volume 13

volume 13

 • 31264 civil procedure/ constitution/ jurisdiction/ cassation procedure/

  የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ በሰበር ችሎት የተሻረ ሲሆን በውሣኔው መብቱ የተነካ ወገን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 358 መሰረት ለሰበር ችሎት መቃወሚያ ማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ፣ መብታቸው የተነካ ወገኖች ሊስተናገዱ ስለሚችሉበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 35ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ) አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 1 Download Cassation Decision

 • 36887contract law/ evidence law/ sale of immovable property/ admission/ form of contract/

  የማይንቀሣቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ጋር በተገናኘ ውል መኖሩን በማመን ነገር ግን ውሉ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1723 መሠረት የተከናወነ አይደለም በሚል የሚቀርብ ክርክር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1723(1) መሠረት የሚከናወን የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ምዝገባ ዓላማ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ውል መኖሩን ለማስረዳት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1723(1),2878 Download Cassation Decision

 • 36935 commercial law/insurance/ financial guarantee bond/ form/ period of limitation

  ለገንዘብ እዳ የሚሰጥ ዋስትና አንድ የመድን ተቋም ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል አንዱ ስለመሆኑ፣ በመድን ሰጪ ድርጅቶች ተዘጋጅቶ የሚሰጥ የገንዘብ የዋስትና የግዴታ ሰነድ (Financial Guarantee Bond) ስለሚኖረው ውጤት የገንዘብ የዋስትና የግዴታ ሰነድ ሊያሟላቸው የሚገቡ ፎርማሊቲዎች እና አቤቱታ ከማቅረብ ጋር በተያያዘ ተፈፃሚነት ስለሚኖረው የይርጋ ደንብ አዋጅ ቁ.86/86 አንቀፅ 2 የፍ/ብ/ህ/ቁ 1845, 1922(2)(3), 1725(ሀ), 1727, 1926, 1929, 1930, 1931 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር 23/2002 አንቀፅ 1(1), 2(1) መመሪያ ቁጥር 24/2004 አንቀፅ 1(3), 2(1), 3 የንግድ ህግ ቁ.36(1)(2), 121(ሰ) አዋጅ ቁ.110/90 አንቀፅ 2(2) አዋጅ ቁ.57/89 አንቀፅ 2(18) Download Cassation Decision

 • 40186 commercial law/ insurance/ financial guarantee bond/ share company/ power of manager of share company

  ስለ የገንዘብ ዋስትና የግዴታ ሰነድ (Financial Guarangee Bond) እና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በማናቸውም ስያሜ የገንዘብ ዋስትና የግዴታ ሰነድ የማውጣት ተግባር እንዳይፈጽሙ የተከለከሉ ስለመሆኑ የአክሲዮን ማህበራት ፕሬዚዳንት ወይም ዋና ሥራ አስኪያጅ ስላለው ስልጣን እና በህግ አግባብ ስልጣኑ ተገድቧል ለማለት ስለሚቻልበት ሁኔታ የገንዘብ ዋስትና የግዴታ ሰነድ እንደ የኢንሹራንስ ፖሊሲ የማይቆጠር ስለመሆኑና በፍ/ብሔር ህጉ ስለ ዋስትና ግዴታ በተመለከቱት ድንጋጌዎች የሚገዛ ስለመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ፡ ቁ. 24/2004 አንቀጽ 3,1(3) ቁ. 23/2004 አንቀጽ 1(1) አዋጅ ቁ. 86/86 አንቀጽ 2(4) ,6,4 32-34 አዋጅ ቁ. 87/89 አንቀጽ 2(18) አዋጅ ቁ. 110/90 አንቀጽ 2(2) የፍ/ብ/ህ/ቁ.1725(ሀ),1727,1922(2),(3) አዋጅ ቁ. 648/2001 አንቀጽ 2(20) የንግድ ህግ ቁ.36(1)(2), 121(ሰ), 348(3), 313(1)-(7), 313(10-12), 34(1),1 09(ረ), 323(2-3), 35(1), 26, 120 Download Cassation Decision

 • 45548 family law/ bigamy/ partition of common property

  አንድ ወንድ ሁለት ሚስቶች ጋር ተጋብቶ በሚገኝ ጊዜ የንብረት ክፍፍል ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የፌዴራል የተሻቫለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 102(1),86(1),62(1),63(1) የአማራ ብ/ክ/መ/የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 113(1),97(1),73(1),74(1) Download Cassation Decision

 • 46386 criminal law/ evidence law/ relevance of criminal convictions in civil cases

  በወንጀል ጉዳይ የተሰጠ ውሣኔ በዚያው ጉዳይ በፍትሐብሔር ክርክሩ አግባብነትና ብቃት የሚኖረው በወንጀል ክሱ ተከሳሹ በወንጀል ፍ/ቤቱ ጥፋተኛ ተብሎ የተወሰነ ከሆነና ወደዚህ ድምዳሜ ለመድረስም በወንጀሉ ጉዳይ የተሰሙት ማስረጃዎች በፍ/ብሔሩ ጉዳይም ቀርበው የተሰሙ መሆን ያለባቸው ስለመሆኑ፣ በወንጀል ጉዳይ የቀረበ ማስረጃ ለፍትሐብሔር ጉዳይ አግባብነትና ብቃት የሚኖረው በሁለቱም ጉዳዩች የተሰሙት ማስረጃዎች አንድ አይነት ሲሆኑ ስለመሆኑ፣ በወንጀልና በፍ/ብሔር ጉዳይ የተሰሙት ማስረጃዎች የተለያዩ ከሆነ እና በወንጀል ጉዳይ ክስ የቀረበበት ነጥብም ከፍ/ብሔሩ ክስ ጋር ግንኙነት የሌለው ከሆነ በወንጀል ክስ ተጠያቂ መሆን ሁልጊዜ በፍ/ብሔር ክስ ኃላፊነትን የሚያስከትል ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.2149 የወንጀል ህግ ቁጥር 702(2) Download Cassation Decision

 • 47004 commercial law/ insurance/ performance guarantee bond/

  ለ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና (Performance Guarantee Bond) የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና ውል በባህሪው ከመድን ውል የሚለይና በፍትሐብሔር ሕግ ድንጋጌዎች የሚገዛ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1921, 1719, 1720, 1727, 1719(2), 1920, 1845, 1924(1), 1922(3), 1926 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁ23/2002 አንቀጽ 1(1), የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ 24/2002 አንቀጽ 1(3) የንግድ ህግ ቁ. 654(1), 657(1), 712 አዋጅ ቁ. 57/1989 አዋጅ ቁ 648/2001 አንቀጽ 2/20 አንቀጸ 2(18) አዋጅ ቁ. 110/90 አንቀጽ 2(2) Download Cassation Decision

 • 50590 public pension/ effect of conviction and imprisonment on pension

  የጡረታ አበል ተጠቃሚ የሆነ የመንግስት ሠራተኛ በወንጀል ጉዳይ የተከሰሰና ጥፋተኛ ተብሎ በጽኑ እስራት ቅጣት በተቀጣ ጊዜ የጡረታ መብቱ የሚቋረጥ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 95/1967 አንቀጽ 34 አዋጅ ቁ. 345/1995 አንቀጽ 52(2) እና (3) አዋጅ ቁጥር 209/1955 Download Cassation Decision

 • 50985 agency/ interpretation of contract

  የውክልና ውሎች በጠባቡ ሊተረጐሙ የሚገባ ስለመሆኑ “በስማችን ውል እንዲዋዋል” በሚል በደፈናው የተሰጠ ውክልና ሊተረጐም የሚችልበት አግባብ የፍ/ብ/ህ/ቁ.2181(3), 2205, 2204 Download Cassation Decision

 • 54117 commercial law/ maritime law/ carraige by sea/ liability of carrier

  በባህር ላይ እቃ አመላላሽ በእቃዎች ላይ ለደረሰ ጉዳት በኃላፊነት ሊጠየቅ ስለሚችልበት አግባብ፣ በባህር ላይ እቃን ለማመላለስ የውል ግዴታ የገባ ወገን ከእቃዎቹ መጐዳት ጋር በተያያዘ ስላለበት የኃላፊነት አድማስና ከኃላፊነት ነፃ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የባህር ህግ ቁ.196,138,205,197,180(3) Download Cassation Decision

 • 54889 custom law/ criminal law/ contraband/responsibility of driver of vehicle

  በኃላፊነት ይዞት በሚገኝ ተሽከርካሪ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓትን በመተላለፍ ዕቃን ሲያጓጉዝ የተያዘ ሰው ሊጠየቅ ስለሚችልበት አግባብና ተፈፃሚ ስለሚሆነው የህግ ድንጋጌ አዋጅ ቁ.60/89 አንቀፅ አዋጅ ቁ.368/95 አንቀፅ 79,80(1), 81,64(4)74 ወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.113(2) Download Cassation Decision

 • 54990 civil procedure/jurisdiction/ social court/ Addi Ababa

  የቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤቶች የገንዘብ መጠኑ ከብር 5000 በታች የሆኑ ማናቸውም የፍትሐብሔር ክርክር ለመመልከት ስልጣን አላቸው ተብሎ በአዋጅ ቁ.361/95 አንቀፅ 50(1) የተመለከተው ድንጋጌ ተግባራዊ መሆን ያለበት የቀረበው ጉዳይ ልዩ ባህሪ እየታየ በጉዳዩ ላይ የሚነሣው የህግ ጥያቄ ውስብስብነት በመመዘኛነት (በመለኪያነት) ተይዞ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.361/95 አንቀፅ 50(1) አዋጅ ቁ.25/88 አንቀፅ 5(1), 6 አዋጅ ቁ.416/96 አንቀፅ 41 Download Cassation Decision

 • 55273civil procedure/jurisdiction/ federal cassation bench/ cassation on cassation/ fact-law/ constitution

  የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤቶች ሰበር ችሎት በክልል ጉዳዮች ላይ የሰጡትንና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበትን ውሣኔ ለማረም ስልጣን ያለው ስለመሆኑ የሰበር ስርዓት በባህሪው ከይግባኝ ሥርዓት የተለየ ስለመሆኑና በሰበር ደረጃ ተጨማሪ ምስክሮችንና ማስረጃዎችን አስቀርቦ መስማትና የፍሬ ነገር ጉዳዮችን ተቀብሎ ማስተናገድ አግባብነት የሌለውና ህገ-ወጥ ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ህገመንግስት አንቀፅ 80(3)ለ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.343(1) Download Cassation Decision

 • 57186 property law/ immovable property/ certificate of ownership/ administrative law/ judicial review/ cancellation of certifocate

  የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ጋር በተያያዘ የሚመለከተው የአስተዳዳር አካል አንዴ የሰጠውን የባለሀብትነት ማረጋገጫ ደብተር (የምስክር ወረቀት) በሌላ ጊዜ የሰረዘው እንደሆነ ይኼው ተግባር በፍ/ቤት ክስ ሊቀርብበት የማይችል ወይም የማይስተናገድ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የአስተዳደር አካል ህጋዊ ምክንያት ሣይኖረው በአንድ ወቅት የሰጠውን የባለቤትነት ደብተር ከሰረዘ ይኸው አካሄድ ህጋዊ አይደለም የሚለው ወገን በፍ/ቤት መብቱን ለማስከበር ክስ ሊያቀርብና ፍ/ቤቱም ጉዳዩን በማስረጃ አጣርቶ ውሣኔ ሊሰጥ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1195,1196 Download Cassation Decision

 • 57280 contract law/ unilateral cacellation of contract/

  ከውል መፈፀም ጋር በተገናኘ ተዋዋይ ወገኖች ውልን በተናጠል ለመሰረዝ (unilateral cancellation of contract) ስለሚችሉበት አግባብ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1771, 1774, 1757, 1787, 1785, 1786, 1789, 1788 Download Cassation Decision

 • 58119 civil procedure/ sharia courts/ res judicata/ constitution

  በተከራካሪዎች ፈቃድ ላይ በተመሰረተ ሁኔታ በህግ ስልጣን ባላቸው የሸሪዓ ፍ/ቤቶች ክርክር ተካሂዶ በፍርድ ያለቀን ጉዳይ በተመለከተ እንደ አዲስ በመደበኛ ፍ/ቤት ክስ ሊቀርብ የማይችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.188/92 አንቀፅ 4(2), 5(4) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 78(5), 34(5) Download Cassation Decision

