criminal law

 • የተሻረው ህግ ይሰራ በነበረበት ጊዜ የተፈጸመ ወንጀል ሲኖርና በዚህ ህግ ግን እንደወንጀል ያልተቆጠረ ሲሆን ሊያስከስስም ሆነ ሊያስቀጣ አይችልም ፣ ክሱም ተጀምሮ እንደሆነ የሚቋረጥ ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 5/3/ አዋጅ ቁ. 622/2001 አንቀጽ 99፣ አዋጅ ቁ. 859/2006

  Download Cassation Decision

 • አቃቤ ህግ በዋስትና መለቀቅ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ ፍርድ ቤት የዋስትና መብትን የሚከለከልበቻው ምክንያቶች ከተለየዩ ሁኔታዎች በመመልከት ሊመዝናቸው የሚገባቸው ስለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር67፣75

   

  የሰ/መ/ቁ. 112725 ቀን 22/02/2008 ዓ/ም

  ዳኞች፡-ተሻገር ገ/ስላሴ

  የወንጀል ጉዳዮችን በመጀመሪያ ደረጃ ይሁን በይግባኝ ደረጃ የሚመለከት ፍ/ቤት ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜ የማስረጃውን አጭር መግለጫ፣ ማስረጃውን የተቀበለበትን እናያልተቀበለበትን ምክንያቶች በፍርድ ላይ ማስፈር የሚገባው ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 149/1/

  Download Cassation Decision

 • በወንጀል ጉዳይ ከአንድ በላይ ሰዎች የተከሰሱ እንደሆነ የእያንዳንዱ ተከሳሽ ሚና እና ተሳትፎ ደረጃው በቂና አሳማኝ በሆነ ሁኔታ በከሳሽ ወገን በኩል በሚቀርበው ማስረጃ ነጥሮ ሊወጣ የሚገባ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32፣40 የወ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 141 ተያያዥነት የሌላቸው ፍሬ ነገሮችን መሰረት ተደርጎና የአንድን ነገር መኖር ያለመኖር ሣይረጋገጥ ለአካባቢ ማስረጃ ክብደት መስጠት የማስረጃው አይነት የምዘና መርህን መሰረት ያደረገ ነው ለማለት የሚቻል ስላለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.173(1)

   

  የሰ/መ/ቁጥር 113464

   

  ህዳር 22 ቀን 2008 ዓ/ም

  በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ መሰረት የጉምሩክ ቁጥጥርን አሰናክለሃል ተብሎ ሊጠየቅ የሚችለው ድርጊቱ ሆነ ተብሎ መፈፀሙን አቃቢ ህግ በበቂ ሁኔታ ሲያስረዳ ስለመሆኑ የጉሙሩክ አዋጅ ቁ. 859/2006 አንቀፅ 166
 • በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ሥርዓት ህግ መሰረት ክስ እንዲሻሻል መፍቀድ የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብትን የሚያጣብብ ነው የሚባል ስላለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 188፣119 ኢፌድሪ ሕግ መንግስት አንቀጽ 20(1)

  Download Cassation Decision

 • ማንኛውም እቃ ወይም መጓጓዣ ሊወረስ በሚችል ወንጀል በተከሰሰ ሰው ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ ተጨማሪ ትእዛዝ መስጠት ሳያስፈልግ እቃው ወይም መጓጓዣው እንዲወረስ የሚደረግ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 622/2001 አንቀፅ 104(1)

   

  የሰ/መ/ቁ. 117065 የካተት 30 ቀን 2008ዓ/ም

  ዳኞች፡-ተሻገር ገ/ስላሴ

  በወ/መ/ህ//አ/ቁ. 676(1) የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል የተከሰሰ ሰው የዋስትና መሰጠት (መፈቀድ) ጥያቄ የሚሰጠው በጉዳዩ ላይ በአግባቡ ተመርምሮ እንጂ ከወዲሁ ስላለመሆኑ አዲሱ የፀረ ሙስና ህግ አዋጅ ቁ. 881/2007 አንቀፅ 31

   

  የሰ/መ/ቁ 117383

  ቀን 6/03/2008 ዓ.ም

  ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ

   

  የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የቅጣት ውሳኔ መመሪያ መሰረት በማድረግ በማረም የሚጠው ውሳኔ ከተጠየቀ ዳኝነት ውጭ ተሰጥቷል የሚያስብል ስላለመሆኑ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ.2/2002 አንቀፅ 21(1) (ሀ) ፣ ወ/ሕ/ቁ 184(!0 (ለ) እና 194 (1) (ለ)

  Download Cassation Decision

 • በእምነት ማጉደል ወንጀል ላይ የተቀመጠው ያልተገባ ጥቅም የማዋል ሓሳብ መርሕ ፤ ለከባድ እምነት ማጉደል ወንጀልም ተፈፃሚነት ያለው ስለመሆኑ ፤ ወ/ሕ/ቁ 675(3) እና 676 (2) (ሀ)

  Download Cassation Decision

 • ወንጀል ፈጽሞ የተከሰሰን ህፃን ደህንነት ሊጠበቅበት ሥለሚችልበት አግባብ ለአዋቂ ጥፋተኞች የተደነገጉት መደበኛ ቅጣቶች ለወጣት ወንጀል አድራጊዎች ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ስለመሆኑ፡- የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህግ መንግሥት አንቀጽ 36 (2)፣ የህፃናት መብቶች ኮንቬንሽን አንቀጽ 3(1)፣ የአፍሪካ የህፃናት መብቶች ደኅንነት ቻርተር በአንቀጽ 4 (1) የወንጀል ህግ አንቀጽ 53 (1)፣ 157፣ 168 የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ 171፣180

