Federal Court Case Tracker

volume 21

volume 21

 • 100295 civil procedure/ material jurisdiction/ res judicata/

  አንድ ፍ/ቤት ክስ ቀርቦለት ጉዳዩን የማየት ሥረ ነገር ስልጣን የለኝም በማለት መዝገቡን የዘጋው እንደሆነ ዋናውን ክርክር እንዳላየ የሚያስቆጥር ሲሆን የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.5፣9 እና 231 በመዝገቡ ላይ የሰጣቸው ማናቸውም ትእዛዞች በማናቸውም ወገን ላይ ህጋዊ የሆነ አስገዳጅነት ውጤት የሌለውና በዚሁ ጉዳይ ለሚመለከተው ፍ/ቤት መዝገቡ ቢቀርብ ከዚህ ቀደም በፍርድ ያለቀ ነው ሊያስብል የማይችል ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 100395 property law/ sale of immovable property/ warranty/ delivery

  የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ጋር በተያያዘ ሻጭ ንብረቱን ከ3ተኛ ወገን ይዞታና ቁጥጥር ነፃ በማድረግ የማስረከብ ግዴታ እና ገዥ ከተረከበ በኃላ ንብረቱ የእኔ ነው ባይ ቢመጣ ሻጩ በዋቢነት የመቆም ግዴታ የተለያየ ግዴታ ስለመሆኑ፤ ፍ/ብ/ሕ/ቁ 2875 ፣ 2274 ፣ 2880 ፣ 2881 ፣ 2882 ፣2879፣ 2888 ፣1206 ፣ 1195 ፤ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 33(2) 36(4) እና 40 (2) Download Cassation Decision

 • 102406 property law/ rural land/ Oromia/ jurisdiction

  በኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀም ህግ መሰረት ግጭትና አለመግባባትን በመጀመሪያ በአስታራቂ ሽማግሌዎች እንዲፈቱ የሚደነገጉት ድንጋጌዎች አርሶ አደር ከአርሶ አደር በሚያደርገው የሚፈጠርን አለመግባባትን ለመፍታት እንጂ በህግ ወለድ እና በአንድ አርሶ አደር ሰዎች መካከል የሚፈጠርን አለመግባባት ጭምር የሚያካትት ሥላለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 130/99 አንቀፅ 16 Download Cassation Decision

 • 102668 civil procedure/ pleading/ counter claim/

  የከሳሽ ተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ሊቀርብ የሚችለው በከሳሽ ወገን ላይ ብቻ ሥለመሆኑ ተከሳሽ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ሲያቀርብ ሊከተለው ሥለሚገባ ሥነ-ሥርዓት የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 30፣36፣224 እና 234(1)(ረ) Download Cassation Decision

 • 104621 civil procedure/ amendment of pleading/ procedure for amendment

  ክስን ከማሻሻል ጋር በተያያዘ ፤ፍ/ቤት ክስ እንዲሻሻል ከፈቀደ በኃላ የቀረበውን ክስ የሚሻሻልበትን ነጥብ ተገቢነት መመርመር ያለበት ከመፍቀዱ በፊት ስለመሆኑ እና ክሱ የተሻሻለበት ነጥብ ፍቃድ ከተሰጠበት ነጥብ ውጭ ከሆነም በውሳኔው ላይ መግለፅ ያለበት ስለመሆኑ ፤ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91 እና 216 (3) Download Cassation Decision

 • 104637 criminal law/intention/ concurrence

  ወንጀል አድራጊው የመጀመሪያውን የጥፋት ዓላማውን ከግብ ለማድረስ ሲል መሰረታዊ ከሆነው ወንጀል በኋላ አከታትሎ ያደረገው ድርጊት ከቀድሞ ሃሳቡና ሊደርስበት ካቀደው ግብ ጋር የተያያዘ ሆኖ ሲገኝ በዋናው ወንጀል ስር መጠቃለል የሚገባው ስለመሆኑ ፣ የወ/ሕ/ቁ. 61/3/ Download Cassation Decision

 • 104755 intellectual property/ trade mark/

  በንግድ ምልከት መመሳሰል በአንድ ምርት ወይም አገልግሎት ጋር በተገናኘ ሁኔታ የሕዝብ ግንዛቤ ያዛባ ወይም ሊያዛባ የሚችል፤ በሁለት ድርጅቶች መካከል መሳከርን የሚፈጥር ከሆነ ሕብረተሰቡ ሊያገኝ የሚገባው ሕጋዊ ጥበቃና ዋስትና በተሟላ ሁኔታ ተፈፃሚ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ በተመሳሳይ የንግድ ምልክት ላይ ምዝገባ እንዲደረግ የሚቀርብ ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 501/1998 አንቀፅ 7 አዋጅ ቁጥር 320/1995 Download Cassation Decision

 • 106994 contract law/ contract of sale/ performance bond/ joint and several liability

  የዕቃ አቅርቦት ውል በአቅራቢው ባለመፈፀሙና ለተወሰደ ቅድሚያ ክፍያ እንዲሆን የቅድሚያ ክፍያ የዋስትና ሰነድ የሰጠ አካል ውል አቅራቢው በውል የገባውን ግዴታ ባለመፈፀሙ ምክንያት በሰጠው የዋስትና ሰነድ መሠረት ከዋናው ባለዕዳ ጋር በአንድነትና በነጠላ ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 108692 judge/appeal procedure

  አንድ ዳኛ ተግባሩን በሚያከናውንበት ወቅት የፍርድ ስራ ስህተት ተፈጽሟል ከተባለ በይግባኝ ፣ በሰበር ወይም በሌላ በህግ በተዘረጋ ስርዓት ከማሳረም በቀር ስልጣንን አላግባብ ተጠቅሟል በሚል ሊቀጣ የማይችል ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 109194 contract law/ urban land lease

  የሊዝ ውል ሊቋረጥ ወይም ሊፈርስ ስለሚችልባቸው መሰረታዊ ምክንያቶች የሊዝ አዋጅ ቁ. 272/94 አንቀጽ 15/1/ Download Cassation Decision

 • 110149 commercial law/ cooperatives/ rights of members

  በአንድ የህብረት ስራ ማህበር ውስጥ አባል የሆነ ሰው በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በአካል ተገኝቶ ድምፅ መሰጠት ያለበት ስለመሆኑ እና ይህ ሁኔታ /አጠቃላይ መርህ/ ሊታለፍ የሚችለው መረጃ ሊቀርብበት የሚችል ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥም ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 147/91 /በአዋጅ ቁጥር 402/96 እንደተሻሻለ አንቀጽ 18/2/ Download Cassation Decision

