Federal Court Case Tracker

volume 19

volume 19

 • 113973 family law/ immovable property/ rural land /

  በገጠር መሬት ላይ የሚኖረው መብት የመጠቀም መብት ሲሆን ይህንን መብት ለ3ኛ ወገን /ለሌላ/ ሰው ለረጅም ጊዜ ሰጥቶ ተጠቃሚነቱ የተቋረጠበት ባለመብት መልሶ መጠየቅ የማይችል ስለመሆኑ፣ የኦሮሚያ ክልለ የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1997 አንቀፅ 9(5)   የሰ/መ/ቁ. 113973 ቀን 21/04/2008 ዓ/ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ ፈይሳ ወርቁ አመልካች፡- ወ/ሮ ጠጅቱ ኡርጋ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ገመዳ ሬባ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የባልና ሚስት ንብረት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የጀመረው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ሮቢ ወ/ፍ/ቤት ነው፡፡ አመልካች በዚህ ወረዳ ፍ/ቤት ባለቤታቸው በነበሩት አቶ አሰፋ ገመዳ ላይ ክስ የመሰረቱት ኤዴ ከተባለ አከባቢ የሚገኝ ሁለት የበሬ መዋያ  መሬት እና ሰምንተኛ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ግማሸ የበሬ መዋያ ይዞታ መሬታችንን እኩል እንደንካፈል ይወሰንልኝ የሚል ሲሆን ተከሳሽ በበኩላቸው የተጠቀሰው ይዞታ መሬት የጋራ ይዞታችን አይደለም ሊካፈል አይገባም ብለዋል፡፡ የአሁኑ ተጠሪ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብተው ግራ ቀኙ የሚከረከሩበት መሬት የግል ይዞታዬ ነው በስሜ ተለከቶ የሚገኝ እና በስሜ የምግብርበት ነው ከሳሽና ተከሳሽ በዚህ መሬት ላይ አንዳችም መብት የላቸውም ብለው ተከራካረዋል፡፡   ከሳሽ (የአሁኑ አመልካች) በበኩላቸው ለክርክር ምክንያት የሆነውን መሬት በ1994 ዓ/ም ከተከሳሽ ጋር ስንጋባ የተከሳሽ አባት የሆኑት ጣልቃ ገብ ሰጥተውን በጋብቻ ውላችን ላይም ተጠቅሶ ከ1994 ዓ/ም ጀምሮ በይዞታችን ስር ሆኖ ስንጠቀምበት ቆይተናል፡፡ ሰሞንኛ ተብሎ ከሚታወቀው አካባቢ ባለን ይዞታ ላይ ቤት ያለን ሲሆን በመ/ቁ. 15710 እና 14792 በሆኑ መዝገቦች በዚህ ቤት ውስጥ ሆኜ ልጆችን እንደሳደግ ፍ/ቤት አዞልኛል...

 • 100474 civil procedure/ amendment of pleading/ new issues

  በክስ ማሻሻል ሥርዓትና ዓላማ ቀድሞ ዳኝነት ከተጠየቀበት ጉዳይ ፈጽሞ የተለየ ጥያቄ ለማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ፣ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91 ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 342 የሰ/መ/ቁ. 100475   ታህሳስ 20 ቀን 2008 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመስል እንደሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- አቶ ሳምሶን አበራ ጠበቃ ክፍሌ አማረ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ፀሐይ አበራ ጠበቃ አሸናፊ ወጂ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡  ፍ ር ድ   ጉዳዩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን እንደቅደም ተከተላቸው አመልካች እና ተጠሪ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ጉዳዩም ፍቺን ተከትሎ የተነሳ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ነው፡፡ ግራ ቀኙ እያከራከረ ያለው መሠረታዊ ጭብጥም የአሁኑ አመልካች የንብረት ክፍፍል በጠየቀበት ጊዜ ለአሁን ክርክር መነሻ የሆነችውን የሰሌዳ ቁጥር 3-15556 መኪና በተመለከተ መኪናው የተፈራችው በጋብቻ ውስጥ ሳይሆን እንደባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ የተፈራች ስለመሆኑ ለማሳየት አመልካች የክስ ማሻሻያ ጥያቄ አቅርበው ፍርድ ቤቱም ፈቅዶ ክሱ ከተሻሻለ በኃላ ጋብቻ ከመመሰረቱ በፊት ከጥቅምት 1998 እስከ ህዳር 2001 ዓ.ም  አብሮው ይኖሩ እንደነበር ግምት ተወስዶ መኪናው የጋራ ንብረት ነች ተብሎ ተወስኗል፡፡   የአሁኑ ተጠሪ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 91 አቤቱታ የሚሻሻልበት ሥርዓትና ዓላማው ዳኝነት ከተጠየቀበት ጉዳይ ፈፅሞ የተለየ ጥያቄ ለማቅረብ እንደማይፈቀድ፤ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ እንደባልና ሚስት አብረን ኖረን ነበር በዚህ ጊዜ የተፈሩ  ንብረቶች  እንዲከፈል  በሚል  ማስረጃዎች  ጭምር  በመጥቀስ  የቀረበው     ጥያቄ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.256 ድንጋጌን ያላገናዘበ ስለመሆኑ፤ የፍቺ ውጤት...

 • 100651 unlawful enrichment/

  አንድ ሰው በህግ ወይም የሚፀና ውል የሚሰጠው አንዳች መብት እንደሌለ እያወቀ የሌላ ሰው የሆነን ንብረት በእጁ ባደረገ ጊዜ ንብረቱ ሊያፈራ የሚችለውን የገንዘብ ግምት እንዲመልስ ሊወሰን የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ.2178   የሰ/መ/ቁ. 100651   መሰከረም 27 ቀን 2008 ዓ/ም   ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ብርሃኑ አመነው ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- ወ/ሮ መንበረ ሰፈርህ - አልቀረቡም   ተጠሪዎች፡- 1ኛ. ወ/ሮ ብርሃኔ ጌቴ የኤርሚያስ ምህረት እና የትዕግስተ ምህረት ሞግዚት 2ኛ. ወ/ሮ ባንቻየሁ አዝመራ የሊዲያ ምህረት እና የውባለም ምህረት ሞግዚት 3ኛ. ወ/ሪት አዜብ ምህረት - አልቀረቡም   መዝገቡ ለምርምራ የተቀጠረ ሲሆን መርምረን ተከታዩን ወስነናል፡፡    ፍ ር ድ   ከግራ ቀኙ የቀደመ ክርክር እና በሰበር መ/ቁ.78774 ጥር 29/2005 ዓ/ም ከተሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ መረዳት እንደሚቻለው አመልካች ከሟች አቶ ምህረት ታዬ ጋር በተደረገ የጋብቻ ውል የክርክሩን ንብረት የጋራ አድርገናል ቢሉም የጋብቻ ውሉ በፍርድ ቤት ያልጸደቀ በመሆኑ ምክንያት ንብረቶቹ የውርስ ሀብቶች ናቸው በሚል ለወራሾች /ለተጠሪዎች/ እንዲያስረክቡ ተወስኗል፡፡   ከዚህ በኋላ አመልካች ከሟች ባለቤታቸው ጋር በጋብቻ አብረው ሲኖሩበት የነበረውን የመኖሪያ ቤት ተጠሪዎች የኪራይ ግምት አውጥተው ሟች ከሞቱበት ሚያዝያ 30/2000 ዓ/ም ጀምሮ እስካስረከቡበት ጊዜ ድረስ የሚታሰብ ኪራይ እንዲከፍሉ እና ንብረቱንም እንዲያስረክቡ ተጠሪዎች በአመልካች ላይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ክስ አቅርበዋል፡፡ ፍ/ቤቱም አመልካች ኪራይ አልከፍልም በማለት የሚከራከሩት ሚስት ነኝ በሚል ቢሆንም ሚስት የሆኑት እስከ ሟች እለተሞት ብቻ ነው ፤ ሟች ከሞቱበት ጊዜ ጀምሮ በንብረቱ ምንም መብትና ጥቅም ሳይኖራቸው በቤቱ መቀመጣቸው የህግ ድጋፍ የለውም ፤ በቤቱ ኪራይ መጠን ላይ ያቀረቡት ክርክርም የለም፡፡ በማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2162 መሰረት...

 • 100931 law of person/ incapacity/ sale of immovable property

  እብደቱ በግልጽ ያልታወቀ ሰው ወራሾች ወይም ባለገንዘቦች ይህ ሰው የፈጸመው ውል ጉድለት የሌለበት ፈቃድ አልሰጠበትምና ውሉ ሊፈርስ ይገባል ሲሉ እብደቱን ምክንያት በማድረግ የውሉን መፍረስ መጠየቅ የማይችሉ ስለመሆኑ፡- የማይንቀሳቅስ ንብረት ሽያጭ ውልን ዋጋ ተጎዳሁ በሚል ምክንያት ሊፈርስ የማይችል ስለመሆኑ፡- የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ሕ/ቁ. 348፣347/1//2/፣349፣350፣341፣342 የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2887   የሰ/መ/ቁ. 100931 ታህሳስ 18 ቀን 2008ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመስል እንደሻው አዳነ ቀንዓ ቂጣታ አመልካች፡- አቶ ጥላሁን ዓለሙ ጠበቃ አቶ ተስፋሁን ጸጋዬ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ደረጀ ማሞ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   1. ጉዳዩ የቀረበው አመልካች ወላጅ እናቴ ሟች ወ/ሮ ዘውዴ በየነ የአእምሮ በሽተኛ በነበሩበት ጊዜ የፈጸሙት የቤት ሽያጭ ውል ፈራሽ ይደረግልኝ በማለት ያቀረቡትን ጥያቄ የበታች ፍ/ቤቶች ውድቅ ያደረጉት በህግ አግባብ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ በመጀመሪያ የታየው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው፡፡ በስር ፍ/ቤት አመልካች በከሳሽነት ቀርቦ ሟች እናቴ ወ/ሮ ዘውዴ በየነ በአእምሮ ህመም ምክንያት በአማኑኤል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲታከሙ ቆይተው፣ ጤናማ አእምሮ ሙሉ ፈቃዳቸውን ለመስጠት በማይችሉበት ሁኔታ በቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 02 ቁጥሩ 1020 የሆነውንና በስማቸው ተመዝግቦ የሚገኘውን ቤት ሰኔ 18 ቀን 2001 ዓ.ም በብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ ለተከሳሽ ሸጠውላቸዋል፡፡ ሟች እናቴ በአእምሮ ህመም ሲሰቃዩ ቆይተው ከዚህ ዓለም በ2003 ዓ.ም በሞት ተለይተዋል፡፡ ስለዚህ እናቴ የአእምሮ ህመምተኛ በሆኑበትና ፈቃዳቸውን ለመስጠት በማይችሉበት ሁኔታ በእርካሽ ዋጋ ቤታቸውን ለተከሳሽ (ተጠሪ) ለመሸጥ የተዋዋሉት ውል...

