Federal Court Case Tracker

 • ውልን /ስምምነትን/ መሰረት ባደረገ ግንኙነት አንድን ንብረት ወስዶ በውሉ መሰረት ለመመለስ ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈጽሟል በሚል የወንጀል ክስ ሊቀርብበት የማይቻል ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁ. 23/2/, 24, 57, 58

  Download Cassation Decision

 • በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ከአንድ አይነት የወንጀል ድርጊት ጋር በተያያዘ በሁለት የተለያዩ የወንጀል ክሶች የተከሰሰ ተጠርጣሪ በአንዱ የወንጀል ክስ የተመለከቱ ፍሬ ነገሮች መከሰት ጋር በተገናኘ ጥፋተኛ ለማለት ያልተቻለ እንደሆነ በሌላኛው ክስ ጥፋተኛ ለማድረግ የማይቻል ስለመሆኑ የወ/ህ/ቁ 407(ሐ), 670, 677 የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 141, 142, 149(1)

  Download Cassation Decision

 • በወንጀል የተከሰሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በግላቸው ጠበቃ ለማቆም የማይችሉ በሆነ ጊዜ በመንግስት ወጪ የጠበቃ ድጋፍና እርዳታ ሊያገኙ የሚችሉበት አግባብ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 20(5) አዋጅ ቁ.27/88 አንቀፅ 35 አዋጅ ቁ.123/90 አዋጅ ቁ.27/885

  Download Cassation Decision

 • ተጨማሪ ማስረጃን ከመቀበል ጋር በተያያዘ በወንጀል ህግ ቁጥር 143/2/ ሥር የተመለከተው ድንጋጌ ፍ/ቤቱ ለፍትህ አሰጣጥ ተገቢ ነው ብሎ ሲያመን ትዕዛዝ ሊሰጥበት የሚችል ስለመሆኑ በፈቃጅነት (permissive) የተቀመጠ እንጂ አስገዳጅ የህግ ድንጋጌ ስላለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁ. 143/2/

  Download Cassation Decision

 • አንድ የወንጀል አፈፃፀም ተግባር ሙከራ ደረጃ ላይ ደርሷል (Attempt) ሊባል የሚችልበት አግባብ የወ/ህ/አ 32(1)(ሀ),27(1),671(1)

  Download Cassation Decision

 • በፍ/ቤት የወንጀል ክስ ቀርቦ የጥፋተኝት ውሣኔ በተሰጠበት የወንጀል ድርጊት ወንጀለኛው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ያገኘው ንብረት ለመንግስት እንዲወረስ መደረግ ያለበት ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ 98(1)(2),

  Download Cassation Decision

 • አንድ ወኪል ከወካዩ በውክልና ስልጣኑ የወሰደውን ንብረት ለመመለስ ፈቃደኛ ያለመሆኑ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 676(2) ድንጋጌ መሰረት ሊያስጠይቀው ስለመቻሉ የወ/ህ/ቁ 676(2)

  Download Cassation Decision

 • ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ ይዞ በመገኘት ወንጀል አንድ ሰው ተጠያቂ የሚሆነው የምዝገባ ሥርዓት የተዘረጋ እንደሆነ ብቻ ነው ለማለት የሚያስችል የህግ አግባብ ስላለመኖሩ የወ/ህ/ቁ.419

  Download Cassation Decision

 • በወንጀል ህግ ቁጥር 448 ስር አንድ ሰው ለፍትህ እርዳታ ለመስጠት እንቢተኛ ሆኗል በሚል ወዲያውኑ ጉዳዩን በያዘው ፍ/ቤት ለመቅጣት ስለሚቻልበት አግባብ የወ/ህ/ቁ 448(1), (3), 23(2), 58

  Download Cassation Decision

 • ፍርድ ቤቶች በወንጀል ጉዳይ የዋስትና ጥያቄን ላለመቀበል ሥልጣን (discretion) ያላቸው ስለመሆኑ፣ ዋስትናን ለመከልከል ፍ/ቤቶች የሚሰጡት ምክንያት በቂና ህጋዊ ናቸው ሊባሉ የሚችሉበት አግባብ፣ የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ.67

  Download Cassation Decision

 • “የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ማውጣት” በሚል በወንጀል ህጉ ውስጥ የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት ለማቋቋም ቼኩ ለክፍያ ባንክ በቀረበበት ጊዜ በቂ ስንቅ የሌለው መሆኑን /ያለመኖሩ ማረጋገጥ ብቻ በቂ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁ. 693/1/

  Download Cassation Decision

 • በወንጀል ጉዳይ የተከሰሰ ሰው የሚያነሳው የጤና ችግር ከዋስትና መብት አኳያ ሲታይ ስላለው ህጋዊ ጥበቃ

  Download Cassation Decision

 • የተጨማሪ እሴት ታክስን ተግባራዊ ለማድረግ በወጣው አዋጅ ቁ.285/94 አንቀጽ 49 መሰረት በወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ተከሳሽ ላይ ቅጣት ሊጣል ስለሚችልበት ሁኔታ፣ አዋጅ ቁ.285/94 አንቀጽ 49,47,50(2) የወ/ህ/አ 2(2)