 • 110507 advocates/conflict of interest

  በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ አንድ ጠበቃ የጥቅም ግጭት ሊፈጥር በሚችልበት ሁኔታ የተለያዩ ተከራካሪዎችን በመወከል መከራከር የማይችልና ይሄንኑ ተግባር ፈፅሞ ሲገኝ እንደ ከባድ የሥነ -ምግባር ጥሰት ሊቆጠር የሚችል ስለመሆኑ የኦሮሚያ ክልል የጠበቆች እና ሕግ ጉዳይ ፀሃፊዎች እና ፍቃድ አሰጣጥ አዋጅ ቁ. 182/2005 አንቀፅ 36(3) ደንብ ቁጥር 57/92 አንቀፅ 10፣11፣12 እና 13 Download Cassation Decision

 • 110736 criminal law/criminal procedure/ consolidation of trials/ concurrence/ sentencing

  በአንድነት ተጣምረው መታየት የነበረባቸው የወንጀል ክሶች በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ወይም ችሎቶች በተናጠል ታይተው የተለያዩ ቅጣቶች በተወሰኑ ጊዜ እንደገና በአዲስ መልክ እያንዳንዱ ቅጣት ተሰልቶና የቅጣት ማቅለያዎች ሁሉ ታይተው የሚወሰን ሳይሆን ሕጉ ጥፋተኛው በፈፀማቸው ተደራራቢ ወንጀሎች በአንድ ጊዜ ቢፈረድበት ኖሮ ሊወሰንበት ይችል ከነበረው ከፍተኛ ቅጣት ሳያልፍ መወሰን ያለበት ሥለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 111960 tax law/ constitution/ criminal law/ retroactivity of law

  የተሻረው ህግ ይሰራ በነበረበት ጊዜ የተፈጸመ ወንጀል ሲኖርና በአዲሱ ህግ ግን እንደወንጀል ያልተቆጠረ ሲሆን ድርጊቱ ሊያስከስስም ሆነ ሊያስቀጣ የማይችልና የተጀመረውን ክስም የማቋረጥ ህጋዊ ውጤት ያለው ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 21(2)፣ የኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 5/3/ አዋጅ ቁ. 622/2001 አንቀጽ 99፣ አዋጅ ቁ. 859/2006 Download Cassation Decision

 • 113013 contract law/ cooperatives/ transfer of shares

  የህብረት ሥራ ማህበር ውስጥ ያለ የማህበር አባል ዕጣውን ወይም ጥቅሙን ሲያስተላልፍ ሊከተለው ስለሚገባ አካሄድ አዋጅ ቁ.147/91 አንቀፅ 19 Download Cassation Decision

 • 113613 civil procedure/ consolidation of suits/ conflicting judgments

  ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ክሶች ወይም ይግባኞች መጣመር በነበረባቸው ሰዓት ሣይጣመሩ ቢቀሩና የግራ ቀኙን የተለያየ መብት በሚያጎናፅፍ ሁኔታ ቢወሰን እነዚህን ውሳኔዎች ተጣጥሞ እንዲፈፀሙ ማድረግ ተገቢ ሥለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.11 Download Cassation Decision

 • 114398 contract law/ defect in consent/

  በተዋዋይ ወገኖች መካከል የተደረገ ውል የፍቃድ ጉድለት ስለመኖሩ ማሳያ ሊሆኑ ከሚችሉ ጉዳዮች ውስጥ ከተዋዋይ ወገኖች በአንዱ ውልን ለማፍረስ የሚያስችል ጉዳይ መኖሩን ማሳየት ሲቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ. 1696፣1710/2/ Download Cassation Decision

 • 114670 property law/ constitution/ rural land/ South Region/ jurisdiction/ appeal

  በደቡብ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ መሰረት በወረዳ በተጀመረ ክርክር በክልሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከፀና ውሳኔው የፀናበት ወገን ለተጨማሪ ይግባኝ ለክልሉ ጠቅላይ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ማቅረብ የሚችል ስለመሆኑ፣ የኢ.ፈ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/3//ሀ/ የደቡብ ክልል ህገ መንግስት አንቀጽ 75/2/ሐ/ የከ/ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ. 43/1994 አንቀጽ 5/3/ የፌደራል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 456/1997 አንቀጽ 12 የደ/ክ/የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 110/1999 አንቀጽ 12/4/ Download Cassation Decision

 • 115387 property law/ government house/ ownership right

  የመንግስት ቤት ተከራይቶ የሚኖሩ ሰዎች የባለቤትነት መብት (የመፋለም ክስ) የመጠየቅ ክስ ማቅረብ የሚችሉበት ህጋዊ ምክንያት ስላለመኖሩ የፍ/ሕ/ቁ. 1205 Download Cassation Decision

 • 115399 property law/ rural land/ Amhara/ transfer of land/ succession

  በአማራ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ መሰረት መሬት በኑዛዜ ተላልፎልኛል የሚል አካል ኑዛዜው ተቀባይነት እንዲያገኝ ሊያደርገው ስለሚገባ እርምጃ የአ/ክ/የመ/አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 133/98 ደንብ ቁ. 51/99ን ለማስፈጸም የወጣው መመሪያ አንቀፅ 13/1/2/ Download Cassation Decision

 • 116860 civil procedure/ Withdrawal or abandonment without leave

  ከሳሽ ወገን ያለፍርድ ቤት ፈቃድ በተወው ወይም በሰረዘው ነገር ሌላ ክስ ለማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.፤278፤ 279/1/ Download Cassation Decision

 • 117036 contract law/ bailment/ non-performance/ interest

  አንድ ዕቃ ለመሸጥ /በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ለማስረከብ/ የተዋዋለ ወገን ከዕርሱ አቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ውሉን መፈጸም ባልቻለ ጊዜ በቅድሚያ ለዚሁ ስራ የተቀበለውን ገንዘብ ከወሰደበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር ከመመለስ ውጭ ውሉን ባለመፈጸሙ ምክንያት ለደረሰው ኪሳራ እንዲከፍል የማይገደድ ስለመሆኑ፣ ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2356/1/ Download Cassation Decision