 • 59504 property law/ joint ownership/ pre-emtive right/

  በአንድ ንብረት ላይ የጋራ መብት ካላቸው ሰዎች ጋር በተገናኘ የቅድሚያ ግዢ መብት ጥያቄ ሊስተናገድ የሚችልበት አግባብ፣ የጋራ ባለሃብቶች ከሆኑ ሰዎች መካከል አንዱ ካለበት ያልተከፈለ ዕዳ የተነሣ ንብረቱ የሚሸጥ ቢሆን ሌሎቹ የጋራ ባለሃብቶች ሊሸጥ ያለውን ድርሻ አስገድዶ ለመግዛት የቅድሚያ መብት ያላቸው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1289(1)(2), 1290, 1261, 1388, 1406, 1281 Download Cassation Decision

 • 60217 criminal law/ constitution/ double jeopardy/

  በአንድ ጉዳይ ድጋሚ ክስ ወይም ድጋሚ ቅጣት (principle of double jeopardy) ክልክል ስለመሆኑ የተደነገገው መርህ ሊተረጐም ስለሚችልበት አግባብ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 23 የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.42(1)(ሀ) Download Cassation Decision

 • 60345 criminal law/

  ማዕድናትና የከበሩ ድንጋዮችን ከማዘዋወርና ለሽያጭ ከማቅረብ ጋር በተገናኘ ስለሚኖር የወንጀል ኃላፊነት፣ የወ/ህ/ቁ 346፣347፣378 አዋጅ ቁ. 52/85 አንቀጽ 53(1), (5), 26(4) ደንብ ቁ. 182/80/ አንቀጽ 30(1)(ሀ), 3(ለ) እና 4(ሐ), 38-40 አዋጅ ቁ. 591/2000 አንቀጽ 26(1)(ለ) Download Cassation Decision

 • 60385 commercial law/ carriage of goods/ liability of consignee

  እቃን ከማጓጓዝ ጋር በተገናኘ ከእቃው አደገኛ (ጉዳት አድራሽ) ባህሪ የተነሣ ዕቃውን በሚያጓጉዘው ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰ ጉዳት የእቃው ባለቤት (ባለንብረት) የዕቃውን በአግባቡና በጥንቃቄ አለመታሸግ (አለመያዝ) ጋር በተገናኘ በኃላፊነት ሊጠየቅ ስለመቻሉ የንግድ ህግ ቁ.578(2) Download Cassation Decision

 • 60489 labor law dispute/ manager/ dispute between manager and owner

  ከሥራ ክርክር ጋር በተያያዘ አሰሪና የሥራ መሪ የሆነ ሰው መካከል የሚፈጠርን አለመግባባት ለመፍታት ተፈፃሚነት ያለው ደንብ (መመሪያ) በስምምነት የተዘጋጀ እንደሆነ ይሄው ደንብ ተፈፃሚ ሊደረግ የሚገባ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 60518 criminal law/ abuse of power

  አንድ ሰው በወንጀል ህጉ አንቀጽ 407 መሰረት በስልጣን ያለአግባብ መገልገል ወንጀል ጥፋተኛ ተደርጐ ቅጣት ሊጣልበት የሚችልበት አግባብ፣ የመ/ህ/ቁ 407(1)(ሀ) Download Cassation Decision

 • 60542 criminal law/ abuse of power/ participation in crime

  የመንግስት ሰራተኛ ሳይሆኑ ነገር ግን ከመንግስት ሰራተኞች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር በህዝብና በመንግስት ጥቅም ላይ ጉዳት ማድረስ በሙስና ወንጀል ሊያስጠይቅ የሚችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.434/97 አንቀፅ 7 የወ/ህ/ቁ.407(1)(ሀ),33 Download Cassation Decision

 • 61331 contract law/ evidence law/ presumption of payment/ telephone bill

  የፍ/ብ/ህ/ቁ 2024(ረ) ድንጋጌ ከስልክ አገልግሎት ክፍያ ጋር በተያያዘ ተፈፃሚነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2024(ረ), 2023, 2022 Download Cassation Decision

 • 61357 family law/ partition of common property

  የጋብቻ ፍቺን በተመለከተ በፍ/ቤት የተሰጠ ውሣኔ ከሌለ በስተቀር የባልና ሚስት የጋራ ንብረትን አስመልክቶ የፍቺ ውጤት የሆነውን የክፍፍል ጥያቄ በፍ/ቤት ማቅረብ አይቻልም ለማለት የሚያስችል የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.213/92 አንቀፅ 76 Download Cassation Decision

 • 61421 contract law/donation/ donation mortis causa/ testamentary disposition/ form of donation

  ስጦታ አድራጊው ሞት በኋላ ተፈፃሚ የሚሆን የስጦታ ውልን በተመለከተ ስለ ኑዛዜ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት ያላቸው ስለመሆኑ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ የሚደረግ ስጦታ በህጉ በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ አስራርን በተከተለ መልኩ መደረግ ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.881, 2428, 2443, 2436 Download Cassation Decision

 • 61480 civil procedure/ appeal/ regional cassation/ final/ Tigray region

  በሥር ፍ/ቤት ቀርቦ የተሰጠ ውሣኔ ለይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ቀርቦ በተወሰነ መልኩ ተሻሽሎ መወሰኑ በጉዳዩ ቅር የተሰኘ ወገን ውሣኔውን አስመልክቶ ለሰበር ችሎት የሚያቀርበው አቤቱታ የመጨረሻ ፍርድ ያልተሰጠበት ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ የትግራይ ብ/ክ/መ/ አዋጅ ቁ.93/97 አንቀፅ 30(2)(ሀ), አዋጅ ቁ.49/94 አንቀፅ 16(ለ) እና 17 Download Cassation Decision

 • 61549 labor law dispute/ income tax/ severance payment

  ከሥራ ክርክር ጋር በተያያዘ ለሠራተኛ የሚከፈል የሥራ ስንብትና ካሣ ክፍያ ላይ የገቢ ግብር ሊቀነስ የሚገባ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.286/94 አንቀፅ 13, 10(2), 2(10) ደንብ ቁ.78/94 Download Cassation Decision

 • 61717 public service/ occupational accident/ death/ compensation to family

  በፌዴራል መንግስት ሠራተኞች ህግ መሠረት አንድን ጉዳት በሥራ ላይ የደረሰ ጉዳት ነው ለማለት የሚቻልበት አግባብ (ሁኔታ) እና በጉዳቱ ሞት በተከሰተ ጊዜ የጉዳት ካሣ ለሟች ቤተሰብ የሚሰጥበት አግባብ፣ አዋጅ ቁ. 515/99 አንቀጽ 47(2)(ሐ) አዋጅ ቁ. 262/94 አንቀጽ 46(2)(5)(ለ) Download Cassation Decision

 • 61808 contract law/ invalidation of contract/ interest of third party

  ተዋዋይ ወገኖች ያደረጉት ውል ምንም እንኳን የተፈፀመ ቢሆንም ውሉ የ3ኛ ወገኖችን መብትና ጥቅም የሚነካ ከሆነ ይህንኑ በመግለፅ ውሉ ፈራሽ እንዲሆን ይወሰን ዘንድ ለፍ/ቤት አቤቱታ ለማቅረብ የሚቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1806 Download Cassation Decision

 • 61913 contract law/ sale of immovable property/ transfer of title

  ከማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ጋር በተገናኘ ሻጭ የሆነ ወገን የሸጠውን ነገር ባለሃብትነት ለገዢው የማስተላለፍ ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2875, 2281,1808(2) Download Cassation Decision

 • 62162 contract law/ loan/ rate of interest

  አንድ ማህበር ለሰጠው ብድር የሚያገኘውን የወለድ መጠን ከመደበኛው የባንክ ማበደሪያ ወለድ መጠን ከፍ አድርጐ ለማበደር ስለመቻሉና ይኸውም ተፈፃሚ መደረግ ያለበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.147/91 አንቀፅ 34(2) አዋጅ ቁ.402/96 አንቀፅ 5 የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1731,1678 የትግራይ ብ/ክ/መንግስት አዋጅ ቁ. 145/2000 Download Cassation Decision

 • 62452 civil procedure/ death of parties to a suit/ right of heirs

  በተከሳሽ ወይም ከሳሽ ሞት ምክንያት በፍ/ቤት በመካሄድ ላይ የነበረ ክርክር በተቋረጠ ጊዜ ክርክሩ በወራሾች አማካኝነት ሊቀጥል የሚችልበት ሁኔታና በህጉ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተፈፃሚ ሊሆን የሚችልበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.49(1), 55(2) Download Cassation Decision

 • 62504 criminal law/ criminal procedure/ exhibits/ suit against the police

  በኤግዚቢትነት በፖሊስ ከተያዙ ንብረቶች ጋር በተገናኘ የንብረቶቹ ባለቤት ነኝ የሚል ወገን ንብረቱ ይመለስለት ዘንድ በፖሊስ ጽ/ቤቱ ላይ የሚያቀርበው ክስ በተገቢው ማስረጃ ተጣርቶ እልባት ሊሰጠው የሚገባ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 63014 criminal law/ cassation procedure/ fact-law/ power of cassation bench

  የሰበር ችሎት ፍሬ ጉዳይ የማጣራት ማስረጃ የመመዘንና የመመርመር ስልጣን የሌለው ቢሆንም በሥር ፍ/ቤቶች ወይም የዳኝነት ስልጣን የተሰጣቸው ሌሎች አካላት መሰረታዊ የሆነ የዳኝነት አካሄድ ስርዓትን ሳይከተሉ፣ መመስረት የሚገባቸውን ጭብጥ ሳይመሰርቱና ጭብጡን የማስረዳት ግዴታ (Buden of proof) ያለበት ተከራካሪ ወገን የማስረዳት ግዴታውን በአግባቡ እንዲወጣ ሳያደርጉና መጣራት ያለበትን (የሚገባውን) ፍሬ ጉዳይ ሳያጣሩ የሰጡትን ውሣኔ በሰበር አይቶ ለማረም ስልጣን ያለው ስለመሆኑ፣ በወ/ህ/አ. 419 Download Cassation Decision

 • 63200 commercial law/ share company/ manager/ restitution/

  የአክሲዮን ማህበር ሥራ አስኪያጅ ያለአግባብ ከስልጣኔ (ከስራ አስኪያጅነቴ) ተሽሬያለሁ በሚል በሚያቀርበው አቤቱታ መነሻነት ፍ/ቤት ግለሰቡን ወደ ስራ አስኪያጅነቱ እንዲመለስ ሊወሰን የሚችል ስለመሆኑ፣ የንግድ ህግ ቁ. 525-537 Download Cassation Decision

 • 63231 extracontractual liability law/ electric accident/ liability of electric power supplier

  በኤሌክትሪክ መስመር ምክንያት ከደረሰ የቃጠሎ አደጋ ጋር በተገናኘ ፍ/ቤቶች የጉዳት ኃላፊነትንና ካሣን ለመወሰን፣ ጉዳቱ በምን ምክንያትና ሁኔታ እንደደረሰ፣ መብራት ሀይል ጥፋት ሳይኖር ኃላፊ ሊያደርጉ የሚችሉ አደገኛ ሁኔታዎችን ስለመፍጠሩ ወይም በሥራው ሊያደርግ የሚገባውን ጥንቃቄ አለማድረጉ ወዘተ ተገቢነት ባላቸው ማስረጃዎች ማንጠር ያለባቸው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2028,2066,2069,2027 በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.246,247,259 Download Cassation Decision

 • 63454 commercial law/ administrative law/ trade mark/ trade name/ appeal

  ከንግድ ስም ወይም ምልክት ምዝገባ ጉዳይ ጋር በተገናኘ በሚመለከተው ተቋም በተሠጠ ውሳኔ ቅሬታ ያለው ወገን ያለው መብት በይግባኝ ሥርዓት የማሳረም ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 501/98/ አንቀጽ 6,17,36,49 Download Cassation Decision

