Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

  • ከሳሽና ተከሳሽ ያልተካካዱበትና ከሳሽ በክሱ ገልፆ ተከሳሽ ባመነው ነጥብ ላይ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ማስረጃ በመመዘን ሳይሆን ተከሳሹ በሰጠው የእምነት ቃል ወይም መልስ መሰረት መወሰን ያለበት ስለመሆኑ

    የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.242

    የሰ/መ/ቁ. 112927

    አንድ ሠራተኛ ከስራ ከተሰናበተ በኋላ የአገልግሎት ክፍያ ከሚያገኝባቸው ሕጋዊ ምክንያቶች አንዱ በድርጅቱ ከ5 ዓመት በላይ አገልግሎ በገዛ ፈቃዱ ስራ መልቀቁ ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑ

    አዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀፅ 2/ሸ/

    የሰ/መ/ቁ. 112956

    ባል ወይም ሚስት የጡረታ አበል ተጠቃሚ ሆነው ባሉበት ፍቺ ቢከሰት የጡረታ መብት ተጠቃሚ የሆነው ባል ወይም ሚስት የጡረታ አበል ለባል ወይም ለሚስት ሊያካፍል የሚገባ ስላለመሆኑ ፣ የመንግስት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 345/95 አንቀጽ 35

    Download Cassation Decision

  • የወንጀል ጉዳዮችን በመጀመሪያ ደረጃ ይሁን በይግባኝ ደረጃ የሚመለከት ፍ/ቤት ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜ የማስረጃውን አጭር መግለጫ፣ ማስረጃውን የተቀበለበትን እናያልተቀበለበትን ምክንያቶች በፍርድ ላይ ማስፈር የሚገባው ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 149/1/

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ጉዳይ ከአንድ በላይ ሰዎች የተከሰሱ እንደሆነ የእያንዳንዱ ተከሳሽ ሚና እና ተሳትፎ ደረጃው በቂና አሳማኝ በሆነ ሁኔታ በከሳሽ ወገን በኩል በሚቀርበው ማስረጃ ነጥሮ ሊወጣ የሚገባ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32፣40 የወ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 141 ተያያዥነት የሌላቸው ፍሬ ነገሮችን መሰረት ተደርጎና የአንድን ነገር መኖር ያለመኖር ሣይረጋገጥ ለአካባቢ ማስረጃ ክብደት መስጠት የማስረጃው አይነት የምዘና መርህን መሰረት ያደረገ ነው ለማለት የሚቻል ስላለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.173(1)

     

    የሰ/መ/ቁጥር 113464

     

    ህዳር 22 ቀን 2008 ዓ/ም

    ለአንድ ውርስ ወራሽ የሆነ አንድ ሰው ውርስ ከተከፈተ በኋላ የሞተ እንደሆነ የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ባያወጣም ለውርሱ አይገባም እስካልተባለ ድረስ የወራሸነት መብቶች ለእርሱ ወራሾች የሚተላለፍ ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ክሶች ወይም ይግባኞች መጣመር በነበረባቸው ሰዓት ሣይጣመሩ ቢቀሩና የግራ ቀኙን የተለያየ መብት በሚያጎናፅፍ ሁኔታ ቢወሰን እነዚህን ውሳኔዎች ተጣጥሞ እንዲፈፀሙ ማድረግ ተገቢ ሥለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.11

    Download Cassation Decision

  • በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ መሰረት የጉምሩክ ቁጥጥርን አሰናክለሃል ተብሎ ሊጠየቅ የሚችለው ድርጊቱ ሆነ ተብሎ መፈፀሙን አቃቢ ህግ በበቂ ሁኔታ ሲያስረዳ ስለመሆኑ የጉሙሩክ አዋጅ ቁ. 859/2006 አንቀፅ 166
  • የገጠር መሬት እንደሌላው ንብረት በመቁጠር ከቤተሰብ ህጉ አንጻር የሚታይ ስላለመሆኑ ፣ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በአንድ ተጋቢ ስም ተዘጋጅቶ ከተሰጠ በኋላ ጋብቻ ቢፈፀምና ተጋቢዎቹ መሬቱን የጋራ ለማድረግ ሊስማሙ የሚችሉ ስለመሆኑ፣ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 133/1999 አንቀጽ 24/3/ ደንብ ቁ. 151/1999 አንቀጽ 20/6/

    Download Cassation Decision

  • በአንድ ሰነድ ላይ ያለን ፊርማ በቴክኒክ ምርመራ የማን እንደሆነ ለማረጋገጥ ባልተቻለ ጊዜ ፊርማው ሲፈረም የነበሩ ምስክሮችን ቃል በመስማትና በሌሎች ማስረጃዎች ፊርማው የማን እንደሆነ በመመዘን ማረጋገጥ የሚቻል ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 2472(1)