 • 117151 pension/ criminal conviction

  በጡረታ አበል ተጠቃሚ ሆኖ በወንጀል ጥፋት ምክንያት ከሦስት ዓመት ያላነሰ ጽኑ እስራት የተፈረደበት የዘለቄታ የጡረታ አበል መብቱን ያጣ ባለመብት የተሻሻለው የጡረታ አዋጅ ከፀናበት ጊዜ ጀምሮ ውዝፍ አበል ሳይጨምር የጡረታ አበል የማግኘት መብት የሚኖረው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 907/2007 አንቀጽ 11/9 Download Cassation Decision

 • 117164 family law/ common property/ business

  ባልና ሚስት የጋራ የሆነውን የንግድ ድርጅታቸውን መልካም ስም የማከራየት መብትና በቤቱ ውስጥ የሚገኘውን የንግድ ዕቃ የመከፋፈል መብት ያላቸው ስለመሆኑ፣ የን/ሕ/ቁ. 127 Download Cassation Decision

 • 117953 contract law/ antichresis/ formation of contract

  በህጉ አግባብ በሕግ ፊት የጸና የወለድ አገድ ዉል መደረጉ ባልተረጋገጠበት የወለድ አገድ ዉል ተቋቋሟል ማለት ስላለመቻሉ የፍትሓ ብሐር ሕግ ቁጥር 3052፤ 3053፤3117—3130 Download Cassation Decision

 • 118246 commercial law/ investment law/ share company

  አንድ የውጪ ዜግነት ያለው ሰው በኢትዩጵያ ውስጥ በሚካሄደው ኢንቨስትመንት ውስጥ አክሲዩንን በመግዛት ለንግድ ስራ ምቹ የሆነ ህንፃ በማሰራት የሥራ መስክ ሊሳተፍ የሚችል ስለመሆኑ አንድ የባለአክሲዮኖቹ ጉባኤ ሕግን፣ መመስረቻ ፅሑፍንና መተዳደሪያ ደንብን በመከተል የተደረገ እስከሆነ ድረስ በሕጉ ጥበቃ የሚያገኝ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 769/2004 አንቀጽ 12(1ሀ))፣ 2(6) እና 38 ደንብ ቁጥር 270/2005 አንቀጽ 3 የን/ሕ/ቁጥር 416(1) Download Cassation Decision

 • 118808 civil procedure/ execution of judgment/ jont and several debtors/ appeal

  ሁለት ባለዕዳዎች በአንድነትና በነጠላ አንድን ዕዳ እንዲከፍሉ ከተፈረደባቸዉ ባለገንዘቡ ገንዘቡ እንዲከፈለዉ ሁለቱን ባለዕዳዎች በአንድነት ወይም አንደኛዉን ባለዕዳ ሙሉ ገንዘቡን እንዲከፍል ሊጠይቅ የሚችል ሥለመሆኑ በአንድነትና በነጠላ ኃላፊ ከሆኑት የፍርድ ባለእዳዎች አንዱ የፍርድ ባለዕዳ በዋናዉ ፍርድ ይግባኝ ጠይቆ የራሱን ኃላፊነት አስመልክቶ ፍርዱን አሽሮት ከሆነ ሙሉ እዳዉን ለመክፈል ኃላፊነት የሚኖርበት ይግባኝ ሳይጠይቅ በመቅረቱ ዋናዉን ፍርድ ባልተሻረለት ወይም ይግባኝ ጠይቆ ፍርዱ በጸናበት ሰዉ ላይ የሚሆን ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 1896፣ 1897 Download Cassation Decision

 • 119233 contract law/ contract on credit/ unlawful object/ non-performance of contract

  የዱቤ የቤት ሽያጭ ውል የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ህገ ወጥ ውል ነው በማለት በውሉ መሰረት ላለመፈፀም የሚቀርብ ክርክር ህጋዊ መሰረት የሌለው ስለመሆኑ የፍትሓ ብሔር ህግ ቁጥር 1792 ንዑስ አንቀጽ 1፤1793 Download Cassation Decision

 • 119435 civil procedure/ jurisdiction/ urban land lease

  የሊዝ ውል እንዲሰረዝ የሚቀርብን የዳኝነት ጥያቄን በተመለከተ መደበኛ ፍርድ ቤቶች ሊያስተናግድ የሚገባ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 119448 labor dispute/ termination of contract of employment/ termination by worker/ notice

  አንድ ሠራተኛ በራሱ ፈቃድ ስራ በሚለቅበት ጊዜ የሠላሳ ቀናት የማስጠንቀቂያ ጊዜ አለመስጠቱ የተረጋገጠ እንደሆነ ለሰራተኛው ከሚከፈለው ክፍያ ከሰላሳ ቀናት ክፍያ ያልበለጠ ካሳ ለአሰሪው ሊከፍል የሚገባ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 31፤አንቀጽ 45 Download Cassation Decision

 • 119571 contract law/ bailment/

  ያለዋጋ ወይም በደመወዝ የሚሰጥ አደራ ሰጭና አደራ ተቀባይ ስምምነት ካላደረጉ በስተቀር በአደራ የሚቀመጥ ዕቃ ዋጋ የማይከፈልበት ስለመሆኑና አደራ ሰጭው አደራ ተቀባዩ ዕቃውን በመልካም አያያዝ ለማኖር ያወጣውን ወጭ ሁሉ ሊከፍለው የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ. 2788 እና 2793/2/ Download Cassation Decision

 • 120087 property law/ civil procedure/ rural land/ Amhara/ splitting claims

  የእርሻ መሬት ይዞታን ከማስለቀቅ ጋር በተገናኘ የሚቀርብ ክስ ከእርሻ መሬት ልዩ ባህሪ አንጻር ከንብረቱ የሚገኘውን አላባ ወይም ሌላ ጥቅም ጭምር ከዋናው ክስ ጋር አጣምሮ ይክሰስ ሊባል ስለማይችል፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216/3/፣218/ሀ/ አዋጅ ቁ. 452/1997 አንቀጽ 12 የአ/ክ የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 130/1999 አንቀጽ 16 ደንብ ቁ. 151/2005 አንቀጽ 18 Download Cassation Decision

 • 120150 contract law/ form of contract/ written contract/ amendment of contract

  በጽሁፍ በተደረገ ውል አንደኛው ወገን ውሉን ለማሻሻል ሲፈለግ ዋናው ውል በፅሁፍ እስከተደረገ ድረስ ማሻሻያውም በዛው አግባብ መሆን ያለበት ሥለመሆኑ በጽሁፍ በተደረገ ውል አንደኛው ወገን የውል ማሻሻያ ጽሁፍ ለሌላኛው ወገን ሲላክልት ሌላኛው ወገን ሊቀበለው እንደሚችል ሲደነግግ ውሉን ለመቀበሉ ግን የተለየ ስርዓት ካለማስቀመጡ በተጨማሪ በምክንያታዊ ጊዜ ውሉን ያለመቀበሉን ካላስታወቀ ውሉን እንደተቀበለ የሚቆጠር ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ. 1722፣2625 Download Cassation Decision