 • 64014 property law/ immovable property/ certificate of ownership/ administrative law/ judicial review/ cancellation of certifocate

  የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትን በማረጋገጥ ከሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ካርታ ወይም ደብተር) ጋር በተያያዘ በአንድ ወቅት በሚመለከተው የአስተዳደር አካል የተሰጠን የምስክር ወረቀት መሰረት በማድረግ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ በሌላ ጊዜ ሰነዱ በአስተዳደር አካሉ መምከን የተሰጠውን ፍርድ በአንድ ጊዜና ሙሉ ለሙሉ ዋጋ የሚያሳጣ ሳይሆን ካርታው በመምከኑ የተጐዳው ወገን የአስተዳደሩን አካል እርምጃ (ውሳኔ) ክርክር ሊያቀርብበት የሚችልና ፍ/ቤቶችም የእርምጃውን አግባብነትና ህጋዊነት ሊያጣሩት የሚችሉት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1195, 1196, 1206 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 40(1)(2) Download Cassation Decision

 • 64115 custom law/ criminal law/ acquittal/ contraband/ confisication

  በጉምሩክ ወንጀል የተከሰሰ ሰው በነፃ የተለቀቀ ቢሆንም ወንጀሉ የተፈፀመበት እቃ ወይም ማጓጓዣየሚወረሰው የጉምሩክ ህግን የመተላለፍ ድርጊት ስለመፈፀሙ ፍርድ ቤቱን የሚያጠግብ ማስረጃ ሲቀርብ ስለመሆኑና ማስረጃው አጥጋቢ ካልሆነ ብቻ ፍ/ቤት እቃውን (ማጓጓዣውን) እንዳይወረስ በማድረግ ተገቢውን ቀረጥና ታክስ እንዲከፈል ሊያዝ የሚገባው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.622/2001 አንቀፅ 104(3)(ሀ), 104(3)(ለ) Download Cassation Decision

 • 64129 civil procedure/execution of judgment/ appeal/ remand

  ፍርድን ከማስፈፀም ጋር በተያያዘ በተጀመረ የአፈፃፀም መዝገብ የተሰጠ ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ ቀርቦበት በበላይ ፍ/ቤት ትዕዛዙ ከተለወጠ የአፈፃፀም ሂደቱ መቀጠል ያለበት አፈፃፀሙን በጀመረው የበታች ፍ/ቤት ደረጃ መሆን ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 371-385 Download Cassation Decision

 • 64371 law of succession/ joint ownership of estate/ agreement of heirs

  የወራሾች የጋራ ሀብት የሆነን ንብረት ለመሸጥና ለማስተላለፍ ወይም በዋስትና ለማስያዝ ወይም የተመደበበትን አገልግሎት ለመለወጥ የጋራ ባለንብረቶቹ ሁሉ ስምምነት አስፈላጊ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1262, 1060(1) Download Cassation Decision

 • 64397 contract law/ loan/ written evidence

  የፍ/ብ/ህ/ቁ 2472 ከብድር ውጪ በሆነ ግንኙነት ከተከፈለ ገንዘብ ጋር በተያያዘ ተፈፃሚ የሚሆንበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2472 Download Cassation Decision

 • 64612 criminal law/ criminal procedure/ power of anti corruption commission/ forgery/

  ከመንግስት ሰራተኞች ውጪ በሆኑ ሰዎች የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎችን በተመለከተ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ክስ ሊያቀርብ ስለመቻሉ ኮሚሽኑ የወንጀል ክስ ለመመስረት ስልጣን ከተሰጠው ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ወይም ወንጀል ፈፅሟል ተብሎ የተከሰሰ ሰው ከሙስና ወንጀሉ ጋር አንድ ላይ መከሰስ ያለበትን የወንጀል ድርጊት አንድ ላይ (አጣምሮ) ሊያቀርብ ስለመቻሉ የወ/ህ/ቁ 379(2), 375, 404(4)(3) አዋጅ ቁ. 434/97 አንቀፅ 58 አዋጅ ቁ.236/93 አንቀፅ የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ.110 Download Cassation Decision

 • 64845 civil procedure/jurisdiction/ concurrent power of regional court/ cassation/ constitution

  የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ባለው የውክልና ስልጣኑ በዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠን ውሣኔ የለወጠው ከሆነ ጉዳዩ ለፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ከመቅረቡ በፊት ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት መቅረብ ያለበት ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 80(3)(ሀ), (2)(4) አዋጅ ቁ.322/95 አዋጅ ቁ.25/88 አንቀፅ 9(2), 5(2) Download Cassation Decision

 • 64887 contract law/ bailement/ evidence law/ donation

  ስለ አስፈላጊ አደራ እና የማስረጃ አይነት የፍ/ብ/ህ/ቁ.2782,2800,2802,2472 ስጦታ አድራጊው ሞት በኋላ ተፈፃሚ የሚሆን የስጦታ ውልን በተመለከተ ስለ ኑዛዜ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት ያላቸው ስለመሆኑ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ የሚደረግ ስጦታ በህጉ በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ Download Cassation Decision

 • 65041 custom law/ criminal law/

  ከጉምሩክ ባለስልጣን ሹም ፈቃድ ሳያገኝ በመተላለፍ ላይ ያሉ ወይም የጉምሩክ ወደብ በደረሱ ወቅት የእቃ መያዣ ላይ የተደረገን ማሸጊያ መፍታት በወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ በጉምሩክ ወደብ በምርመራ ላይ ካሉ ዕቃዎች ለሳምፕልነት በሚል ወስዶ አለመመለስ በወንጀል የሚያስጠይቅ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.622/2001 አንቀፅ 100, 95(ሀ) Download Cassation Decision

 • 65140 property law/ immovable property/ condominium house/ limitation on ownership

  የኮንዶሚኒየም ቤት እጣ የደረሰው ሰው እዳውን ከፍሎ ያጠናቀቀ ቢሆን እንኳን እጣው ከደረሰው ቀን አንስቶ እስከ አምስት ዓመት ድረስ ለሶስተኛ ወገን በሽያጭ ወይም በስጦታ ለማስተላለፍ የማይችል ስለመሆኑና ከዚህ ጊዜ በፊት ቤቱን አስመልክቶ የሚደረግ ውል ፈራሽ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 370/95 አንቀጽ 14(2) የአ.አ አስተዳዳር አዋጅ ቁ 19/97 አንቀጽ 21 የፍ/ብ/ህ/ቁ 1678,1808(2) Download Cassation Decision

 • 65325criminal law

  በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ከአንድ አይነት የወንጀል ድርጊት ጋር በተያያዘ በሁለት የተለያዩ የወንጀል ክሶች የተከሰሰ ተጠርጣሪ በአንዱ የወንጀል ክስ የተመለከቱ ፍሬ ነገሮች መከሰት ጋር በተገናኘ ጥፋተኛ ለማለት ያልተቻለ እንደሆነ በሌላኛው ክስ ጥፋተኛ ለማድረግ የማይቻል ስለመሆኑ የወ/ህ/ቁ 407(ሐ), 670, 677 የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 141, 142, 149(1) Download Cassation Decision

 • 65361 tax law/ rental income/ withholding

  ተከራይ የሆነ ወገን ለአከራይ ከሚከፍለው የኪራይ ገንዘብ ለመንግስት የሚከፈለውን ግብር ሳይቀንስ ለአከራዩ እንዲከፈል ለማስገደድ የማይቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1716, 1718, 1711 አዋጅ 286/94 አንቀጽ 56, 91, 83 Download Cassation Decision

 • 65395 extracontractual liability law/ environment/ Ethiopian electric corporation

  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ማንኛውንም ኤሌክትሪክ የማመንጨት፣ የማስተላለፍና የማከፋፈል ብሎም የመሸጥ ስራዎች በሚያከናውንበት ወቅት ሁሉ የአካባቢ ጥበቃን በሚመለከት የወጡ ህግጋትን በማክበር መሆን ያለበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.86/89 አንቀፅ 13(1) ደንብ ቁ.49/91 አንቀፅ 23(2), 35 Download Cassation Decision

 • 65566 criminal law/ constitution/ members of armed forces/ public defence

  በወንጀል የተከሰሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በግላቸው ጠበቃ ለማቆም የማይችሉ በሆነ ጊዜ በመንግስት ወጪ የጠበቃ ድጋፍና እርዳታ ሊያገኙ የሚችሉበት አግባብ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 20(5) አዋጅ ቁ.27/88 አንቀፅ 35 አዋጅ ቁ.123/90 አዋጅ ቁ.27/885 Download Cassation Decision

 • 65708 family law/ common property/ land reclamation/ compensation

  ከባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ጋር በተገናኘ በአንደኛው ተጋቢ በውርስ የተገኙ ንብረቶች (ሀብቶች) ለልማት በሚል በመፍረሳቸው የተገኘ የካሳ ክፍያ በግብይት እንደተገኘ ተቆጥሮ የግል ስለመሆኑ በፍ/ቤት አልተረጋገጠም በሚል እንደ የጋራ ሀብት ሊቆጠር የማይችል ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.213/92 አንቀፅ 58, 57 Download Cassation Decision

 • 65814 civil procedure/execution of judgment/ contempt of court

  ከፍርድ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ በፍ/ቤት የተሰጠን ትዕዛዝ አለማክበር ስለሚያስከትለው ውጤት፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 156, 409(1) የፍ/ብ/ህ/ቁ.400 Download Cassation Decision

 • 66350 tax law/ tax appeal/ time to appeal

  ከታክስ/ግብር አከፋፈል ጋር በተገናኘ ግብር ከፋዩ ያለውን ቅሬታ ለግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በይግባኝ ለማቅረብ የተፈቀደው ጊዜና ስሌቱን ተግባራዊ ስለማድረግ አዋጅ ቁ.286/94 አንቀፅ 107(2), 108 Download Cassation Decision

 • 66474 tax law/ income tax/ civil societies/ tsx exemptions

  የበጐ አድራጐት ሥራን የሚሰሩ ድርጅቶች ከቦታ ኪራይ እና የቤት ግብር ነፃ ሊሆኑ የሚችሉበት አግባብ አዋጅ ቁ.80/68 አንቀፅ 14(ለ) የህግ ክፍል ማስታወቂያ ቁ.36/68 አንቀጽ 8 Download Cassation Decision

 • 66856 criminal law/ attempt/ aggravated robbery

  አንድ የወንጀል አፈፃፀም ተግባር ሙከራ ደረጃ ላይ ደርሷል (Attempt) ሊባል የሚችልበት አግባብ የወ/ህ/አ 32(1)(ሀ),27(1),671(1) Download Cassation Decision

 • 66935 contract law/ non performance of contract/ cancellation of contract

  የፀና የውል ግዴታ የገባ ሰው ውሉ በፍርድ እንዲሰረዝ ለመጠየቅ የሚችለው ሌላኛው ተዋዋይ ወገን ግዴታውን በአግባቡ ያልፈፀመ (ያልተወጣ) እንደሆነ ወይም የፈፀመው ፍፁም ባልሆነ አኳኋን ከሆነ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1784 1785(2),(1) Download Cassation Decision

 • 66943 criminal law/ confisication

  በፍ/ቤት የወንጀል ክስ ቀርቦ የጥፋተኝት ውሣኔ በተሰጠበት የወንጀል ድርጊት ወንጀለኛው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ያገኘው ንብረት ለመንግስት እንዲወረስ መደረግ ያለበት ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ 98(1)(2), Download Cassation Decision

 • 66957 civil procedure/jurisdiction/ constitution/ religious dispute/ secularism

  ሃይማኖታዊ ከሆኑ አለመግባባቶች ጋር በተያያዘ ፍ/ቤቶች የአምልኮት ሥርዓትን ሆነ ሃይማኖታዊ ህገ-ደንቦችን በመተርጐም ውሣኔ ለመስጠት የማይችሉ ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 11(1)(3), 37(1) Download Cassation Decision

 • 67011 property law/ immovable property/ certificate of ownership/ administrative law/ judicial review/ cancellation of certificate

  የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነትን አስመልክቶ የሚሰጥ የባለቤትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ተገቢውን ስርዓት እና ደንብ በመከተል የተሰጠ መሆን ያለበት ስለመሆኑና በተመሳሳይም በአንድ ወቅት የተሰጠን የባለቤትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለመሰረዝ አግባብነት ያላቸውን ስርዓቶች በመከተል መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1195-1198 Download Cassation Decision

 • 67127 civil procedure/ third party intervention

  በአንድ ጉዳይ በከሳሽነትና በተከሳሽነት በተሰየሙ ወገኖች መካከል በተካሄደ ክርክር የተሰጠ ፍርድ ጋር በተያያዘ መብት ወይም ጥቅም አለኝ የሚል ወገን ወይም እርሱ ባልተካፈለበት ሁኔታ በመካሄድ ላይ ባለ ክርክር መብቱ/ጥቅሙ የሚጐዳበት ሰው በክርክሩ በመግባት መብቱን በህግ አግባብ ሊያስከብር ስለሚችልበት ሁኔታ፣ ከላይ በተመለከተውና ባልተካፈልኩበት ክርክር የተሰጠ ፍርድ ሥርዓትን ባለመከተል የተሰጠ ነው በሚል ምክንያት ብቻ ፍርዱ ዋጋ እንዲያጣ ወይም አንዴ የተሰጠ ፍርድን ወደ ጐን በመተው በሌላ ጊዜ በሚሰጥ አዲስ ፍርድ እንዲቀየር ለማድረግ የሚያስችል የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህቁ. 41, 358, 212 Download Cassation Decision

 • 67201 labor law dispute/occupational accident/ responsibility of worker

  ሠራተኛ በሥራ ቦታና በሥራ ወቅት ሆን ብሎ በራሱ ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት አሰሪው ኃላፊነት የማይኖርበት ስለመሆኑ የአደጋ መከላከያ ደንቦችን በመጣስ ወይም አካሉን ወይም አእምሮውን በሚገባ ለመቆጣጠር በማይችልበት ሁኔታ በአደንዛዥ ዕፅ አስክሮ በሥራ ላይ በመገኘቱ በሠራተኛ ላይ የደረሰ ጉዳት ሆን ተብሎ እንዳደረሰ የሚቆጠርና አሠሪው ጉዳቱን ለመካስ የማይገደድ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 96(ሀ)(ለ), 96(1) Download Cassation Decision

 • 67225 extracontractual liability law/ damage/ mode of payment/ lump sum payment

  ከውል ውጪ በሆነ ግንኙነት ከደረሰ ጉዳት ጋር በተያያዘ ለተጐጂው የሚከፈል የጉዳት ካሣ አከፋፈል በአንድ ጊዜ እንዲከፈል ሊወሰን የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2154, 2095(2) Download Cassation Decision

 • 67376 agency/ unauthorized agency/ period of limitation

  ወካይ የሆነ ወገን በተወካይ አማካኝነት የተደረገን ህገ ወጥ ውል እንዲፈርስ በሚል የሚያቀርበው አቤቱታ በአሥር አመት ይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 2187(1)(2),2198,1810,1808(1),1845 Download Cassation Decision

 • 67382 labor law dispute/ termination of contract of employment/ payments/ lien right of employer

  ከአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ጋር በተያያዘ ሰራተኛው ከሥራ ሲሰናበት ከአሰሪው የተረከበውን ንብረት አላስረከበም በሚል ሰራተኛው ሊከፈለው ከሚገባው ክፍያ ቀንሶ ለማስቀረት የሚቻለው በሰራተኛው በኩል ዕዳ ስለመኖሩ መተማመን ላይ ሲደረስ ስለመሆኑ ሰራተኛው ከተረከበው ንብረት አለመመለስ ጋር በተገናኘ ዕዳ ስለመኖሩ በግራ ቀኙ መካከል ክርክር (አለመግባባት) ያለ እንደሆነ አሰሪው ጉዳዩን በፍ/ቤት አቅርቦ መብቱን ማስከበር ያለበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 36-38, 59(1), 53(2)(1) Download Cassation Decision

 • 67408 criminal law/ breach of trust

  አንድ ወኪል ከወካዩ በውክልና ስልጣኑ የወሰደውን ንብረት ለመመለስ ፈቃደኛ ያለመሆኑ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 676(2) ድንጋጌ መሰረት ሊያስጠይቀው ስለመቻሉ የወ/ህ/ቁ 676(2) Download Cassation Decision

 • 67411 criminal law/ possession of unexplained property

  ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ ይዞ በመገኘት ወንጀል አንድ ሰው ተጠያቂ የሚሆነው የምዝገባ ሥርዓት የተዘረጋ እንደሆነ ብቻ ነው ለማለት የሚያስችል የህግ አግባብ ስላለመኖሩ የወ/ህ/ቁ.419 Download Cassation Decision

 • 67533 labor law dispute / definite period/ indefinite period

  ከሥራ ክርክር ጋር በተያያዘ የሠራተኛን ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ የቅጥር ሁኔታ ለመወሰን የተቋሙን ድርጅታዊ አቋም ብቻ መሰረት በማድረግ የሚሰጥ ውሣኔ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 9,10 Download Cassation Decision

 • 67631 property law/ expropriation/ government houses/ wrongful restitution of property

  ከአዋጅ ውጪ የተወሰደ ንብረት ነው በሚል ንብረትን ከመንግስት አካል ያስመለሰ ወገን የንብረቱ አመላለስ አግባብነት የሌለው ሆኖ በመገኘቱ ንብረቱ ወደ መንግስት እንዲመለስ ሲወሰን ንብረቱን ያለአግባብ በእጁ ያቆየው ወገን ንብረቱ ያስገኝ የነበረውን ገቢ ወይም የታጣ ገቢ ጭምር የመክፈል ግዴታ የሚኖርበት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ 572/2000 አንቀጽ 6 Download Cassation Decision

 • 67691 property law/ contract law/ possessory action/ contract of rent

  አከራይ የሆነ ወገን ተከራይ ለሆነው ወገን ቤት እንዲለቀቅ በሚል የሚፅፈው ማስጠንቀቂያ ከአከራይና ተከራይ ውልና ግንኙነት አንፃር የሚታይ እንጂ እንደ ሁከት ተግባር የማይቆጠር ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1149(1), 2966(1) Download Cassation Decision

 • 67777 criminal law/ refusal to aid justice/

  በወንጀል ህግ ቁጥር 448 ስር አንድ ሰው ለፍትህ እርዳታ ለመስጠት እንቢተኛ ሆኗል በሚል ወዲያውኑ ጉዳዩን በያዘው ፍ/ቤት ለመቅጣት ስለሚቻልበት አግባብ የወ/ህ/ቁ 448(1), (3), 23(2), 58 Download Cassation Decision

 • 67874 criminal law/ criminal procedure/ bail/ power of court/ rejection of bail application

  ፍርድ ቤቶች በወንጀል ጉዳይ የዋስትና ጥያቄን ላለመቀበል ሥልጣን (discretion) ያላቸው ስለመሆኑ፣ ዋስትናን ለመከልከል ፍ/ቤቶች የሚሰጡት ምክንያት በቂና ህጋዊ ናቸው ሊባሉ የሚችሉበት አግባብ፣ የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ.67 Download Cassation Decision

 • 67924 family law/ divorce/ long separation

  በጋብቻ ተሳስረው የነበሩ ሰዎች ግንኙነታቸው እስካልተቋረጠ ድረስ ለረጅም ጊዜ ተለያይተው በመኖራቸው ብቻ በመካከላቸው ያለው የትዳር ግንኙነት ፈርሷል ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 67996 labor law dispute/ civil society organizations/ scope of labor proclamation

  ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች (መያዶች) በስራቸው የሚቀጥሯቸውን ሠራተኞች በተመለከተ አግባብነት ባላቸው የኢትዮጵያ ሕጎች የሚዳኙ መሆኑን በመግለጽ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ያደረጉ እንደሆነ በድርጅቶቹ እና በሰራተኞቻቸው መካከል የሚነሱ አለመግባባቶች በስምምነቱ መሠረት እልባት ሊያገኝ የሚገባ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 3(3) Download Cassation Decision

 • 68138 labor law dispute/ occupational accident/ place and time of accident/ liability of the employer

  በሥራ ላይ ከሚደረስ አደጋ ጋር በተያያዘ አደጋው የደረሰው ከሥራ ሰዓትና ከሥራ ቦታ ውጪ ከሥራው ጋር ግንኙነት በሌለው አጋጣሚ እና ከአሰሪው ትዕዛዝ ሳይኖር እንደሆነ አሰሪው ለደረሰው ጉዳት ኃላፊነት የማይኖርበት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 95, 96, 97 Download Cassation Decision

 • 68190 family law/ commercial law/ common debt of spouses/

  በባል ወይም በሚስት ለጋራ መተዳደሪያቸው በሚል ከሚካሄድ የንግድ ሥራ ማስኬጃ ጋር በተያያዘ የተገባ ዕዳ የተጋቢዎች የጋራ እዳ እንደሆነ የሚቆጠር ስለመሆኑ የንግድ ህግ ቁ.19 የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.213/92, አንቀፅ 70 Download Cassation Decision

 • 68369 intellectual property/ copyright/ conditions for violation of copyright

  ከቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጋር በተያያዘ የመብቱ ተጠቃሚዎችና የመብቱ አድማስ የቅጅ መብት እንዲከበር ለመጠየቅ መሟላት ስለሚገባቸው ነገሮችና መብቱ እንደተጣሰ የሚቆጠርበት አግባብ አዋጅ ቁ. 410/96 አንቀፅ 7, 9-19, 2(6) Download Cassation Decision

 • 68422 tax law/criminal law/ VAT/ sentencing

  የተጨማሪ እሴት ታክስን ተግባራዊ ለማድረግ በወጣው አዋጅ ቁ.285/94 አንቀጽ 49 መሰረት በወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ተከሳሽ ላይ ቅጣት ሊጣል ስለሚችልበት ሁኔታ፣ አዋጅ ቁ.285/94 አንቀጽ 49,47,50(2) የወ/ህ/አ 2(2) Download Cassation Decision

 • 68498 agency/ manager/ enterprise

  አንድን ተቋም ወክሎ ውል ለመዋዋል በህግ ስልጣን የተሰጠው ሥራ አስኪያጅ ስልጣኑን ለሌላ ሰው በህግ ተቀባይነት ባለው ሁኔታ አስተላልፎ ውል የተደረገ እንደሆነ ተቋሙ በሥራ አስኪያጁ በራሱ በመፈረም ውል አላደረገም በሚል ምክንያት ብቻ በውሉ አንገደድም ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1731 2274 2214(1 2215(3),2180) Download Cassation Decision

 • 68573 civil procedure/jurisdiction/ cassation procedure

  የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በአንድ ወቅት የሰጠውን የህግ ትርጉም በሌላ ጊዜ በተመሳሳይ ጭብጥ ላይ የተለየ የህግ ትርጉምና የተለየ አቋም መያዙ በቀደመው የህግ ትርጉም መሠረት ዳኝነት የተሰጠበት ጉዳይን እንደገና እንደ አዲስ እንዲስተናገድ ለማድረግ የማያስችል ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 68613 extracontractual liability law/ plurality of tortfeasors/ joint and several liability

  ብዙ ሰዎች በአንድ ጉዳይ ለደረሰ ጉዳት ካሣን እንዲከፍሉ የተገደዱ እንደሆነ እያንዳንዳቸው ለደረሰው አጠቃላይ ጉዳት ኃላፊ የሚሆኑ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2155(1) Download Cassation Decision

 • 68708 banking law/ foreclosure/ power of court

  በፎርክሎዠር ህግ መሰረት የሚከናወን ሐራጅ በፍ/ቤት የሚሰረዝበት አግባብ ስላለመኖሩና ሐራጁ በህግ አግባብ ያለመከናወኑ በባንኩ ላይ የጉዳት ካሣ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.97/90 አንቀፅ 7, አዋጅ ቁ.216/92 የፍ/ብ/ሥ/ሣ/ህ/ቁ 447(1), 423(2) የፍ/ብ/ህ/ቁ 2143(1), 2027, 2028, 2035 Download Cassation Decision