 • 101053 contract/ rent/ cost of maintainance

  በአከራይና ተከራይ መካከል በሚደረግ የኪራይ ስምምነት መሠረት አከራዩ ለተከራዩ ባከራየው ቤት ላይ ስለተደረገው ጥገና /ማሻሻያ/ አከራይ የሰጠው ስለመሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ አከራዩ ለተከራዩ አወጣሁ ያለውን ወጪ የመክፈል ኃላፊነት የሌለበት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 555/2000 አንቀጽ 6/3/ የፍ/ብ/ሕ/ቁ አንቀጽ 2917፣2973/1/፣2912 የሰ/መ/ቁ. 101053 ታህሳስ 22 ቀን 2008 ዓ/ም   ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ አመልካች፡- የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ - ነ/ፈጅ ጌታቸው መንትስኖት ተጠሪ፡- አቶ የምሩ ነጋ - ጠበቃ አሳምነው አረጋ መዝገቡን መርምረን ተከታን ወስነናል፡፡    ፍ  ር ድ   ጉዳዩ በኪራይ የተያዘን ቤት ጥገና መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ ታህሳስ 10 ቀን 2004 ዓ/ም ባቀረበው ክስ መነሻ ነው፡፡   የክሱ ይዘትም ንብረትነቱ የአሁኑ አመልካች የሆነ በቦሌ ክ/ከተማ ቀበሌ 20 የሚገኝ የቤት ቁጥሩ 695 የሆነ ቤት ተከራይቼ እንዳድሰውና ለዕድሳት የማወጣው ወጭ ከቤቱ ኪራይ እንዲታሰብልኝ ለመ/ቤቱ የቦርድ አመራር አመልክቼ ቦርዱ ህዳር 29/1998 ዓ/ም በፈቀደልኝ መሰረት የቤቱን ጥገና ለማካሄድ ከንኮማድ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/ግል ማህበር ጋር ተዋውዬ ለቤቱ ጥገና ብር 1,415,604.80 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ አስራ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አራት ከ80/100) ወጪ አድርጌ ሳስጠግን የቆየሁ ቢሆንም ተከሳሽ ሀምሌ 18/2000 ዓ/ም በጻፈው ደብዳቤ ዋናውን የቤቱን አካል በማፍረስ በህገ-ወጥ መንገድ ግንባታ እያደረጉ ነው የሚል ምክንያት በመስጠት በአዋጅ ቁጥር 555/2000 የተሰጠውን ስልጣን ያላግባብ ተጠቅሞ ሀምሌ 23/2000 ዓ.ም በፖሊስ ኃይል አስለቅቆ ቤቱን የወሰደው ስለሆነ...

 • 101618 criminal law/ forgery

  አንድ ሰው በሀሰት የተዘጋጀን ወይም የተለወጠን ሰነድ እያወቀ የተገለገለበት ካልሆነ በቀር የወንጀል ኃላፊነት የሌለበት ስለመሆኑ፣ የወ/ሕ/ቁ 378

 • 101631 civil procedure/ execution of judgment

  አንድ ፍርድ የማይፈፀምበት ምክንያት ያለመኖሩ ሲረጋገጥ ለአፈፃፀም ተስማሚ በሆነ መንገድ ፍርድ እንዲፈፀም ትእዛዝ መስጠት የሚቻል ስለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 392(1)   የሰ/መ/ቁ. 101618   ታህሳስ 19 ቀን 2008 ዓ.ም   ዳኞች ፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመስል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- የደቡብ ብ/ብ/ሕ/መ/ፀረ- ሙስና ኮሚሽን - ዐ/ህግ የቀረበ የለም ተጠሪ፡- መስከረም ፋንታዬ የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ይህ የሰበር ጉዳይ መንግስታዊ ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀትና ወደ ሐሰት መለወጥ የሙስና ወንጀል ድርጊትን የሚመለከት ክርክር ነው፡፡ የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ፡- የሥር ከሳሽ /የአሁን አመልካች / ለጌድኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ ተከሳሽ የወንጀል ሕግ ቁ. 379/1/ሀ በመተላለፍ ተከሳሽ በ26/03/2001 ዓ.ም የንግድ ሥራ ፈቃድ ቁጥር የተጠቀሰ የንግድና ኢንዲስትሪ ቢሮ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ክትትልና ድጋፍ አሰጣጥ የሥራ ሂደት በሚል የሚጀምር እና በሀሮ ወላቦ ክ/ከተማ ንግድ ምዝገባና ፍቃድ ክትትልና ድጋፍ አሰጣጥ የስራ ሂደት የተዘጋጀ በማስመሰል በስሙ የተዘጋጀ የቡና አቅራቢነት ሀሰተኛ ንግድ ፈቃድ በሀሰተኛ ክብ ማህተም፣ ሀሰተኛ ስምና ስልጣን ቲተሮች የተዘጋጀውን ሰነድ በመያዝ በቀን 18/08/2005 ዓ.ም 9፡30 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ ከሀሮ ወላቡ ክ/ከተማ ንግድ ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ወደ ጌድኦ ዞን ንግድ ማስፋፊያ ይዛወርልኝ በማለት ሲገለገል ሊያዝ ችሏል ፡፡ በመሆኑም ተከሳሹ የሕዝብ ጥቅም የሚሰራበት ሰነድ ላይ በሀሰት የተዘጋጀ ስለመሆኑ እያወቀ በመገልገሉ በፈጸመው መንግስታዊ ወይም ወታደራዊ ሰነዶችን አስመስሎ በማዘጋጀት ወይም ወደ ሀሰት መለወጥ የሙስና ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ የሥር ተከሳሽ/ የአሁን ተጠሪ/ ፍ/ቤት ቀርቦ ይህ ክስ ተነቦለት የመጀመሪያ ደረጃ...

 • 101675 labor dispute/ scope of labor proclamation/ foreign employment/ period of limitation

  በውጭ ሃገር ስለሚኖር የስራ ውል የግል አገልግሎት(በውጭ ሃገር ለተሰጠው አገልግሎት) ተፈፃሚ ሊሆን የሚገባው ህግ ስለስራና ሰራተኛ ማገናኘት አገልግሎት የወጣ አዋጅ 632/2001 ስለመሆኑ በዚህ አይነት የውል ግንኙነት ውስጥ የሚቀርብ የክፍያ ጥያቄ በአስር አመት ይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 1677(1) እና 1845

 • 102056 civil procedure/ opposition/ appeal procedure

  በክርክሩ ተካፋይ ያልሆነውን ወገን የሚጎዳ ውሳኔ የተላለፈው ጉዳዩን በተዋረድ ባየው የሰበር ችሎት በሚሆንበት ጊዜ ይህ በክርክሩ ተካፋይ ያልሆነው ወገን አለኝ የሚለውን መብት ለማስከበር ይችል ዘንድ መብቴን ተጋፍቷል በሚለው ሰው ላይ በስሙ ቀጥታ ክስ በመመስረት መብቱን ከማስከበር ውጪ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.358 መሰረት ተቃውሞውን ለሰበር ችሎቱ ሊያቀርብ የሚችል ስላለመሆኑ የሰ/መ/ቁ. 102056 ታህሳስ 18 ቀን 2008 ዓ.ም           አመልካች፡- አቶ ሳምሶን ካሳዬ - የቀረበ የለም ተኽሊት ይመስል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ ተጠሪ፡- 1. ወ/ሮ መሰረት ግርማ - ተወካይ ኃይሉ ቦሰት ቀረቡ 2. አቶ ሳሙኤል ካሳዬ 3. አቶ ኢሳያስ ካሳዬ     ቀረቡ 4. ወ/ሮ ሜላት ካሳዬ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡  ፍ ር ድ ጉዳዩ የውርስ ንብረት ይለቀቅልኝ ጋር ተያይዞ የተሰጠው ውሳኔ ላይ የቀረበውን የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በአደአ ወረዳ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ነው፡፡ አመልካች በዚህ ፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ በ17/04/2006 ዓ/ም የተፃፈ ሁኖ 1ኛ ተጠሪ ተከሳሽ፣ የአሁኑ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተራ ያሉት ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረው በመ/ቁጥር 24515 በ16/10/2002 ዓ/ም የተሰጠው ውሳኔ ከእናቴ ከወ/ሮ ፀሐይ ገብሬ በውርስ ሊተላለፍልኝ በሚገባ ንብረት ላይ የተሰጠና መብቴን የነካ ነው በሚል ምክንያት ውሳኔ ተነስቶ የክርክሩ ተካፋይ ልሆን ይገባል የሚል ሲሆን የአሁኑ ሥር ፍርድ ቤትም ለፍርዱ መሰረት የሆነው ንብረት ላይ የተሰጠው ውሳኔ የተፈጸመ ነው በሚል ድምዳሜ የአመልካች የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ በመዝገቡ ሊስተናገድ እንደማይችል፣ ሆኖም አመልካች መብታቸውን ቀጥታ ክስ አቅርበው ማስጠበቅ የሚችሉ መሆኑን ጠቅሶ የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አድርጎባቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ የአሁኑ አመልካች ይግባኛቸው ለምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን...

 • 102662 family law/ divorce/ common property/ period of limitation

  ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል ሊባልባቸው ስለሚችሉባቸው ሁኔታዎች ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል ተብሎ ከሚታሰብበት ጊዜ አንስቶ በአስር ዓመት ጊዜ ውስጥ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ካልቀረበ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ   የሰ/መ/ቁ.102662 የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ/ም ዳኞች፡-አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- ወ/ሮ አልማዝ ለሼ- ጠበቃ ኤርሚያስ ደስታ ቀረቡ፡፡ ተጠሪ፡- አቶ በቀለ በላቸው- ወኪል  ትርፍነሽ በቀለ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡  ፍ ር ድ   ጉዳዩ ጋብቻ ፈርሷል ሊባል የሚችልበትን አግባብ የሚመለከት ነው፡፡ጉዳዩ የተጀመረው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደብረብርሃን ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን ክሱን ያቀረቡት የአሁኑ አመልካች ናቸው፡፡ የክሱ ይዘትም፡- ከአሁኑ ተጠሪ ጋር በአገር ባህል የጋብቻ አፈጻጸም ስርዓት ጋብቻ ፈጽመው ለአርባ አመታት ያህል አብረው መኖራቸውን፣ ይሁን እንጂ ከመስከረም 2006 ዓ/ም ጀምሮ ሊስማሙ ባለመቻላቸው በመካከላቸው ሰላም እንደሌለ ገልፅው ጋብቻው ፈርሶ የጋራ ንብረት እንዲካፈሉ ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስም ከአመልካች ጋር ባልና ሚስት የነበሩ መሆኑን ሳይክዱ አመልካች ከአስራ ዘጠኝ አመታት በፊት ቤቱን ጥለው መሄዳቸውንና ተለያይተው የሚኖሩ መሆኑን ጠቅሰው ክሱ በይርጋ ሊታገድ ይገባል  በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያስቀደሙ ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድ ደግሞ ከአመልካች ጋር ያፈሩት የጋራ ንብረት የሌለ መሆኑን ዘርዝረው ክሱ ውድቅ ሊሆን ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል፡፡   የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለት የሥር ፍ/ቤትም ጉዳዩን መርምሮ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ ከአስር አመታት በፊት ፈርሷል የሚል ድምዳሜ ደርሶ የአመልካች ክሱ በይርጋ የታገደ ነው በማለት ውድቅ አድርጎታል፡፡...

