Federal Court Case Tracker

volume 22

if you want the whole pdf click here volume 22

volume 22

 • 131151 contract law/ sale of immovable property/ period of limitation

  ከ ቤት ሽያጭ ውል ጋር በተያያዘ የይርጋው ጊዜ ስለሚታሰብበት አግባብ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 Download Cassation Decision

 • 120468 contract law/ non binding agreement

  አ ንድ ሥራን ለመስራት የመተባበርና የመተጋገዝ ስምምነት ማድረግ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ስምምነት ነው ከሚባል በስተቀር አስገዳጅነት ያለው በሕግ ፊት ግዴታን የሚፈጥር ውል አለ ለማለት የሚያስችል ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1678፤1731፤1771 Download Cassation Decision

 • 122595 criminal law/ custom duty/ confiscation

  ማ ንኛውም ሰው አግባብነት ካለው አካል ፍቃድ ባላገኘበት ሁኔታ የተሸከርካሪውን የሞተር፣ የሻንሲ ቁጥር እና መሠለ መረጃዎችን የመቀየር ተግባር የፈጸመ ከሆነ አደራጎቱ የተከለከለና በወንጀል ህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ፣ አንድ ተሽከርካሪ የጉምሩክ ሕግን በመተላለፍ በህገወጥ መንገድ ወደ ሃገር ውስጥ መግባቱ በበቂ ማስረጃ የተረጋገጠ ከሆነ የጉምሩክ አዋጅ በሚደነግገዉ አግባብ መኪናዉ በመንግስት ከመወረስ ሊድን የሚችልበት ሁኔታ ስላለመኖሩ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 104/3/ /ሀ/ ፤ ስለተሽከርካሪዎች መለያ፤መመርመሪያ እና መመዝገቢያ የወጣ አዋጅ ቁጥር 681/2002 አንቀጽ 42/5/ እና 48/2/ Download Cassation Decision

 • 123761 contract law/ sale of immovable property/ registration effect on third party

  አ ንድ የሽያጭ ውል ያደረገ ወገን የተደረገው የሽያጭ ውል ያለመመዝገቡን የማይንቀሳቀስ ንብረት በእጁ ባስገባ 3ኛ ወገን ላይ በመቃወሚያነት ለማንሳት የማይችል ስለመሆኑ፣ የሽያጭ ውል ያደረገ ወገን በውሉ መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረት ለ3ኛ ወገን ለማስተላለፍ የተከናወኑ ተግባራትን ሁሉ ለመቃወም የሚችለው የተደረገው የሽያጭ ውል የተመዘገበ ከሆነ ብቻ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2878Download Cassation Decision

 • 124725 contract law/ urban land lease/ unlawful object/ Tigray

  በሊዝ አዋጅ ቁጥር 272/94 እና አዋጁን ለማስፈጸም በወጣዉ የትግራይ ክልል ደንብ መሰረት የአምልኮ ቦታዎች በመንግስት የሚሰጡ መሆናቸዉን ቢደነግጉም ከግለሰቦች እንዳይገዛ በግልጽ ክልከላ የማያደርግ ስለመሆኑ፡- አንድ ውል ህገወጥ ነው በሚል ምክንያት ፈራሽ ሊሆን የሚችለው የውሉ መሰረት የሆነው መብትና ግዴታ በህግ በተከለከለ ነገር ላይ መደረጉ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ፣ ሊዝ አዋጅ ቁጥር 272/94 እና አዋጁን ለማስፈጸም የወጣ የትግራይ ክልል ደንብ ቁጥር 62/2002 እና የፍትሐብሄር ህግ አንቀጽ 1716Download Cassation Decision

 • 126411 family law/ irregular union/ evidence

  ጋ ብቻ ሳይፈጸም እንደባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነትን ለማስረዳት የቀረበ ማስረጃ ግንኙነቱን የማሳየት ብቃት ያለው መሆኑ ከተረጋገጠ የግንኙነቱን ያለመኖር በማንሳት የሚከራከረው ሌላኛው ወገን በህግ ጥበቃ ሊደረግለት የሚገባ ግንኙነት ስላለመኖሩና ንብረቶችም የግል ስለመሆናቸው የማስረዳት ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 75/1995 117/4/ እና 114 እና 97 አንቀጽ 109፣110፣113 እና 117 Download Cassation Decision

 • 126529 administrative law/ valuation

  አ ንድ ቀድሞ በነበረ መመሪያ ዋጋ የወጣለትን ንብረት የተረከበ ወገን የንብረቱን መጥፋት ተከትሎ ክስ ሲመሰረት የንብረቱ ዋጋ በሌላ አዲስ መመርያ የተሻሻለበት ሁኔታ መኖሩ ከተረጋገጠ ንብረቱ የጠፋበት ወገን ተጠያቂ የሚሆነው አዲስ በወጣው መመርያ መሠረት በወጣው የዋጋ ተመን አግባብ ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 126667 labor law dispute/ probation/ termination of contract of employment

  የ ሙከራ ጊዜ ቅጥር ሲፈጸም ሰራተኛው በግልጽ እንዲያውቀው ሳይደረግና ስምምነት ሲደረግም በጽሁፍ ተደርጎ በሁለት ምስክሮች ባልተረጋገጠበት አሰሪው ሠራተኛው ለተቀጠረበት የሥራ መደብ ተስማሚ ሆኖ አልተገኘም በሚል የቅጥር ውሉን ያለምንም ማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ በህጉ መብት ያልተሰጠው ስለመሆኑ፣ የአ/ቁ. 377/96 አንቀጽ 1/1/ /2/ እና /3/ Download Cassation Decision

 • 127313 criminal law/ criminal procedure/ non appearance of accused

  የ ተከሰሰ ሰው የዓቃቤ ህግ ማስረጃ ሲሰማ በመገኘት የዓቃቤ ህግና ምስክሮች የመጠየቅና የመመርመር መብቱን በአግባቡ ከተጠቀመና መከላከያ ማስረጃ በማቅረብ እንዲከላከል ተፈቅዶለት ቀጠሮውን አክብሮ ያልቀረበ በሆነበት አግባብ ፍ/ቤቶች ጉዳዩ በሌለበት የሚታይ አይደለም በማለት የሚሰጡት ውሳኔ አግባብነት የሌለው ስለመሆኑ፡- የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 161 እና 164 እና የህ/መ አንቀጽ 20/4/ Download Cassation Decision

 • 127352 commercial law/ share company/ winding up/ directors of board

  የ አክሲዮን ማህበር ህልውና ከተቀጣሪዎች እና በአጠቃላይ ከሚኖሩ ተያያዥ እንቀውስቃሴዎች ጋር ጭምር በአንድም ሆነ በሌላ አግባብ ግንኙነት የሚኖረው በመሆኑ የማህበር መፍረስ አለመፍረስ አከራካሪ ሆኖ በቀረበ ጊዜ ማህበሩ እንዲፈርስ ሊወሰን የሚገባው ተከሰተ የተባለው ችግር ማህበሩን እንዲፈርስ በመወሰን ካልሆነ በሰተቀር በሌላ የህግ አግባብ መፍታት ወይም ማስወገድ እንደማይቻል ሲረጋገጥ ስለመሆኑ፣ የማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድም .ሆነ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ አንድ ማህብር ከተቋቋመ ጀምሮ ተደርጎ አያውቅም በሚል ምክንያት ብቻ አንድ ማህበር እንዲፈርስ ሊወሰን የማይገባ ስለመሆኑና በንግድ ህጉ መሠረት እንደበቂ ምክንያት ሊወሰድ የማይችል ስለመሆኑ፣ የንግድ ህግ 217 እና 218፣ 495/1/ እና /3/ Download Cassation Decision

 • 127459 contract law/ administrative contract/arbitration

  የ አስተዳደር መስሪያ ቤቶች ውልን የሚመለከቱ ጉዳዮች በግልግል ዳኝነት (አርቢትሬተር) እንዳይዳኙ የተጣለው ገደብ ወይም ክልከላ ገላጋይ ዳኛ (አድጁዲኬተር) ጋር በተያያዘም ተፈጻሚነት ያላቸው ስለመሆኑ፡- የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 315/2/፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1678/ለ፣3131 እና 3132/ለ/Download Cassation Decision