 • 69064 civil procedure/jurisdiction/ Addis Ababa city court

  የአዲስ አበባ ከተማ ነክ ፍ/ቤቶች የከተማው አስተዳዳር የሚያስተዳድራቸውን የንግድ ቤቶች ባለቤትነትን በተመለከተ በግለሰቦች መካከል የሚነሱ ክርክሮችን ለማየት ስልጣን የሌላቸው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 361/95 አንቀጽ 41(1)(ረ) አዋጅ ቁ. 408/96 አንቀጽ Download Cassation Decision

 • 69125 labor law dispute/ termination of contract of employment/ government directive/ notice

  ህግ ስልጣን በተሰጠው የመንግስት አካል በግልጽ በተላለፈ መመሪያ መሰረት የሠራተኛን የሥራ ውል ያቋረጠ አሠሪ የሥንብትና የማስጠንቀቂያ ክፍያ እንዲከፍል የሚገደድበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 28, 12(1)(ሀ) Download Cassation Decision

 • 69153 law of succession/ liquidator of succession/ fees of liquidator

  በፍርድ ቤት የተቋቋመ የውርስ አጣሪ አበል መጠን ሊወሰን የሚችልበት አግባብ የፍ/ብ/ህ/ቁ 959, 946-1125 Download Cassation Decision

 • 69160 contract law/ bailment/ transaction facilitation service

  አንድ ጉዳይ ለመፈፀም (ለማስፈፀም) በሚል ምክንያት መነሻነት የሰጠሁትን ገንዘብ ለመመለስ ወይም ለተሰጠበት ዓላማ አላዋለም በሚል የሚቀርብ አቤቱታ የአደራ ህግ ጽንስ ሀሳብን መሠረት በማድረግ ሊስተናገድ የማይገባ ስለመሆኑና ጉዳዩን ለማስረዳት የሰው ማስረጃ ማቅረብ የሚቻል ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 69179 public service/ loss of property of employer

  አንድ የመንግሥት ሠራተኛ ከአሰሪው ፈርሞ የተረከበው ንብረት በጠፋ ጊዜ ተጠያቂ የሚሆነው ንብረቱ በእጁ እያለ እንዳይጠፋ ተገቢውን ጥንቃቄ ያላደረገ ወይም ለንብረቱ መጥፋት የሠራተኛው ቸልተኛነት መኖሩ የተረጋገጠ እንደሆነ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.515/99 አንቀፅ 65 Download Cassation Decision

 • 69208 contract law/ sale of immovable property/ evidence law/ loss of written contract/ witnesses

  የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል የጠፋበት ሰው የሽያጭ ውሉ የጠፋ ስለመሆኑ ለማስረዳት በሚል የሚያቀርበው ጥያቄ ተቀባይነት ያለውና የሚቀርቡት ማስረጃዎች በተገቢው ሁኔታ ተመርምረው አሳማኝ መሆናቸው ከታወቀ (ሲረጋገጥም) ተከራካሪው የሽያጭ ውሉን በምስክሮች ለማስረዳት የሚያቀርበው ጥያቄ ተቀባይነት ሊኖረው የማገባ ስለመሆኑ የፍ/ህ/ብ/ህ/ቁ 2003,2002 Download Cassation Decision

 • 69291 property law/ constitution/ land law/ possessory right/ right to transfer use right/ oromia land law

  የመሬት ይዞታና በመሬት የመጠቀም መብት ያለው ወገን በውል ለ3ኛ ወገን ሊያስተላልፍ ስለሚችለው የመብት አድማስ በመሬት የመጠቀም መብት የተላለፈለት ሰው በመሬቱ ላይ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረት ያፈራ እንደሆነ ንብረቱን አፍርሶ (ነቅሎ) የመውሰድ መብትን ብቻ ሊያገኝ የሚችል ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 40(3), (4) አዋጅ ቁ.456/97 የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/አዋጅ ቁ.130/99 አንቀፅ 6 Download Cassation Decision

 • 69302 property law/ constitution/ oromia rular land law/ period of limitation/ use right

  የመሬት ባለ ይዞታ የሆነና በመሬቱ የመጠቀም መብት ያለው ሰው ለሁለት ዓመት ያህል መሬቱን በመተው ከአካባቢው ከጠፋ የመሬት ባለይዞታ የመሆንና በመሬቱ የመጠቀም መብቱ ቀሪ የሚሆን ስለመሆኑ በገጠር የእርሻ መሬት ላይ አርሶአደሮች ያላቸውን የይዞታና የመጠቀም መብት መደፈር ጋር በተያያዘ የሚነሣ ጥያቄ በ10 ዓመት ይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.456/97 የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/አዋጅ ቁ.130/99 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 40(4) የፍ/ብ/ህ/ቁ 1677(1)(3), 1845 Download Cassation Decision

 • 69385 civil procedure/execution of judgment/ objection/ foreclosure/ common property

  ለባልና ሚስት በብድር ገንዘብ የሰጠ ባንክ የባልና ሚስቱ ጋብቻ በፍቺ እንዲፈርስ ተወስኖ ንብረት ለመከፋፈል በአፈፃፀም ደረጃ ለሚገኝ ፍ/ቤት መብቱን ለማስከበር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 418 የሚያቀርበው የተቃውሞ አቤቱታ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.418, 419 አዋጅ ቁ. 97/90 አዋጅ ቁ.97/90 የተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 89 Download Cassation Decision

 • 69428 extracontractual liability law/ moral damage/

  ለጉዳት ከሚከፈል የሞራል ካሣ ጋር በተያያዘ ልጃቸውን በሞት ያጡ ወላጆች ሁለት በመሆናቸው ለእያንዳንዳቸው 1000 ብር ሊከፈል የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2116(3) Download Cassation Decision

 • 69471 labor law dispute/ civil procedure/ execution of judgment/ impossible judgments

  ከሥራ ክርክር ጋር በተያያዘ በፍርድ ቤት የተሰጠ ውሣኔ አስቀድሞ በሥራ ላይ የነበረን የድርጅት መዋቅርን መሰረት በማድረግ ሆኖ ጉዳዩ ለአፈፃፀም በቀረበ ጊዜ የድርጅቱ መዋቅር የተለወጠ መሆኑ ከተረጋገጠ ፍርዱ ሊፈፀም የማይችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.392(1),(2) Download Cassation Decision

 • 69602 custom law/ criminal law/ duty free/ vehicle/ sentencing

  ለግል አገልግሎት ከቀረጥና ከታክስ ነፃ የገባን መኪና ለብድር መያዣነት መስጠት በወንጀል ኃላፊነትን (ተጠያቂነትን) የሚያስከትል ስለመሆኑ በወንጀል ጉዳይ በቅጣት መልክ የሚጣለው የገንዘብ መቀጮ በፍ/ብሔር ጉዳይ ከሚኖረው የአንድነትና የነጠላ ኃላፊነት የተለየ ስለመሆኑና ቅጣቱ በእያንዳንዱ አጥፊ ላይ ለየብቻ ሊጣል የሚገባው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.345/95 አንቀጽ 73(1) አዋጅ ቁ. 60/89 አዋጅ ቁ.280/94 የወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1)(ሀ), 41 Download Cassation Decision

 • 69603 commercial law/ administrative law/ trade name/

  ከንግድ ስም አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የንግድ ሚኒስቴር በሚሰጠው ውሣኔ ቅሬታ ያለው ወገን አቤቱታ በይግባኝ ሊስተናገድ የሚችልበት አግባብ አዋጅ ቁ.686/2002 አንቀፅ 6, 7, 30, 2(9), 16, 61 Download Cassation Decision

 • 69657 family law/ divorce/ divorce by agreement/ ratification by court/ oromia family law

  የጋብቻ ፍቺ ውጤት በስምምነት በሚያልቅበት ወይም በሽማግሌዎች ወይም በባለሞያዎች በሚወሰንበት ጊዜ ውሣኔው ተፈፃሚነት የሚኖረው ለፍ/ቤት ቀርቦ ተቀባይነትን ሲያገኝ ብቻ ስለመሆኑ ፍቺን እና የፍቺን ውጤት በተመለከተ ውሣኔ የመስጠትና የማፅደቅ ስልጣን የፍ/ቤት ብቻ ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.213/92 አንቀፅ 83(3), 117 የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.69/95 እና አዋጅ ቁ.83/96 አንቀፅ 110(5) Download Cassation Decision

 • 69677 tax law/ income tax/ rental income/ witholding tax/ execution of judgment

  ህንፃን (ቤትን) በኪራይ ይዞ የሚገለገል ወገን ለአከራዩ ከሚከፍለው የኪራይ ዋጋ ላይ በህግ የተመለከተውንና ለመንግስት ገቢ ሊሆን የሚገባውን ግብር ተቀናሽ ለማድረግ ስለመቻሉና ይህንን ለማድረግም የግዴታ የፍ/ቤት ውሣኔ የማያስፈልገው ስለመሆኑ በፍርድ የኪራይ ዋጋን ለአከራይ እንዲከፍል የተወሰነበት ተከራይ ለመንግስት የሚከፈልና ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ግብርን ቀንሶ እንዲያስቀር የተጣለበትን ግዴታ መወጣት ያለበት በመሆኑ ሙሉውን የኪራይ ዋጋ ለአከራዩ እንዲያስረክብ በአፈፃፀም ሊገደድ ስላለመቻሉ አዋጅ ቁ.286/94 አንቀፅ 91, 101, 53(1) ደንብ ቁጥር 78/94 አንቀፅ 24, 2(ሸ) Download Cassation Decision

 • 69821 property law/ rural land law/ certificate of possessory right/ Amhara rural land law

  የገጠር መሬት ባለይዞታነትን በማረጋገጥ የተሰጠ የምስክር ወረቀት የመጨረሻና የማይስተባበል ማስረጃ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ የአማራ ብ/ክ/መ/አዋጅ ቁ.133/99 አንቀፅ 24(4) ደንብ ቁ.51/99 አንቀፅ 20(4) Download Cassation Decision

 • 69822 criminal law/ crime against national economy/ object of contract unlawful/ mining license

  የግንባታና የኮንስትራክሽን ማዕድን ማውጣት ሥራ ጋር በተያያዘ በሚመለከተው የመንግስት አካል የተሰጠ የፀና ፈቃድ ሣይኖር ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የመግዛትና የመሸጥ ውል መፈፀም በወንጀል ተጠያቂነትን ሊያስከትል ስለመቻሉ ህገ ወጥ ወይም ወንጀል ስለመሆኑ የተደነገገ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የተደረጉ ውለታዎችን (ውሎችን) በህግ ኃይል እንዲፈፀሙ በሚል ለፍ/ቤት ጥያቄውን በቀረበ ጊዜ ዳኞች ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ የሚገባቸው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1718, 1716 የወ/ህ/ቁ.353(1)(ለ) አዋጅ ቁ.52/85 አንቀፅ 53(5) ደንብ ቁ.182/86 አንቀፅ 39 Download Cassation Decision

 • 69915 contract law/ non performance of contract/ damage/ damage assessment

  እንደ ውል አልተፈፀመልኝም በሚል የጉዳት ኪሣራ ጥያቄ በቀረበ ጊዜ ፍ/ቤቶች የጥያቄ አቅራቢውን ተነፃፃሪ የውል ግዴታ ግምት ውስጥ በማስገባት የጉዳት ኪሣራ ሊወሰኑ የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1771, 1802 Download Cassation Decision

 • 69921 tax law/ record keeping/ estimation

  ግብር ከፋይ የሆነ ወገን ምንም አይነት የሂሣብ መዝገብና ሰነድ ያልያዘ እንደ ሆነ ወይም በማናቸውም ምክንያት የሂሣብ መዝገቡንና ሰነዱን የግብር አስገቢው ባለስልጣን ያልተቀበለው እንደሆነ ሊከፈል የሚገባው የግብር መጠን በግምት ሊወሰን ስለመቻሉ አዋጅ ቁ.286/94 አንቀፅ 69(1), 71 Download Cassation Decision