 • 103049 law of succession/ partition of estate/ valuation

  የወራሾች ድርሻ በክፍያ ጊዜ ሊገመትበት ስለሚችልበት አግባብ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1083 የሰ/መ/ቁ. 103049 ቀን 28/01/2008 ዓ/ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ብርሃኑ አመነው   . ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- ወ/ሮ ሊዕማ ሓዲሽ ተጠሪ፡- አቶ አንዋር ሓዲሽ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ወስነናል፡፡    ፍ ር ድ   በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳዩ የውርስ ንብረትን በተመለከተ የተሰጠን ውሳኔ አፈጻጸም የሚመለከት ነው፡፡ የአፈጻጸም ከሳሽ የተባሉት የአሁን አመልካች በአፈ/ ተከሳሽ የአሁን  ተጠሪ ላይ በወረዳው ፍ/ቤት ንብረቱን ለመከፋፈል የአፈጻጸም ክስ አቅርበዋል፡፡   ጉዳዩ የቀረበለት የመቐለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት አስቀድሞ ሌላ የአፈጻጸም ክስ ተከፍቶ እንደነበር ፤ በቀደመው መዝገብ ንብረቱ በባለሙያ እንዲገመት ተደርጎ ብር 163,349.50 መገመቱን ፤ በዚህ ላይ ከግራ ቀኙ ወገኖች የቀረበ ተቃወሞ አለመኖሩን ፤ ነገር ግን ከወራሾች መካከል አካለ መጠን ያላደረሱ በመኖራቸው እድሜያቸው ደርሶ ቤቱን በጋራ ተስማምተን እንሽጠው መዝገቡ ተዘግቶ ይቆይ የሚል ሃሳብ በማቅረባቸው መዝገቡ ተዘግቶ እንደነበር ፤ ለአፈጻጸሙ ምክንያት የሆነው በፍ/መ/ቁ.03151 ታህሳስ 22/2005 ዓ/ም የተሰጠው ውሳኔ ለአፈ/ከሳሽዋ “በድርሻዋ ይሰጣት” የሚል በመሆኑና ከውሳኔው ውጭ ወደ ሽያጭ የሚኬድበት ህጋዊ አግባብ ባለመኖሩ እና ለአንድ ልጅ ሲባል በቤቱ የሚኖሩ አራት ልጆችን በማስወጣት ቤቱ ይሸጥ ማለት ፍትሃዊነት የለውም በማለት የባለሙያው ግምት ለአምስቱ ወራሾች ተካፍሎ የከሳሽ ድርሻ የሆነው ብር 32,669.09 እንዲከፈላቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ይግባኙ የቀረበለት የከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠው ትዕዛዝ ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሰርዟል፡፡   አመልካች ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ቅሬታቸውን ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ “አመልካች ያላቸውን ድርሻ በገበያ  ዋጋ  ሊያገኙ ይገባል...

 • 103151 family law/ minors/ acts of minor

  ሞግዚት የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ፈጽሞ ሲገኝ ሊወሰዱ ስለሚገቡ ዝርዝር ሁኔታዎች የሕግ ድንጋጌዎችን በመተላለፍ ሞግዚቱ ለሚፈጽማቸው ድርጊቶች፤ ወኪል የሆነ ሰው ከተሰጠው ሥልጣን በላይ በሚሠራበት ጊዜ አግባብነት ያላቸው የውክልና ሕግ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁ.213/1992 አንቀጽ 306፣277 የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2207/1 የሰ/መቁ.103151 መስከረም 24 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ረታ ቶሎሳ ሙስጠፋ አህመድ ቀነዓ ቂጣታ ሌሊሴ ደሳለኝ   አመልካች፡- አቶ ግርማ ብሩ አየለ - ቀረቡ   ተጠሪ፡- አቶ መርዕድ ብስራት - ጠበቃ አበበ ማስረሻ ጋር ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡  ፍ ር ድ   ይህ ጉዳይ የቤት ሽያጭ ውል እንዲፈርስ የቀረበ ክስን መነሻ ያደረገ ክርክር ነው፡፡ የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ፡- የሥር ከሳሽ /የአሁን ተጠሪ/ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ የወላጅ አባቴ እና የ2ኛ ተከሳሽ የጋራ ንብረት የሆነውን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 03 የቤት ቁጥር አዲስ ካረታ ቁ.3329 የሆነውን ቤት 2ኛ ተከሳሽ ከሞግዚትነት ስልጣን ተቃራኒ ሚያዝያ 23 ቀን 2000 ዓ.ም በተደረገ ሽያጭ ውል ለ1ኛ ተከሳሽ በብር 350,000 የሸጠች ስለሆነ 1ኛ ተከሳሽም /የአሁኑ አመልካች/ የከሳሽና የሌሎች ሰዎች የጋራ ንብረት መሆኑን እያወቀ ለቅን ልቡና ተቃራኒ በሆነ መንገድ ስለገዛ የሽያጭ ውሉ እንዲፈርስልኝ፣ 1ኛ ተከሳሽ ቤቱን እንዲያስረክበኝ በማለት አመልክቷል፡፡   ይህን ክስ በተመለከተ ተከሳሾች መልስ እንዲሰጡበት የታዘዘ ሲሆን የሥር 1ኛ ተከሳሽ /የአሁን አመልካች/መጥሪያ ደርሶት የጽሑፍ መልስ ስላልሰጠ ታልፏል፡፡ የሥር 2ኛ ተከሳሽ በሰጠችው መልስ ባለቤቴ ከሞተ በኋላ ልጆች ለማሳደግ የተቸገርኩ በመሆኑ የቤት ሽያጭ ውል ፈጽሜአለሁ፡፡ 1ኛ ተከሳሽም የቤቱን ሸያጭ ገንዘብ እንደውሉ...

 • 103458 pension/ scope of public pension law

  የመንግስት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 714/2003 የተፈፃሚነት ወሰን   የሰ/መ/ቁ 103458 ቀን 27/01/2008 ዓ.ም ዳኞች፡-  ተገኔ ጌታነህ   ተሻገር ገ/ስላሴ ተፈሪ ገብሩ ሹምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- አቶ ጋረድ ለበሰ   ተጠሪ፡- የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡  ፍ ር ድ   ጉዳዩ የጡረታ መብትን የሚመለከት ሲሆን አመልካች በተለየዩ መ/ቤቶች ለ17 ዓመት እና በአ/ብ/ክ/መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ኃላፊ ሆነው ለ1ዐ አመት አገልግለው በራሳቸው ጥያቄ ከሹመት የተነሱ መሆኑን በአዋጅ ቁ 714/2003 አንቀፅ 19/5/ መሰረት ከአንድ የምርጫ ዘመን ያገለገሉና ዕድሜያቸው ከ5ዐ አመት በላይ በመሆኑ የጡረታ መብታቸው እንዲከበርላቸው አሰሪ መ/ቤታቸውን ጠይቀው የተሰጣቸው ምላሽ ፍትሐዊ አለመሆኑን ገልፀው ቅሬታቸውን ለሰሜን/ምዕ/ሪጅን ማ/ዋ/ኤጀንሲ አቅርበው ኤጀንሲው አመልካች ስራቸውን የለቀቁት በራስ ፈቃድ በመሆኑ በአ/ቁ 714/2003 አንቀፅ 19/3/ መሰረት ዕድሜያቸው 55 አመት ሲሞላ ከየካቲት 1/2010 ጀምሮ የጡረታ አበል የሚወሰንላቸው መሆኑን ኮሚቴው የወሰነ ሲሆን፡-   በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅሬታቸውን ለማህበራዊ ዋሰትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የይግባኝ አቤቱታ አቀርበው የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋሰትና ኤጀንሲ የሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ነው በማለት ያፀናው መሆኑን ከቀረበው የአመልካች አቤቱታ እና ውሳኔዎች ለመረዳት ተችሏል፡፡   አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት በይግባኝ አቀርበው ይግባኝ የተባለበት ውሳኔ ጉድለት የለበትም ተብሎ በፍ/ብ/ስ/ስ/ቁጥር 337 የዘጋው ሲሆን አመልካች በዚህ ውሳኔ ተፈፀመ ያሉትን ስህተት በመዘርዘር በዚህ ሰበር ችሎት እንዲታረምላቸው አቅርበዋል፡፡ የአመልካች አቤቱታ ለሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀርባል የተባለው ከአማራ ክልል አዋጅ ቁጥር...

 • 103721 family law/ administration of common property

  በተሻሻለው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የቤተሰብ ህግ መሰረት ባልና ሚስት የጋራ ንብረታቸውን እኩል የማስተዳደር መብት ያላቸውና የጋራ ስምምነት ሳይኖር ንብረትን ለሌላ 3ኛ ወገን በአንደኛው ተጋቢ ፍቃድ ብቻ የተላለፈ ከሆነና ይህንን ስምምነቱን ያልሰጠው ተጋቢ በህጉ በተፈቀደለት ጊዜ ገደብ ውስጥ የይፍረስልኝ ጥያቄውን ካላቀረበ የተፈፀመው ተግባር እንደፀና የሚቆይ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.213/92 አንቀፅ 68፣69   የሰ/መ/ቁ. 103721 የካቲት 03 ቀን 2008 ዓ.ም     ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ   አመልካች፡-  ወ/ሮ ሰሚራ ጀማል ከጠበቃ ሰለሞን ታደሰ ቀረቡ ተጠሪ፡- 1ኛ. አቶ ጀማል እንዲሪስ ከጠበቃ መሰረት ስዩም ጋር ቀረቡ 2ኛ. ወ/ሮ ሉላ አረፈ አልቀረቡም 3ኛ.አቶ ሀጎስ አብዱራህማን በመዝገብ ቤት በኩል እንዲሰሙ ተናግሯል፡፡ መዝገቡ ተመርምሮ ተገቢውን ዳኝነት ለመስጠት ለየካቲት 01 ቀን 2008 ዓ/ም ቀጠሮ የያዘ ሲሆን በዚህም መሰረት መዝገቡን መርምረን በአዳሪ በዚሁ እለት የሚከተለውን  ፍርድ ሰጥተናል፡፡  ፍ ር ድ ይህ የሰበር ጉዳይ በአሁን አመልካችና 1ኛ ተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ በፍ/ቤት የፍቺ ውሳኔ መሰረት መፍረሱን ተከትሉ በአሁን አመልካች የጋራ ንብረት ድርሻ ጥያቄ መነሻ የስር ፍ/ቤቶች የጋብቻ ውጤት በሆነው የንብረት ክርክር ላይ የሰጡትን ዳኝነት በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ክርክር ካስነሳው የውሳኔ ክፍል አንፃር ተመልክቶ የውሳኔውን አግባብነት ከግራ ቀኙና ክርክሩ የሚመለከተው ሆኖ የተገኘው 3ኛ ተጠሪም ካቀረቡት ክርክር ጋር በማገናዘብ አስፈላጊውን ዳኝነት ለመስጠት በሚል የቀረበ ነው፡፡   የጉዳዩም አመጣጥ ባጭሩ እንደሚከተለው ነው በአሁን አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ መካከል ሚያዚያ 21  ቀን 1987 ዓ/ም ተደርጎ የነበረው ጋብቻ ግንቦት 24 ቀን 2003 ዓ/ም  በፍ/ቤት የፍቺ ውሳኔ መፍረሱን ተክትሎ የአሁን...

