Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • የከተማ ቦታ የሊዝ ይዞታ በሚቋረጥበት ወቅት /ሲቋረጥ / ባለይዞታው እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ በቦታው ላይ ያሰረፈውን ንብረት በማንሳት ቦታውን አግባብ ላለው አካል መልሶ ማስረከብ ያለበት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 26(5) እና (6)

    Download Cassation Decision

  • ከመንግስት ገዥና አቅርቦት ጋር በተያያዘ የሚነሳ ክርክር በመጀመሪያ ስልጣኑ የማየት መብት ያለው የመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ ቅሬታ ሰሚ ቦርድ እንጂ የመደበኛ ፍ/ቤት ስላለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 649/2001 አንቀፅ 75(1) አዋጁን ለማስፈፀም የወጣው መመሪያ አንቀፅ 49(1)

     

    የሰ/መ/ቁ. 107805

     

    ጥቅምት 04 ቀን 2008 ዓ.ም

     

    ዳኞች፡- ተገኔ

    ...
  • አንድ ተከሳሽ በከሳሽ በመጀመሪያ ክስ ሲቀርብበት መጥሪያ ደርሶት በተከራከረበት እና ከሳሽ ክስ ያሻሽል ተብሎ በተዘጋ መዝገብ ላይ ክሱ ተሻሽሎ መዝገቡ ከተከፈተ በኋላ ለተከሳሽ በተገቢው መንገድ መጥሪያ ሳይደርስ የሚሰጥ ውሳኔ ስነ- ስርዓታዊ ስላለመሆኑ፣

    የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. አንቀጽ 94-110

     

    የሰ/መ/ቁ. 107838

    የካሳን መጠን በርትዕ ለመወሰን የሚያስገድድ ሁኔታ በገጠመ ጊዜ መጠኑን ለመወሰን የጉዳት ካሳው መጠን ከጉዳቱ ተመጣጣኝ ይሆን ዘንድ ሚዛን ላይ ሊቀመጡ የሚገባቸው መለኪያዎች ሊኖሩ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ.2102 እና 2153

     

    የሰ/መ/ቁ. 108251 ቀን ጥር 5/2008ዓ.ም

    ዳኞች፡-  ተሻገር ገ/ስላሴ

     

    ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ

    አንድ ፍ/ቤት የውርስ ክርክርን አስመልክቶ የሚቀርብለትን የውርስ አጣሪዎች ቃለ- ጉባኤ ከማስጽደቁ በፊት በእርግጥ የውርስ ሀብት የማጣራት ሕጋዊ ሂደት ተከትሎ የተካሄደ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ. 946፣950፣1062፣1079፣1080

    Download Cassation Decision

  • በኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ መሰረት ይዞታን የመጠቀም መብት የሚተላለፈው በውርስ ሕግ መሰረት በይዞታው የመጠቀም መብት ላለው የቤተሰብ አባል ሲሆን በዚሁ አግባብ ቅድሚያ የውርስ መብት የሚሰጠው ከመሬቱ በሚያገኙት ገቢ ለሚተዳደሩ(ሌላ መተዳደሪያ)ገቢ ለሌላቸው ወራሾች ሥለመሆኑ የኦሮሚያ የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 130/1999 አንቀፅ 9(1)(2) አዋጁን ለማስፈፀም የወጣው ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀፅ 10(1)

     

    የሰ/መ/ቁ.ጥር 108335

    የካቲት 4 ቀን 2008 ዓ.ም.

     

    ዳኞች፡-ተሻገር ገ/ሥላሴ

    የጉምሩክ ወንጀል ጋር በተያያዘ ፤ተከሳሽ በወንጀሉ ጥፋተኛ ባይባልም ንብረቱ የሚወረሰው ሰለድርጊቱ አፈፃፀም ሁኔታ የሚያሰረዳ አጥጋቢ ማስረጃ መቅረቡን ፍ/ቤቱ አሳማኝ ሆኖ ሲያገኘው ስለመሆኑ ፤ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀፅ 104 እና አዋጅ ቁጥር 859/2006

    Download Cassation Decision

  • የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ በይዞታው ስር የሚገኙትን የመንግስት ቤቶች ለማከራየት የሚያደርጋቸው ውሎች ያልተጠበቁ ምክንያቶች ካልተከሰቱ እና በተለይም ደግሞ ውሉን ለማቋረጥ የሚያስችል በተከራይ ወገን በኩል ጥፋት ተፈጽሟል ካልተባለ በቀር በድርጅቱና በተከራዮች መካከል የሚደረጉ ውሎች በየዓመቱ እየታደሱ የሚቆዩ ስለመሆኑ፣ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቁጥር 555/2000 አንቀጽ 6/1/

    Download Cassation Decision

  • በክርክር ወቅት ጣልቃ እንዲገባ የተፈቀደለት ተከራካሪ በመጀመሪያ ሊያቀርብ የሚፈልገውን መቃወሚያ እንዳያቀርብ የሚከለክለው ህግ የሌለ ስለመሆኑ፣ ( የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 41 ፣234/1/