 • 120355 law of person/ name/ change of name

  ፍርድ ቤቶች የሥም ይቀየርልኝ ጥያቄ በሚቀርብላቸው ጊዜ የአመልካችን ስም መለወጥ አስፈላጊ የሚያደርጉ ሁኔታዎች መኖር አለመኖራቸውን በማስረጃ አጣርተውና የሶስተኛ ወገን ጥቅም የማይጎዳ ለመሆኑ ጭምር ካረጋገጠ በኋላ ተገቢውን መወሰን ያለባቸው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41/1/ /1/ Download Cassation Decision

 • 121565 civil procedure/ execution of judgment/ family law/ common property

  የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ነው የተባለ ንብረትን አፈፃፀምን በተመለከተ የንብረቱ ሕጋዊነት ላይ የሚመለከተው አስተዳደር አካል አግባብ ያለው ውሣኔ እስኪሰጥ ድረስ መሸጥ መለወጥ ባይቻልም ባለበት ሁኔታ የግራ ቀኙን እኩል ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ አግባብ በጋራ የሚያስተዳድሩበት ወይም ተከፋፍለው የሚጠቀሙበት ወይም አከራይተው ጥቅሙን እኩል የሚከፋፈሉበት ሁኔታ መመቻቸት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ 386/2/ Download Cassation Decision

 • 121660 civil procedure/ jurisdiction/ constitution/ Addis Ababa land issues appeal commission

  የአዲስ አበባ ከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ቀደም ብሎ በሰጠው ፍርድ ላይ የሚቀርብለትን የፍርድ መቃወሚያ ተቀብሎ የመዳኘት ስልጣን ያለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358፣የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37/1/ አዋጅ ቁ. 721/2004 Download Cassation Decision

 • 121663 property law/ rural land/ abandoned land/ jurisdiction

  በትግራይ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ መሰረት ወራሽ የሌለው መሬት በቀበሌው የገጠር መሬት አስተዳደር ኮሚቴ መሬት ለሌላቸው ከተሸጋሸገ በኋላ የሚቀርብ አቤቱታ ከመሬት ዳኝነትና ከፍርድ ቤት ውሳኔ ውጭ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 239/2006 አንቀጽ 14/8/ ደንብ ቁ. 85/2006 አንቀጽ 22/1//ሀ/፣21/8/ Download Cassation Decision

 • 121938 civil procedure/ pauper procedure/ corporate entities

  በህግ የሰውነት መብት የተሰጣቸው ተቋማት በድሃ ደንብ ዳኝነት ሳይከፍሉ ለመስተናገድ በማስረጃ ሊያቀርቡት ስለሚገባቸው ጉዳዮች የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.467-479 Download Cassation Decision

 • 122258 repeal of law/priority right

  በዕዳ አከፋፈል ሂደት የቀደምትነት መብትን ለመወሰን መታየት ያለበት ህጎች ከወጡበት ጊዜ አንፃር ሳይሆን በክርክሩ ለተያዘው ጉዳይ በልዩ ህግ /special law/ የተቋቋመው የቀደምትነት መብት ስለመሆኑ የአዋጅ ቁጥር 715/2003 አንቀጽ 11/12/ ፤ 57/(1)፤ አዋጁ ቁጥር 97/1990 Download Cassation Decision

 • 122740 property law/ rural land/ Oromia/ transfer of land/ land tax

  የገጠር መሬት ሕጋዊ በሆነ ሁኔታ አግባብ ባለው አካል በስጦታ የተላለፈለት ተጠቃሚ ለረጅም ጊዜ ተጠቃሚ የሆነበት መሬት መሆኑ ከተረጋገጠ መሬቱ በስጦታ ሰጪዉ ስም ተመዝግቦ መገኘቱ እና ግብር በስሙ መከፈሉ ብቻ ይዞታዉ በስጦታ ዉል አልተላለፈም የሚያሰኝ ወይም በመሬቱ ላይ ያለዉን የባለይዞታነቱን መብት የማያስቀር ስላለመሆኑ የኦሮሚያ ክልል ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀፅ 2/3፤9(5) Download Cassation Decision

 • 122766 criminal law/sentencing/ sentencing guideline

  ፍርድ ቤቶች በተከሳሽ ላይ የሚጣለው ቅጣት ከወንጀል አፈጻጸሙ ሆነ ባህሪዉ እንዲሁም ከተፈፀመው ወንጀል ክብደት አንፃር ፍትሃዊ ውሳኔ ለመስጠት በቅጣት አወሳሰን መመሪያዉ መሠረት ለመወሰን የማያስችል ሆኖ በተገኘ ጊዜ በቅጣት አወሳሰን መመሪያው መሰረት ምክንያቱን በማስቀመጥ በመመሪያው ከተቀመጠው በተለየ መልኩ ቅጣት ሊወስኑ የሚችሉ ሥለመሆኑ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 አንቀፅ 21(1) የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 88(2) Download Cassation Decision

 • 123046 criminal law/ car accident/ negligence/sentencing/ concurrence

  አንድ አሽከርካሪ በአንድ ቸልተኝነት ተግባር በተለያዩ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ሲያደርስ የወንጀል ሕግ ቅጣቱን ከፍ ከሚያደርግበት በስተቀር በቸልተኝነት ተደሪራቢ አካል ማጉደል ወንጀል እንደፈፀመ ተቆጥሮ ተደራራቢ ወንጀል ክስ ሊቀርብበትና በተደራራቢ ወንጀል በመፈፀም ጥፋተኛ ተብሎ ሊቀጣ የሚገባ ስላለመሆኑ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 60(ሐ)፣61፣ 543(3)፣559(2) Download Cassation Decision

 • 123123 civil procedure/ period of limitation/ Withdrawal or abandonment with leave

  በክስ አቀራረብ ሥርዓት ላይ ጉድለት ያለበት መሆኑ ተረጋግጦ የተዘጋ መዝገብ ምንም አይነት ክስ እንዳልቀረበ የሚያስቆጥርና የይርጋ ጊዜ የማቋረጥ ውጤት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 278 (2) (ሀ) እና (3) Download Cassation Decision