 • 103787 civil procedure/ execution of judgment

  በፍርድ ባለመብት አማካኝነት የተፈረደን ፍርድ ለማስፈጸም የቀረበው የአፈጻጸም የክስ ማመልከቻ ይፈጸም የተባለውን ፍርድ ብቻ መሰረት ሊያደርግ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 378   የሰ/መ/ቁ. 111086   የካቲት 25 ቀን 2008 ዓ.ም.   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኸሊት ይመስል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጠታ አመልካች፡- የኢትዮጲያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዐ/ህግ ማትሪያሲን ተጠሪ፡- አሚኮ/ሽማቾች የህብረት ስራ ማህበር የቀረበ የለም መዝገቡ መርምረን ፍርድ ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የወንጀል ክስ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረው በአፋር ክልል የገቢርሱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ መነሻነት ነው፡፡ አመልካች  ያቀረበው ክስ አጭር ይዘትም የአሁኑ ተጠሪ የኢፈደሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 34/1/ እና የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 98/1/ሀ/ለ/ የተመለከተውን በመተላለፍ ለሱማሌ ክልል ህዝብ የሚያገለግል የምግብ ሸቀጥ የለውም ምንዛሪ /ፈራኮ ቫሎታ/ ከቀረጥ ነፃ ሆኖ እንዲገባ የተደረገው 400 ኩንታል ስኳር የመመሪያ ቁጥር 25/2002 አንቀጽ 6 እና 7/2/ የተመለከተውን በመተላለፍ ተጠሪ ሆነ ብሎ ህገወጥ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ መመሪያው መሰረት ባለስልጣኑ ባዘዘው መሰረትና ቀን ማጓጓዝ ሲገባው ከተመለከት አላማው ውጭ በመገልገል መብቱን ሽፋን በማድረግ በሌላ ሰው ይዞታ ስር ለማዋዋል በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር በአዋሽ ጉምሩክ ኬላ በመያዙ በፈጸመው ከቀረጥ ነፃ በገባ እቃ አላግባብ መገልገል ወንጀል መከሰሱን የሚያሳይ ነው፡፡   የተጠሪ ድርጅት ወኪል ቀርቦ በሰጠው መልስ ድርጅቱ ወንጀል አለመፈጸሙን፤ በንብረቱ አጓጓዥ ላይ አመልካች ያቀረበው ክስ በብይን ውድቅ ተደርጓል በማለት ተከራክሯል፡፡ የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ክርክር ከመረመረ በኃላ አመልካች ባቀረበው ክስ ስኳሩን ጭነው ሲሄዱ የተያዙ ሹፌሮች በፍ/መ/ቁ/ 03544 ተከሰው...

 • 103826 traffic violation/ execution of judgment

  የትራፊክ ደንብን በመጣስ የሚተላለፍ ቅጣትን ለአፈፃፀሙ ፍ/ቤት ሊቀርብ የሚችል ስላለመሆኑ የትራፊክ ፍሰትን ለመቆጣጠር የወጣው ደንብ ቁጥር 208/2003 አንቀፅ   የሰ/መ/ቁጥር 103826 ቀን 25/01/2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ረታ ቶሎሳ ሙስጠፋ አህመድ ቀነዓ ቂጣታ ሌሊሴ ደሳለኝ   አመልካች፡- አንዋር አህመድ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- የቤ/ጉ/ክ/መ/ፍትህ ቢሮ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የአፈፃፀም ክስ ሂደትን የተመለከተ ነው፡፡ ክርክሩ የተጀመረው ከፓዊ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የፓዊ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት የፍርድ ባለመብት በመሆን በአመልካች ላይ ያቀረበው የአፈፃፀም ክስ ሲሆን ዝርዝሩም አመልካች ያለፈቃድ በማሽከርከር በቀን 12/6/2005 - 13/06/2005 ዓ.ም የትራፊክ ደንብ በመጣስ 5000 ብር የተቀጣ ስለሆነ በቅጣቱ መሰረት ይፈጽምልኝ በማለት አቅርቧል፡፡ አመልካችም ያለአግባብ ስለተቀጣሁ ልፈፅም አይገባም በማለት መልስ ሰጥቷል፡፡ የፓዊ ወረዳ ፍ/ቤት አመልካች በውሳኔው መሰረት ለመፈፀም ፈቃደኛ ስለአልሆነ በስድስት /6/ ወር/ እስራት እንዲቀጣ ገንዘቡን የሚከፍል ከሆነ ደግሞ ከእስራት እንዲፈታ በማለት ይወስናል፡፡   አመልካች በውሳኔው ቅር በመሰኘት ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሲያቀርቡ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የሕዝብ የመንገድ ትራንስፖርት የስነ ስርዓት መቆጣጠሪያ መመሪያ ስራ ጥፋት ሪኮርድ አያያዝና ስለቅጣት ደረጃ በዝርዝር የሚገልፅ እንጅ ይህ ቅጣት ባልተፈፀመ ጊዜ ምን መደረግ እንዳለበት በሕጉ የተገለጸ ነገር ስለሌለ በፍ/ቤት የተሰጠ ምንም ውሳኔ ሳይኖር አመልካች እንዲፈፅም መደረጉ ትክክል አይደለም በማለት ወረዳው ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር በአብላጫ ድምፅ ወስኗል፡፡ ተጠሪ ውሳኔውን በመቃወም ለክልሉ /የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ...

 • 103910 contract/ interpretation of contract

  አንድ ውልን ለመተረጎም አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም የውሉ ድንጋጌ መተርጎም ያለበት በውሉ አስገዳጅ የሆነው ወገን በሚጠቀምበት ሁኔታ ሳይሆን በውሉ ተገዳጅ ለሆነው ሰው ምቹ በሚሆንበት አኳኋን ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1738(1) የሰ/መ/ቁ. 103910 ቀን 28/01/2008 ዓ/ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ብርሃኑ አመነው ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ - አልቀረቡም   ተጠሪ፡- አቶ ሀብታሙ ተመስገን - ጠበቃ አቶ ሙሉ ገ/ስላሴ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ወስነናል፡፡      ፍ       ር ድ   ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ለስልጠና የወጣ ወጪ በውሉ መሰረት ይመለሰልኝ በማለት አመልካች በተጠሪ ላይ ላቀረበው ክስ የተሰጠው ውሳኔ ነው፡፡   ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው በግራ ቀኙ መካከል በቅድሚያ ህዳር 9/2002 ዓ/ም በተደረገ ውል በአመልካች የስልጠና ት/ቤት ውስጥ የሚሰጠውን የቢ 737 አውሮፕላን አካላት ስልጠና ተጠሪ በመውሰድ ለ24 ወራት ለማገልገል ይህን ግዴታውን ባይወጣ ግን የስልጠናውን ወጪ ብር 50,000.00 ለአመልካች ለመክፈል ተስማምቶ ለ 9 ወራት ቀሪ አገልግሎት ሳይስጥ ስላቋረጠ ብር 16,664.00 እንዲመልስ ፣ በሌላም በኩል ሀምሌ 24 ቀን 2002 ዓ/ም በተደረገ ውል ተጠሪ በአሜሪካን ሀገር ቢሲያትል በሚገኘው የቦይንግ ስልጠና ማዕከል የሚሰጠውን የቢ 777 አውሮፕላን አካላት ስርዓተ ትምህርት ለመውሰድ የሚያስፈልገውን ወጪ ብር 389,059.23 አመልካች ለመሸፈን ተጠሪ ደግሞ ስልጠናውን ወስዶ ለ36 ወራት ለማገልገል ይህን ግዴታውን ባይወጣ ግን የስልጠናውን ወጪ ለመክፈል የተሰማማ ቢሆንም ስራውን ጥሎ ስልጠፋ የሁለተኛውን ውል የስልጠና ወጪ ብር 389,059.23 በአጠቃላይ ብር 407,806.23 ከነወለዱ እንዲከፈላቸው እንዲወሰን ዳኝነት...

 • 103940 criminal law/ telecommunication offense

  ህጉ በሚጠይቀው አግባብ ፈቃድ ሳያወጣ ወይም የጸና ፈቃድ ሳይኖረው ከቴሌኮሚኒኬሽን እውቅናና ፈቃድ ወጭ ሶፍትዌሮችን በመገልግል በኢንተርኔት ስልኮች ማስደወል ሊያስከትለው ስለሚችለው ኃላፊነት የቴሌኮሚኒኬሽን አዋጅ ቁጥር 49/1989 ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 281/1994 አንቀጽ 13   የሰ/መ/ቁ. 103940 ቀን 24/05/2008 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል .እንደሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- ወ/ሮ አመለወርቅ ጌታነህ ቀረቡ   ተጠሪ፡- የፌዴራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዐ/ህግ የቀረበ የለም መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡  ፍ ር ድ   ጉዳዩ የወንጀል ክስ የሚመለከት ሲሆን የተጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው፡፡ የአሁኑ ተጠሪ የአሁኗ አመልካች ጨምሮ በ17 ተከሳሾች ላይ ክስ ማቅረቡን መዝገቡ ያስረዳል፡፡ የአሁኑ ተጠሪ በስር ፍ/ቤት 9ኛ ተከሳሽ በነበሩት የአሁኗ አመልካች ያቀረበው ክስ ባጭሩ፡- በንፋስ ስልክ ከተማ ቀበሌ 12/13 የቤት ቁጥር የማይታወቅ ንግድ ቤት ውስጥ ስልክ የማስደወል ፈቃድ ሳይኖራት ከቴሌ ኮሚንኬሽን ሲስተም በመደበቅ ስልክ ማስደወል የሚያስችል  ራስ አዲስ ፒሲቶከር እና ራስ ዳሽን የተባሉ ሶፍትዌሮችና የካርድ ቁጥሮች (Accounts numbers) ከ3ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በመግዛት እንዱሁም ለጊዜው ማን እንዳስመጣው የማይታወቅ ኔት 2ፎን ዲያለር የተባለ ሶፍትዌር በመጠቀም 3ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ከ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ጋር በስውር በመመሳጠር ባዘጋጁት ህገወጥ ተግባር በመታገዝ ወደ ወጭ አገር ስልክ በማስደወል እ.ኤ.አ ከ01/11/2004 እስከ 06/10/2010 ለ5 አመታት ከ339 ቀናት 779,040 ደቂቃዎች ወደ ተለያየ አገራት ከኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን ሲስተም መደበቅ የሚያስችል ቴክኖሎጄ በመጠቀም በህገወጥ መንገድ በማስደወል ብር 7,70,400 (ሰባት ሚሊዮን ሰባት መቶ ዘጠና...