 • 127484 criminal law/ criminal procedure/ appeal/ remand

  በ ይግባኝ ፍ/ቤቶች አንድ ማስረጃ እንዲቀርብ በማድረግ ውሳኔ ለመስጠት የሚችሉ ቢሆንም የሚሰጠው ውሳኔ የግራ ቀኙን ተከራካሪዎች የይግባኝ መብት የሚያጣብብ ሆኖ ሲገኝ የቀረበው ማስረጃ ተገቢ በሆነ ምክንያት ድጋሚ እንዲጣራ እና ውሳኔ እንዲሰጥ ጉዳዩን ወደ ስር ፍ/ቤት ለመመለስ የሚችሉ ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 143 እና 195/2/ለ//2/ Download Cassation Decision

 • 127505 criminal law/ attempt/ homicide

  አ ንድ በወንጀል የተከሰሰ ሰው በመግደል ሙከራ ወንጀል ጥፋተኛ ሊደረግ የሚገባው የወንጀሉ አፈፃፀም ጠቅላላ ሁኔታ እና በተበዳዩ ላይ ከደረሰው ጉዳት አንፃር እውነትም ወንጀሉን ለመፈፀም ሀሳብ የነበረው እና የተፈለገው ውጤት ያልተገኘው ሀሳቡን ለማሳካት የማያስችል ሁኔታ በመፈጠሩ ምክንያት መሆኑን ለማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ አንቀፅ 555 (1) እና 540፣ 27(1) Download Cassation Decision

 • 128035 commercial law/ unfair competition/ period of limitation

  ተ ገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ተፈጽሟል የሚል ክስ ለፌደራል የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የዳኝነት ችሎት ማቅረብና አስተዳደራዊ እርምጃና ቅጣት እንዲጣል የማድረግ ስልጣን ያለው የባለስልጣኑ ዓቃቤ ህግ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 813/2006 አንቀጽ 37/1 Download Cassation Decision

 • 128650 contract law/ constitution/ sale of immovable property/invalidation/ restitution

  የ ማይፀናና ህገ ወጥ የሆነ የቤት ሽያጭ ውል ፈራሽ ሆኖ ግራ ቀኙ ወገኖች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ውሳኔ ሲሰጥ በህገ ወጥ በመንገድ በተገኘው ባዶ ቦታ ላይ ቤት የገነባው ወገን ቤቱን በራሱ ወጪ በማፍረስ ለባለይዞታው እንዲያስረክብ ከማድረግ ባለፈ ለግንባታው ያወጣውን ወጪ ባለይዞታ የሆነው ወገን እንዲከፍለው ሊደረግ የማይገባ ስለመሆኑ፡- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕ/መ አንቀፅ 40(3) እና የፍ/ብ/ህ ቁ 1815Download Cassation Decision

 • 128746 civil procedure/ evidence law/ expert testimony/ audit report

  የ ኦዲት ሪፖርት የሚያሻማና ግልጽነት የሌለው በሆነበትና በሪፖርቱ የቀረበውን ሀሳብ ይዘት እንዲያስረዱ ሪፖርቱን ያዘጋጁ የሂሳብ ባለሙያዎች ቀርበው እንዲያስረዱ ባልተደረገበት ሁኔታ ፍርድ ቤቶች የኦዲት ሪፖርቱን ራሳቸው በተረዱት አግባብ ተርጉመው የሚሰጡት ውሳኔ ስነ ስርዓታዊ ነው ሊባል የማይችል ስለመሆኑ የፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 133 (3) Download Cassation Decision

 • 129534 contract law/ administrative contract/ cancellation

  አ ንድ ውል በይዘቱ የአስተዳደር ውል ሲሆን የአስተዳደር አካል ወይም መንግስት ውሉን ለመሰረዝ መብት ያለው ስለመሆኑና ሌላኛው ወገን በውሉ መፍረስ የደረሰበት ጉዳት ካለ ከመጠየቅ በስተቀር ውሉ እንዲሻሻል ሆነ ለስራ ማስኬጃ የተቀበለውን ቅድመ ክፍያ ላለመመለስ የሚያቀርበው መከራከሪያ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፡- የፍ/ብ/ ህ/ቁጥር 1815፣3180 እናአ ንድ ውል በይዘቱ የአስተዳደር ውል ሲሆን የአስተዳደር አካል ወይም መንግስት ውሉን ለመሰረዝ መብት ያለው ስለመሆኑና ሌላኛው ወገን በውሉ መፍረስ የደረሰበት ጉዳት ካለ ከመጠየቅ በስተቀር ውሉ እንዲሻሻል ሆነ ለስራ ማስኬጃ የተቀበለውን ቅድመ ክፍያ ላለመመለስ የሚያቀርበው መከራከሪያ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፡- የፍ/ብ/ ህ/ቁጥር 1815፣3180 እና 3181 Download Cassation Decision

 • 130284 law of succession/ certificate of heir

  የ ውርስ ሰርተፊኬት አንድ ሰው የራሱን ወራሽነት ለማስረዳት የሚወስደው ማስረጃ እንጂ ሌሎች ወራሾች አለመኖራቸውን የሚያሳይ ሰነድ ስላለመሆኑ፣ እና በግራ ቀኙ የሟች ወራሾች መሆናቸው በማረጋገጥ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ከማስረጃነት በዘለለ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ በሚያዘው መሰረት ከሌሎች ሰዎች ክርክር ተደርጎበት ውሳኔ ያገኘና በፍርድ ያለቀ መቃወሚያ የማይቀርብበት ተደርጎ ሊወሰድ የማይገባ ስለመሆኑ፡- ፍ/ህ/ቁ. 996/1/ እና ተከታዬቹ Download Cassation Decision

 • 130410 civil procedure/ land dispute/res judicata

  የ ይዞታ ክርክርን በተመለከተ አንድ ተከራካሪ ወገን ካርታዉ እንደተሰረዘ እና በዚያ ካርታ ይዞታዉን ለመጠየቅ መብት እንደሌለዉ ዉሳኔ ተሰጥቶ እያለ ተከራካሪ ወገን በመቀየር ክስ ስላቀረበ ብቻ የክርክሩ ጭብጥና ተከራካሪ ወገን ስለሚለያይ ከዚህ ቀደም ዉሳኔ ተሰጥቷል የሚያስብል አይደለም በማለት አዲስ ክስ ማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ፡- የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5(1) Download Cassation Decision

 • 130676 contract law/ contract of carriage/ bill of lading/ evidence law

  ዕቃ ማጓጓዝ ውል በማጓጓዣ ሰነድ ወይም መሰል ሰነዶች ሊረጋገጥ የሚችል ስለመሆኑ፣ በየብስ የዕቃ ማጓጓዝ ስራን ለመደንገግ ተሻሽሎ የወጣ አዋጅ ቁጥር 547/99 አንቀጽ 4፤8 Download Cassation Decision

 • 131084 civil procedure/ execution of judgment/ auction/ aggrieved party

  በ አፈፃፀም ሂደት ንብረቴ አላግባብ ተሸጠ ወይም መብቴ ተጎዳ የሚል ሰው ፤ አቤቱታውን አፈፃፀሙን ለያዘው ፍርድ ቤት ወይም አፈፃፀሙን የያዘው ፍርድ ቤት ስህተት የፈፀመ ነው በማለት በይግባኝ እንዲታረም ማድረግ እንጂ የአፈፃፀሙ መዝገብ ከተዘጋ እና አመታት ካለፉ በኃላ መብቴ ይከበረልኝ በማለት አዲስ ክስ ማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ፤ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 404 እና 231(1) (ሀ) Download Cassation Decision

 • 131498 civil procedure/ constitution/ accelerated procedure/summary procedure

  የ ተፋጠነ ሥነ-ሥርዓት የክርክር አመራር የሰዎችን የመከላከልና የመሰማት ሕገ መንግስታዊ መብትን በሚነካ መልኩ መተርጎም እና ሥራ ላይ መዋል የማይገባው ስለመሆኑ፡- ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.284-287 Download Cassation Decision

 • 131677 law of succession/land lease

  በ ነባር ይዞታ ላይ ያረፈ ንብረት በውርስ የሚተላለፍ እንደሆነ ወደ ሊዝ ስሪት ማስገባት የማይችል እና ለጉዳዩ የሊዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 ተፈጻሚነት የሌለው ስለመሆኑ፡- Download Cassation Decision