 • 123132 family law/ private international law/ evidence law

  በሌላ አገር ህግ እና በኢትዮጵያ የቤተሰብ ህግ መካከል እንደባልና ሚስት አብረው በመኖር ግንኙነት ውስጥ የተፈራ ንብረት የጋራ እንዲሆን ለመወሰን በሁለቱም ህጎች መካከል ግጭት መኖር ያለመኖሩን የሌላኛው አገር ህግ እንዲቀርብ በማድረግ መወሰን የሚገባው ስለመሆኑ በዓለም አቀፍ የግለሰብ ህግ /Private International law/ መሠረት በዘርፉ እውቀት ያለ ወይም ምሁር /Scholar/ የሰጠውን አስተያየት በማስረጃነት ሲቀርብ የቀረበውን አስተያየት እንደማንኛውም ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን አስተያየቱ የቀረበለት ፍርድ ቤት ስለመሆኑ የኢ.ፊ.ድ.ሪ ቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 5፤102 /1/ Download Cassation Decision

 • 123833 civil procedure/ parties to a suit/ appeal/ injunction

  በክርክር ተሳታፊ ያልሆነ ወገን በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ እግድ ትዕዛዝ የዕግድ ትዕዛዙን ለሰጠው ፍ/ቤት የዕግድ ይነሳ አቤቱታ ሳያቀርብ በቀጥታ ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይግባኝ የሚያቀርብበት እና የዕግድ ትዕዛዙ ላይ ውሣኔ የሚያሰጥበት ስርዓት የሌለ ስለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 154፤158 Download Cassation Decision

 • 123984 commercial law/ check/ loan/ evidence law

  ቼክ የብድር ዉልን ተክቶ ብድር መኖሩን ለማስረዳት አግባብነት ያለዉ ሰነድ ነዉ ለማለት የሚያስችል የሕግ መሰረት የሌለ ስለመሆኑ በብድር የተሰጠዉ ገንዘብ 500 /አምስት መቶ/ የኢትዮጵያ ብር በላይ ሲሆን የብድሩ ዉል በጽሑፍ ወይም በፍ/ቤት በተደረገ የእምነት ቃል ወይም መሐላ ካልሆነ በቀር ለማስረዳት የማይቻል ሥለመሆኑ ንግድ ሕጉ ቁጥር 827 /ሀ/ እና 854 የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2472(1) Download Cassation Decision

 • 123986 civil procedure/ jurisdiction/ Value added tax (VAT)/ federal tax/ tax appeal

  የተጨማሪ እሴት ታክስ የፌዴራል ታክስ በመሆኑና የክልል የገቢዎች ቢሮዎች ታክሱን የሚያስተዳድሩት በዉክልና ስልጣናቸዉ በመሆኑ ምንም እንኳ ታክሱ የተወሰነዉ በክልሉ የገቢዎች ቢሮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ቢሆንም የሕግ ስህተት አለበት የሚል ወገን ይግባኝ ማቅረብ የሚገባዉ ስልጣን ላለዉ የፌዴራል ፍ/ቤት ወይም የዉክልና ስልጣን ላለዉ የክልል ፍ/ቤት ሥለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 28(2) እና አንቀጽ 30፣አንቀጽ 43(3)፣ 112 Download Cassation Decision

 • 124313 law of succession/civil procedure/ jurisdiction/

  የውርስ ንብረት የመከፋፈል ጥያቄ ንብረቱ በአይነት ተለይቶና ተገምቶ እስከቀረበ ድረስ በቀረበው ግምት መሰረት የፍርድ ቤቶችን የስረ ነገር ስልጣን ሊወሰንበት የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 18፣23 Download Cassation Decision

 • 124552 civil procedure/ summary procedure/

  በአጭር ስነ ሥርዓት ክስ ሊቀርብ ስለሚችልበት አግባብ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 284 Download Cassation Decision

 • 124618 civil procedure/ execution of judgment/ auction/ priority right

  በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት ተይዞ የሚሸጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሁለት /ከሁለት በላይ የሆኑ ሰዎች በህብረት የያዙት እና ያልተከፋፈሉት በሆነ ጊዜ ከተከፋዮቹ አንዱ ንብረቱን ለመግዛት በጨረታ ተወዳዳሪ ሆኖ የቀረበ እንደሆነ የፍርድ ባለእዳው እንደቀረበ ተቆጥሮ የቀዳሚነት መብት የሚሰጠው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 443፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 126/1/፣ 1386-1409 Download Cassation Decision

 • 124669 civil procedure/ examination of parties/ judgment on admission/

  ተከራካሪ ወገኖች ባላነሱት የመከራከሪያ ነጥብ ወይም የግራ ቀኙ ወገኖች ባልተለያዩበት ጉዳይ እንዲጣራ በማድረግ ውሳኔ መስጠት ተገቢ ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 241፣242 Download Cassation Decision

 • 125186 property law/ rural land/ Amhara/ donation/ testament

  በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ መሰረት ስጦታው በተደረገበት የእርሻ መሬት ላይ በቤተሰብነት የተመዘገበ አባልን ያገለለ መሆኑ ከታወቀ ይኸው ሰነድ በህግ ተቀባይነት የማይኖረው ስለመሆኑ ህጉን ያልጠበቀ የገጠር መሬት ይዞታ በኑዛዜ ወይም በስጦታ ተላልፏል የሚለው ወገን መብቱን ለማስጠበቅ በሁለት ዓመት መጠየቅ ነበረበት ሊባል የሚችል ስላለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2441፣ አዋጅ ቁጥር 456/97 የአ/ብ/ክ/መ/የመ/አስ/አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 133/98 አንቀጽ 16/3 ፣ ደንብ ቁጥር 51/99 አንቀጽ 11/2 Download Cassation Decision

 • 126017 criminal law/criminal procedure/evidence law/ exhibit

  በወንጀል ጉዳይ በኤግዚቪትነት የተያዘ ንብረት በፍርድ ውሳኔ የሚያገኘው በወንጀሉ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ሲሰጥ ለባለንብረቱ ይመለስ ወይም ለመንግስት ገቢ ይሁን ተብሎ ሲወሰን ወይም ተገቢውን የህግ ስርዓት ተከትሎ ሥልጣን ባለው አካል ትዕዛዝ ሲተላለፍ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 127312 criminal law/ criminal procedure/amendment of charges