 • 69966 insurance law/ property insurance/ damage/ purchase replace of property

  የደረሰን ጉዳት ከመካስ ጋር በተገናኝ በንግድ ህጉ እውቅና ስለተሰጣቸው የመድን ሽፋን (የኢንሹራንስ ውል) አይነቶችና ባህሪያት ለንብረት የሚሰጥ የኢንሹራንስ ሽፋን አደጋው በደረሰበት ጊዜ ንብረቱ የነበረውን ዋጋ ለመካስ የሚያስችል መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ የንግድ ህግ ቁ. 654(2)(3),657, 674, 675, 688, 665, 678, 681, 680 Download Cassation Decision

 • 70057 law of succession/ form of public will will/ authentication

  ውል አዋዋይ ወይም ዳኛ ፊት የተደረገ ኑዛዜ በህጉ የተመለከተውን የኑዛዜው መነበብ ሥርዓትን ያላሟላ ከሆነ ህጋዊ ፎርማሊቲን የሚያሟላ እንደሆነ ለመቁጠር የማይቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 881(2), 882, 857 Download Cassation Decision

 • 70378 civil procedure/execution of judgment/ public auction/ sale of immovable by auction

  ከፍርድ አፈፃፀም ጋር በተገናኘ የሚንቀሳቀስ ንብረት የሀራጅ ሽያጭን አስመልክቶ ተፈፃሚነት ያላቸው የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌዎች የሚንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ የተካሄደ ጨረታ ሊፈርስ የሚችልበት አግባብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.432-438, 445 Download Cassation Decision

 • 70442 family law/ common property/ payment from bank account/

  ከባልና ሚስት የጋራ ንብረት ጋር በተገናኘ በጋብቻ ወቅት በአንደኛው ተጋቢ አማካኝነት ከባንክ ወጪ ተደርጐ ለ3ኛ ወገን የተላለፈ (የተሰጠ) ገንዘብ ለትዳር ጥቅም እንደዋለ የሚገመትበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.213/92 አንቀፅ 85-93 Download Cassation Decision

 • 70500 intellectual property/criminal law/ copyright/ film/

  ከቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጋር በተያያዘ የፊልም ባለቤት ለመሆን በማሰብ በባለሃብትና ፊልሙን ለመስራት በሚል በተደረገ ስምምነት መነሻነት ፊልሙን ለህዝብ ከማቅረብ ጋር ተያይዞ ጉዳዩ በፍ/ብሔር ክርክር ተደርጐበት በተሰጠ ውሣኔ መሰረት ፊልሙን በእጅ አድርጐ መገኘት በወንጀል ተጠያቂነት የማያስከትል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.410/96 አንቀፅ 7(1)(ሀ), 36(1) የወ/ህ/ቁ.23(2), 57-59 Download Cassation Decision

 • 70801 property law/ possessory action

  በከሳሽነት የተሰየመ ወገን አንድ ንብረት በአንድ ህጋዊ ተግባር ሳቢያ ወደ እጄ ገብቷል በይዞታዬ ላይ እያለ ሁከት ተፈጠረብኝ በሚል የሚያቀርበው የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ በእርግጥም ሁከት ተፈጥሯል አልተፈጠረም የሚል ጭብጥ በመያዝ ሊስተናገድ የሚገባ እንጂ ክርክር የተነሣበት ንብረት በከሳሹ እጅ እንዴት እንደገባ ወይም ወደ ከሳሹ እጅ ሊገባ የቻለበትን ህጋዊ ተግባር ለመመርመር የሚያበቃ ምክንያት የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1149 Download Cassation Decision

 • 70824 banking law/ foreclosure/ power of course/ order of sale of properties

  ባንክ ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዘውን ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ንብረቶች አሻሻጥ ቅደም ተከተል ጋር በተገናኘ አቤቱታ ሊቀርብበትና ፍ/ቤቶችም ውሣኔ ሊሰጡበት የሚያስችል የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ97/90 አንቀፅ 7, 6 አዋጅ ቁ.216/92 Download Cassation Decision

 • 70963 contract law/ labor law dispute/ scholarship/ non performance of contract

  በአሰሪው በኩል የተመቻቸን የውጪ የትምህርት እድል ተጠቃሚ በመሆን በምትኩ ለተወሰነ ጊዜ ለማገልገል ከተደረገ ውል ጋር በተገናኘ ሠራተኛው በውሉ ያለበትን ግዴታ እንዲወጣ ከሚጠበቅበት ጊዜ በፊት ከአሰሪው ፈቃድና እውቅና ውጪ ለሌላ ትምህርት ወደ ሌላ አገር በመዛወር የመጀመሪያው ውል ውጤት እንዳይኖረው ያደረገ እንደሆነ ሠራተኛው በውሉ የተመለከተውን ግዴታ ለመፈፀም እንዳልቻለ የሚያስቆጥረው ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 71126 family law/ common property/ manner of partition of common property

  የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል ጋር በተገናኘ አንድን የጋራ ንብረት በዓይነት ለመካፈል ተጋቢዎቹ ከስምምነት ላይ ለመድረስ ያልቻሉ እንደሆነና ሁለቱም የቅድሚያ ግዢ መብት ጥያቄ ያቀረቡ እንደሆነ ንብረቱ ለጨረታ ቀርቦ እንዲሸጥ በማድረግ ገንዘቡን መካፈል ያለባቸው ስለመሆኑ፣ የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ብ/መ/ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 75/96 አንቀጽ 103(1) Download Cassation Decision

 • 71134 commercial law/ private limited company/ winding up/ mismanagement of PLC

  አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንዲፈርስ ለመጠየቅ በቂና ህጋዊ መስፈርቶች መሟላታቸው መረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ፣ የማህበር ሥራው በአግባቡ አልተመራም ከሚል ጥያቄ ጋር በተያያዘ አግባብነት ያለው አካል የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ወይም ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ህጐች መሠረት በማድረግ እንዲስተካከል ለመጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ፣ የንግድ ህግ ቁጥር 217, 218, 511, 543 Download Cassation Decision

 • 71184 criminal law/ evidence law/ employment exchage services/

  የሥራና ሠራተኛን ማገናኘት አዋጅ ቁ.632/2002 በመተላለፍ ሊኖር ስለሚችለው የወንጀል ተጠያቂነት ከቀረበ የወንጀል ክስ ጋር በተያያዘ የግል ተበዳይ የሆነ ሰው ቀርቦ ካልመሰከረ በስተቀር ክሱን ለማስረዳት የሚቀርቡ ሌሎች ማስረጃዎች ተከሳሹን ጥፋተኛ ለማለት ብቁ አይደሉም ሊባል የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.632/2002 አንቀፅ 16(1)(መ), 18(1)(ሀ), 20(2), 40(3) Download Cassation Decision

 • 71316 civil procedure/ injunction/ reconsideration of injunction order

  በንብረት ላይ በፍ/ቤት የተሰጠን የእግድ ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 158 መሠረት መልሶ ለማንሳት ስለሚቻልበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 158 Download Cassation Decision

 • 71375 contract law/ offer and acceptance

  ውሎች በቃል፣ በተለመዱ ጠቅላላ ምልክቶች ወይም ግዴታ ለመግባት መፍቀድን በማያጠራጥር አሰራር በማስታወቅ ሊደረጉ ስለመቻላቸው የፍ/ብ/ህ/ቁ.1681(1) Download Cassation Decision

 • 71507 labor law dispute/ termination of contract of employment/ debt of worker/ lien right over provident fund

  ከሚሠራበት ድርጅት ብድር ወስዶ ከፍሎ ያላጠናቀቀ ሠራተኛ በገዛ ፈቃዱ ሥራ ሲለቅ ተከፍሎ ያላለቀው ብድር ከሚያገኘው ፕሮቪደንት ፈንድ ሊቀንስ የሚችለው ሠራተኛው ዕዳ እንዳለበት ያመነ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 59(1) Download Cassation Decision

 • 71753 criminal law/ unlawful sending of Ethiopians abroad for work

  አንድ ሰው በወንጀል ህግ አንቀጽ 598(2) መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ውጪ አገር ልኳል በሚል ጥፋተኛ ተብሎ ሊቀጣ ስለሚችልበት አግባብ የወ/ህ/ቁ 598(2) Download Cassation Decision

 • 71895 law of succession/ liquidation of succession/

  የውርስ ሀብት ማጣራት ጋር በተገናኘ የንብረት አጣሪው የሟች ያለኑዛዜ ወራሾች በሚል የተጠቀሱ ወራሾች በአካባቢው በሚገኘው የመረዳጃ እድር ሰፍሯል በማለት የውርስ ድርሻ አላቸው በሚል የሚያቀርበው የውሣኔ ሀሳብ ህጋዊ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 842, 856, 962, 944(ሀ),1097,1113 Download Cassation Decision

 • 71927 contract law/ evidence law/ denial of signature/

  በሰነድ ላይ የተመለከተ ፊርማ በተካደ ጊዜ ሰነዱ ሲፈረም የነበሩ የምስክሮችን ቃል በመስማትና በሌሎች ማስረጃዎች ፊርማው የማን እንደሆነ ለማረጋገጥ /Authenticate ለማድረግ/ የሚቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2472(1) እና (3) Download Cassation Decision

 • 72189 civil procedure/ appeal/ remand/ power of court

  በበላይ ፍ/ቤት ትዕዛዝ አንድን በነጥብ ወደ ሥር ፍ/ቤት የተመለሰ ጉዳይ አይቶ እልባት እንዲሰጥበት የተላለፈለት ፍ/ቤት የተመለሰውን ጉዳይ የበላይ ፍ/ቤት የሰጠውን ፍርድ መሠረት በማድረግ በአግባቡ ውሣኔ ለመስጠት ተገቢውን ጥረት ማድረግ ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍብ/ሥምሥ/ህ/ቁ. 343(1) Download Cassation Decision

 • 72286 law of succession/ will/ donation/ revocation of will

  ሟች አድርጐት የነበረ ኑዛዜ በተመሣሣይ ንብረት ላይ በኋላ በተደረገና ከሞተ በኋላ ተፈፃሚነት ባለው ስጦታ የተተካ እንደሆነ ኑዛዜው በስጦታው እንደተሻረ የሚያስቆጥረው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2428, 2443, 881, 826(2), 856, 898 Download Cassation Decision

 • 72304 criminal law/ constitution/ double jeopardy/ content of charges

  ማንኛውም ሰው በወንጀል ህግና ሥርዓት መሠረት ተከስሶ የመጨረሻ በሆነ ውሣኔ ጥፋተኝነቱ በተረጋገጠበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም (Principle of Double Jeopardy) በሚል የሚታወቀው የወንጀል ህግ መርህ ሊተረጐምና ሥራ ላይ ሊውል የሚችልበት አግባብ፣ አንድ በወንጀል የተከሰሰ ሰው በድጋሚ የቀረበበትን የወንጀል ክስ በአንድ ጉዳይ በድጋሚ ያለመከሰስና ያለመቀጣት መብቴ ተጥሷል በሚል ክርክር ለማቅረብ ሊሟሉ ስለሚገቡ ህጋዊ መስፈርቶች፣ ዐቃቤ ህግ በአንድ ተከሳሽ ላይ የወንጀል ክስ ከማቀርቡ በፊት ተከሳሹ አንድ ወንጀል በመፈፀም ሀሣብ የሠራው አንድ የወንጀል ድርጊት ያስከተላቸውን ወይም ሊያስከትላቸው የሚችላቸውን ውጤቶች ሁለተናዊ በሆነ መንገድ በማገናዘብ አግባብነት ያላቸውን የህግ ድንጋጌዎች በመለየትና በመጥቀስ የወንጀል ክሱን በጥንቃቄ የማቅረብ ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ 2(5), 24(1) የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 130,131, 41, 111, 112 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ህግ መንግስት አንቀጽ 23,13(2) Download Cassation Decision

