች፡- አልማው ወሌ

     

    ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመስል እንደሻው

    ...
  • በአንድ የወንጀል ድርጊት በዋና ወንጀል አድራጊነት ወይም ግብረ አበርነት የተሳትፉ ተከሳሾች በግል ሁኔታዎች ሊኖር ከሚችለው ልዩነት በስተቀር ለተመሳሳይ የወንጀል አፈፃፀምና የወንጀል ተሳትፎ ተመጣጣኝና ተመሳሳይ ቅጣት ሊወሰን የሚገባ ስለመሆኑ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ስርዓት ቁጥር 196(1) ለሰበር ስርዓትም ተፈፃሚነት ያለውና ከተከሳሾች አንደኛው ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ውድቅ የሆነበትና አያስቀርብም የተባለን ተከሳሽ ጭምር ሊያካትት የሚገባ ስለመሆኑ፡- የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 25፣22 የወንጀል ሕግ አንቀጽ ፣4፣6 የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ 2/2006 አንቀፅ.3(2)

    Download Cassation Decision

  • በአከራይና ተከራይ መካከል በሚደረግ የኪራይ ስምምነት መሠረት አከራዩ ለተከራዩ ባከራየው ቤት ላይ ስለተደረገው ጥገና /ማሻሻያ/ አከራይ የሰጠው ስለመሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ አከራዩ ለተከራዩ አወጣሁ ያለውን ወጪ የመክፈል ኃላፊነት የሌለበት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 555/2000 አንቀጽ 6/3/ የፍ/ብ/ሕ/ቁ አንቀጽ 2917፣2973/1/፣2912

    የሰ/መ/ቁ. 101053

    ታህሳስ 22 ቀን 2008 ዓ/ም

     

    ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ

    አግባብ ባለው የዩኒቨርስቲ አካል በተሰጠ አስተዳደራዊ ውሳኔ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ቅሬታ ሲኖራቸው የይግባኝ መብት ያላቸው ስለመሆኑ፤ ይግባኙን የማስተናገድ ስልጣን የፌደራል የመንግስት ሠራተኞች አስተዳደር ፍ/ቤት ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision

  • የሰበር አቤቱታ በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ሳይቀርብ ጊዜው ካለፈ የሰበር አቤቱታ ከመቅረቡ በፊት የይግባኝ ማስፈቅጃ ማመልከቻ መቅረብ ያለበት ሰለመሆኑ፤ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 22(4) ፣ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 324

    Download Cassation Decision

  • ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ የወጣ ህግ ለተከሳሹ ወይም ለተቀጣው ሰው ጠቃሚ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ተፈጻሚነት ሊኖረው የሚገባው ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ የወጣው ህግ ስለመሆኑ፣ በአዲሱ የጉሙሩክ አዋጅ ቁ. 859/2006 አንቀጽ 182 ስር የተመለከተው ድንጋጌ ተፈጻሚነት ሊኖረው የሚገባው ክርክር ካላስነሳው ጉዳይ በሌሎች ህጎች የተመለከቱት ድንጋጌዎች በማይነካ ሁኔታ ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 22/2/ የኢፌድሪ የወንጀል ህግ ጠቅላላ ክፍል በአንቀጽ 6

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰው በሀሰት የተዘጋጀን ወይም የተለወጠን ሰነድ እያወቀ የተገለገለበት ካልሆነ በቀር የወንጀል ኃላፊነት የሌለበት ስለመሆኑ፣ የወ/ሕ/ቁ 378
  • አንድ ፍርድ የማይፈፀምበት ምክንያት ያለመኖሩ ሲረጋገጥ ለአፈፃፀም ተስማሚ በሆነ መንገድ ፍርድ እንዲፈፀም ትእዛዝ መስጠት የሚቻል ስለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 392(1)

     

    የሰ/መ/ቁ. 101618

     

    ታህሳስ 19 ቀን 2008 ዓ.ም

     

    በውጭ ሃገር ስለሚኖር የስራ ውል የግል አገልግሎት(በውጭ ሃገር ለተሰጠው አገልግሎት) ተፈፃሚ ሊሆን የሚገባው ህግ ስለስራና ሰራተኛ ማገናኘት አገልግሎት የወጣ አዋጅ 632/2001 ስለመሆኑ በዚህ አይነት የውል ግንኙነት ውስጥ የሚቀርብ የክፍያ ጥያቄ በአስር አመት ይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 1677(1) እና 1845

  • በውጭ ሃገር ስለሚኖር የስራ ውል የግል አገልግሎት(በውጭ ሃገር ለተሰጠው አገልግሎት) ተፈፃሚ ሊሆን የሚገባው ህግ ስለስራና ሰራተኛ ማገናኘት አገልግሎት የወጣ አዋጅ 632/2001 ስለመሆኑ በዚህ አይነት የውል ግንኙነት ውስጥ የሚቀርብ የክፍያ ጥያቄ በአስር አመት ይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 1677(1) እና 1845

  • በክርክሩ ተካፋይ ያልሆነውን ወገን የሚጎዳ ውሳኔ የተላለፈው ጉዳዩን በተዋረድ ባየው የሰበር ችሎት በሚሆንበት ጊዜ ይህ በክርክሩ ተካፋይ ያልሆነው ወገን አለኝ የሚለውን መብት ለማስከበር ይችል ዘንድ መብቴን ተጋፍቷል በሚለው ሰው ላይ በስሙ ቀጥታ ክስ በመመስረት መብቱን ከማስከበር ውጪ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.358 መሰረት ተቃውሞውን ለሰበር ችሎቱ ሊያቀርብ የሚችል ስላለመሆኑ

    የሰ/መ/ቁ. 102056

    ታህሳስ 18 ቀን 2008 ዓ.ም

    አንድ በፍርድ ቤት የተወከለን ሰው በችሎት ተገቢ ያልሆነ ስነ ምግባር አሳይቷል በማለት ፍ/ቤት የውክልና ስልጣንን መሻር የማይቻል ስለመሆኑ፣ ፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 58

    Download Cassation Decision

  • ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል ሊባልባቸው ስለሚችሉባቸው ሁኔታዎች ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል ተብሎ ከሚታሰብበት ጊዜ አንስቶ በአስር ዓመት ጊዜ ውስጥ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ካልቀረበ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ

     

    የሰ/መ/ቁ.102662

    የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ/ም

    ዳኞች፡-አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ

    አመልካች፡- ወ/ሮ አልማዝ ለሼ- ጠበቃ ኤርሚያስ ደስታ ቀረቡ፡፡ ተጠሪ፡- አቶ በቀለ በላቸው- ወኪል 

    ...