  ዓቃቤ ህግ በቅድሚያ ያቀረበው ክስ ላይ ማስረጃዎቹን ካሰማና እንዲከላከሉ ታዞ የክሱ መሰማት በቀጠለበት ሂደት ላይ ያቀረበው ክስ ማሻሻል አቤቱታ ተቀባይነት ሲያጣ ይህንን በህጉ አግባብ በይግባኝ ከማሳረም በቀር ክሱን በማንሳት በሌላ መዝገብ አዲስ ክስ ማቅረብ ሥነ-ሥርዓታዊ ሥላለመሆኑ የወ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 118/፣119፣38፣40/1/ እና 41፣ Download Cassation Decision

 • 127580 civil procedure/ appeal/ issue in dispute/ remand

  የሥር ፍ/ቤት በጭብጥነት ይዞ በአግባቡ ባጣራው ፍሬ ጉዳይ ላይ በይግባኝ ፍርዱን የሚመለከተው ፍ/ቤት ያለበቂና ህጋዊ ምክንያት የተጣራውን ፍሬ ነገር በድጋሚ እንዲጣራ ወደ ሥር ፍ/ቤት መመለስ ተገቢ ስላለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.136(1)፣343(1) Download Cassation Decision

 • 127587 extra contract law/ evidence law/ car accident/ valuation/ compensation

  በተሽከርካሪዎች ላይ የደረሰን ጉዳት በተመለከተ የገበያ ዋጋ አስልቶ ግምት ለማቅረብ በህግ ለትራፊክ ፖሊስ የተሰጠ ተግባር ስላለመሆኑ የተሽከርካሪ ዋጋ ግምት የመተመን አገልግሎት መስጠት የትራንስፖርት ባለሥልጣን ስለመሆኑ በአንድ ንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት ጠቅላላ ጉዳት (total loss) በሚሆንበት ጊዜ በንብረቱ ላይ የደረሰውን አጠቃላይ ግምት ከመጠየቅ ውጪ ይገኛል ተብሎ የሚታሰበውን ገቢ መጠየቅ አግባብነት የሌለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.681/2002 አንቀፅ 2(25)፣37(2(ሐ) አዋጅ ቁ.468/97 አንቀፅ 7(1(ዘ)) የፍ/ሕ/ቁ.2090(1)፣2092 እና 2119(1)(2) Download Cassation Decision

 • 127714 family law/ private international law/ conflicts of law/ jurisdiction

  ጋብቻ የተፈጸመው በአንድ ክልል ውስጥ እና በዚያው ክልል ሕግ መሰረት ሆኖ ክስ በቀረበበት ጊዜ ተጋቢዎቹ የሚኖሩት በተለያዩ ክልሎች ውስጥ መሆኑ ቢረጋገጥ እንኳ ከፍቺ እና መሰል ጥያቄዎች ጋር ተይይዘው የሚነሱ ጉዳዮችን የማስተናገድ የስረ ነገር ስልጣን በክልሉ ሕግ መሰረት ጉዳዩን የማየት ስልጣን የተሰጠው የክልሉ ፍርድ ቤት እንጂ ተጋቢዎቹ መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልሎች ውስጥ እንደሆነ ተቆጥሮ ጉዳዩ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የስረ ነገር ስልጣን ስር የሚወድቅ ስላለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 25/1988 (እንደተሻሻለ) አንቀጽ 5 (2) Download Cassation Decision

 • 128466 advocates/ duty of a a lawyer/

  አንድ ጠበቃ ከጅምሩ የሕግ መሠረት የሌለዉና አዋጭ አለመሆኑ የተረጋገጠን ወይም ተከራክሮ የመርታት ዕድል የሌለዉ መሆኑን እያወቀ ደንበኛዉን አላስፈላጊ ለሆነ ክርክርና ወጪ መጋበዝ የሌለበት ስለመሆኑ አንድ ጠበቃ የጥብቅና አገልግሎት ዉል ከመዋዋሉ በፊት ማስረጃ ሰብስቦ ማጠናቀቅ ወይም ምስክሮችን አስቀርቦ መጠየቅና የሚያዉቁትን አስቀድሞ ማወቅ የሚጠበቅበት ሥላለመሆኑ የደንብ ቁጥር 57/92 አንቀጽ 4 Download Cassation Decision

 • 128776 civil procedure/ execution of judgment/ auction/ valuation

  በፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ ማናቸውም ንብረት በሐራጅ እንዲሸጥ በሚወሰንበት ጊዜ የሚሸጠው ንብረት ከትክክለኛው የዋጋ ግምት አላግባብ ከፍ ወይም ዝቅ ተደርጎል ብሎ የሚያስበው ወገን የጨረታው ቀን ከመድረሱ በፊት የጨረታውን ትዕዛዝ ለሰጠው ፍ/ቤት ግምቱ ተጋኗል በማለት መቃወሚያ ማቅረብ የሚጠበቅበት ሥለመሆኑ በሁለተኛው የጨረታ ማስታወቂያ በተወሰነው ቀን ተጫራች ያልቀረበ እንደሆነ ለጨረታ የቀረበውን ንብረት የፍርድ ባለገንዘቡ ተረክቦ እንዲይዝ ትዕዛዝ ሊሰጥ የሚችለው የፍርድ ባለገንዘቡ ንብረቱን ለመረከብ ፈቃደኛ ከሆነ ብቻ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 423/(1)(2)፣የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 428/2 Download Cassation Decision

 • 129430 civil procedure/ jurisdiction/ live animals marketing

  በህገወጥ መንገድ ተይዘው በተገኙ የቁም እንስሳት ላይ አግባብ ያለው አካል በሚወስደው እርምጃ ላይ በቀጥታ ክስ ስልጣን ላለው ፍ/ቤት ማቅረብ የሚቻል ስለመሆኑ፣ የቁም እንስሳት ግብይት አዋጅ ቁጥር 819/2006 አንቀጽ 15/5/ እና 8 ደንብ ቁጥር 341/2007 አንቀጽ 19/4/ እና 5 Download Cassation Decision

 • 129933 family law/ paternity/ contesting paternity

  በፌደራል የቤተሰብ ህግ መሰረት በአባት በኩል ያለን መወለድ የመካድ ክስ በማቅረብ መቃወም ስለሚችሉ ሰዎች የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 177/1-3 Download Cassation Decision

