Federal Court Case Tracker

 • ከዋስትና መብት ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤቶች የተከሳሽን የዋስትና መብት ለመንፈግ የተከሰሰባቸውን የወንጀል ክሶች ብዛትና ከባድነት መነሻ ሊያደርጉ ስለመቻላቸው የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.67/ሀ/

  Download Cassation Decision

 • በህጉ በጠቅላላ የቅጣት ማቅለያነት የተመለከተን ምክንያት ወንጀሉን ለማቋቋም የቀረበ በሆነ ጊዜ ፍ/ቤቶች ይህንን ምክንያት እንደ አንድ የቅጣት ማቅለያነት ሊጠቀሙበት የማይችሉ ስለመሆኑ ፍርድ ቤቶች በህጉ ለዳኞች የሚሰጠውን አመዛዝኖ ቅጣትን የመወሰን ስልጣን ሲጠቀሙ በቅጣት አወሳሰን ረገድ ህጉ ያስቀመጣቸውን መሰረታዊ መርሆዎች ሊጥሱ የማይገባ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁ. 82/2/, 189,86, 180, 179, 182, 184, 82/1/, 88/2/

  Download Cassation Decision

 • የወንጀል ክስ ቀርቦ ተከሳሹ እንዲከላከል በሚል በፍ/ቤት ብይን የተሰጠ መሆኑ ጉዳዩ የመጨረሻ ፍርድ እንደተሰጠበት በመቁጠር የሰበር አቤቱታ ሊቀርብበት የማይቻል ስለመሆኑ

  Download Cassation Decision

 • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤቶች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) አዋጅን በመተላለፍ የሚፈፀሙ የወንጀል ጉዳዮችን ለማየት ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 361/95 አንቀጽ 52/4/ /5/ 41/2/ አዋጅ ቁ. 286/94 አንቀጽ 96 አዋጅ ቁ. 285/94 አንቀጽ 49 የወንጀል ህግ ቁ. 349/1/

  Download Cassation Decision

 • በወንጀል የተከሰሰ ሰው የዋስትና መብት እንዲከበርለት ትዕዛዝ ከተሰጠ በኋላ ትዕዛዙ ተነስቶ ዋስትናውን ሊከለከል ስለመቻሉ የወ/መ/ሥ/ህ/ቁ. 74

  Download Cassation Decision

 • በአንድ ጉዳይ ድጋሚ ክስ ወይም ድጋሚ ቅጣት (principle of double jeopardy) ክልክል ስለመሆኑ የተደነገገው መርህ ሊተረጐም ስለሚችልበት አግባብ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 23 የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.42(1)(ሀ)

  Download Cassation Decision

 • ማዕድናትና የከበሩ ድንጋዮችን ከማዘዋወርና ለሽያጭ ከማቅረብ ጋር በተገናኘ ስለሚኖር የወንጀል ኃላፊነት፣ የወ/ህ/ቁ 346፣347፣378 አዋጅ ቁ. 52/85 አንቀጽ 53(1), (5), 26(4) ደንብ ቁ. 182/80/ አንቀጽ 30(1)(ሀ), 3(ለ) እና 4(ሐ), 38-40 አዋጅ ቁ. 591/2000 አንቀጽ 26(1)(ለ)

  Download Cassation Decision

 • አንድ ሰው በወንጀል ህጉ አንቀጽ 407 መሰረት በስልጣን ያለአግባብ መገልገል ወንጀል ጥፋተኛ ተደርጐ ቅጣት ሊጣልበት የሚችልበት አግባብ፣ የመ/ህ/ቁ 407(1)(ሀ)

  Download Cassation Decision

 • የመንግስት ሰራተኛ ሳይሆኑ ነገር ግን ከመንግስት ሰራተኞች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር በህዝብና በመንግስት ጥቅም ላይ ጉዳት ማድረስ በሙስና ወንጀል ሊያስጠይቅ የሚችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.434/97 አንቀፅ 7 የወ/ህ/ቁ.407(1)(ሀ),33

  Download Cassation Decision

 • ፍ/ቤት በወንጀል ጉዳይ የተከሰሰን ሰው በተመለከተ አስቀድሞ የፈቀደውን የዋስትና መብት በራሱ አነሳሽነት ወይም በማናቸውም ባለጉዳይ አመልካችነት አዲስ ነገር ተከስቷል ብሎ ካመነ ዋስትናው እንዲነሳ ትዕዛዝ ሊሰጥ የሚችል ስለመሆኑ የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 74

  Download Cassation Decision

 • በወንጀል ድርጊት በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ያደረሰ ሰው ከጉዳቱ በኋላ ተጐጂውን ወደ ህክምና ቦታ የወሰደው መሆኑ ብቻ በድርጊቱ የተፀፀተ መሆኑን ያሳያል በሚል ቅጣትን ከመነሻው በታች በመወረድ ቀልሎ እንዲወሰን ለማድረግ የሚያስችል ስላለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁ. 543/3/, 59/1/, 575/2/, 82/1/ የትራንስፖርት ማሻሻያ ደንብ ቁ. 279/56 አንቀጽ 35

  Download Cassation Decision

 • በኤግዚቢትነት በፖሊስ ከተያዙ ንብረቶች ጋር በተገናኘ የንብረቶቹ ባለቤት ነኝ የሚል ወገን ንብረቱ ይመለስለት ዘንድ በፖሊስ ጽ/ቤቱ ላይ የሚያቀርበው ክስ በተገቢው ማስረጃ ተጣርቶ እልባት ሊሰጠው የሚገባ ስለመሆኑ