 • 104028 civil procedure/ review of judgment/ period of limitation

  የዳግም ዳኝነት ጥያቄ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለሟሉ ስለሚገባቸው  ጥብቅ መስፈርቶች;- አንድ   ክስ  በይርጋ   መዘጋቱ   ዳግም   ዳኝነት  ጥያቄውን   ለማስተናገድ እንደበቂ ምክንያት/እንደመመዘኛ/ የማይወሰድ ስለመሆኑ:-    የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.6   የሰበር መዝገብ ቁጥር 104028 የካቲት 17 ቀን 2008 ዓ/ም ዳኞች፡-1.አልማው ወሌ   2.ዓሊ መሐመድ   3.ተኽሊት ይመስል   4. እንዳሻው አዳነ   5.ቀነዓ ቂጣታ   አመልካች፡- ወ/ሮ ብዙአየሁ ያለው - ቀረቡ ተጠሪ፡-አቶ ሲሳይ ካሴ   - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የገጠር እርሻ መሬት መብት መሰረት አድርጎ የቀረበውን ይዞታ ይለቀቀልኝ ጥያቄን የሚመለከት የቀረበውን ክርክር በግራ ቀኙ ማስረጃና ከሚመለከተው አካል በቀረበው ማረጋገጫ መሰረት ይዞታው የተጠሪ ነው ተብሎ ከተወሰነ በኋላ ለውሳኔው መሰረት የሆነውና ከሚመለከመተው አስተዳደር አካል የተሰጠው የሰነድ ማስረጃ ሐሰተኛነቱ ከውሳኔው በኋላ ማስረጃውን በላከው አካል ተረጋግጧል በሚል የቀረበውን የዳግም ዳኝነት ይታይልን ጥያቄ የሚመለከት ነው፡፡ ክርክሩ የጀመረው በላይ ጋይነት ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 02162 ሲሆን ጉዳዩ በመጀመሪያ ሲጀመር የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ፣ አመልካች ደግሞ ተከሳሾች ነበሩ፡፡ የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ አመልካችና አመልካች እና አቴ ብርሃን ደመቀ ደግሞ ተከሰሽ ነበሩ የአሁን ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ይዘትም፡- ቁበላይ ገይንት 01 ቀበሌ አስተዳደር መኮቢያ ገብሬኤል ገብር ውሥት ጥሩ 498/ለ እና 501 የሆኑ ቤቶች ግማሹ የሟች አባታችን የአቶ ገብሬ ድንቅነህ ሲሆኑ ወረሾች ነን፣ ግማሹን ደግሞ ሟች ወ/ሮ ብዙነሽ አደራ በኑዛዜ ሰጥተውናል በማለት ቤቱን ተጠሪዎች ያላግባብ መያዛቸውን ዘርዝረው ቤቱ እንዲለቀቅ ይወሰን  በማለት ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚሳይ ነው፡፡ የአሁኑ ተጠሪዎችም ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስ ክሱ በይርጋ የታገደ ነው በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ከማቅረባቸውም በተጨማሪ በፍሬ ነገሩም ተገቢ ነው ያሉትን ክርክር አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱን...

 • 104061 contract/ suretyship/ validity of surety contract

  አንድ የዋስትና ውል ዋሱ ግዴታ የገባበትን ኃላፊነት መጠን ወይም ልኩ ምንያህል እንደሆነ በዋስትና ውሉ ላይ በገንዘብ ካልተገለፀ በስተቀር ዋስትናው ፈራሽ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ-1922(3) የሰ/መ/ቁ.104061   መስከረም 25ቀን 2008ዓ᎐ም   ዳኞች:-አልማዉ ወሌ   ረታ ቶሎሣ ሙስጠፋ አህመድ ቀነዓ ቂጣታ ሌሊሴ ደሣለኝ   አመልካቾች፦ አቶ ፍቅሬ ግርማ ቀረቡ ተጠሪ፦    አቶ ደስታ ጫምሶ አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።    ፍ ር ድ   ጉዳዩ ከዋስትና ውል ጋር ተያይዞ የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩም የጀመረው ያአሁኑ አመልካች በኦሮሚያ ክልል አርሲ ነገሌ ወረዳ ፍ/ቤት የሰበር ክርክሩ ተከፋይ ያልሆነው አቶ አበበ ኤርጊቾ እና ሰበር ተጠሪ ላይ በመሠረተው ክስ መነሻነት ነው።የክሱ ፍሬ ነገርም ባጭሩ፦ግምቱ 20,000 ብር የሆነውን የኢጣሊያን ስሪት እህል ሚዛን 1ኛተከሳሽ በ 24/2/2001 ዓም በተደረገ ኪራይ ውል ወስዶ በኋላ ላይ እንዲመልስ ሲጠየቅ ለመመለስ ፊቃደኛ አልሆነም፣2ኛ ተከሳሽም በበኩሉ ሚዛኑን ለመመለስ ወይም መተካት የዋስትና ግዴታ ገብቷል፣ስለዚህ ተከሳሾቹ ተጠይቀው ሚዛኑን የማይመልሱ ከሆነ በገቡት ግዴታ መሠረት ግምቱን ይክፈሉኝ በሚል ዳኝነት የተጠየቀበት መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን 1ኛ ተከሳሽን በተመለከተ ክሱ ስነ-ስርዓቱን ጠብቆና ተሟልቶ አልቀረበም በሚል ምክንያት ተከሳሹ በወረዳ ፍ/ቤቱ ከክሱ ወጭ መደረጉን ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ ግን ቀርቦ ለክሱ በሰጠው መልስ የገባው የዋስትና ግዴታ የሌለ መሆኑን፣የዋስትና ውል ነውተብሎ በቀረበው ሰነድ ላይ ያለውም ፊርማ የራሱ ያለመሆኑንና የዋስትና ውሉም ራሱ ለምን ያህል ገንዘብ ግዴታ እንደተገባ ስለማያሳይ በፍ/ብ/ህ/ቁ-1922(3) መሠረት ውሉ ፎርማሊቲን አያሟላም ተብሎ ክሱ ውድቅ እንዲደረግ በማለት ተከራክሯል። ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ወረዳ...

 • 104512 environment law/ dangerous substance/ license

  የአካባቢ ጥበቃ መስሪያ ቤት ፈቃድ ሳይዝ ማንኛውንም አደገኛ ቆሻሻን ማመንጨት፣ ማስቀመጥ፣ ማከማቸት፣ ማጓጓዝ፣ ማምከን ወይም ማስወገድ የተከለከለ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 300/95 አንቀጽ 4/1/   የሰ/መ/ቁ/104512 መስከረም 24 ቀን 2008 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ረታ ቶሎሳ ሙስጠፋ አህመድ ቀነዓ ቂጣታ ሌሊሴ ደሳለኝ   አመልካች፡- አቶ አባስ ኢብራሂም   ቀረቡ ተጠሪዎች፡- የሐረር ቢራ አ/ማህበር                              አልቀረቡም መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የንብረት ጉዳት ካሳ ክፍያ ጥያቄን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩም የጀመረው ያሁን አመልካች በሀረሪ ክልል ጠ/ፍ/ቤት በሰበር ተጠሪ ላይ በመሰረተው ክስ መነሻነት ነው፡፡ የክሱ ፍሬ ነገርም ባጭሩ፡- ተጠሪ ኮስቲክ ሶዳና ሃይድሮሊክ አሲድ የተባለ መርዛማነት ያለው ተረፈ ምርት በእርሻ ማሳዬ ላይ አፍስሶ የተለያዩ ቋሚ ተክሎችና ሰብሎቹን በማድረቅ ስላወደመብኝ በዚህ ምክንያት ለደረሰብኝ ጉዳት በድምሩ ብር 1,526,700 ካሳ ይከፈለኝ የሚል ነው፡፡ ተጠሪም በበኩሉ ቀርቦ ለክሱ በሰጠው መከላኪያ መልስ፡- በክሱ የተጠቀሰውን መርዛማ ኬሚካል በአመልካች ማሳ ላይ አለማፍሰሱን፣ ያም ሆኖ ግን የድርጅቱን ፍሳሽ ወይም ተረፈ ምርት የክልሉ አርሶ አደሮች ለእርሻ ማሳቸው በማዳባሪያነት ጠቃሚነቱን ተረድተው እንዲደፋላቸው በጠየቁት መሰረት የተደፋላቸው መሆኑን፣ ተረፈ ምርቱም ለእርሻ ማሳ ማዳበሪያነት ጠቃሚ መሆኑን፣ በጉዳዩ ላይ በሐሮሚያ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ያለው ጥናትም ይህንኑ የሚያረጋግጥ መሆኑንና የጉዳት ካሳ መጠኑም የተጋነነ ነው የሚልና የመሳሰሉትን በማንሳት ተከራክሯል፡፡ ጉዳዩን የተመለከተው የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት በበኩሉ የግራ ቀኙን ክርክርና ምስክሮች ቃል ከሰማ በኃላ በተጨማሪነትም ከክልሉ አካባቢና ጥበቃ ባለስልጣን ጽ/ቤትም ባለሙያ አስቀርቦ በጉዳዩ ላይ ሙያዊ አስተያየቱን ከተቀበለ በኃላ ጉዳዩን መርምሮና ማስረጃውንም ከመዘነ በኃላ የተጠሪ ተረፈ ምርት በአመልካች...

