criminal law

  • አንድ የወንጀል ድርጊትን ማስረዳት ጋር በተያያዘ የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃ (circumstantial evidence) በይዘቱ አንድ ክስተት ከመፈጠሩ በፊት፣ ክስተቱ ሲፈጠር ወይም ድርጊቱ ሲፈፀምና ክስተቱ ከተፈጠረ ወይም ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ፣ ያሉትን አካባቢያዊ ሁኔታዎች የሚያሣይና የሚገልጽ በመሆኑ ህጋዊ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 137(1)

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ፍርድ ሂደት አንድ ጉዳይ ተከሳሽ በሌለበት ወይም በክርክሩ ሂደት ተሳታፊ ሳይደረግ (ሳይሆን)(default procedure) ነው የታየው ለማለት ስለሚቻልበት አግባብ፣ የቅጣት አስተያየት በሚሰጥበት ጊዜ ያለመቅረብ ተከሳሽ በሌለበት የተሰጠ ውሣኔ ነው ሊያስብል የማይችል ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.161, 164, 197, 202, 149 (4) (1) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 20(4))

    Download Cassation Decision

  • የተሽከርካሪ ባለቤት የሆነ ሰው በተሽከርካሪው የተፈፀመ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ህግን የመጣስ ወንጀል ከራሱ እውቀት ወይም ፈቃድ ወጪ መሆኑን ማስረዳት የቻለ እንደሆነ የተፈፀመው ወንጀል ክብደት እየታየ የገንዘብ መቀጮ ከፍሎ ተሽከርካሪው ሊለቀቅለት (ላይወረስ) የሚችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.622/2001 አንቀጽ 109(1) የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መመሪያ ቁ.50/2003 አንቀጽ 6(2)

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ጉዳይ የወንጀል ክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን አቆጣጠር ጋር በተገናኘ ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱን ፈጽሟል በሚል የተጠረጠረ ሰው ላይ የሚያደርገው ምርመራ የይርጋ ጊዜውን የሚያቋርጠው ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ.221 106(1), 420(2), 271 (1) (ሠ) 219 (2)

    Download Cassation Decision

  • የወንጀል ህግ አንቀጽ 692(1)ን በመተላለፍ አንድ ሰው በወንጀል ተጠያቂ ሊሆን ስለሚችልበት ሁኔታ፣ የወ/ህ/አ. 692,32(1)(ለ)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ተከሳሽ የተከሰሰበትን የወንጀል ክስ ይዘት በሚገባ ተረድቶና አድራጐቱን በተመለከተም እንደቀረበበት የወንጀል ክስ በዝርዝር መፈፀሙን ገልፆ በማመን የእምነት ቃሉን ሰጥቷል በሚል መነሻ በተከሣሹ ላይ የጥፋተኝነት ውሣኔ በአግባቡ ተሰጥቷል ለማለት ስለሚቻልበት አግባብ፣  ፍ/ቤቶች ተከሣሹ የቀረበበትን ክስ በተመለከተ በድርጊቱ አፈፃፀም ረገድ የገለፀውን ዝርዝር የአፈፃፀም ሁኔታ በመዝገብ ላይ ባለማስፈር በደፈናው ክሱን አምኗል በማለት የሚሰጡት የጥፋተኛነት ውሣኔ ተገቢ ስላለመሆኑ፣ የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ.134(1) የወ/ህ/አ.23

    Download Cassation Decision

  • የባንክ ሥራ ጋር በተገናኘ የሥራ አመራር ላይ ጉድለት በመፈፀም ስለሚደረግ ወንጀል፣ የወ/ህ/አ. 703

    Download Cassation Decision

  • የሥራ ግዴታን ካለመወጣት ጋር በተገናኘ ሠራተኛ የሆነ ሰው ከአሰሪው የተረከበው ንብረት ላይ ጉዳት እንዲከሰት በማድረጉ ወይም ንብረቱ እንዲጐድል (እንዲጠፋ) በማድረጉ ምክንያት በወንጀል ጉዳይ ክስ ቀርቦበት ጥፋተኛነቱ የተረጋገጠ እንደሆነ በተመሣሣይ ጉዳይ ሠራተኛው በአሰሪው ንብረት ላይ ባደረሰው ጉዳት መጠን በፍትሐብሔር ሊጠየቅ ስለመቻሉ፣  ከአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሠራተኛው በአሰሪው ንብረት ላይ የደረሰ ጉዳትን በተመለከተ በወንጀል ጉዳይ ተከስሶ ጥፋተኛ የተባለ እንደሆነ ጉዳት የደረሰበትን ንብረት በተመለከተ በፍትሐብሔር ተጠያቂ ሊደረግ የሚገባ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 515 የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2149