 • 130685 labor dispute/ scope of labor proclamation/ manager

  አንድ ሠራተኛ የሥራ መሪ ሆኖ ሥራውን ሲመራ በፈጸማቸው ማናቸውም ክንውኖች ምክንያት በተወሰደበት እርምጃ ሊያነሳቸው የሚችላቸው የመብት ጥያቄዎች የሥራ መሪው በሂደት ወደ ሠራተኛ የሥራ መደብ የተዛወረ ቢሆንም እንኳን በፍትሐብሔሩ ድንጋጌዎች የሚገዙ ስለመሆናቸው አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 3/1፣3/2/ሐ This cassation decision deals with the application of labor proclamation on managers. Download Cassation Decision

 • 130931 family law/obligation of maintenance/child

  ለህፃን ልጅ ማሳደጊያ ቀለብ የመስጠት ግዴታ ያለበት ወላጅ፣ የሚከፍለውን የገንዘብ መጠን በተመለከተ ለመወሰን ግምት ውስጥ ሊገቡ ስለሚገባቸው ሁኔታዎች የተሻሻለው ፌዴራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 197 (2) ፣202 Download Cassation Decision

 • 130944 labor dispute/ civil service/ pension law/ temporary contract

  በኮንትራት /በጊዜያዊነት/ የተሰጠ አገልግሎት ለጡረታ ተግባር ስለሚያዝበት አግባብ ዋጅ ቁጥር 345/1995 ፤በአዋጅ ቁጥር 907/2007 Download Cassation Decision

 • 131088 criminal law/criminal procedure/ appeal/ sentencing

  ተከሳሽ በሚያቀርበው ይግባኝ መነሻነት ቅጣትን በማክበድ መወሰን መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለመሆኑ የወንጀል መ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 196(2 Download Cassation Decision

 • 131622 civil procedure/ jurisdiction/ pendency/ parties to a suit/ agency

   አንዱን የፍትሓብሔር ክስ ባንድ ወይም ካንድ በበለጡ ፍርድ ቤቶች ዘንድ ለማቅረብ የሚቻል ሲሆን የክሱ ማመልከቻ በቀደምትነት የቀረበለት ፍርድ ቤት ብቻ የዳኝነት ሥልጣን እንዳለው ተቆጥሮ ለክርክሩ ውሳኔ ሊሰጥ የሚችል ሥለመሆኑ  አንድን ሰው በመወከል በፍርድ ቤት ቀርቦ ለመሟገት በህጉ የተቀመጠውን የዝምድና ደረጃ ወይም በህጉ የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟላ የውክልና ስልጣን የሚያስፈልግ ስለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 7(2)፣32፣57፣58 እና 63 Download Cassation Decision

 • 131705 criminal law/ constitution/sentencing/ criminal record/ finger print

  አንድ ተከሳሽ በወንጀል ተጠርጥሮ የጣት አሻራ ሰጥቷል በመባሉ ብቻ እንደጥፋተኛ ተቆጥሮ የወንጀል ጥፋት ሪከርድ እንዳለበት ተደርጎ ግምት በመውሰድና እንደ ቅጣት ማቅለያ ሳይያዝ የሚሰጥ ውሳኔ መሰረታዊ የህገ መንግስት መርህን የሚጣረስ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ አንቀጽ 82 Download Cassation Decision

 • 132208 law of person/ absence/ succeeding absent person

  በጠፋው ሰው መሞት ምክንያት መብት የሚያገኙ ሰዎች በመብታቸው መጠቀም የሚችሉት መጥፋቱን የሚወስነው ፍርድ የመጨረሻ ከሆነ በኃላ ስለመሆኑ የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 165(1) Download Cassation Decision

 • 132266 criminal law/ criminal fault and accident

  ሰውን ለአደጋ ማጋለጥ ወይም መተው ወንጀል ተፈጽሟል ለማለት ስለሚገባቸው ሁኔታዎች የወ/ሕ/ቁ. 57 Download Cassation Decision

 • 132714 labor dispute/ civil service/ temporary contract

  በመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚፈጸም ጊዜያዊ ቅጥር ውል ሊከተላቸው ስለሚገባ መስፈርቶች መንግስት መስሪያ ቤት የሚደረግ የጊዜያዊ ሰራተኛ ቅጥር ውል ለፕሮጀክት ስራ ካልሆነ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 515/99 አንቀጽ 22/3/፣93 የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ህዳር 18/2005 በቁጥር መ80-893/1/ የተጻፈ ደብዳቤ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር በቁጥር ሲሰመ30/መ/18/22/459 በ16/04/2005 የተጻፈ ደብዳቤ Download Cassation Decision

 • 132861 labor dispute/ civil service/ public pension

  ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ቢያንስ 10 ዓመት ያገለገለ እና በራሱ ፈቃድ ወይም በአዋጅ ከተጠቀሱት ውጪ በሆነ ምክንያት አገልግሎት ካቋረጠ የጡረታ መውጫ እድሜው ሲደርስ የአገልግሎት ጡረታ አበል ለዘለቄታው ሊከፈለው የሚችል ስለመሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ጡረታ(ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር907/2007 አንቀጽ 5/2/፤በአንቀጽ 18 Download Cassation Decision

 • 133773 tax law/ presumtive taxation/ keeping record

  አንድ ግብር ከፋይ የሂሳብ መዝገብ እና ሰነድ ካልያዘ ወይም በማናቸውም ምክንያት የሂሳብ መዝገቡን እና ሰነዱን የግብር አስገቢው ባለስልጣን ያልተቀበለው እንደሆነ ወይም ግብር ከፋዩ በሕጉ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ገቢውን ያላስታወቀ እንደሆነ ግብር አስገቢው ባለስልጣን የግብሩን ልክ በግምት ሊወስን የሚችል ስለመሆኑ፡- የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 69 Download Cassation Decision

 • 134188 labor dispute/ occupational accident/ permanent injury

  በሥራ ላይ የደረሰ የአካል ጉዳት ወደ ዘላቂ የአካል ጉዳት ከተሸጋገረ የካሣ ጥያቄው የይርጋ ጊዜ መነሻ መቆጠር ያለበት ጉዳቱ ከደረሰበት ጊዜ ሳይሆን ዘላቂ የአካል ጉዳት መሆኑ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 162(1) Download Cassation Decision

 • 134834 criminal law/criminal procedure/appeal procedure

  በወንጀል ጉዳይ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ ይግባኝ የሚጠይቅ አካል ሊከተላቸው ስለሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎች የወንጀል ሥነ- ሥርዓት ሕግ ቁጥር 187/1 Download Cassation Decision