 • 131832 civil procedure/ rural land law/Tigray jurisdiction

  በ ትግራይ ክልል የጎጆ መውጫ ይዞታና ቤት የሚመለከትን ጉዳይ የቀበሌ መሬት ዳኝነት ኮሚቴ ጉዳዩን ተቀብሎ አይቶ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ በተሰጠዉ ዉሳኔ መብቴን ይነካል በማለት የመቃወሚያ ማመልከቻ ሲቀርብ የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻውን ተከትሎ የቀደመዉን ዉሳኔ የማጽደቅ ወይም የማሻሻል ወይም የመለወጥ ወይም የመሰረዝ ስልጣን ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የቀበሌ መሬት ዳኝነት ኮሚቴ ስለመሆኑ፡- የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.358 ፣ 360(2) Download Cassation Decision

 • 131900 Tax law/ income tax/ loss carry forward

  አ ንድ ኩባንያ በደረሰበት ችግር ምክንያት ከገበያ እንዳይወጣ እና ተወዳዳሪ መሆን እንዲችል ተሰጥቶት የነበረው የኪሣራ ማሸጋገር መብት፤ በቀጥታ ወይም ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ የተለወጠ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ኩባንያው አስቀድሞ ከነበረበት ኪሣራ ወጥቶ በተጨባጭ ያደገ መሆኑ የሚገመት ከሆነ በዚያው የግብር ዘመንም ሆነ ቀደም ባሉት የግብር ዓመታት የደረሰበትን ኪሣራ በሚመለከት አስቀድሞ ተሰጥቶት የነበረው ኪሣራ የማካካስ መብት የሚቋረጥ ስለመሆኑ፡-አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 28(1)(2) Download Cassation Decision

 • 131950 civil procedure/ res judicata/ judgment

  በ ቀድሞ ክርክር ጊዜ በግልጽ ዳኝነት ተጠይቆበት በዝምታ የታለፈ ጉዳይ በሌላ ጊዜ የክስ እና የክርክር ምክንያት ሊሆን አይችልም ማለት እንጂ ፍ/ቤቶች በተከራካሪ ወገኖች በግልጽ ዳኝነት የተጠየቀበትን ጉዳይ በዝምታ ማለፍ የማይችሉ ስለመሆኑ የፍ/ስ/ስ/ሕ ቁጥር 5 (3) ፤182 (1) Download Cassation Decision

 • 132017 extra contractual liability/ car accident/ damage

  በ ግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰበት መኪና በወቅቱ ተጠግኖ ወደ ስራ ቢመለስ በአደጋው ምክንያት የተቋረጠን የገቢ መጠን ለመቀነስ ወይም ለማቅለል በቅን ልቦናና በማስተዋል የተደረገ እንቅስቃሴ ከሌለ በደረሰ ጉዳት መጠን በሙሉ ካሳ ሊጠየቅ ስላለመቻሉ፡- በፍ/ብ/ህ/ቁ.2098 /1/፤2097(2) Download Cassation Decision

 • 132280 labor law dispute/ pension/ severance pay

  አ ንድ ሠራተኛ መደበኛ የጡረታ ዕድሜው ደርሶ የመብቱ ተጠቃሚ መሆኑ በተረጋገጠበት አግባብ ለጡረታ መብት ላልተያዘለት ጊዜ የሥራ ስንብት ካሳ ሊከፈለኝ ይገባል በማለት የሚያቀርበው ጥያቄ የህግ መሰረት የሌለው ስለመሆኑ፡- የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 39፤ 43 (4)ፈ አዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 2/2/ሰ/ እና /ሸ/፤ Download Cassation Decision

 • 132518 family law/ debt of one spouse/ execution of judgment

  በ ጋብቻ በተሳሰሩ ባልና ሚስት መካከል ከአንዱ ጋር የውል ግዴታ የገባ ሰው በዋናው ክርክር ሁለቱን አጣምሮ ሊከስ የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ እንዲሁም ተዋዋይ በሆነው ተጋቢ ላይ የተሰጠ ውሳኔ የተጋቢዎች የጋራ እዳ ነው ወይስ የተወሰነበት ተጋቢ የግል እዳ ነው የሚለው ክርክር ሊነሳ የሚችለው በአፈጻጸም ወቅት እንጂ ሌላኛው ተጋቢ ሊከሰስም ሆነ ሊፈረድበት ስላለመቻሉ፡- Download Cassation Decision

 • 133203 contract law/ non-performance/ default notice/ interest

  አ ንድ ውል ሳይፈጸም በቀረ ጊዜ እንደውሉ አልተፈጸመልኝም የሚለው ተዋዋይ ወገን ሳይፈጸምልህ ቀርቷል በማለት ክርክር ለማቅረብ በቅድሚያ ውሉን ያልፈጸመው አካል ግዴታውን እንዲፈጸምለት ለማድረግ አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ሊሰጠው የሚገባ ስለመሆኑና በዚህ መሰረት ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ወለድ የሚሰላበትን ጊዜ በመወሰን ረገድ ጠቀሜታ ያለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ. 1772 Download Cassation Decision

 • 133309 government house/ right of renter

  አ ንድ የመንግስት ቤት ተከራይ የራሱ ቤት ካገኘ የመንግስት ቤትን በተከራይነት ይዞ መቀጠል የማይችል ስለመሆኑ፡- መመሪያ ቁጥር 10/2006 አንቀፅ 15(2) Download Cassation Decision

 • 133667 investment law/ jurisdiction

  በ ሁለት የህግ ሰውነት በተሰጣቸው አካላት መካከል የኢንቨስትመንት መሬት ያላግባብ ተይዞብኛል በሚል የሚነሳ ክርክርን በተመለከተ ክርክር ባስነሳው መሬት ላይ ግራ ቀኙ ያወጡት የኢንቨስትመንት ፈቃድ የፌዴራል ከሆነ ጉዳያቸው ሊታይ የሚችለው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሲሆን፣ ፈቃድ ያገኙት ግን በክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ ከሆነ በክልል ፍርድ ቤቶች የሚታይ ስለመሆኑ፤ እንዲሁም ከሁለቱ አንዱ ወገን የፌዴራል ተመዝጋቢ ከሆነ ደግሞ ጉዳዩ ሊታይ የሚገባው በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5/6 መሠረት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስለመሆኑ የፌደራል ኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 769/2004 ፣የኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 138/2000 Download Cassation Decision

 • 133708 civil procedure/ intervention/ opposition/ liquidation of succession

  አ ንድ ወራሽ በሟች የውርስ ንብረት ከሌሎች ወራሾች ጋር እንዲጣራ በግልፅ ተስማምቶና ውክልና ሰጥቶ በሚጣራው የውርስ ፋይል ተሳታፊ ሆኖ እያለ ከሚጣራው ንብረት ላይ የግል ንብረት ያለ በመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.41 መሰረት ጣልቃ ገብቼ እንድከራከር እንዲፈቀድልኝ በማለት የሚያቀርበውን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ በውርስ አጣሪ ተጣርቶ የቀረበውን ሪፖርት ተቀብሎና መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ ከመስጠት ባለፈ የጣልቃ ገብ ክርክሩን ሊቀበለው የማይገባ ስለመሆኑ፡- የፍ/ሕ/ቁ. 947 Download Cassation Decision

 • 133736 law of succession/government house/ contract of rent/

  በ ውርስ የተላለፈን የመንግስት ንግድ ቤት የማከራየት መብትን ከወራሾች መካከል አንዱ ያለ ከተማ አስተዳደሩ እውቅና ያከራየ እንደሆነ ፤ የተከራይነት መብት የሚቌረጠው ያከራየው ወራሽን በተመለከተ ብቻ እንጂ ሌሎች እሱ በሞግዚትነት የሚያስተዳድራቸው ወራሾች የመከራየት መብታቸው የሚቀጥል ስለመሆኑና ፤አከራዩ ሞግዚታቸው ባከራያቸው ወገኖች ላይ በንግድ ቤት የኪራይ ውል መነሻነት ክስ ለማቅረብ የሚያበቃ መብትና ጥቅም ያላቸው ስለመሆኑ፡- Download Cassation Decision