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሠው በፍ/ብሔር ጉዳይ ተከስሶ ኃላፊነት የለበትም ተብሎ የመጨረሻ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ በተመሳሳይ ማስረጃ በወንጀል ጉዳይ ተከስሶ ተጠያቂ ነው (ኃላፊነት አለበት) ለማለት የሚያስችል የህግ አግባብ ስላለመኖሩ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2149 የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 141

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰው በወ/ህ/አ. 429 ጉቦ ማቀባበል የወንጀል ድርጊት ክስ ሊቀርብበትና ጥፋተኛ ተብሎ ቅጣት ሊጣልበት ስለሚችልበት አግባብ፣ የወ/ህ/አ. 429,23(4,(1),58)

    Download Cassation Decision

  • ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተገናኘ በወንጀል ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦ የተጣለበትን ቅጣት ፈጽሞ ያጠናቀቀ ሰው በፍርድ ቤት መሰየም በግለሠቡ የጡረታ መብት ላይ ስለሚኖረው ውጤት  በመሰየም ሊገኝ የሚችለው መብት ግለሰቡ ከመሰየሙ አስቀድሞ በቅጣት ቀሪ ሆኖበት የነበረውን መብት ሳይሆን ግለሰቡ ከተሰየመበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ፊት ሊጠበቅለት የሚገባውን መብት በተመለከተ ብቻ ስለመሆኑ፣  የመንግስት ሰራተኛ የነበረና የጡረታ መብት ተጠቃሚ የሆነ ሠው በወንጀል ጉዳይ ተከስሶና ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦ በፍ/ቤት ቢያንስ የ3 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት የተወሰነበት በመሆኑ የጡረታ መብቱን እንዲያጣ የተደረገ ሠው ከቅጣቱ በኋላ በፍ/ቤት መሰየሙ አስቀድሞ በቅጣት ቀሪ ሆኖበት የነበረውን የጡረታ መብቱን መልሶ ለማግኘት የማያስችል ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ. 231,235(1),232 አዋጅ ቁ. 209/55 አዋጅ ቁ. 5/67 አዋጅ ቁ.345/95 አንቀጽ 52/1/

    Download Cassation Decision

  • በሌላ ሰው ጥቅም የሥራ አመራር ላይ ወንጀል ተፈጽሟል ለማለት ስለሚቻልበት አግባብ፣  በተከታታይ ለተፈፀመ ወንጀል ይርጋ ስለሚቆጠርበት አገባብ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ/፣702/3/፣219/2/

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ጉዳይ የተከሰሰው ሰው ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦ ንብረቱ በቅጣት ለመንግስት እንዲወረስ በተወሰነ ጊዜ በአፈፃፀም ደረጃ ከአጥፊው (ወንጀለኛው) ንብረት ውስጥ ለቤተሰቡ ህይወትና መተዳደሪያ ሊውል የሚገባውን ድርሻ ለመወሰን ስለሚቻልበት አግባብ፣  በውርስ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ከተወሰነው የአጥፊው (የወንጀለኛው) ሀብትና ንብረት ውስጥ ለቤተሰቡ ህይወት መተዳደሪያ ሊውል የሚገባው ድርሻ ሊሸፍናቸው የሚገባው የወጪ አይነቶችና መጠናቸው፣  የአጥፊው (ወንጀለኛው) ጋር ጋብቻ የመሠረተ ሰው እንዲወረስ ከተወሰነው ንብረት ግማሽ ድርሻ የነበረው መሆኑን መሠረት በማድረግ በአፈፃፀም የሚያነሣው የቅድሚያ ግዢ መብት ጥያቄ የህግ መሠረት የሌለው በመሆኑ ጥያቄው እንደ መብት አቤቱታ ሊቀርብበት የማይችል ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 98(ለ)(መ), 98(3) (ለ)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሠው የአራጣ ወንጀል ድርጊት ፈጽሟል በሚል በወንጀል ተጠያቂ ሊሆን ስለሚችልበት አግባብ፣  በወር 10% ወለድ ታስቦ እንዲከፈል በመስማማት ገንዘብ ማበደር በአራጣ የወንጀል ድርጊት የሚያስጠይቅ ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ 667(1)

    Download Cassation Decision

  • የውጭ ምንዛሬ ከአገር ውስጥ ወደ ውጭ አገር ያለህጋዊ እውቅናና ፈቃድ ማስወጣት የወንጀል ኃላፊነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ፣  የወንጀል ድርጊትን የፈፀምኩት ባለማወቅ ነው በሚል የሚቀርብ ክርክር ተቀባይነት የሌለውና ህግን አለማወቅ ይቅርታ የማያሰጥ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 622/2001 አንቀጽ 99 አዋጅ ቁ. 591/2000 አንቀጽ 20(3) የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 22(1) የወንጀል ህግ አንቀጽ 2(2),25,23(2),81(1)(3)