 • 104858 jurisdiction/ land reclamation/ compensation/ Addis Ababa

  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሣ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በምትክ ቦታ ይሰጠኝ ጥያቄ ላይ የሚሰጠው የመጨረሻ ፍርድ የሠበር አቤቱታ ለከተማው ፍ/ቤት ሳይቀርብ ለፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር አቤቱታ የሚቀርብበት የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የከተማው ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 43(5)፣ አንቀጽ 42(2) አንቀጽ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 29(6)   የሰ/መ/ቁ. 104858   ታህሳስ 22 ቀን 2008 ዓ.ም       ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ     አመልካች፡-   አቶ ታደሰ ካሣ - ጠበቃ እንዳልካቸው ይሳቅ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1ኛ. ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር 2ኛ. ቦሌ ክ/ከተማ የመሬት አስተዳደር     አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ወስነናል፡፡  ው ሳ ኔ   የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአዲስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት ከከተማ ቦታ ማስለቀቅ እና የካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ምትክ ቦታን በተመለከተ በተሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ የሚቀርብ አቤቱታን ተቀብሎ ለመወሰን የዳኝነት ሥልጣን የለኝም በማለት ያሳለፈውን ትዕዛዝ በመቃወም ነው፡፡   አመልካች ነሀሴ 27/2006 ዓ.ም ያቀረቡት የሰበር ማመልከቻ ተመርምሮ የአዲስ አበባ አስተዳደር ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ትዕዛዝ ከአዋጅ ቁጥር 721/2003 አንቀጽ 29 እና 30 ድንጋጌዎች አንፃር ተገቢ መሆኑን  ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡ ተጠሪዎች መጥሪያ ደርሷቸውና መልስ ለመስጠትም ቀጠሮ እንዲለወጥላቸው ጠይቀው ነገር ግን መልስ ስላላቀረቡ በፅሑፍ መልስ የማቅረብ መብታቸው ታልፎ መዝገቡ ለምርምራ ተቀጥሯል፡፡ በበኩላችን የከተማው ሰበር ችሎት ያሳለፈውን ትዕዛዝ አመልካች ካቀረቡት ቅሬታ እና ተገቢነት ካላቸው ህጎች ጋር በማያያዝ መርምረናል፡፡ ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው አመልካች በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12...

 • 105054 family law/ common property/ agreement on partition of common property

  አንድ ጋብቻ ሲፈርስ ንብረት ክፍፍልን በሚመለከት በእርቅ ውል ስምምነት በሽማግሌ የተደረገው እርቅ በፍ/ቤት ተመዝግቦ ከተዘጋ በኋላ እንደገና እንደ ባልና ሚስት አብረን እየኖርን ስለነበር በድጋሚ የንብረት ክፍፍል ይደረግ የሚል ጥያቄ አግባብነት ያለው ስላለመሆኑ፣   የሰ/መ/ቁ. 105054 ታህሳስ 22 ቀን 2008ዓ/ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ሙስጠፋ  አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- ወ/ሮ ጌጤ እጅጉ -ቀርበዋል ተጠሪ፡-አቶ ብርሃኑ ተሰማ   -ቀርቧል መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የባልና ሚስት አፈፃፀም የሚመለከት ነው፡፡ ክርክሩ የተጀመረው በሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ፍርድ ቤት ተጠሪ ባቀረቡት የአፈፃፀም ክስ ነው፡፡ የአቤቱታውን ይዘትም ባጭሩ በመ/ቁ.343/96 በቀን 21/8/1996 ዓ/ም የነበረው ጋብቻ ሲፈርስ ንብረት ክፍፍል በሚመለከት በእርቅ ውል ስምምነት በሽማግሌ የተደረገው እርቅ በፍርድ ቤት ተመዝግቦ ተዘግተዋል፡፡ በዚሁ መሰረትም አንድ ወፍጮ ቤት፤ አንድ የዘይት መጭመቂያ ቤት እና አንድ ፒፒሻ ሽጉጥ የተጠሪው እንደሆነ ፍርድ ቤት በውሳኔው አረጋግጠዋል፡፡ ከውሳኔ በኃላ ታርቀን በባልና ሚስት ሆነን ስንኖር የዲገሉና ጢጆ ወረዳ ፍርድ ቤት መ/ቁ.19963 በቀን 9/8/ 2005ዓ/ም እና የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.6054 በቀን 19/10/05ዓ/ም በመ/ቁ. 343/96 በሆነው መዝገብ ላይ የተሰጠ የንብረት ክፍፍል እንዳይነካ ሲል ተወስነዋል፡፡ ስለዚህ የወፍጮ ቤት የነበረው አሁን የእንጨት መሰንጠቂያ የሆነው እና የዘይት መጭመቂያ ቤት ስም ይዛወርልኝ ፒፒሻ ሽጉጥ ታስረክበኝ ወይም ግምቱ 26,000 ብር እንዲከፈለኝ ሲሉ አፈፃፀም መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ የአሁኑ አመልካችም በሰጡት መልስ በ1996 ዓ/ም ባልና ሚስት መሆናችን የማይካድ እውነት ነው፡፡ ትዳር ሲፈርስ ለኔ የተሰጠኝ የያዝኩት እንጂ የተጠሪ አይደለም፡፡...

 • 105211 jurisdiction/ certificate of inheritance/ Addis Ababa City court

  የአዲስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች አስቀድመው የወራሽነት የምስክር ወረቀት ለማግኘት በቀረበ አቤቱታ ላይ ባሳለፉት ውሳኔ የሚነሳን ተቃውሞ አቤቱታ ተቀብለው ለማስተናገድ የሥረ ነገር ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ አዋጅ ቀ/361/1995 አንቀጽ41/ሸ/ አዋጅ 408/96 አንቀጽ 2/ንኡስ ቁ፣1   የሰ/መ/ቁ. 105211 ጥቅምት 1/2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ብርሃኑ አመነው ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካቾች፡- 1. አቶ እንዳለ ደንቦባ   2. አቶ ንጉሴ ደንቦባ   3. ወ/ሪት ውቢት ደንቦባ           ጠበቃ አብዮት አበበ ቀረቡ   4. ወ/ሮ ሽቶ ደንቦባ ተጠሪዎች፡- 1. ወ/ሮ አልማዝ ደንቦባ 2. ወ/ሮ ዘውዲቱ ደንቦባ   3. ወ/ሮ እታፈራሁ ደንቦባ              ጠበቃ ሰለሞን ስዩም ቀረቡ   4. አቶ ጌታቸው ደንቦባ   5. ወ/ሮ ወይንሐረግ ደንቦባ   መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ተወስኗል፡፡    ፍ ር ድ   የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአዲስ አበባ ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪዎች ያቀረቡትን የመቃወም አቤቱታ ተቀብሎ የቀደመ ውሳኔውን በመሻሩ እና ይግባኝ ሰሚውና የሰበር  ችሎቱም ውሳኔው ጉድለት የለበትም በማለት የቀረበላቸውን አቤቱታ ባለመቀበል መዝገቡ በመዝጋተቸው የሕግ ስህተት ተፈፅሟል በሚል ነው፡፡   የአሁን ተጠሪዎች ለስር ፍ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ባላንባራስ ደንቦባ ውፍዬ ህዳር 1996 ዓ.ም ኑዛዜ አድርገዋል ተብሎ ለፍ/ቤቱ ቀርቦ ፍ/ቤቱ ኑዛዜውን በማፅደቅ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ነገር ግን በኑዛዜው ላይ የተጠቀሱት ምስክሮች ኑዛዜው በተደረገበት ዕለት በቦታው ያልነበሩ ኑዛዜው ላይ የፈረሙት ኑዛዜው ከተደረገ በኋላ ቢሮዋቸው ድረስ በሄደላቸው መሰረት በመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 881/3/ የተመለከተውን የሚያሟላ አይደለም፤ በኑዛዜው ተራ ቁጥር 5 የተመለከተው የንግድ ድርጅት ሟች ከባለቤታቸው ጋር ያፈሩት በመሆኑ የራሳቸው ብቻ ባልሆነ ንብረት ላይ ኑዛዜ ማድረጋቸው ተገቢ አይደለም፤ ለመቃወም አመልካቾች የተናዘዙትም ሊደርሳቸው ከሚገባው ድርሻ በታች ነው፤ ስለሆነም ኑዛዜው ፈራሽ ሊሆን ይገባል በማለት የመቃወም አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡   የአሁን አመልካቾች...

 • 105628 contract/ rent/ damage

  የህንጻ ኪራይ ውል ካለቀ በኋላ የታጣ ገቢ የኪራይ ዋጋ በሚያጠራጥር ጊዜ የማዘጋጃ ቤት ባለስልጣኖች በወሰኑት ታሪፍ መሠረት ወይም ታሪፍ የሌለ እንደሆነ የቦታዎች ልማድ በመከተል መወሰን የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ሕ/ቁ. 2950/2/   የሰ/መ/ቁ. 105628 ጥቅምት 24/2008 ዓ.ም ዳኞች ፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመስል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡……… ዩኒቨርሳል ሜታልስና ሚኒራል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጠበቃ ማርሻል ፍ/ማርቆስ ቀረቡ   ተጠሪ፡…………... ባሰፋ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር- የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡  ፍ ር ድ   ይሄ ጉዳይ የሕንጻ ኪራይ ውል ካለቀ በኋላ ያልተከፈለውን ከሕንጻው የታጣ ገቢን ለማስከፈል የቀረበ ክስን መሰረት ያደረገ ክርክር ነው፡፡ የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የሥር ከሳሽ /የአሁን ተጠሪ/ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ የባለ ሁለት ፎቅ ህንጻ ተከሳሽ ህዳር 15 ቀን 2003 ዓ.ም በተሻሻለው የኪራይ ውል ስምምነት የኪራይ እና የተለያዩ ክፍያዎችን ጨምሮ በየወሩ በብር 51,750.00 ተከራይቶ ከህዳር 9 ቀን 2003 ዓ.ም እስከ ህዳር 8 ቀን 2005 ዓ.ም ሲገለገልበት ቆይቶ የውሉ ዘመን እስከሚያልቅ በዚህ አልገደድም በማለት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ተከሳሽ ያለበትን የቤቱን ኪራይ ከፍሎ ቤቱን እንዲያስረክበን ከሰን በ20/03/2005 ዓ.ም ፍርድ ተፈርዶበት ፣ በአፈጻጸም በ30/08/2005 ዓ.ም ሕንጻውን ሊያስረክበን ችሏል ፡፡ ስለዚህ ተከሳሽ በአዲስ የኪራይ ታሪፍ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በቀን በብር 3,333.33 ወይም በወር ብር 100,000.00 ሂሳብ የ172 ቀናት ጊዜ ማግኘት የነበረብንን ገቢ በድምሩ ብር 573,333.28 ከህጋዊ ወለድ ጋር እንዲከፍለን በማለት ጠይቋል፡፡   ይህን ክስ...