 • 134240 extra contractual liability/ fatal accident/ damage

  በ ተጎጂ ላይ ከደረሰ የሞት አደጋ የተነሳ በራሳቸው ስም ሆነው በመተዳደሪያ ረገድ ለሚደርስባቸው ጉዳት ካሳ ለመጠየቅ የሚችሉት፤ የተጎጂ ባል ወይም ሚስት፤ ወይም ወላጆቹና ልጆቹ ብቻ እንጂ ወንድም ወይም እህት መጠየቅ ስላለመቻላቸው፡- የፍ/ብ/ህ/ቁ.2095/1/ Download Cassation Decision

 • 134549 criminal law/ concurrence

  በ አንድ የወንጀል የማድረግ ሃሳብ ወይም ቸልተኝነት የተፈጸመዉ የወንጀል ድርጊት በሕግ በተጠበቀ አንድ መብት ላይ በሚሆንበት ጊዜ እና ድርጊቶቹ በሙሉ በአንድ ድንጋጌ ስር መሸፈን ከተቻለ፤ ፈጻሚዉ የሚቀጣዉ ድርጊቶቹ በሚሸፈኑበት በአንድ ድንጋጌ ስር እንጂ በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ተደራራቢ ወንጀሎች ስላለመሆኑ፡- በወንጀል ሕግ አንቀጽ 61(1) Download Cassation Decision

 • 134681 land law/ jurisdiction

  የ ድሬድዋ ከተማ ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 416/96 መሰረት የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን ለማስፈፀም ሲባል ከይዞታ ባለቤትነት፣ ከፈቃድ አሰጣጥ እና ከቦታ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የሚነሱ ክርክሮችን ከማየት ባለፈ በእርሻ መሬት ባለይዞታነት ይገባኛል ጥያቄን መሰረት ያደረገ ክርክርን ለማስተናገድ የስረ ነገር ስልጣን የሌለው ስለመሆኑ፡- የአ/ቁ 416/1996 አንቀፅ 31(1) Download Cassation Decision

 • 134836 law of succession/ will/ joint will

  ኑ ዛዜ ጥብቅ የሆነ፣ የግል ጠባይ ያለው እና በሟች ብቻ የሚፈፀም በመሆኑ ብዙ ሰዎችን አንድ በሆነ ፅሁፍ በጋራ ማናዘዝ የማይቻል እና ኑዛዜውን ፈራሽ የሚያደርግ ስለመሆኑ፡- የፍ/ብ/ህ/ቁ 857፣858 እናኑ ዛዜ ጥብቅ የሆነ፣ የግል ጠባይ ያለው እና በሟች ብቻ የሚፈፀም በመሆኑ ብዙ ሰዎችን አንድ በሆነ ፅሁፍ በጋራ ማናዘዝ የማይቻል እና ኑዛዜውን ፈራሽ የሚያደርግ ስለመሆኑ፡- የፍ/ብ/ህ/ቁ 857፣858 እና 880 Download Cassation Decision

 • 135197 property law/ registration of immovable property/ mortgage

  የ ማይንቀሳቀስ ንብረት መያዥያ በማናቸዉም አይነት ሰነድ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ከተጻፈበት ቀን አንስቶ የማይንቀሳቀሰዉ ንብረት በሚገኝበት ሀገር ባለዉ በማይንቀሳቀስ ርስት መዝገብ ካልተፃፈ በቀር ማንኛውንም አይነት ውጤት የማያስገኝ ስለመሆኑና ዕዳው እንዲከፈል በተወሰነበት ጊዜ ሳይከፈል የቀረ እንደሆነ ገንዘብ ጠያቂው የመያዣ መብት ያገኘበትን የማይንቀሳቀስ ንብረት ይወስዳል የሚል ስምምነት ሁሉ ተቀባይነት የማይኖረዉ ስለመሆኑ፡- ፍ/ሕ/ቁ 3052 እና 3060 Download Cassation Decision

 • 135254 civil procedure/ intervention/ opposition

  በ አንድ ክርክር ከሳሽ የሆነው ወገን ጣልቃ በገባ ተከራካሪ ወገን ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክርክር ከማንሳት የሚከለከልበት የሕግ መሰረት የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብሥ/ሥ/ሕ/ቁ.39፤40፤በ አንድ ክርክር ከሳሽ የሆነው ወገን ጣልቃ በገባ ተከራካሪ ወገን ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክርክር ከማንሳት የሚከለከልበት የሕግ መሰረት የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብሥ/ሥ/ሕ/ቁ.39፤40፤41 Download Cassation Decision

 • 135590 civil procedure/ injunction/ lifting injunction

  የዕግድ ትእዛዝ በባህሪው ጊዜያዊ በመሆኑ ለዕግዱ ምክንያት የሆነው ክርክር ዕልባት ሲያገኝ የሚነሳ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 154 Download Cassation Decision

 • 135787 criminal law/ sentencing/ sentencing guideline/constitution

  በ ትምህርት ደረጃው ከፍተኛ የሆነና በባህሪው ለህብረተሰብ አርአያ ሊሆን የሚገቡ ሰዎች ፍፁም ነውረኛ በሆነና ጨካኝነት በተሞላበት ሁኔታ የፈፀሙት ከባድ የወንጀል ድርጊት የወንጀል አፈጻጸሙን ከባድነት እና የወንጀለኛውን አደገኛነት የሚያሳይ በሆነ ጊዜ ወንጀለኛው ላይ የቀረበ የቀደመ የወንጀል ሪከርድ ያለመኖር ወንጀለኛው ጥሩ ፀባይ ወይም መልካም ፀባይ ያለው ነው የሚል ግምት ለመውሰድ የማያበቃ ስለመሆኑ፣ -የወ/ህ/ቁ. 184/1/ሀ/ እና ለ ቁ. 539 ቁ. 671/1/0/ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ. 2/2006 የኢ.ፌ.ዲ.ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት በአንቀጽ 15 እና የወ/ህ/ቁ. 117 Download Cassation Decision

 • 135902 family law/divorce/ indemnities

  የጉዳት ካሳ ጥያቄ ከጋብቻ ፍቺ ጋር ተያይዞ የቀረበ በሆነበት እና ጉዳቱም የደረሰው ከፍቺው ጋር ተያያዞ መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ ጥያቄው የባልና ሚስት ፍቺን ተከትሎ ከሚነሳ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ጋር በአንድ ላይ ሊስተናገድ አይችልም በሚል የሚሰጥ ውሳኔ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ፡- የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 84Download Cassation Decision

 • 136024 contract law/ rent of business

  የ አገልግሎት ድርጅት ያከራየ ወገን ያከራየው ድርጅት ተገቢውን አገልግሎት እንዳይሰጥና ታሽጎ እንዲቆይ ለፍርድ ቤት ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ እግድ የተሰጠ በሆነበት እና ተከራዩም ከድርጅቱ ገቢ ባላገኘበት ሁኔታ ድርጅቱ ታሽጎ ለቆየበት ጊዜ ተከራይ የኪራይ ክፍያ እንዲከፍል የማይገደድ ስለመሆኑ፡ Download Cassation Decision

 • 136030 commercial law/ contract of carriage/accident/ damage

  አ ንድ ሰው የትራንስፖርት ክፍያ ከፍሎ በመኪና ሲጓዝ በነበረበት ወቅት የአካል ጉዳት ቢደርስበት የንግድ ህጉን መሠረት ያደረገና በውል ላይ የተመሰረተ ግንኙነት በተጎጂው እና በአጓዡ መካከል ተመስርቷል ማለት ስለሚቻልበት ሁኔታና አጓዡ ለመንገደኛው ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ ኃላፊነቱ ሊታይ የሚገባው በንግድ ህጉ ስለ አጓዥ እና ተጓዥ በተደነገገው ድንጋጌ መሠረት መሰረት ስለመሆኑ፡- የንግድ ሕግ ቁጥር 561፣ 595 ፣596 ፣ 597 እና 599 Download Cassation Decision

 • 136092 civil procedure/ execution of judgment/ auction/ fraud

  በ ሀራጅ አካሄድና ሽያጭ ስርዓት ተገቢ ያልሆነ ድርጊት፣ ማጭበርበር ወይም ማታለል መኖሩ በማስረጃ ከተረጋገጠ ጨረታውን ለማፍረስ በቂ ምክንያት ስለመሆኑ፣ የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁበ ሀራጅ አካሄድና ሽያጭ ስርዓት ተገቢ ያልሆነ ድርጊት፣ ማጭበርበር ወይም ማታለል መኖሩ በማስረጃ ከተረጋገጠ ጨረታውን ለማፍረስ በቂ ምክንያት ስለመሆኑ፣ የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 445 Download Cassation Decision