    Download Cassation Decision

  • አንድ ከሳሽ ክሱን የመሰረተው በብዙ ጉዳዮች ወይም በተለያዩ ነገሮች ላይ የሆነ እንደሆነ በተለይ በእያንዳንዱ ጉዳይ እንዲታይ የሚጠይቀውን ዳኝነት መግለጽ ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 224(2)

    Download Cassation Decision

  • የደረሰው ጉዳት አጓዥ በፈጸመው ተግባር ወይም ባደረገው ጉድለት እንዲሁም ይህ ተግባር አደጋ ሊያደርስ ወይም ሊፈጥር የሚችል መሆኑ እየታወቀ ሲሆን የኃላፊነት መጠኑ በህጉ ከተቀመጠው ውጪ ሊሆን የሚችል ስለመሆኑ፣ በልጅ ቀለብ አወሳሰን ረገድ ልንከተላቸው ስለሚገቡ መሰረታዊ መርሆች ( የን/ሕ/ቁ. 597፣ 599) (የፍ/ሕ/ቁ. 2091፣ 2092 የኢ.ፌ.ድ.ሪ የቤተሰብ ህግ ቁ.. 213/92 አንቀጽ 197

    Download Cassation Decision

  • ተከሳሽ የተከሰሰበትን ነገር በሙሉ ወይም በከፊል የሚያምን መሆኑን የገለፀ እንደሆነ በእምነቱ መሰረት ይገባኛል የሚለው ማናቸውም ዳኝነት እንዲሰጠው አመልካች(ከሳሽ) ሊጠይቅ የሚችል ስለመሆኑ

    የሰ/መ/ቁ. 109206

     

    የካቲት 3 ቀን 2008 ዓ.ም.

    ፍ/ቤቱ የግዛት ስልጣን የለውም በማለት ለሚቀርብለት መቃወሚያ የሚሰጠው ውሳኔ ፍትህን የሚያጓድል ካልሆነ በቀር ይግባኝ ሊቀርብበት የማይችል ስለመሆኑ

    የፍ/ሥ/ሥ/ቁ. 10(2)

    የሰ/መ/ቁ. 109383

    የካቲት 2 ቀን 2008 ዓ.ም

    የዋስትና ውል ግዴታ ሰራተኛው ተቀጥሮ በሚያገለግልበት ወቅት ለሚደርሰው የገንዘብና የንብረት መጥፋትና መጉደል ተጠያቂ የሚያደረግ ስለመሆኑ፣ የፍ/ሔር/ሕ/ቁ. 1933/1/ 1897

    Download Cassation Decision

  • የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃ የአስረጅነት ብቃት ያለው ተአማኒነት ያለው ማስረጃ ተደርጎ እንዲወስድ ሚዛን ላይ ሊቀመጡ ስለሚገባቸው ነገሮች

     

    የሰ/መ/ቁ. 109441 ቀን 17/05/2008 ዓ/ም

    ዳኞች፡-አልማው ወሌ

     

    ...
  • ፍ/ቤት በተዋዋዮች መሃል የተደረገን ውል (የእርቅ ስምምነት) ህጋዊነታቸውን ሳይረጋገጥ ሊያፀድቅበት የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ

    የፍ/ሕ/ቁ.1731

    የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.277

     

    ...

  • የድለላ አበል ክፍያ መጠን ከተሰጠው አገልግሎት ጋር ተመጣጣኝ ሊሆን የሚገባ ስለመሆኑ በድለላ አበል መጠን ላይ በሚደረገው ክርክር እንደ ጉዳዩ ዓይነት እና የተሰጠው አገልግሎት እየተገናዘበ የሚወሰን ስለመሆኑ የን/ሕ/ቁ. 59(3)

     

    የሰ/መ/ቁ.109535 የካቲት 24 ቀን 2008 ዓ/ም


    መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰትተናል፡፡

    ...

  • ፍ/ቤቶች እውነትን ለማውጣት ማስረጃ አስቀርበው መስማት አለባቸው ሲባል በቀረበው ማስረጃ እውነት እስከተረጋገጠ ድረስ የግድ ተጨማሪ ማስረጃ እንዲያቀርቡ የሚገደድበት ምክንያት የሌለ ስለመሆኑ፣ የፍትሐብሔር ክርክር ማስረጃ የሚሰማውና ፍሬ ነገር እንዲጣራ የሚደረገው በማስረጃ የሚገኘው ፍሬ ለዳኝነት አሰጣጡ እጅጉን አስፈላጊና የግድ ሆኖ ሲገኝ ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision

  • በፍ/ብ/ህ/ቁ. 842/3/ መሰረት የተተኪ ወራሽነት ጥያቄ ተቀባይነት እንዲያገኝ ሊሟሉ ስለሚገባቸው ጉዳዮች፣

    Download Cassation Decision

  • ተተኪ ወራሽ ለመሆን ሊሟሉ ስለሚገባቸው ሁኔታዎች የፍ/ሕ/ቁ. 842(3)

    የሰ/መ/ቁ/ 110040

     

    የካቲት 3 ቀን 2008 ዓ/ም

     

     

    ...