 • 72337 agency/ special agency/ content of agency document

  ልዩ የውክልና ስልጣን ለመስጠት በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ልዩ ውክልና ስለመስጠት በተመለከተ አግባብነት ያላቸው የህግ ድንጋጌዎች ያለመጠቀስ ልዩ የውክልና ስልጣን እንዳልተሰጠ የሚያስቆጥር ስላለመሆኑ የአስተዳደር አካል የሆነ ተቋም በአንድ ወቅት የሰጠውን የፅሁፍ ማስረጃ በሌላ ጊዜ ማስተካከሉ በአንድ ጉዳይ ላይ ሁለት የተለያዩ ሰነድ ቀርቧል በሚል እንደማስረጃ ሰነድ ዋጋ የሚያጣበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ በውክልና ሰነድ ላይ ለተወካይ የተሰጠው ስልጣን በይዘቱ ልዩ ውክልና የሚያመለክት ሆኖ ሰነዱ ስለ ልዩ ውልክና አስፈላጊነት የተቀመጠውን የፍ/ብ/ህ/ቁ 2208 ያለመጥቀሱ ብቻ ለተወካዩ ልዩ የውክልና ስልጣን እንዳልተሰጠ የሚያስቆጥር ስላለመሆኑ፣ ከሰነድ ማስረጃ ተቀባይነት ጋር በተያያዘ የሚነሣ ጥያቄ የህግ ጥያቄ በመሆኑ በሰበር ችሎት ሊስተናገድ የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2205, 2005(1), 2179, 2199, 2203, 2204 Download Cassation Decision

 • 72420 family law/ constitution/ sharia court/ divorce/ consent of parties/ jurisdiction

  ከባልና ሚስት ጋብቻና ፍቺ ጉዳይ ጋር በተገናኘ የቀረበን ጉዳይ ስልጣን ያለውና ተከራካሪዎቹ ለመዳኘት ፈቃዳቸውን የገለፁለት የሽሪአ ፍ/ቤት ለመዳኘት ፈቃደኛ አለመሆኑን በመግለጽ መዝገቡን የዘጋው እንደሆነ መደበኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን ማስተናገድ የሚገባው ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. አንቀጽ 37(1), 34(5), 78(5), Download Cassation Decision

 • 72463 contract law/ antichresis/ repayment

  በወለድ አገድ ውል መሰረት የማይንቀሣቀስ ንብረቱን ያስያዘ ተዋዋይ ወገን በውል የተገለፀው ጊዜ ካለፈ በኋላም በማናቸውም ጊዜ ዕዳውን ከፍሎ ንብረቱን ለማስለቀቅ የሚችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 3128/2/ 3117-3130 Download Cassation Decision

 • 72645 labor law dispute/ occupational accident/ death/ insurance

  በሥራ ላይ በደረሰ ጉዳት በሞት ምክንያት የሥራ ውል ሲቋረጥ የሠራተኛው የጉዳት ካሣ በመድን ፖሊሲ ተሸፍኖ ሲገኝ የካሣ ክፈያውን ሊጠይቁ ስለሚችሉ ወገኖች፣ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 110(1)(2),134(2),128,129,133 የፍ/ብ/ህ/ቁ. 842, 1732, 1735, 1736, 1734 Download Cassation Decision

 • 72824 tax law/ income tax/ tax declaration

  የግብር ከፋይ የሆነ ሰው ገቢውን በህጉ አግባብ ለግብር አስገቢው መስሪያ ቤት ከማሣወቅ ውጪ ደረጃውን በራሱ ሊወሰን /ሊለወጥ/ የማይችል ወይም የማይገባ ስለመሆኑ፣ የግብር አከፋፈል ስርዓት ለግብር ከፋዩ ግልጽ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 286/94 አንቀጽ 38 ደንብ ቁ. 78/94 አንቀጽ 18,22 አዋጅ ቁ. 308/95 አንቀጽ 10(2)(ሐ) አዋጅ ቁ. 587/2001 Download Cassation Decision

 • 73041 civil procedure/execution of judgment/ partition of common property/ property without title

  አንድን የማይንቀሳቀስ ንብረት በተመለከተ የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ነው በሚል ፍርድ ከተሰጠ በኋላ ክፍፍሉን በተመለከተ ጥያቄ የቀረበለት የአፈፃፀም ችሎት ንብረቱ ሰነድ አልባ ነው የሚል ምክንያትን ብቻ በመያዝ ለአፈፃፀም የቀረበውን መዝገብ በመዝጋት የሚሠጠው ትዕዛዝ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 225(2),423,392(1),371(1) Download Cassation Decision

 • 73258 labor law dispute/ public pension/ severance payment

  ከአምስት አመት በላይ ያገለገለ ሰራተኛ የጡረታ መዋጮው ተመላሽ የተደረገለት መሆኑ የጡረታ አበል ተጠቃሚ እንደሆነ ተቆጥሮ የስራ ስንብት የሚያስከለክለው ስላለመሆኑ በአሰሪና ሰራተኛ ህጉ የጡረታ ”አበል” በሚል የተመለከተው ሀረግ የጡረታ መዋጮ ተመላሽንም የሚጨመር ስላለመሆኑ አዋጅ ቁ.345/95 አንቀፅ 2(13),(14) አዋጅ ቁ.494/98 አንቀፅ 2(1)(ሸ) Download Cassation Decision

 • 73264 criminal law/ criminal procedure/ appeal/ time to appeal

  በወንጀል ጉዳይ በተሰጠ ውሣኔ ቅሬታ ያለው ወገን ይግባኙን ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ለማቅረብ በህጉ ተለይቶ ስለተመለከተ የጊዜ ገደብ፣ የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 187(2) Download Cassation Decision

 • 73291 agency/ unauthorized agency

  የፀና የውክልና ስልጣን ከሌለው ሰው ጋር የተደረገ ውል ከጅምሩ ፈራሽና ህጋዊ ውጤት የሌለው ስለመሆኑ ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2232(2),2015(ሀ),2005(2),1204 Download Cassation Decision

 • 73549 civil procedure/jurisdiction/ public service/

  የፌዴራል መንግስት ተቋማት በአጠቃላይና የከፍተኛ ት/ት ተቋማት በተለይ የራሳቸው የሆነ የእድገት አሰጣጥ፣ የቅሬታ አፈታትና አጠቃላይ አስተዳደራዊ ሥራዎች የሚከናወንበት አግባብ ያለ በመሆኑ በቀጥታ ለመደበኛ ፍ/ቤቶች ጉዳዩ ቀርቦ ውሣኔ የሚሰጥበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 515/99 Download Cassation Decision

 • 73569 criminal law/ criminal procedure/ bail/

  በወንጀል ጉዳይ የተከሰሰ ሰው የዋስትና መብቱ በፍ/ቤት ከተከበረለት በኋላ ህጋዊ ምክንያቶችን በማቅረብ የዋስትና መብቱን በመተው ያስያዘው ገንዘብ ተመልሶለት ጉዳዩን ማረሚያ ቤት ሆኖ ለመከታተል የሚያቀርበውን ጥያቄ ውድቅ ለማድረግ የሚያስችል የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 73696 civil procedure/ court motions/ qourem

  በህጉ አግባብ ሊሟላ የሚገባው የዳኞች ቁጥር ባልተሟላበት ሁኔታ የሚሰጥ ትዕዛዝ ወይም ውሣኔእንደተሰጠ የማይቆጠርና ህጋዊ ውጤት ሊኖረው የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 73,337 Download Cassation Decision

 • 73881 labor law dispute/ termination of contract of employment/ discipline committee/ validity of discipline committee decision

  ከስራ ክርክር ጋር በተገናኘ በዲሲፕሊን ተከስሶ በዲሲፕሊን ኮሚቴ ሠራተኛው በፈፀመው የማታለል ድርጊት ጥፋተኛ የተባለ መሆኑን መነሻ በማድረግ የተሰናበተ ሰራተኛ የዲስፕሊን ኮሚቴው አባላት በሥራ ክርክር ሰሚው አካል ፊት ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን ስላልሰጡ ስንብቱ ህገ ወጥ ነው በሚል የሚያቀርበው አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 27(1)(ሐ) እና (መ) Download Cassation Decision

 • 73953 criminal law/ criminal procedure/ dealings endangering the credits of public finance

  የትራፊክ ደንብ መተላለፍ ጋር በተያያዘ የክስ ቻርጅን ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆን በወ/ህ/አ.438 በየመንግስት ሥራን ማሰናከልና የመተባበር ግዴታን መጣስ ወንጀል ሊያስጠይቅ ስለመቻሉ፣ የወ/ህ/አ.348 Download Cassation Decision

 • 74041 criminal law/ criminal procedure/ motion for case/ appeal/ interlocutory appeal/ cassation/ corruption

  አንድ ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ በሚል ፍ/ቤት በሚሰጠው ብይን ላይ ይግባኝ ለማቅረብ የሚያስችል የህግ መሠረት የሌለ ስለመሆኑ የሙስና ክስ ከሚመራበት ሥርዓት ጋር በተገናኘ ተከሳሽ የሆነ ተከራካሪ ወገን ይግባኝ ለማቅረብ ስለሚችልባቸው ህጋዊ ጉዳዮች፣ ለሰበር ችሎት የሚቀርቡ ማናቸውም ጉዳዮች የይግባኝ አቅራረብ ሥርዓትን ያጠናቀቁና የመጨረሻ ፍርድ የተሠጠባቸው መሆን የሚገባቸው ስለመሆኑ፣ አዋጀ ቁ. 25/88 አንቀጽ 22 አዋጀ ቁ. 434/97 አንቀጽ 36(2) 40, 55 አዋጀ ቁ. 236/93 Download Cassation Decision

 • 74111 extracontractual liability law/ recruitment of workers abroad/liability of employment agency

  ከአሰሪና ሠራተኛ አገናኝ አገልግሎት ጋር በተገናኘ ሰዎችን ወደ ውጪ አገር የላከ ሰው በተላኩት ሰዎች ላይ ለሚደርስ ጉዳት ካሣ የመክፈል ግዴታ የሚኖርበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 632/2001 Download Cassation Decision

 • 74230 labor law dispute/ workers' reduction/ procedure in workers' reduction

  አሰሪ ሲሰራው የነበረው ሥራ በመቀነሱ ወይም በመቀዝቀዙ ምክንያት ካሉት ሠራተኞች መካከል ከአሥር ፐርሰንት በታች የሆኑትን የሥራ ውል ሟቋረጡ የግድ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሥራ ውላቸው የሚቋረጥና ሥራ የሚቀጥሉትን ሠራተኞች ለመለየት ሊከተለው ስለሚገባ አካሄድ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 28(8), 29(3) Download Cassation Decision

 • 74376 family law/ divorce by agreement/ agreement on effect of divorce/

  ፍቺን በስምምነት ለመፈፀም ለፍ/ቤት አቤቱታ ያቀረቡ ባል እና ሚስት የፍቺ ውጤትን በተመለከተ ያደረጉትን ስምምነት ፍ/ቤት ለህግና ለሞራል የማይቃረን መሆኑን በማረጋገጥ ያፀደቀው እንደሆነ ስምምነቱ ተፈፃሚ መደረግ ያለበት ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 80,83(3) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 277(2) Download Cassation Decision

 • 74400 labor law dispute/ damage to to the property of the employer

  አንድ ሠራተኛ በአሠሪው በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ የሚባለው ንብረቱ የአሰሪውን ወይም ከአሠሪው ድርጅት ሥራ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 27(ሸ) Download Cassation Decision

 • 74530 criminal law/ breach of trust

  አንድ ሰው በወ/ህ/አ. 675(1) የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት ፈጽሟል በሚል ሊከሰስና ጥፋተኛ ተብሎ ሊቀጣ ስለሚችልበት አግባብ፣ የወ/ህ/አ.675(1),23 Download Cassation Decision

 • 74538 agency/ unauthorized agency

  የውክልና ውል ሳይኖር ወኪል ነኝ በሚል የሚደረግ ውል ህጋዊ ውጤት አግኝቶ የሚፀናበት አግባብ ስላለመኖሩ፣ የውክልና ሥልጣኑ ከመሰጠቱ በፊት የተደረገ ውል ውክልና ከተሰጠ በኋላ ሊፀና ይችላል ለማለት የሚያስችል የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑና ወካይ የሆነ ሰው የወካዩን ድርጊት እንደተቀበለ ሊቆጠር የሚችለው በህግ የሚፀና የውክልና ውል ኖሮ ነገር ግን ወኪሉ ከተሰጠው ስልጣን በላይ ሰርቶ የተገኘ እንደሆነ ወይም የውክልና ስልጣኑ ካበቃ (ከተቋረጠ) በኋላ ወካዩን በመወከል የሰራቸውን ሥራዎች በተመለከተ ብቻ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2190, 1678 (ሐ),1719(2),1723 Download Cassation Decision