 • 136245 contract law/ evidence law/ documentary evidence

  ገ ንዘብ የተከፈለ መሆኑን የሚገልጽ ሰነድ ወይም ደብዳቤ ሰነዱን ባዘጋጀዉ ወይም ደብዳቤዉን በፃፈዉ ሰዉ ላይ ማስረጃ የሚሆን ስለመሆኑ፡- ፍ/ሕ /ቁ 2018(1) Download Cassation Decision

 • 136262 criminal procedure/ juvenile delinquency/

  ወ ጣት ጥፋተኞችን የተመለከቱ የጥንቃቄ እርምጃዎች አፈጻጸም በተቻለ መጠን አጥፊውን በማረም መልካም ውጤት ሊያስገኝ በሚያስችል አግባብ መሆን የሚገባው ስለመሆኑ፣ ለወጣት ጥፋተኞች የሚያገለግል የጠባይ ማረሚያ ተቋም በሌለበት ፣ በወላጅ ቁጥጥር ስር ሆኖ የሚደረግ የባህሪ ሁኔታ ክትትል የተሻለ ውጤት እንደማይመጣ እና የጥፋተኛው አደገኛነት በተገቢው አግባብ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ቅጣቱ በአዋቂዎች እስር ቤት እንዲፈፀም የሚሰጥ ውሳኔ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ፡- የወንጀል ህግ አንቀጽ 168/2 Download Cassation Decision

 • 136571 labor law dispute/ termination of contract by worker

  ሠ ራተኛ በህይወቱ ላይ አደጋ ሊደርስበት በሚችል አኳኋን እንዲሰራ ማድረግ ህገወጥ ድርጊት ስለመሆኑና ሠራተኛው ያለማስጠንቀቂያ ውል እንዲያቋርጥ በቂ ምክንያት ስለመሆኑ፣ የአ/ቁ. 14/ሠ/ እና አንቀጽ 32/1/ለ Download Cassation Decision

 • 136872 family law/ common property/ business

  አ ንድ የንግድ ቤት በኪራይ የተሰጠው በትዳር ግንኙነት ወይም በጋብቻ ውስጥ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ የንግድ ፈቃድ የተሰጠው ከትዳር ግንኙነት በፊት መሆኑ ብቻ የንግድ ሱቅ ከጋብቻ በፊት የተገኘ የግል ንብረት ነው ለማለት የማያስችል ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 136901 civil procedure/ compromise agreement

  አ ንድ ጉዳይ በማንኛውም የክርክር ደረጃ ላይ በሚገኝበት ወቅት ተከራካሪ ወገኞች በእርቅ ወይም በግልግል ስምምነት የመጨረስ መብት ያላቸው ቢሆንም፤ ክሱን በእርቅ ለመጨረስ ቀጠሮ ያስለወጠ ወገን ቀጠሮ በተሰጠበት ቀን ፍ/ቤትን ቀርቦ የተደረሰበትን ደረጃ ያለማሳወቅ እና ለረጅም ጊዜ ጉዳዩን ያለመከታተል ኪሳራ እንዲከፈል ሊወሰንበት ከመቻሉ በላይ አዲስ ክስ መመስረት የማይቻል ስለመሆኑ፡- የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 69 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ቁ. 275 እና 79/1/ Download Cassation Decision

 • 137262 criminal law/ rape/ sentencing guideline/sentencing

  በ ወንጀል ህግ አንቀጽ 620/3/ ስር የጥፋተኝነት ውሳኔ ለመስጠት በግል ተበዳይ ላይ ከባድ የአካል ወይም የአይምሮ ጉዳት ወይም ሞት የደረሰ መሆኑ ሊረጋገጥ የሚገባ ስለመሆኑ እና አንድ የወንጀል ክስ የወ/ህ/አንቀጽ ቁጥር 620/2/መ/ መሰረት በማድረግ በቀረበበት ሁኔታ ፍ/ቤቶች የጥፋተኝነት ውሳኔ ሲሰጡ የክስ መሰረት የሆነውን አንቀጽ ወደ አንቀጽ ቁጥር 620/3 በመቀየር ውሳኔ ለመስጠት የማይችሉ ስለመሆኑ፣ የወንጀል አፈጻጸሙ አፀያፊነት ከወንጀል ፈጻሚው ድርጊት ከተረጋገጠና በቅጣት አወሳሰን መመሪያው በወጣው ደረጃ መሰረት ቅጣቱ ቢወሰን የወንጀል ህጉን የቅጣት አላማና ግብ የሚያሳካ የማይሆንበት ሁኔታ ሲኖር ቅጣቱን ከቅጣት አወሳሰን መመሪያ ውጪ መወሰን የሚቻል ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/ቁ. 620/2/ መ፣ 620/3/ እና የወ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 113/2/ የወ/ህ/ቅ/አ/መ/ቁ.2/2006 27/1/ እና 4/9/ የወ/ህ/ቁ. 539/1/2//ሀ/፣ የወ/ህ ቁ. 82 Download Cassation Decision

 • 137353 government house/ nationalization/ jurisdiction/constitution

  በ ከተማ አስተዳደር ወይም በቀበሌ ያላግባብ የተያዘን የምርጫ ቤት ለማስመለስ የሚቀርብን ክስ የማየት ስልጣን በህግ ለሌላ የመንግስት አካል ባልተሰጠበት ሁኔታ መደበኛ ፍርድ ቤቶች የማየት ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ፡- ኢ.ፊ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 37 Download Cassation Decision

 • 137401 civil procedure/ intervention/ splitting of claims

  አ ንድ ሰው ቀድሞ በቀረበ ክርክር ጣልቃ ገብ በመሆን ክርክር ያቀረበ ወይም በጉዳዩ ተሳታፊ የነበረ መሆኑ በጣልቃ ገብነት በቀረበበት ክርክር ግልጽ ዳኝነት ባልተጠየቀባቸው ጉዳዮች በሌላ ጊዜ ክስ ለማቅረብ የሚችል ስለመሆኑና በዚህ አግባብ የሚቀርብን ክስ በቀድሞው ክርክር ተጠቃሎ መቅረብ የነበረበትና ተከፋፍሎ ዳኝነት ሊቀርብበት አይገባም በሚል አቤቱታን ዉድቅ በማድረግ የሚሰጥ ውሳኔ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 41፣216 እና 218 Download Cassation Decision

 • 137545 criminal law/ criminal procedure/evidence law/testimony

  በ ወንጀል የተከሰሰ ሰው የግል ተበዳይን በመከላከያ ምስክርነት ያቀረበና የግል ተበዳይም ድርጊቱ ያለመፈፀሙን በመግለጽ የምስክርነት ቃል የሰጠ ከሆነ ዓ/ህግ የግል ተበዳይ የምስክርነት ቃል በድለላ ወይም በጥቅም የተገኘ መሆኑን ለማረጋገጥ እስካልቻለ ድረስ ተከሳሽ ክሱን አላስተባበለም ሊባል የማይገባ ስለመሆኑ፡- የወ/መ/ሥ/ሥ/ህግ/ ቁጥር 149 (2) Download Cassation Decision

 • 137589 extra contractual liability/ vicarious liability/ public servants

  የ መንግስት ተቋማት ሠራተኞቻቸውን የመቆጣጠር እና የመከታተል ግዴታቸውን ሳይፈጽሙ ቀርተው በተገልጋዮች ላይ ጉዳት በደረሰ ጊዜ ጉዳዩ አይመለከተንም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፡- የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2126 (2) እና 2127 (1) Download Cassation Decision

 • 137672 criminal law/ source unexplained property

  ም ንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ በማከማቸት የሙስና ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ ክስ የቀረበበት ተከሳሽ የማስረዳት ግዴታ ዐቃቤ ሕግ በክሱ ከገለፀውና በማስረጃ ካረጋገጠው ውጭ ተከሳሽ ሌላ ገቢ የሚያገኝበት ስራ ወይም የገቢ ምንጭ ያለው መሆኑን ብቻ ለፍርድ ቤቱ በማሳየት የሚወሰን ሳይሆን፣በዓቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ ከተረጋገጠው ገቢ ውጭ በእጁ እንደተገኘ የተረጋገጠው ገንዘብና ሀብት ትክክለኛ ምንጭ ምን አንደሆነ የማስረዳት ግዴታና ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ፡- የወንጀል ሕግ አንቀጽ 419 /1//ሀ/ እና /ለ/ Download Cassation Decision