 • 105919 contract/ condominium/ exchange of houses

  የኮንዶሚኒየም ቤት የደረሰው ሰው ሌላ የኮንዶሚኒየም ቤት ከደረሰው ሰው ጋር እጣው ከደረሰው አምስት ዓመት ባይሞላውም በልውውጥ(በስምምነት ሊቀያየሩ የሚችሉ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 19/97 አንቀፅ 14(2)   የሰ/መ/ቁ. 105919 ቀን ጥቅምት 4/2008ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ብርሃኑ አመነው ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- ወ/ሮ መኪያ አብደላ -ጠበቃ ቶማስ ወ/ሰንበት ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ጣሰው ሸምሱ                       -ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ የኮንዶሚኒየም ቤት ልውውጥ ውል መሰረት ያደረገ ክርክር ነው፡፡ በስር ፍ/ቤት ከሳሽ የአሁኑ ተጠሪ ሲሆን ክሱም ከአመልካች ጋር ባደረግነው የኮንዶሚኒየም ቤት ልውውጥ ውል መሰረት ቤቱን ታስረክበኝ የሚል ሲሆን አመልካች ክሱ ከደረሳቸው በኋላ ውሉ በተንኮልና በማሳሳት የተደረገ ነው በሚል እንዲፈርስ እንዲወሰን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርበዋል፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ ያከራከረው የፌዴራል የመ/ደረጃ ፍ/ቤት በአመልካች  እና በተጠሪ መካከል የተደረገው የኮንዶሚኒየም ቤት ልውውጥ ውል የሚፈርስበት ምክንያት የለም አመልካች በዚህ የልውውጥ ውል መነሻም ተጨማሪ ብር 9000 (ዘጠኝ ሺ) መቀበላቸው ስለተረጋገጠ በውሉ መሰረት ይፈጸም በማለት ወሰነ፡፡   አመልካች ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው የነበረ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን አከራክሮ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ አጽንቷል፡፡   ለዚህ ሰበር ችሎት አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ሲሆን የሰበር ችሎቱም ኮንኮሚኒየም ቤት የደረሰው ሰው እስከ አምስት አመት ድረስ ቤቱን ለሌላ ሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ ይችላል ወይ? የሚለውን ጭብጥ ከአዋጅ ቁጥር 19/1997 አንቀጽ 14(2) አንጻር ለመመርመር ተጠሪ መልስ እንዲሰጡ አዝዟል፡፡ ተጠሪም በግራቀኙ መካከል የተደረገው የቤት ልውውጥ ውል ያልተሻረ እና ጸንቶ ያለ ስለሆነ ሊፈጸም ይገባል...

 • 106535 contract/ form/ witnesses

  በጽሑፍ የተደረገ ውል ውስጥ እማኞች በመሆን የፈረሙ ምስክሮች ስለ ውሉ መኖር አለመኖር እንዳያስረዱ ክልከላ ማድረግ ተገቢ ስላለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ.2005   የሰ/መ/ቁ.106535 ቀን 17/05/2008 ዓ/ም ዳኞች፡-አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመስል እንደሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- አቶ ረዲ ተፈራ ቀረቡ   ተጠሪዎች፡- 1ኛ አቶ አብሹ በቀለ          የቀረበ የለም 2ኛ አቶ ዳመሳ ኤርጳዛ መዝገቡን ተመርምሮ ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል አዳሚ ቱሉ ወረዳ ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪዎች በመ/ቁ. 21265 በቀረበው ክስ መነሻነት ነው፡፡ የክሱ ይዘት ባጭሩ የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ በሬ ሳይወሰደበት ዳለቻ በሬ ወሰደሃል በሚል ጥቁር ጋሬ የሆነ በሬ ግምቱ 8000 (ስምንት ሺህ) የሚያወጣ እንደወሰደበት የራሱ በሬ ከሌላ ሰው ጋር አግኝቶ የወሰደ ቢሆንም በሬውን አልመለስም በሽማግሌዎች አማካይነት በሬው ለመመለስ በ26/12/2005 በተፃፈ ውል በ03/13/2006 ዓ/ም በሬውን ለማቅረብ ተስማምተው እንደፈረሙ፤ 2ኛ ተጠሪም 1ኛ ተጠሪ በሬው የማይመለስ ከሆነ ዋስ እንደሆነ፣ በተጨማሪነትም 1ኛ ተጠሪ 27/08/2006 ዓ/ም በተፃፈው ውል ብር 6000.00 /ስድስት ሺህ/ ለመክፈል ፈርሞ የተቀበለ ቢሆንም ገንዘቡን ባለመክፈሉ ለመክሰስ እንደተገደደ በመሆኑም የበሬው ግምት 8,000.00 ብር ብድር 6,000.00 ከኪሰራና ወጪ  ጭምር እንዲከፈለው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው፡፡   የአሁኑ ተጠሪዎች በቀረቡት የመከላከያ መልስ 1ኛ ተጠሪ በሬውን አለማግኘቱን በሽማግሌዎች ፊት ተስማምተናል በማለት ያቀረበው ውል በሕግ ተሟልቶ የቀረበ አይደለም፤  03/13/2006 ዓ/ም የተባለው ቀን ስላልደረሰ አመልካች መክሰስ አይችሉም፤ የብድር ውሉ የተባለው    በሐሰት የተዘጋጀ ሰነድ ነው፤ በ2006 ዓ/ም ይበል እንጅ በየትኛው ቀን እንደሚከፈል...

 • 106856 law of succession/ collation

  የሟች ወራሾች ተመላሽ የሚያደርጉት ንብረት ስለሚመለስበት ሥርዓት የፍ/ሕ/ቁ. 1074 እና 1076   የሰ/መ/ቁ. 106856 ጥር 16/2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንደሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ     አመልካች፡- ወ/ሮ እየሩሳሌም ገመቹ ወኪል ሀቢብ መሐመድ   ተጠሪ፡-    ወ/ሪት ሮማን ገመቹ ጠበቃ እንዳርጋቸው ዳኘው ጋር - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩን ፍርድ ተሰጥቷል፡፡  ፍ ር ድ   ጉዳዩ የውርስ ሀብት ነው የተባለው ንብረት ለይቶ ከመወሰን ጋር የተያያዘ የቀረበ ክርክር ሲሆን የተጀመረው የአሁኗ ተጠሪ ባቀረቡት የውርስ ሀብት ይጣራልኝ ጥያቄ መሰረት የውርስ አጣሪ ተሾሞ ጉዳዩን አጣርቶ ለፍርድ ቤት ባቀረበው ሪፖርት መነሻነት ነው፡፡ የውርስ አጣሪው በ29/03/2005 እና ግንቦት 08 ቀን 2005 አሻሽሎ ያቀረበው ሪፖርት ላይ የውርስ ሀብት ንብረት የሆኑና ያልሆኑ ለይቷል፡፡ የውርስ ሀብት ንብረት አይደለም ተብሎ የተለየው እና ለዚህ ክርክር ምክንያት የሆነውን በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በቀድሞ ወረዳ 24 ቀበሌ 15 የቤት ቁጥር 3215 የሆነውን መኖሪያ ቤት ሲሆን የአሁኗ ተጠሪ ቤቱ የውርስ ሀብት ነው በማለት ሲከራከሩ፤ አመልካች በበኩላቸው አውራሻቸው (ገመቹ ውለታ) በሕይወት እያሉ  ቤቱን ለአመልካች የገዙት መሆኑን ገልጸዋል፡፡   የውርስ አጣሪው ባደረገው ማጣራት ቤቱ በ18/05/1994 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ውል በቀድሞ ወረዳ 24 ቀበሌ 15 የኑሮ በህብረት የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር ውስጥ ያለው በ160 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ጅምር ቤት በብር 27,000.00 /ሀያ ሰባት ሺህ ብር/ ከወ/ሮ ከድጃ ሀሰን በአመልካች ስም መገዛቱን አረጋግጠዋል፡፡ በማጠቃለያ አስተያየቱም ቤቱ በሟች ገንዘብ እንደተገዛ ማስረጃ አልቀረበም በሚል ምክንያት የውርስ ሀብት ሊሆን የሚችልበት አግባብ የለም ሲል ደምድመዋል፡፡ የውርስ አጣሪው ሪፖርት የመረመረው የፌዴራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግራ...

 • 107166 criminal law/ rape

  በወንጀለኛ ህግ ቁጥር 627(2) መሰረት በክብረ ንህፅና ላይ የሚደረግ ድፍረት የተበዳይ ክብረ ንፅህና በጥቃቱ መገርሰስ ወይም አለመገርሰስ እንደ መስፈርት ሊቆጠር የሚገባው ስላለመሆኑ   የሰ/መ/ቁ. 107166 ቀን ጥቅምት 4/2008 ዓ.ም     ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ብርሃኑ አመነው ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብራሃ መለሰ አመልካች ፡- መኳንንት ማሞ - አልቀረቡም ተጠሪዎች፡- የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ - አልቀረቡም መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡  ፍ ር ድ   የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 627(1) ተላልፎ እድሜዋ 8 ዓመት የሆናት የግል ተበዳይ ሕፃን ያብስራ አብይ ላይ የግብረሥጋ ግንኙነት ፈፅሟል ተብሎ የቀረበበት ክስ የሥር ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ እና የ16 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት ወስኖበት በየደረጃው ያሉት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ስለፀኑበት ውሳኔው መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ስለሆነ ይታረምልኝ ሲል አመልካች ስለጠየቀ ነው፡፡   የአመልካች የቅሬታ ነጥብ የግል ተበዳይ ክብረ ንፅህና ያልተገረሰሰ ስለሆነ በሙከራ ደረጃ የቀረ ስለሆነ የጥፋተኝነት ውሳኔም ሆነ ቅጣቱ እንዲሻሻል የሚል ነው፡፡   ይህንኑ ጉዳይ ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ያስቀርባል ተብሎ ዐቃቤ ሕግ መልስ ሰጥቷል ፡፡ ዐቃቤ ሕግም የአመልካች ድርጊት በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ተበዳይን ጨምሮ የተረጋገጠ መሆኑን ጠቅሶ በሥር ፍርድ ቤት የተላለፈው የጥፋተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔ በአግባቡ ነው ተብሎ አንዲፀና ተከራክሯል ፡፡በእኛ መኩል ጉዳዩን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምረናል አመልካች የሚከራከረው የሕፃኗ ክብረ ንፅህና አለመገርሰሱ በህክምና ማስረጃ ተረጋግጧል በሚል  ምክንያት ድርጊቱ በሙከራ ቀርቷል በማለት ነው፡፡ከመዝገቡ መገንዘብ የተቻለው አመልካች የተከሰሰበትን የወንጀል ተግባር (ድርጊት) ስለመፈፀሙ በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ የተረጋገጠ ስለመሆኑ ፍሬ...