    Download Cassation Decision

  • የአንድ ደርጊት ወይም ግድፈት ወንጀልነት በህግ በግልጽ ተደንግጐ በማይገኝበት ሁኔታ የድርጊቱን ወይም የግድፈቱን ፈፃሚ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ የማይቻል ስለመሆኑ፣  በወንጀል ጉዳይ የሚቀርብ ክስ ስለ ድርጊቱና አፈፃፀሙ የሚሰጠው መግለጫ ድርጊቱን ወንጀል ከሚያደርገው ህግ አነጋገር በጣም የተቀራረበ መሆን የሚገባው ስለመሆኑ፣  በንግድ ሥራ ለተሰማሩ ወይም ሌሎች ሰዎች በግለሰብ ደረጃ መጠኑ በርካታ የሆነ ገንዘብን በተደጋጋሚ በብድር የመስጠት ተግባር በህግ የተከለከለ ወይም በወንጀል የሚያስቀጣ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 2, 23(2), 3, 61 የወ/መ/ህ/ሥሥ/ቁ. 112 አዋጅ ቁጥር 83/86 አንቀጽ 59(1), (ሸ), 2(ሀ),

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ጉዳይ ተከስሶ ጥፋተኛ የተባለ ሰው ላይ የሚወሰነው ቅጣት በቅጣት አወሣሠን መመሪያው የተሸፈነ እንደሆነ ቅጣቱ በመመሪያው አግባብ ሊወሰን የሚገባ ስለመሆኑ፣  በወ/ህ/አ 539(1)(ሀ) ድንጋጌ ክስ ቀርቦበት ጥፋተኛ የተባለ ሰው ለእያንዳንዱ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ሶስት እርከን ሊቀነስለት የሚገባ ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ. 539(1)(ሀ) የፌ/ጠ/ፍ/ቤት የቅጣት አወሣሠን መመሪያ ቁ.1/2002 አንቀጽ 16(7)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰው ለመንግስት ሊከፍል የሚገባውን ግብር ባለመክፈሉ በወንጀል ተግባር ሊጠየቅና ጥፋተኛ ተብሎ ሊቀጣ የሚችለው ግብሩን ላለመክፈል በማሰብና ግብር አስገቢው መ/ቤትም ንብረቶቹን በመያዝና በመሸጥ የግብር ገንዘቡን ገቢ እንዳያደርግ ለማድረግና ግብር የመክፈል ኃላፊነቱን ለማምለጥ ንብረቶቹን ለማሸሽ፣ የመሰወር ወይም ሌሎች ተገቢነት የሌላቸው ህገ ወጥ ተግባራትን በመፈፀም ግብርን ያልከፈለ መሆኑ ሲረጋገጥ እንጂ በሌሎች በህግ ተቀባይነት ባላቸው ምክንያቶች ግብሩን ለመክፈል ሳይችል የቀረ እንደሆነ ስላለመሆኑ፣  ማንኛውም ሰው በፍ/ብሔር ጉዳይ ያለበትን እዳ ለመክፈል ባለመቻሉ ምክንያት ብቻ በወንጀል ጉዳይ ጥፋተኛ ተብሎ ሊቀጣ የማይገባ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 285/94 አንቀጽ 49 አዋጅ ቁ. 286/94 አንቀጽ 96, 162 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 13(2) ደንብ ቁጥር 78/94 ICCPR- አንቀጽ 11

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሠው በአንድ ወንጀል ድርጊት ክስ ቀርቦበት የመጨረሻ የሆነ ውሣኔ ተሰጥቷል በማለት በድጋሚ ልከሰስ አይገባም በሚል የሚያቀርበው ክርክር ከዚህ ቀደም ተጣርቶ ክስ የቀረበበትና የመጨረሻ ውሣኔ የተሰጠበት የወንጀል ድርጊትን በድጋሚ (ለሁለተኛ ጊዜ) ክስ ቀርቦበታል ከተባለው የወንጀል ድርጊት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለመሆኑ ተገናዝቦ ሊታይ የሚገባው ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 2(5), 678, 696(ሐ) እና 378 ህገ መንግስት አንቀጽ 23

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ተከሣሽ ላይ የሚወሰነው የእስራት ቅጣት አፈፃፀም እንዲገደብ ለማድረግ ስለማይችልባቸው ሁኔታዎች፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 194(1) እና (2)¸190¸192

    Download Cassation Decision