 • 137831 civil procedure/ appeal procedure/ new claims

  •ይ ግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በተለይ ካልፈቀደ በቀር ይግባኝ ባይ በይግባኝ ማመልከቻ ላይ ዘርዝሮ ያልገለጸውን አዲስ ነገር በማንሳት ወይም መሠረት በማድረግ ለመከራከር የማይችል ስለመሆኑ፡- •ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በይግባኝ ማመልከቻ ተዘርዝሮ ከተገለጸ ወይም ክርክር ከተነሳበት ውጭ በሆነ ነገር ፍርድ መስጠት የማይችል ስለመሆኑ፡- የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 328 /2/፤328 /3/ Download Cassation Decision

 • 137853 law of succession/ adoption/ Oromia

  በ ፍርድ ቤት ቀርቦ የፀደቀ ወይም ተቀባይነት ያገኘ የጉዲፈቻ ውልን መሰረት በማድረግ ወራሽነትን ያረጋገጠ ወገን የውርስ ንብረት ድርሻን ለማግኘት ያቀረበው ጥያቄ ቀድሞ በጉዲፈቻ ውል የፀደቀበት ውሳኔ መብቴ ተነካ በሚል ወገን በቀረበ መቃወሚያ መሰረት እንዲፈርስ እንዲሻር ባልተደረገበት የውርስ ድርሻ ክፍያ ጥያቄው ውድቅ ማድረግ ህግን መሰረት ያላደረገ በ ፍርድ ቤት ቀርቦ የፀደቀ ወይም ተቀባይነት ያገኘ የጉዲፈቻ ውልን መሰረት በማድረግ ወራሽነትን ያረጋገጠ ወገን የውርስ ንብረት ድርሻን ለማግኘት ያቀረበው ጥያቄ ቀድሞ በጉዲፈቻ ውል የፀደቀበት ውሳኔ መብቴ ተነካ በሚል ወገን በቀረበ መቃወሚያ መሰረት እንዲፈርስ እንዲሻር ባልተደረገበት የውርስ ድርሻ ክፍያ ጥያቄው ውድቅ ማድረግ ህግን መሰረት ያላደረገ ስለመሆኑ የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ ቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/1995 በአዋጅ ቁጥር 83/96 እንደተሻሻለ አንቀጽ 202. የፍ/ብ/ስ/ስ/ቁ. 41፣358 Download Cassation Decision

 • 137869 family law/ dissolution of marriage/ liquidation of property/ Oromia

  በ ኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ ጋብቻ በፍቺም ሆነ በሞት ምክንያት ሲፈርስ ንብረት የሚጣራበት አግባብ በውል ወይም በስምምነት ተለይቶ ባልተቀመጠበት ሁኔታ የባልና ሚስት ሀብት የሚጣራው በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 113 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት ስለመሆኑ፡- ኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/95 በአዋጅ ቁጥር 83/96 እንደተሻሻለው አንቀጽ 93 Download Cassation Decision

 • 137918 extra contractual liability/ defamation/ equity

  የ ባንኮችን መልካም ስም፣ የአገልግሎት ብቃት፤ ታማኝነት እና የሥራ እንቅስቃሴን ሌሎች ሰዎች እንዲጠራጠሩ የሚያደርግ ተግባር መፈጸም የፍትሐብሄር ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ. 2109 የፍ/ብ/ህ/ቁየ ባንኮችን መልካም ስም፣ የአገልግሎት ብቃት፤ ታማኝነት እና የሥራ እንቅስቃሴን ሌሎች ሰዎች እንዲጠራጠሩ የሚያደርግ ተግባር መፈጸም የፍትሐብሄር ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ. 2109 የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2102 Download Cassation Decision

 • 137939 intellectual property/ invention

  የ ኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት በህጉ አግባብ በሁለት ኢንዱስትሪዊ ንድፎች መካከል ተመሣሣይነት አለ ወይስ የለም የሚለውን ለመለየት የአከራካሪውን ንድፍ አዲስነት ለመወሰን የኢንዱስትሪያዊ ንድፉ ዋና ዋና ባህሪያት በመለየት በኢትዮጵያ ወይም በውጪ ከታወቁ ተመሳሳይ ንድፎች የተለየ ወይም ተመሳሳይነት ያለው ስለመሆኑ በዘርፉ ያለውን የዳበረ እውቀት እና ልምድ መሰረት በማድረግ ማጣራት አድርጎ ውሳኔ መስጠት ያለበት ስለመሆኑ የአነስተኛ ፈጠራና ኢንዱስትሪ ንድፍ አዋጅ ቁጥር 123/1987 አንቀጽ 46(1)፤ 48(1) ፤ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤትን ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ ቁጥር 320/1995 Download Cassation Decision

 • 138062 civil procedure/ possessory action/ res judicata

  ሁ ከት ተወግዶ ይዞታ እንዲለቀቅ ክስ ቀርቦ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ በድጋሚ ይዞታ ይለቀቅልኝ በሚል ክስ መመስረት ዳኝነት በተሰጠበት ጉዳይ ላይ በድጋሚ የቀረበ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 5፣ 244(ለ) Download Cassation Decision

 • 138286 family law/ constitution/ women right/ common property/ Oromia

  ባ ል እና ሚስት በጋራ ሲጠቀሙበት የነበረ መሬት ጋብቻው በአንደኛው ተጋቢ ሞት የተቋረጠ ቢሆንም ሌላኛው ተጋቢ በሌላ ህጋዊ ምክንያት መብቱ እስካልተቋረጠ ድረስ ይዞታው በስሙ ተመዝግቦ ደብተር ለማግኘት እና በይዞታው ለመጠቀም የሚችል ስለመሆኑ፣ ሴቶች መሬትን በመጠቀም፤በማስተላለፍ፤በማስተዳደርና በመቆጣጠር ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት ያላቸዉ ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕ/መ አንቀጽ 35/7/፣ የኦሮሚያ የገጠር መሬት አዋጅ ቁ. 130/99 አንቀጽ 6/3/ እና ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 15 Download Cassation Decision

 • 138340 civil procedure/ sharia court/constitution/ cassation/ jurisdiction

  ሰ በር ችሎቶች ሥነ ሥርዓታዊ የሆነ የህግ ጥያቄን ብቻ ለማየት ስልጣን እንዳላቸው ግንዛቤ በመውሰድ በአንድ ጉዳይ ላይ የተሰጠ ውሳኔ ስነ-ስርዓታዊ ሕጎችን መሰረት አድርጎ የተሰጠ መሆን ያለመሆኑን መመርመር አንጂ ከዚህ ውጪ መደበኛ ሕጎችን መሰረት አድርገው በሸሪዓ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ሊመረምሩ የሚችሉበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፡- በኢ.ፌ.ዲ.ሪፐብሊክ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ))፣ 80(3(ለ)) እና አዋጅ ቁጥር 53/94 እና አዋጅ ቁጥር 188/1992 አንቀጽ 6 Download Cassation Decision

 • 138386 contract law/ invalidation of contract/

  ዉ ል እንዲፈርስ ጥያቄ የሚያቀርብ ወገን ዉሉ ሊፈርስ የሚችልበት በህግ ተቀባይነት ያለዉ ምክንያት ስለመኖሩ የማስረዳት ግዴታ ያለበት ሲሆን የዉል ይፍረስልኝ ጥያቄ የሚቀርብለት ፍርድ ቤትም ለዉሉ መፍረስ በምክንያትነት የተጠቀሰዉ ሁኔታ ዉሉ እንዲፈርስ ለማድረግ በህግ ተቀባይነት ያለዉ እና በቂ ምክንያት መሆን አለመሆኑን ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸዉ የህጉ ድንጋጌዎች ድንጋጌዎች ጋር አገናዝቦ የማጣራት ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ፡- የፍ/ብ ህግ አንቀጽ 347(1)፣ 347(2) እና ፍ/ህ አንቀጽ 1710(2)Download Cassation Decision