 • 74636 labor law dispute/ termination of contract of employment/ delay of payments due

  የሠራተኞች ስንብት ተከትሎ አሰሪ የሆነ አካል የከራካሪ የሆኑ ክፍያዎችን በተመለከተ ሊያዘገይ እንደሚችልና ክፍያ በማዘግየት በሚል ሊቀጣ የሚችለው ከቁጥጥር ውጪ በሆነ ምክንያት ሳይኖር ወይም የሚያከራክር ክፍያ ሳይኖር ያለአግባብ ያዘገየ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 37, 38, 36 Download Cassation Decision

 • 74753 tax law/ VAT/ cash register/

  የተጨማሪ እሴት ታክስ የመክፈል ግዴታ መወጣት ጋር በተያያዘ ታክስ ከፋዮች የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያን የመጠቀም ግዴታ የሚኖርባቸው የንግድ ፈቃድ የሥራ ዘርፍ በግልፅ ተለይቶ በተመለከተባቸው ሽያጮች ጋር በተገናኘ ብቻ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.285/94 አንቀፅ 55 አዋጅ ቁ.609/201 አንቀፅ 50(መ)(2) ደንብ ቁ.139/99 አንቀፅ 5(1)(ለ) የወ/ህ/ቁ.23(2) Download Cassation Decision

 • 74785 civil procedure/appeal/ leave to appeal/ invalid judgment

  ግዜው ያለፈበት የይግባኝ አቤቱታን ማስፈቀጃ በመቀበል ፍርድ ከተሰጠ በኋላ በበላይ ፍ/ቤት በተካሄደ ክርክር የማስፈቀጃ አቤቱታው ተቀባይነት ማግኘቱ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ ወሣኔ የተሰጠ እንደሆነ የስር ፍ/ቤት በዋናው ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ፍርድ ተፈፃሚነት የማይኖረው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 325,326,349 Download Cassation Decision

 • 74898 civil procedure/ execution of judgment/ period of limitation

  የፍርድ አፈፃፀም ጥያቄ በህጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ የባለዕዳው ንብረት እዳውን ለመሸፈን ባለመቻሉ በከፊል ተፈጽሞ ከቆየ በኋላ የፍርድ ባለመብት የባለዕዳውን ንብረት አፈላልጐ በማግኘት አፈፃፀሙን ለመቀጠል ሲፈልግ ይርጋ ሊቆጠር ስለሚችልበት አግባብ፣ አበዳሪ የሆነ ባንክ ከዕዳው አከፋፈል ጋር በተያያዘ በባለዕዳው ላይ የአፈፃፀም ክስ መስርቶ እንደ ፍርዱ ለመፈፀም የማይችል መሆኑ የተረጋገጠ ከሆነ በሌላ ጊዜ በባለዕዳው ንብረት ላይ በፍርድ ባለመብቱ የሚቀርበው የአፈፃፀም አቤቱታ ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው የይርጋ ጊዜ መቆጠር ስለሚጀምርበት ጊዜ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 384, 329(2) አዋጅ ቁ. 97/90 Download Cassation Decision

 • 75562 family law/ common property/ condominium

  በጋብቻ ወቅት በአንደኛው ተጋቢ ስም የተመዘገበና በጋብቻ ወቅት ዕጣው የወጣ የኮንዶሚንየም ቤት ላይ ያለ መብት የቤቱ ውል ከጋብቻ መፍረስ በኋላ የተፈፀመና ቅድሚያ ክፍያ የተከፈለ መሆኑ (የንብረት ክፍፍል እስካልተፈፀመ ድረስ) ንብረቱን የግል የሚያስብል ስላለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 75902 contract law/ mortgage/ change of house number/ reconstruction/ priority right

  አንድ ቀድሞ በመያዣ የተሰጠ የማይንቀሳቀስ ንብረት ካርታ ቁጥሩና የቤት ቁጥሩ ተለውጦ እንዲሁም ቀደም ሲል የነበረው ቤት ፈርሶ በቦታው ላይ አዲስ ቤት ተሠርቶና አዲስ ካርታና የቤት ቁጥር ተሰጥቶ በተገኘ ጊዜ አዲሱን ቤት በመያዣ የያዘ አበዳሪ ቀድሞ የነበረውን ቤት በመያዣ ከያዘው አበዳሪ የቅድሚያ መብት ያለው ስለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 3052, 3066 Download Cassation Decision

 • 75922 criminal law/ evidence law/ direct evidence/ indirect evidence

  በወንጀል ጉዳይ የተከሰሰን ሰው የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈፀሙ ለማስረዳት መቅረብ የሚገባው የማስረጃ አይነት ለጉዳዩ ቀጥተኛ ተዛማጅነት ያላቸው ፍሬ ነገሮች ለማስረዳት የሚችልና ድርጊቱ ሲፈፀም አይቻለሁ ወይም/እና ሰምቻለሁ የሚል ቀጥተኛ ማስረጃ ብቻ ነው ለማለት የሚያስችል የህግ መሠረት የሌለ ስለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 137, 141, 149 Download Cassation Decision

 • 75980 criminal law/ evidence law/ circumstantial evidence/

  አንድ የወንጀል ድርጊትን ማስረዳት ጋር በተያያዘ የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃ (circumstantial evidence) በይዘቱ አንድ ክስተት ከመፈጠሩ በፊት፣ ክስተቱ ሲፈጠር ወይም ድርጊቱ ሲፈፀምና ክስተቱ ከተፈጠረ ወይም ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ፣ ያሉትን አካባቢያዊ ሁኔታዎች የሚያሣይና የሚገልጽ በመሆኑ ህጋዊ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 137(1) Download Cassation Decision

 • 76601 civil procedure/ period of limitation/ ex parte judgment

  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህጉ ውስጥ የተመለከቱት የይርጋ ድንጋጌዎች የሚታዩበት አግባብ በፍ/ብ/ህጉ በተመለከቱት የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር ድንጋጌዎች ስለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 78 መሠረት በሌለሁበት የተሰጠ ፍርድ ይነሳልኝ በሚል ጥያቄ በቀረበ ጊዜ በህጉ የተመለከተው የአንድ ወር ግዜ ገደብ በፍታብሔር ህጉ የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር ስሌት መሠረት ሊሰላ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1848, 1856(2) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 78, 195 Download Cassation Decision

 • 76786 civil procedure/ customary law/ summon/ court fee/ refund of court fee

  የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ በግልጽ ያልሸፈናቸውና ለፍ/ቤት የቀረቡ ጉዳዮችን አካሄድ (አሰራር) በተመለከተ ህጉ ከመውጣቱ በፊት ተጽፈው በሥራ ላይ የነበሩ አግባብነት ያላቸው ህጐች እንደ አግባብነቱ ሥራ ላይ ሊውሉ የሚችሉ ስለመሆኑ፣ ክስ አቅርቦ ለከሳሽ የሚላከውን መጥሪያ ከፍ/ቤት ወጪ አድርጐ ነገር ግን ለተከሣሽ መጥሪያውን ከማድረሱ በፊት ክሱ እንዲቋርጥ ያደረገ ከሣሽ ለዳኝነቱ የከፈለው ገንዘብ በመሉ እንዲመለስለት የሚያቀርበው ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ በፍ/ቤት ክስ የመሰረተ (ያቀረበ) ወገን የክስ መሰማቱ ሂደት ከመጀመሩ በፊት ክሱን በማንሣት መዝገቡ እንዲዘጋ ያደረገ ከሆነ ለዳኝነት ከከፈለው ገንዘብ ለፍ/ቤቱ በኪሣራ ስም የሚቀነሰው ተቀንሶ ቀሪው ገንዘብ ሊመለስለት የሚገባ ስለመሆኑ የፍብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 232(1) (ለ) ,245(4),3,278(1) የህግ ክፍል ማስታወቂያ 177/74 አንቀጽ 11 Download Cassation Decision

 • 76909 criminal law/ criminal procedure/ default procedure/ sentencing

  በወንጀል ፍርድ ሂደት አንድ ጉዳይ ተከሳሽ በሌለበት ወይም በክርክሩ ሂደት ተሳታፊ ሳይደረግ (ሳይሆን)(default procedure) ነው የታየው ለማለት ስለሚቻልበት አግባብ፣ የቅጣት አስተያየት በሚሰጥበት ጊዜ ያለመቅረብ ተከሳሽ በሌለበት የተሰጠ ውሣኔ ነው ሊያስብል የማይችል ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.161, 164, 197, 202, 149 (4) (1) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 20(4)) Download Cassation Decision

 • 77113 labor law dispute/termination of contract of employment/ transfer/

  አሰሪ ደንብን ባልጠበቀ መንገድ ሠራተኛው ወደ ሌላ ቦታ ተዛውሮ እንዲሰራ ተመድቦ ፈቃደኛ አልሆነም በሚል ሠራተኛውን ማሰናበቱ ተገቢ ስላለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 77175 civil procedure/jurisdiction/ Addis Ababa city court/

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር አስፈፃሚ አካላት ወይም በከተማው አስተዳዳር ባለቤትነት ሥር ያሉ ተቋማት የሚገቧቸው የሊዝ ውሎችን መሠረት አድርጐ የሚነሱ የውል አፈፃፀምና ተያያዥ ጉዳዮችን አይቶ ለመወሰን የከተማው ፍ/ቤቶች የሥረ-ነገር ስልጣን ያላቸው (የተሰጣቸው) ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 361/95 አንቀጽ 41(1)(ሀ) እና (መ) Download Cassation Decision

 • 77322 civil procedure/ third party intervention

  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 41 የተመለከተው የጣልቃ ገብነት ሥርዓት አፈፃፀም እንደተሰጠ የማይቆጠርና ህጋዊ ውጤት ሊኖረው የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 73,337 Download Cassation Decision

 • 77592 criminal law/ fraudulent misrepresentation

  የወንጀል ህግ አንቀጽ 692(1)ን በመተላለፍ አንድ ሰው በወንጀል ተጠያቂ ሊሆን ስለሚችልበት ሁኔታ፣ የወ/ህ/አ. 692,32(1)(ለ) Download Cassation Decision

 • 77989 criminal law/ banking/ mismanagement of private interest

  የባንክ ሥራ ጋር በተገናኘ የሥራ አመራር ላይ ጉድለት በመፈፀም ስለሚደረግ ወንጀል፣ የወ/ህ/አ. 703 Download Cassation Decision

 • 78793 criminal law/ corruption/ acting as a go between

  አንድ ሰው በወ/ህ/አ. 429 ጉቦ ማቀባበል የወንጀል ድርጊት ክስ ሊቀርብበትና ጥፋተኛ ተብሎ ቅጣት ሊጣልበት ስለሚችልበት አግባብ፣ የወ/ህ/አ. 429,23(4,(1),58) Download Cassation Decision

 • 79096 labor law dispute/ occupational accident/ termination of contract of employment

  በሥራ ላይ ንብረትንም ሆነ ህይወትን ለአደጋ የሚያጋልጥ ድርጊት መፈፀም ህገ ወጥ በመሆኑ ያለማስጠንቀቂያ ሊያሰናብት የሚችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 27(1)(ቀ) 14(2)(ሀ) Download Cassation Decision

 • 79105 labor law dispute/ brawl at work place/ work place

  የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ህግ ውስጥ ""እንደ ጥፋቱ ክብደት በሥራ ቦታው አምቧጓሮ ወይም ጠብ አጫሪነት ተጠያቂ መሆን..."" በሚል የተመለከተው ሀረግ ሊተረጐምና ተግባራዊ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ፣ ""የሥራ ቦታ"" የሚለው ሀረግ አሰሪው (ተቋሙ) ለሥራና ለመኖሪያ በሚል ለሰራተኞች የሚሰጠውን ቦታ እንዲሁም ተፈፀመ የተባለውን የአምባጓሮ ድርጊት ከሥራ ሰዓት ሙጪ መሆኑንም ጭምር የሚያካትት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 27(1)(ረ),97,4 Download Cassation Decision

 
 
 

Google Adsense