 • 135094 arbitration/ recuse

  አንድን ጉዳይ በግልግል እንዲያይ የተቀመጠን የግልግል ዳኛ ከተከራካሪ ወገኖች በአንዱ እንዲነሳ ጥያቄ ሲቀርብ ዳኛው ገለልተኛ ወይም ነፃ ላይሆን የሚችልበት ግምት ለመውሰድ የሚያስችል ወይም ጥርጣሬን የሚፈጥር አከባቢያዊ ምክንያት መኖሩ ብቻ በቂ ሥለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 3340(2)፣3342 Download Cassation Decision

 • 135694 law of succession/ testamentary disposition/ civil procedure/

  ፍ/ቤት የሟችን ኑዛዜ ፈራሽ መሆን አለመሆን ላይ ተመስርቶ በሚቀርብለት የዳኝነት ጥያቄ ላይ አግባብ ያለው ዳኝነት ከመስጠት አልፎ በኑዛዜ የሚደርሳቸውን ድርሻ በትክክል ለይተው ሳይጠይቁ የውርስ ንብረት መጠን ግምት በመቀመጡ ብቻ ይኼው ግምት መሰረት ተደርጎ ሊፈጸም የሚችል ዳኝነት ስላለመኖሩ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 182(1) Download Cassation Decision

 • 136775 civil procedure/ constitution/ cause of action/ justiceable matters

  በፍርድ ቤት የቀረበ ጉዳይ የክስ ምክንያት አለው ብሎ ለመወሰን የሚቻለው በክሱ ላይ የተገለፀው ነገር ቢረጋገጥ ከሳሹ የጠየቀውን ዳኝነት ለማግኘት ሕግ የሚፈቅድለት የሆነ እንደሆነ ስለመሆኑ፡- ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በህግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብ እና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ፡- የኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37(1) Download Cassation Decision

 • 136981 labor dispute/ period of limitation

  ከቅጥር ውል በመነጨ ግንኙነት የሚጠየቅ ማንኛውም ክስ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ ፣ የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው በመብቱ ለመጠቀም ከሚችልበት ቀን ቀጥሎ ካለው ቀን ጀምሮ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 162/1/፣163/1/ Download Cassation Decision

 • 138054 labor dispute/ contract for definite period/termination of contract of employment

  ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠረን ሠራተኛ የሥራ ውሉ የሚቋረጥበት ጊዜ ሲደርስ አሰሪው ማሰናበት የሚችል ሲሆን ስንብቱ ከህግ ውጪ ነው ሊያሰኝ የማይችል ሲሆን በዚህ አግባብ የተሰናበተን ሰራተኛ የሥራ ሥንብት ክፍያ ሊያገኝ ይገባል የማያስብል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 24/1/፣ አንቀጽ 30/1/ Download Cassation Decision

 • 139932 commercial law/check/ period of limitation/

  ቼክ አምጪው በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ባንክ ሣያቀርብ ይህንኑ ጊዜ አሳልፎ አንድ ዓመት ሣያልፍ ባንክ አቅርቦ በቼክ አውጪው ስም በቂ ስንቅ የሌለው መሆኑን ያረጋገጠ ቼክ አምጪ ቼኩን መሰረት አድርጎ የሚያቀርበው ክስ አንድ ዓመት አላለፈም በሚል የሚያቀርበው ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ በንግድ ህግ ቁጥር 881/1/ ስር በተመለከተው የአንድ ዓመት የጊዜ ገደብ ክስ የማቅረብ መብታቸው በህግ ፊት ተቀባይነት ሊኖር የሚችለው በን/ሕ/ቁ. 855 ስር ቼኩን በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ለባንክ የማቅረብ ቅድመ ሁኔታ ሲያሟላ ስለመሆኑ፣ የን/ሕ/ቁ. 855፣881/1 Download Cassation Decision

 • 140781 labor dispute/ probation/termination of contract of employment

  አንድ አሠሪ የቀጠረውን ሠራተኛ በሙከራ ጊዜ አጥጋቢ ውጤት አላሳየህም በማለት የሥራ ውሉን ያለምንም ማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ መብት የሚኖረው በህጉ አግባብ የተደረገ የሙከራ ጊዜ ስምምነት መኖሩ ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 11/1/ /2/ እና /3/ Download Cassation Decision

 • 142752 labor dispute/ period of limitation/ waiver of right/ power of court

  ማንኛውም ወገን የይርጋው ጊዜ ካለፈ በኋላ የይርጋ ጊዜን እንደመቃወሚያ አድርጎ ለማንሳት ያለውን መብት ሊተው የሚችል ስለመሆኑ፣ ዳኞች በገዛ ስልጣናቸው የይርጋውንም ደንብ መከላከያ ለመጥቀስ የማይችሉ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 165/5/፤ የፍ/ሕ/ቁ. 1856/2/ Download Cassation Decision

 • 183200 civil procedure/ jurisdiction/ private international law/ judicial jurisdiction

  የአንድ ሃገር ፍ/ቤት በጉዳዩ ላይ ብሔራዊ የዳኝነት(judicial jurisdiction) ስልጣን አለው ለማለት ሊወሰዱ ስለሚገባቸው ዝርዝር ነጥቦች Download Cassation Decision

 • 97023 civil procedure/ evidence law/ expert testimony/

  በልዩ አዋቂነት ጉዳዩን የያዘው ፍርድ ቤት በሒሳብ አጣሪነት የሾመው ባለሙያ ለማጣራቱ ሥራ ይረዳው ዘንድ ሊቀርቡለት የሚገቡ ጠቃሚ ማስረጃዎች ከአንደኛው ተከራካሪ ወገን ወይም በሁለቱም ወገን ተከራካሪዎች ወይም በሌላ ሶስተኛ ሰው ሳያቀርቡለት ቢቀሩ ሊከተላቸው ስለሚገቡ እርምጃዎች በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 132፣136፣145(1)እና 250 Download Cassation Decision

 • 99474 civil procedure/ evidence law/ appeal/ documentary evidence

  አንድ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ከተከራካሪ ወገኖች አንዳቸው በስር ፍ/ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት የይግባኝ አቤቱታ ሲያቀርቡለት በስር ፍ/ቤት የታዩ ሰነዶችን ወይም መታየት የነበረባቸውን ሰነዶች አስቀርቦ ሳይመረምር በይግባኙ ላይ ውሳኔ፣ ፍርድ ወይም ትእዛዝ መስጠት የሌለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 145/1/ Download Cassation Decision