    Download Cassation Decision

  • በኦሮሚያ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚነሱ የከተማ ቦታን ከማስለቀቅና ምትክ ቦታ እና ካሣን ከመክፈል አንጻር የሚነሱ የመብት ጥያቄዎችን በመጀመሪያ ደረጃ የማየት ስልጣኑ በከተማው አስተዳደር የተዋቀረው አካል ስለመሆኑ፣ የኦሮሚያ ክልል የመሬት ሊዝ አዋጅ ቁ. 721/2004 አንቀጽ ቁ. 26፣27፣28፣29 እና 30 አዋጁን ለማስፈጸም የወጣው ደንብ ቁጥር 155/2005 አንቀጽ 26፣55 እና 56

    Download Cassation Decision

  • ተከራካሪ ወገኖች በፍርድ ቤት የሚከራከሩበትን ጉዳይ በእርቅ መጨረስ የሚችሉና የእርቅ ውሉን ጉዳዩን ለሚያየው ፍርድ ቤት አቅርበው ማፀደቅ እንደሚችሉ ፍርድ ቤት ቀርቦ የፀደቀ የእርቅ ውል ሥምምነት በፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ ያህል አስገዳጅነትና ተፈፃሚነት ያለው ከመሆኑ ባሻገር በዚህ እርቅ ውል ተካፋይ ያልሆነ መብቴ ተነክቷል የሚል ወገን የፍርድ መቃወሚያ ሊያቀርብ የሚችል ሥለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.276፣277(1) እና 358

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሠራተኛ በጊዜ ቀጠሮ ከ30 ቀን በላይ መታሰሩ እና ከስራ ገበታው መቅረቱ ከ30 ቀናት የሚበልጥ እስራት እንደተወሰነበት ተቆጥሮ የስራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ ማቋረጥ ተገቢ ስላለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27 /1/በ/

     

    መ/ቁ.114669

    ጥቅምት 24 ቀን 2008 ዓ/ም

    አንድ ሠራተኛ በጊዜ ቀጠሮ ከ30 ቀን በላይ መታሰሩ እና ከስራ ገበታው መቅረቱ ከ30 ቀናት የሚበልጥ እስራት እንደተወሰነበት ተቆጥሮ የስራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ ማቋረጥ ተገቢ ስላለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27 /1/በ/

     

    መ/ቁ.114669

    ጥቅምት 24 ቀን 2008 ዓ/ም

    በደቡብ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ መሰረት በወረዳ በተጀመረ ክርክር በክልሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከፀና ውሳኔው የፀናበት ወገን ለተጨማሪ ይግባኝ ለክልሉ ጠቅላይ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ማቅረብ የሚችል ስለመሆኑ፣ የኢ.ፈ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/3//ሀ/ የደቡብ ክልል ህገ መንግስት አንቀጽ 75/2/ሐ/ የከ/ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ. 43/1994 አንቀጽ 5/3/ የፌደራል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 456/1997 አንቀጽ 12 የደ/ክ/የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 110/1999 አንቀጽ 12/4/

    Download Cassation Decision

  • ተከሳሽ ከሳሽ ያቀረበውን ክስ አምኖ ነገር ግን ሕግ ወይም ሌላ ፍሬ ነገር በመጥቀስ የቀረበብኝ ክስ ዋጋ የለዉም ብሎ የሚከራከር ከሆነ ሙግቱን የሚጀምረው ተከሳሽ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 258/1/

    Download Cassation Decision

  • አንድ ጠበቃ ሕግን የማስከበር ፣ፍትህን የማስገኘትና ለፍትህ አስተዳደሩ የማገዝ ኃላፊነቱን በመተው ተቃራኒ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ መሆኑ ከተረጋገጠ የጥብቅና ፍቃዱ ሊሰረዝ የሚችል ስለመሆኑ የአማራ ክልል የጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥ ምዝገባና የጠበቆች ሥነምግባር ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁ. 75/1994

    Download Cassation Decision

  • ለአንድ ንብረት የሚከፈለው የኢንሹራንስ ገንዘብ የመያዣ መብት ላላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች ይሰጣል የሚለው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ኢንሹራንስ ሰጪው ላልተከፈለ የአርቦን ክፍያ ኢንሹራንስ ገቢውን ከመጠየቅ ውጪ የመያዣ መብት ያለውን አካል መጠየቅ የማይችል ስለመሆኑ የን/ሕ/ቁ.684(1)

    Download Cassation Decision

  • መብቴን የሚነካ ፍርድ ተሰጥቷል በሚል የሚቀርብ የፍርድ መቃወሚያን ለይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ይቅርብ በማለት የሚሰጥ ውሳኔ ተገቢ ሰላለመሆኑ፤ መቃወሚያ መቅረብ ያለበት ክርክሩን ሰምቶ ውሳኔውን ለሰጠው ፍ/ቤት ሰለመሆኑ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418

    Download Cassation Decision

  • በክርክር ሂደት ላይ ፤ የቀረቡት የባለሙያ አሰተያየቶች ተቃራኒ ይዘት ካላቸው ፤ ግልፅ መሰፈረት እና ምክንያት በሌለበት አንደኛውን ተቀብሎ ሌላውን ውድቅ ማደረግ ተገቢ ሰላለመሆኑ፤ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 250 እና 136(1)

    Download Cassation Decision