 • 138479 civil procedure/ adjournment

  ለ ቀጠሮ ምክንያት የሆነ ጉዳይ ሳይፈፀም የቀረው ከተከራካሪዎቹ ወገኖች በአንደኛው ጉድለት የሆነ እንደሆነ መፈፀም ይገባው የነበረው ጉዳይ ያልተፈፀመ ቢሆንም እንኳ ፍርድ ቤቱ የጉዳዩን መፈፀም ሳይጠብቅ የመሰለውን ውሳኔ መስጠት ስለመቻሉ፡- የፍ/ብ/ስ/ሥ/ህ/ቁ 199(1) Download Cassation Decision

 • 138591 contract law/ unconcsionable contract/ invalidation/ period of limitation

  በ መርህ ደረጃ አንድ ዉል ለአንደኛው ወገን የበለጠ ጥቅም ይሰጣል በሚል እንደማይፈርስ ነገር ግን ፈቃድ የተገኘዉ በዕድሜ መግፋት ወይም የንግድ ልምድ ዕዉቀቱ ማነስ ካለና በሕሊና ግፍ መስሎ ከታየ ዉሉ የሚሰርዝበት ሁኔታ ስለመኖሩ፡- አንድ ተዋዋይ የዉል ይሰረዝልኝ ክስ ዉሉ የማይረጋበት ምክንያት ከቀረበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ዓመት ዉስጥ ማቅረብ ያለበት ስለመሆኑ ፡- የፍ/ሕ/ቁ. 1710(1)እና(2) ፤ የፍ/ሕ/ቁ.1810(1) Download Cassation Decision

 • 138717 civil procedure/ first hearing/ admission

  አ ንድ ተከራካሪ ወገን በመከላከያ መልስ ወይም በማናቸዉም ሌላ መንገድ የተከሰሰበትን ነገር በሙሉ ወይም በከፊል ያመነ እንደሆነ ሌላኛዉ ተከራካሪ ወገን በዚህ እምነት መሰረት ዉሳኔ እንዲሰጠዉ መጠየቅ እንደሚችል እና ፍ/ቤትም ሌላ በማስረጃ የሚረጋገጥ ነገር ቢኖርም እንኳን በታመነዉና ዉሳኔ እንዲሰጥበት በተጠየቀዉ ጉዳይ ብቻ ፍርድ መስጠት የሚገባው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.242 Download Cassation Decision

 • 138837 Tax law/ custom duties/ tax free privilege

  ከ ቀረጥ ነጻ መብትን በመጠቀም ወደ ሀገር የገባን እቃ ለመሸጥ ወይም ወደ ሌላ ለማስተላለፍ ከተፈለገ ቀድሞ ቀረጡን በመክፈል ነጻ ማድረግ የሚገባ ስለመሆኑ፡- አዋጅ/ቁ 859/2006 አንቀጽ 30(1) Download Cassation Decision

 • 139107 criminal law/ criminal procedure/ evidence law/ court warrant

  ወ ንጀል መፈጸሙን ለማጣራትና ምርመራ ለማጠናቀቅ ወሳኝ የሆኑ መረጃዎች በህግ ጥበቃ የሚደረግላቸው እና ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ለማግኘት የማይቻል በሆነ ጊዜ ፍ/ቤቶች የሚቀርብላቸውን ጥያቄ በአግባቡ በማጤን ተገቢውን ትእዛዝ መስጠት ያለባቸው ስለመሆኑ የአ.ቁ 592/2000 አንቀጽ 28/4/ /ሠ/ አ.ቁ 720/2004 አንቀጽ 6 Download Cassation Decision

 • 139138 civil procedure/ plurality of parties/appeal

  በ አንድ ክርክር ውስጥ የከሳሾች ወይም የተከሳሾች ብዛት ከአንድ በላይ ሲሆንና ክርክሩም ከሳሾችን ወይም ተከሳሾችን በአንድ ዓይነት መልክ የሚመለከታቸው ሲሆን ከሳሾቹ ወይም ከተከሳሾቹ አንዱ በጠቅላላው ውሳኔ ላይ ይግባኝ ሲጠይቅና ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤት ፍርዱን በመለወጥ ያሻሻለው ወይም የለወጠው ወይም ያጸናው ፍርድ ይግባኙን ባላቀረቡት ከሳሾች ወይም ተከሳሾች ላይም በይግባኝ ደረጃም በቀረበው ጉዳዩ ከከሳሾቹ መካከል አንዱ ይግባኝ ጠይቆ የሚሰጠው ውሳኔ ሌሎችንም የሚያካትት ስለመሆኑ፡- የፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 35 እና 331 Download Cassation Decision

 • 139334 Tax law/ income taxes/ expenses

  አ ንድ ግብር ከፋይ ለንግድ ስራው ዋስትና ለመስጠትና እንቅስቃሴውን ለማስቀጠል የተደረጉ ወጪዎች ተቀናሽ እንዲደረግለት ለንግድ ስራው ያወጣውን ወጪ ማስረዳት የሚችለው በሚያቀርበው በስሙ ወጪ በሆነ ህጋዊና ተቀባይነት ያለው ደረሰኝ ስለመሆኑ፤- የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 20 የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀፅ 22(2) ፤ደረሰኝ አያያዝና አጠቃቀም መመሪያ ቁጥር 28/2001 አንቀፅ 4(1) Download Cassation Decision

 • 139385 commercial law/ share company/registration of share transfer

  በ አክሲዮን ዝውውር ማመልከቻ ሰነድ ላይ የአክስዮን ማህበሩ ማህተም ማረፉ አልያም ዝውውሩ ፀድቋል ወይም ተመዝግቧል የሚል ምልክት መደረጉ ብቻውን በንግድ ህግ ስር በአዛዥ ሁኔታ የተቀመጠውን በባለአክሲዮኖች መዝገብ የመመዝገብ ግዴታን የማይተካ ወይም ቀሪ የማያደርግ ስለመሆኑ የንግድ ህግ 331 (1) እና 341 (2) Download Cassation Decision

 • 139942 civil procedure/ local jurisdiction/ land dispute

  ለ አንድ ክርክር መነሻ የሆነ ቤትና ይዞታ በክልል የሚገኝ ሲሆንና የስረ ነገር ስልጣኑ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቢሆንም ጉዳዩ መታየት ያለበት ንብረቱ በሚገኝበት ክልል የዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስለመሆኑ፡- Download Cassation Decision

 • 140461 labor law dispute/ civil service/ sick leave/ termination of contract of employment

  ሠ ራተኞች በሙሉ እውቀታቸውና ብቃታቸው ሰርተው እኩል የምርት ጥራትና መጠን ያመርታሉ ተብሎ የማይገመት ስለመሆኑና የአንደኛው ሠራተኛ ያመረተው ምርት መጠንና ጥራት ብቻ ለሌላው ሠራተኛ ከአቅም በታች ሰርቷል ለማለት በቂ መሰፈርት ሆኖ ሊወሰድ የማይገባ ስለመሆኑ፡- Download Cassation Decision

 • 140538 rural land/ period of limitation/ Oromia

  በ ኦሮሚያ የገጠር መሬት አጠቃቀም ለረጅም ጊዜ በሌላ ሰው የተያዘና ጥቅም ላይ ሲውል የነበረን የገጠር መሬት የተያዘው ሕገወጥ ውልን መሰረት በማድረግ መሆኑ እስካልተረጋገጠ ድረስ መሬቱ እንዲለቀቅ የሚቀርብ ክስ በአስራ ሁለት ዓመት ይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ፣ የኦሮሚያ የገጠር መሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 32 Download Cassation Decision

 • 140677 labor law dispute/ manager/ scope of labor proclamation

  ለ አንድ ሠራተኛ ማስጠንቀቂያ መፃፍ ብቻውን “የስራ መሪ” የማያስብልና ጉዳዩ በስራ ክርክር ችሎት ሊታይ አይችልም የሚባልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፡- አሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁ. 377/96 3/2/ /ሐ/ ስ እና ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 2/1/ /ሐ/ Download Cassation Decision