  Download Cassation Decision

 • የሰበር ችሎት ፍሬ ጉዳይ የማጣራት ማስረጃ የመመዘንና የመመርመር ስልጣን የሌለው ቢሆንም በሥር ፍ/ቤቶች ወይም የዳኝነት ስልጣን የተሰጣቸው ሌሎች አካላት መሰረታዊ የሆነ የዳኝነት አካሄድ ስርዓትን ሳይከተሉ፣ መመስረት የሚገባቸውን ጭብጥ ሳይመሰርቱና ጭብጡን የማስረዳት ግዴታ (Buden of proof) ያለበት ተከራካሪ ወገን የማስረዳት ግዴታውን በአግባቡ እንዲወጣ ሳያደርጉና መጣራት ያለበትን (የሚገባውን) ፍሬ ጉዳይ ሳያጣሩ የሰጡትን ውሣኔ በሰበር አይቶ ለማረም ስልጣን ያለው ስለመሆኑ፣ በወ/ህ/አ. 419

  Download Cassation Decision

 • በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ክስ የቀረበበት ሰው በዋስትና ወረቀት ለመለቀቅ የሚያቀርበውን ጥያቄ ፍ/ቤቶች ተከሳሹ በቀረበበት የሙስና ወንጀል ክስ ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝ ሊጣልበት የሚችለውን የቅጣት ጣሪያ መነሻ በማድረግ ውሣኔ ሊሰጡበት የሚገባ ስለመሆኑ ተከሳሹ የተከሰሰበት ወንጀል ከአስር ዓመት በላይ በእስራት ሊያስቀጣ የሚችል በሆነ ጊዜ በዋስትና ወረቀት እንዲለቀቅ ሊፈቀድ የማይችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 434/97 አንቀጽ 4/1/ አዋጅ ቁ. 239/93 አንቀጽ 2 አዋጅ ቁ. 236/93 የወንጀል ህግ ቁጥር 676/1/

  Download Cassation Decision

 • አንድ የወንጀል ድርጊት በእርግጥም ተጀምሯል /ተፈጽሟል/ ለማለት የሚቻለው የተደረገው ተግባር በማያጠራጥር ሁኔታና በቀጥታ ወንጀሉን ለመፈፀም ወደታሰበለት ግብ ለማድረስ የተደረገ መሆኑን ለማረጋገጥ ሲቻል ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁ. 27/1/ 540 555/ሀ//ለ/

  Download Cassation Decision

 • በወንጀል ተከስሶ የቀረበ ተጠርጣሪ በፍ/ቤት በሰጠው የእምነት ቃል መሰረት ጥፋተኛ ተብሎ ቅጣት ከተጣለበት በኋላ በተሰጠው የጥፋተኝነት ውሣኔ ላይ ይግባኝ ለማለት የማይችል ስለመሆኑ

  Download Cassation Decision

 • በጉምሩክ ወንጀል የተከሰሰ ሰው በነፃ የተለቀቀ ቢሆንም ወንጀሉ የተፈፀመበት እቃ ወይም ማጓጓዣየሚወረሰው የጉምሩክ ህግን የመተላለፍ ድርጊት ስለመፈፀሙ ፍርድ ቤቱን የሚያጠግብ ማስረጃ ሲቀርብ ስለመሆኑና ማስረጃው አጥጋቢ ካልሆነ ብቻ ፍ/ቤት እቃውን (ማጓጓዣውን) እንዳይወረስ በማድረግ ተገቢውን ቀረጥና ታክስ እንዲከፈል ሊያዝ የሚገባው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.622/2001 አንቀፅ 104(3)(ሀ), 104(3)(ለ)

  Download Cassation Decision

 • ከመንግስት ሰራተኞች ውጪ በሆኑ ሰዎች የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎችን በተመለከተ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ክስ ሊያቀርብ ስለመቻሉ ኮሚሽኑ የወንጀል ክስ ለመመስረት ስልጣን ከተሰጠው ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ወይም ወንጀል ፈፅሟል ተብሎ የተከሰሰ ሰው ከሙስና ወንጀሉ ጋር አንድ ላይ መከሰስ ያለበትን የወንጀል ድርጊት አንድ ላይ (አጣምሮ) ሊያቀርብ ስለመቻሉ የወ/ህ/ቁ 379(2), 375, 404(4)(3) አዋጅ ቁ. 434/97 አንቀፅ 58 አዋጅ ቁ.236/93 አንቀፅ የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ.110

  Download Cassation Decision

 • ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ በሥር ፍ/ቤቶች በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ እውነታ የተጠቀሰውን ወንጀል የሚያቋቁም መሆን አለመሆኑ ጉዳይ የህግ ጭብጥ በመሆኑ በሰበር ችሎት ሊመረመር የሚችል ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁጥር 675/1/

  Download Cassation Decision

 • ከጉምሩክ ባለስልጣን ሹም ፈቃድ ሳያገኝ በመተላለፍ ላይ ያሉ ወይም የጉምሩክ ወደብ በደረሱ ወቅት የእቃ መያዣ ላይ የተደረገን ማሸጊያ መፍታት በወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ በጉምሩክ ወደብ በምርመራ ላይ ካሉ ዕቃዎች ለሳምፕልነት በሚል ወስዶ አለመመለስ በወንጀል የሚያስጠይቅ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.622/2001 አንቀፅ 100, 95(ሀ)

  Download Cassation Decision