  Download Cassation Decision

 • ለግል አገልግሎት ከቀረጥና ከታክስ ነፃ የገባን መኪና ለብድር መያዣነት መስጠት በወንጀል ኃላፊነትን (ተጠያቂነትን) የሚያስከትል ስለመሆኑ በወንጀል ጉዳይ በቅጣት መልክ የሚጣለው የገንዘብ መቀጮ በፍ/ብሔር ጉዳይ ከሚኖረው የአንድነትና የነጠላ ኃላፊነት የተለየ ስለመሆኑና ቅጣቱ በእያንዳንዱ አጥፊ ላይ ለየብቻ ሊጣል የሚገባው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.345/95 አንቀጽ 73(1) አዋጅ ቁ. 60/89 አዋጅ ቁ.280/94 የወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1)(ሀ), 41

  Download Cassation Decision

 • የግንባታና የኮንስትራክሽን ማዕድን ማውጣት ሥራ ጋር በተያያዘ በሚመለከተው የመንግስት አካል የተሰጠ የፀና ፈቃድ ሣይኖር ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የመግዛትና የመሸጥ ውል መፈፀም በወንጀል ተጠያቂነትን ሊያስከትል ስለመቻሉ ህገ ወጥ ወይም ወንጀል ስለመሆኑ የተደነገገ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የተደረጉ ውለታዎችን (ውሎችን) በህግ ኃይል እንዲፈፀሙ በሚል ለፍ/ቤት ጥያቄውን በቀረበ ጊዜ ዳኞች ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ የሚገባቸው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1718, 1716 የወ/ህ/ቁ.353(1)(ለ) አዋጅ ቁ.52/85 አንቀፅ 53(5) ደንብ ቁ.182/86 አንቀፅ 39

  Download Cassation Decision

 • የንግድ ፈቃድ መብትን መጣስ በአዋጅ ቁ. 501/98 መሰረት የወንጀል ተጠያቂነትን ስለሚያስከትልበት አግባብ

  Download Cassation Decision

 • ከቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጋር በተያያዘ የፊልም ባለቤት ለመሆን በማሰብ በባለሃብትና ፊልሙን ለመስራት በሚል በተደረገ ስምምነት መነሻነት ፊልሙን ለህዝብ ከማቅረብ ጋር ተያይዞ ጉዳዩ በፍ/ብሔር ክርክር ተደርጐበት በተሰጠ ውሣኔ መሰረት ፊልሙን በእጅ አድርጐ መገኘት በወንጀል ተጠያቂነት የማያስከትል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.410/96 አንቀፅ 7(1)(ሀ), 36(1) የወ/ህ/ቁ.23(2), 57-59

  Download Cassation Decision

 • የሥራና ሠራተኛን ማገናኘት አዋጅ ቁ.632/2002 በመተላለፍ ሊኖር ስለሚችለው የወንጀል ተጠያቂነት ከቀረበ የወንጀል ክስ ጋር በተያያዘ የግል ተበዳይ የሆነ ሰው ቀርቦ ካልመሰከረ በስተቀር ክሱን ለማስረዳት የሚቀርቡ ሌሎች ማስረጃዎች ተከሳሹን ጥፋተኛ ለማለት ብቁ አይደሉም ሊባል የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.632/2002 አንቀፅ 16(1)(መ), 18(1)(ሀ), 20(2), 40(3)

  Download Cassation Decision

 • አንድ ሰው በወንጀል ህግ አንቀጽ 598(2) መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ውጪ አገር ልኳል በሚል ጥፋተኛ ተብሎ ሊቀጣ ስለሚችልበት አግባብ የወ/ህ/ቁ 598(2)

  Download Cassation Decision

 • ማንኛውም ሰው በወንጀል ህግና ሥርዓት መሠረት ተከስሶ የመጨረሻ በሆነ ውሣኔ ጥፋተኝነቱ በተረጋገጠበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም (Principle of Double Jeopardy) በሚል የሚታወቀው የወንጀል ህግ መርህ ሊተረጐምና ሥራ ላይ ሊውል የሚችልበት አግባብ፣ አንድ በወንጀል የተከሰሰ ሰው በድጋሚ የቀረበበትን የወንጀል ክስ በአንድ ጉዳይ በድጋሚ ያለመከሰስና ያለመቀጣት መብቴ ተጥሷል በሚል ክርክር ለማቅረብ ሊሟሉ ስለሚገቡ ህጋዊ መስፈርቶች፣ ዐቃቤ ህግ በአንድ ተከሳሽ ላይ የወንጀል ክስ ከማቀርቡ በፊት ተከሳሹ አንድ ወንጀል በመፈፀም ሀሣብ የሠራው አንድ የወንጀል ድርጊት ያስከተላቸውን ወይም ሊያስከትላቸው የሚችላቸውን ውጤቶች ሁለተናዊ በሆነ መንገድ በማገናዘብ አግባብነት ያላቸውን የህግ ድንጋጌዎች በመለየትና በመጥቀስ የወንጀል ክሱን በጥንቃቄ የማቅረብ ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ 2(5), 24(1) የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 130,131, 41, 111, 112 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ህግ መንግስት አንቀጽ 23,13(2)

  Download Cassation Decision