 • 141527 family law/ common property/ partition of property

  የ ባልና ሚስት ንብረት ክፍፍልን በተመለከተ ለአፈፃፀም የቀረበ አከራካሪ የሆነ ቤት ሊካፈልም ሆነ ሊሸጥ የማይችል ሲሆን ሊካፈል የሚችለው በፕሮፖርሽን / በተነጻጻሪ ካርታ / ነው በማለት ባለሙያ አስተያየት በተሰጠበት ሁኔታ በዚሁ አግባብ ክፍፍሉ ሲደረግ የበለጠ ይዞታ የደረሰው ወገን ለሌላው ወገን ግምቱን እንዲከፍል በማድረግ መፈፀም የሚገባው እንጂ በፍርዱ በተቀመጠው ሌላ አማራጭ መሠረት ክፍፍሉ እንዲፈጸም ማድረግ የማይገባ ስለመሆኑ፡- የተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 91(1)እና(2) Download Cassation Decision

 • 141606 contract law/ constitution/ sale of land/ unlawful object/ indemnity

  አ ንድ የመሬት ሽያጭ ውል ህገ ወጥ ውል መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ ገዥ ወገን በመሬቱ ላይ የሰራው ቤት በሻጭ ፈቃድ እንደተሰራ ተደርጎ የህግ ግምት የሚወሰድበት አግባብ የማይኖር ስለመሆኑ የኢፌድሪ ህ/መ አንቀፅ 40 (3) እና የፍ/ብ/ህ ቁጥር 1678 (ለ) እና 1716 Download Cassation Decision

 • 141663 criminal law/ members of armed forces/ jurisdiction

  የ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር እና የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን የተለያየ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ስለመሆኑና የሠራዊት አባላት በፋውንዴሽኑ ንብረት ላይ የሚፈጽሟቸው ማንኛውም ወንጀሎች በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ላይ እንደተፈጸሙ ተደርጎ የማይቆጠሩ ስለመሆናቸው፡- የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ንብረት ላይ የሚፈጽማቸው ወንጀሎችን የማየት ስልጣን የመደበኛ ፍ/ቤቶች ሆኖ የፌ/ከ/ፍ/ቤትም ጉዳዩን የማስተናገድ የመጀመሪያ ደረጃ የፍርድ ስልጣን የሚኖረው ስለመሆኑ፡- የአዋጅ ቁጥር. 434/1997 አንቀጽ 7/1/ እና የአዋጅ ቁጥር 809/2006 አንቀጽ 28 እና 38 ደንብ ቁ. 179/2002 Download Cassation Decision

 • 141677 criminal law/ criminal procedure/ amendment of charges

  ተ ሻሽሎ የቀረበ አንድ የወንጀል ክስ የተከሳሹ መሰረታዊ መብት ላይ የሚኖረዉ አሉታዊ ተጽእኖ ጋር ተመዛዝኖ በስነስርዓት ህጉ የተጠበቀለት የመሰማት መብቱን በጥብቅ ተግባራዊ በማድረግ ክሱ እንደገና ተሰምቶ መወሰን ያለበት ስለመሆኑ በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ 118፤119/2/ ፤120 እና 121 Download Cassation Decision

 • 141978 criminal law/ criminal procedure/ crimes punishable upon formal complaint/

  “… ማናቸውም የግል አቤቱታ በቀረበ ጊዜ ይቀጣል..” የሚል አገላለጽ በውስጣቸው የሚገኙ ድንጋጌዎችን በመተላለፍ ወንጀል በተፈጸመ ጊዜ በግል አቤቱታ እንዲያቀርብ ከተፈቀደለት ሰው በቀር በሌላ በማንም ሰው የክስ ጉዳይ ሊንቀሳቀስ የማይችል ስለመሆኑና የግል ከሳሽ የሆነው ሰውም የማመልከቻውን አዘገጃጀት በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 150-153 መሰረት መምራት የሚኖርበት ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 556/2/ እና 575/2/ሀ/ መሰረት ተደርጎ የቀረበ የወንጀል ክስ በግል ተበዳይ ወይም ህጋዊ ወኪሉ አማካይነት የሚቀርብ እና በግል አቤት ባይ የቀረበ ክስ በሚመራበት ስነ-ስርዓት የሚመራ ሳይሆን በዓቃቤ ህግ ወይም በመንግስት የሚቀርቡ የወንጀል ክሶች በሚመሩበት ስርዓት የሚስተናገዱ እና በግል ተበዳይ ፍላጎት መሰረት ሊቋረጡ የማይችሉ ወንጀሎች ስለመሆናቸው፣ የወ/ህ/ስ/ስ/ህ/ቁ 150-153 እና የወ/ህ/ቁ. 559/2/ እና 575/2/ሀ/፣ በወ/ህ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 132- 135፣ 185፣196፣ 117 94.88 123-131 እና 186-149 Download Cassation Decision

 • 143334 labor law dispute/ bankruptcy/ termination of contract of employment

  አንድ ድርጅት በመክሰር ወይም በሌላ ምክንያት ለዘለቄታው መዘጋት ሠራተኞችን የሥራ ውልን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለማቋረጥ የሚያስችል ሲሆን መረጋገጥ ያለበት መሰረታዊው ነጥብ የአሰሪው ድርጅት ለዘለቄታው መዘጋት ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 24(4) Download Cassation Decision

 • 146727 criminal law/ bail/ appeal

  ተ ከሳሽ በዋስትና ወረቀት እንዲለቀቅ ጠይቆ የሥር ፍ/ቤት የተከሳሽን የዋስትና መብት ጠብቆ ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው ይግባኝ መነሻነት ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሥር ፍ/ቤት የተከሳሽን የዋስትና መብት በመጠበቅ የሰጠውን ውሳኔ በመሻር በሰጠው ውሳኔ ላይ ተከሳሽ ይግባኝ ማቅረብ የሚችል ስለመሆኑ፡- የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 75/2 Download Cassation Decision

 • 149962 cassation procedure/ Amhara

  የ አ/ብ//ክ/መ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሠራተኞች መተዳደሪያ ደንብ “በይግባኝ በቀረበለት ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል” በሚል ተገልጸው የሚገኙት ድንጋጌዎች በይግባኝ ደረጃ ቀርበው ለመታዬት የማይችሉ የመጨረሻ ውሳኔዎች መሆናቸውን የሚገልጽ እንጂ በሰበር ሰሚው ችሎት መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለባቸውን ጉዳዮች ለማረም የሚቀርቡ ጉዳዮችን የሚጨምር ስላለመሆኑ፡- የአ/ብ//ክ/መ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሠራተኞች መተዳደሪያ ደንብ ቁጥር104/2004 አንቀጽ 75(3) Download Cassation Decision

 • 150947 labor law dispute/ loss of capacity to perform

  ሠ ራተኞች በሙሉ እውቀታቸውና ብቃታቸው ሰርተው እኩል የምርት ጥራትና መጠን ያመርታሉ ተብሎ የማይገመት ስለመሆኑና የአንደኛው ሠራተኛ ያመረተው ምርት መጠንና ጥራት ብቻ ለሌላው ሠራተኛ ከአቅም በታች ሰርቷል ለማለት በቂ መሰፈርት ሆኖ ሊወሰድ የማይገባ ስለመሆኑ፡- Download Cassation Decision

 • 151474 labor law dispute/ provident fund/ pension/ severance pay

  አ ንድ ሠራተኛ የፕሮቪደንት ፈንድ ወይም የጡረታ መብት ተጠቃሚ ከሆነ አሰሪው የስራ ስንብት ክፍያ በተደራቢነት የመክፈል ግዴታ የሌለበት ሲሆን በራሱ ፍላጎት እና ፈቃደኝነት የስራ ስንብት ክፍያን በተደራቢነት እንዳይከፍል ክልከላ የሚያደርግ ስላለመሆኑ፡- አዋጅ ቁጥር 494/1998 አንቀጽ 2 (ሰ) Download Cassation Decision

 • 78629 unlawful enrichment/ period of limitation

  ፍ/ብ/ሕ/ቁ 2143(1) የተመለከተው የይርጋ ዘመን አላግባብ መበልፀግን አስመልክቶ በሚቀርቡ ክሶች ላይ ተፈፃሚነት የሌለው ስለመሆኑ እና ተፈፃሚነት ሊኖረው የሚገባው የአስር ዓመት የይርጋ ዘመን ስለመሆኑ፤ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2143(1)፤1845 Download Cassation Decision