  Download Cassation Decision

 • በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 188/5/ መሰረት አንድ ፍርድ በተከሳሽ ላይ ከተሰጠ ተከሳሹ ለበላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብሎ ሲቀርብ የበታች ፍርድ ቤትን ውሳኔ የበላይ ፍርድ ቤቱ ማገድ የሚችልበትን አግባብ የሚያሳይ ድንጋጌ ከመሆኑ ውጪ ከሳሽ ወገን በተከሳሽ ነፃ መለቀቅ ላይ ይግባኝ ብሎ ሲሄድ ፍርዱ እንዳይፈፀም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለመስጠት መነሻ የሚያደርገው ስላለመሆኑ

   

  የሰ/መ/ቁ. 118252

  ቀን 24/05/2008 ዓ/ም

  ዳኞች፡- አልማው ወሌ

   

  ...
 • ከአንድ የወንጀል ድርጊት በኃላ ተከታትሎ የተፈፀመ ድርጊት ፤አንድን ወንጀል ከግብ ለማድረስ ሲል ተከታትሎ የተደረገ ድርጊት ከቀድሞ አሳቡና ሊደርስበት ከቀደው ግብ ጋር የተያያዘ በዋናው ወንጀል የሚጠቃለል ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ የሚጣራበት አግባብ፤ ዓ/ሕግ ባስከፈተው የይግባኝ መዝገብ ላይ መ/ሰጭ ሕግን መሰረት አድርጎ የሚቀርበው ክርክር ተቀባይት ሊያጣ የማይገባው ሰለመሆኑ፤ ወ/ሕ/ቁ 88(3)

  Download Cassation Decision

 • በሙከራ ደረጃ ለተፈፀመ ወንጀል ቅጣት እንደሚቀንስ በግልፅ በመመሪያ ቁ.2/2006 ላይ ባይደነገገም ነገር ግን በወንጀል ህጉ ቅጣትን በመሰለው እንዲያቀል ለፍ/ቤቱ በተፈቀደበት ሁኔታ መሰረት ቅጣትን አቅሎ ሊወሰን የሚችል ሰለመሆኑ ፤ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ.2/2006 አንቀፅ 24 ፣ የወ/ሕ/ቁ 31 እና 180

  Download Cassation Decision

 • በወንጀል ጉዳይ ተከሳሽ በሌለበት ጠበቃ ብቻውን ሊቀርብ አይችልም የሚለው ጉዳይ ተፈፃሚ የሚሆነው ለተፈጥሮ ሰዎች እንጂ የህግ ሰውነት ላላቸው ሰዎች ስላለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.127

   

  የሰ/መ/ቁ/120762 የካቲት 25 ቀን 2008 ዓ.ም

  ዳኞች፡-አልማው ወሌ

  በወንጀል ተጠርጥሮ በህግ ከለላ ስር የሚገኝን ተጠርጣሪ በዋስትና የመለቀቅ ጥያቄ ባነሳ ጊዜ ተጠርጣሪው በከተማው ውስጥ ቋሚ የመኖሪያ /የመታወቂያ/ አድራሻ የለውም በማለት የዋስትና መብቱን መከልከል ህገ መንግስታዊ ስላለመሆኑ፣ አንቀጽ 19/6/፣ 25 እና የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 69/ሀ/

  Download Cassation Decision

 • የዋስትና መብት የሚነፈግባቸው ምክንያቶች ፍርድ ቤቶች ከተለያዩ ሁኔታዎች አንፃር እየተመለከቱ ሊመዝኗቸው የሚገባቸው ስለመሆኑ አንድ ተከሣሽ የዋስትና መብት ቢከበርለት ግዴታውን የሚፈጽም የማይመስል ነው ተብሎ ግምት የሚወሰደው በቂና ህጋዊ ሊባሉ በሚችሉ ምክንያቶች ሊሆን እንደሚገባ፤ እንዲሁም ምክንያቶቹ በቂና ህጋዊ ናቸው የሚለው ጉዳይ ከተለያዩ ከባባዊ ሁኔታዎችና ከጉዳዩ ልዩ ባህርይ አንፃር ፍርድ ቤቱ ሊገነዘበው የሚችለው ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባ ስለመሆኑ የወ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 67(ሀ)

  Download Cassation Decision

 • በወንጀል ጉዳይ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ አዲስ የወጣ ህግ ተከሳሹን የሚጠቅም በሆነ ጊዜ ተከሳሹ አዲሱ ህግ ተፈፃሚ እንዲሆን አቤቱታ ባቀረበ ጊዜ አዲስ የወጣው ህግ ተፈፃሚ እንዲሆን መደረግ ያለበት ስለመሆኑና በዚሁ ጉዳይ አቤቱታ የቀረበበት ጉዳይ በባህሪው እንደመደበኛ የክርክር ጉዳይ የሚታይ ሳይሆን በቀረበ ጊዜ ሊስተናገድ የሚችል በመሆኑ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የቀረበ አቤቱታ ነው በማለት ተቀባይነት የለውም የማይባል ስለመሆኑ 

  የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 22(2)፣ የወ/ሕ/አንቀጽ 6 እና 9(1)፤ ዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት አንቀጽ15/1/ 

  Download here

 • Cassation Decision no. 21411

 • በወንጀል ህግ የሃሳብ ክፍል የሚረጋገጠው ከወንጀል ድርጊት አፈፃፀሙ በመነሳት ስለመሆኑ የወ/መ/ህ/ቁ. 522 /1/ /ሀ/

  Cassation Decision no. 22069