 • 107805 jurisdiction/ government procurement

  ከመንግስት ገዥና አቅርቦት ጋር በተያያዘ የሚነሳ ክርክር በመጀመሪያ ስልጣኑ የማየት መብት ያለው የመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ ቅሬታ ሰሚ ቦርድ እንጂ የመደበኛ ፍ/ቤት ስላለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 649/2001 አንቀፅ 75(1) አዋጁን ለማስፈፀም የወጣው መመሪያ አንቀፅ 49(1)   የሰ/መ/ቁ. 107805   ጥቅምት 04 ቀን 2008 ዓ.ም   ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ   ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ     አመልካች፡-   ጄዳው አማካሪ አርክተክቶችና መሐንዲሶች ባለቤት አቶ ዳንኤል አሰፋ ጠበቃ አለሙ ገበየህ - ቀረቡ ተጠሪ፡- 1ኛ. የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ነገረ ፈጅ አቶ ፋሲል ተሰማ - ቀረቡ 2ኛ. የኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር - አልቀረቡም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፤ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ይህ የሰበር ጉዳይ በአስተዳደር አካል የተወሰነ ጉዳይ በመደበኛ ፍ/ቤት ቀርቦ ሊታይ የሚችልበትን የአቤቱታ አቀራረብ ሥርዓትና ቅሬታውን ተቀብሎ የማየትና የመወሰን ሥልጣን ያለው በየትኛው ደረጃ የተዋቀረው ፍ/ቤት ነው? የሚለውን አስመልክቶ ግራ ቀኙ ከተከራከሩበት ጉዳይና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ህጎች ጋር በማገናዘብ ለይቶ ለመወሰን በሚል የቀረበ ነው፡፡   የጉዳዩም መነሻ የአሁን አመልካች በአሁን 1ኛ ተጠሪ ላይ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በቀጥታ ያቀረበው ክስ ሲሆን የክሱም ይዘት ተከሳሹ ለብሔራዊ ስታድየም ግንባታ የሚሆን የዲዛይን ሥራ ፈልጎ ባወጣው የጨረታ ውድድር መሠረት ተወዳዳሪ አሸናፊ ሆኛለሁ በጨረታ ሰነዱ (በዝክር ተግባሩ) መሠረት ሥራው ለ2ኛው ዕጩ ተወዳዳሪ ሊሰጥ የሚችለው አሸናፊው በእርሱ ምክንያት ሥራውን ለማከናወን አለመቻሉ የተረጋገጠ እንደሆነ ብቻ መሆኑ ተገልፆ እያለ ተከሳሹ በህገ-ወጥ መንገድ ጨረታ እንደገና እንዲደረግ የሚያስችል ተግባር በሚከናወን በሁለተኛ ደረጃ ለተሰየመው ተወዳዳሪ ሰጥቶ በዚሁ መሠረት እያከናወነ ስለሚገኝ ይህንኑ ተግባሩን አቁሞ...

 • 107838 civil procedure/ amendment of pleading/ summon

  አንድ ተከሳሽ በከሳሽ በመጀመሪያ ክስ ሲቀርብበት መጥሪያ ደርሶት በተከራከረበት እና ከሳሽ ክስ ያሻሽል ተብሎ በተዘጋ መዝገብ ላይ ክሱ ተሻሽሎ መዝገቡ ከተከፈተ በኋላ ለተከሳሽ በተገቢው መንገድ መጥሪያ ሳይደርስ የሚሰጥ ውሳኔ ስነ- ስርዓታዊ ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. አንቀጽ 94-110   የሰ/መ/ቁ. 107838 ቀን 19/4/2008 ዓ.ም     ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ ፈይሳ ወርቁ አመልካች፡-   1. አቶ ታከለ አርአያ - አልቀረቡም 2. አቶ አብርሃ ተክሉ - ቀርበዋል ተጠሪ፡-  አቶ ደጀን ገ/እግዚአብሔር - ቀርበዋል   መዝገቡን ተመርምሮ የሚከተለውን ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   በዚህ የሰበር አቤቱታ መዝገብ ክርክር አመልካች 1.አቶ ታከለ አረአያ 2.አቶ አብረሃ ተክሉ በቀን 23/3/2007 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 05504 አከራክሮ በቀን 11/2/2007 ዓ.ም የሰጠውን ፍርድ በመቃወም የቀረበ ነው፡፡ ቅሬታቸውም የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የአሶሳ ከፍ/ፍ/ቤት መጀመሪያ የቀረበው ክስ መጥሪያ ደርሶን ከቀረብን በኃላ በፍ/ቤቱ ክሱ እንዲሻሻል ታዞ መዝገቡን ዘግቶታል፡፡ ክሱ ተሻሽሎ መዝገቡ ሲንቀሳቀስ ግን የአሁን ተጠሪ (ከሳሽ) አድራሻችንን እያወቀ የሁመራ ቤት ሲታገድ መጥሪያ ሊሰጠን ሲችል በቤታችን ላይ መለጠፍ ሲቻል ፍ/ቤት ግቢ ውስጥ መጥሪያውን በመለጠፍና በጋዜጣ ጥሪ ማስደረጉ ሆን ብሎና ተገቢ አለመሆኑን መገንዘብ ሲቻል የስር ፍ/ቤት በሌለንበት የተሰጠው ውሳኔ ይነሳልን ብለን ያቀረብነውን ማመልከቻ ውድቅ ማድረጉ ስህተት በመሆኑ ይታረምል የሚል ነው፡፡ መዝገቡ ተመርምሮ አመልካቾች መጀመሪያ ክስ ሲቀርብባቸው ቀርበው መልስ የሰጡ ሲሆን በሌሉበት ይታይ የሚል ትዕዛዝ የተሰጠው ተጠሪ ክስ አሻሽሉ ተብለው መዝገቡ ከተዘጋባቸው በኃላ ባቀረቡት የተሻሻለ ክስ ጊዜ አመልካቾች ከአካባቢው...

 • 108251 extracontractual liability/ damage assessment/ equity

  የካሳን መጠን በርትዕ ለመወሰን የሚያስገድድ ሁኔታ በገጠመ ጊዜ መጠኑን ለመወሰን የጉዳት ካሳው መጠን ከጉዳቱ ተመጣጣኝ ይሆን ዘንድ ሚዛን ላይ ሊቀመጡ የሚገባቸው መለኪያዎች ሊኖሩ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ.2102 እና 2153   የሰ/መ/ቁ. 108251 ቀን ጥር 5/2008ዓ.ም ዳኞች፡-  ተሻገር ገ/ስላሴ   ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ ፈይሳ ወርቁ አመልካች፡- የኢትዮጵያ መንገድ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የጎዴ ደናን መንገድ ፕሮጀክት   -ነ/ፈ አብርሃም አሰፋ ቀረቡ፡፡ ተጠሪ፡- አቶ አመካክ ከሊፋ                       -አልቀረቡም፡፡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ወስነናል፡፡    ፍ ር ድ   የሰበር አቤቱታ የቀረበው የሸበሌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. M/S/Sh – 60/2006 ግንቦት 26 ቀን 2007ዓ.ም እንዲሁም የኢትዮጵያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 05-1-185/06 ህዳር 5ቀን 2007ዓ.ም ያሳለፉትን ውሳኔ በመቃወም ነው፡፡   የአሁን ተጠሪ በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ አመልካች ድርጅት በቆፈረው የውሃ መሄጃ ጉድጓድ ልጃቸው መሃመድ አመካክ ከሊፋ ህዳር 12/2006ዓ.ም ጉድጓዱ ውሃ  ሞልቶ በቸልተኝነት ሳይሸፈን በመቅረቱ ምክንያት ገብቶ ስለሞተ ለደረሰባቸው ጉዳት አመልካች ሃላፊ እንዲባልና ልጁ የ4ኛ ክፍል ተማሪ የነበረ ከትምህርት ሰዓት በኋላ በአህያ ውሃ እየቀዳ ለሰፈር ነዋሪዎች በበርሚል 25ብር በመሸጥ በቀን የስምንት በርሚል ብር 200.00 በወር ብር 6000.00 ለቤተሰቡ ገቢ በማስገባት ደረጃ ስለነበር ትምህርቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ታስቦ በጠቅላላ ብር 564,000.00፤ እንዲሁም የሞራል ካሳ ብር 1,000.00 እና የቀብር ማስፈጸሚያ ብር 25,000.00 እንዲከፈላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ የአሁኑ አመልካች ለክሱ መቃወሚያ እና በሃላፊነት ሆነ በጉዳቱ መጠን ላይ የበኩሉን ክርክር አቅርበዋል፡፡   የስር ፍ/ቤት ክርክሩን እና ማስጃዎችን ሰምቶ አመልካች ለጉዳቱ...

 • 108335 rural land/ Oromia region

  በኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ መሰረት ይዞታን የመጠቀም መብት የሚተላለፈው በውርስ ሕግ መሰረት በይዞታው የመጠቀም መብት ላለው የቤተሰብ አባል ሲሆን በዚሁ አግባብ ቅድሚያ የውርስ መብት የሚሰጠው ከመሬቱ በሚያገኙት ገቢ ለሚተዳደሩ(ሌላ መተዳደሪያ)ገቢ ለሌላቸው ወራሾች ሥለመሆኑ የኦሮሚያ የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 130/1999 አንቀፅ 9(1)(2) አዋጁን ለማስፈፀም የወጣው ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀፅ 10(1)   የሰ/መ/ቁ.ጥር 108335 የካቲት 4 ቀን 2008 ዓ.ም.   ዳኞች፡-ተሻገር ገ/ሥላሴ   ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካቾች፡-   1.  አቶ ዓለሙ ስሜ - ቀረቡ 2. ወ/ሮ ታደሱ ስሜ - የቀረበ የለም ተጠሪዎች፡- 1.  ወ/ሮ ብዙነሽ ስሜ - ቀረቡ 2.  ወ/ሮ ፀዳሉ ስሜ -  ቀረቡ 3.  አቶ ተሾመ ሽሜ 4.  ወ/ሮ ሰላማዊት ስሜ         ወኪል 1ኛ ተጠሪ ቀረቡ 5.  ወ/ሮ ወርቅነሽ ስሜ 6.  አቶ ብርሃኑ ስሜ           የቀረበ የለም   መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ በገጠር የእርሻ ይዞታ ላይ የተነሳ የውርስ ይገባኛል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም ከሳሾች የነበሩት የአሁኖቹ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ያሉት ተጠሪዎች በደብረ ሊባኖስ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽ በነበሩት የአሁኑ 1ኛ አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው፡፡የአሁኗ 2ኛ አመልካች በዋናው ክርክር ጊዜ በጉዳዩ በጣልቃ ገብነት የተከራከሩ ሲሆኑ የአሁኖቹ 5ኛ እና 6ኛ ተጠሪዎች ደግሞ በጉዳዩ ላይ የወረዳ ፍርድ ቤቱ በ27/07/2006 ዓ.ም. ውሳኔ ከሰጠ በኃላ በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 358 ድንጋጌ መሰረት ወደ ጉዳዩ የገቡ ናቸው፡፡   ፍርድ ቤቱ በከሳሾች እና በተከሳሽ፣እንደሁም በጣልቃ ገቧ የአሁኗ 2ኛ አመልካች መካከል የነበረውን ክርክር መርምሮ ክርክር ያስነሳውን የእርሻ መሬት፣ እንዲሁም የእንስሳት ግምት ብር 7,000 (ሰባት ሺህ) ከሳሾች እና ተከሳሽ እኩል ይካፈሉ በማለት በመዝገብ ቁጥር 12083...

 • 109206 civil procedure/ admission

  ተከሳሽ የተከሰሰበትን ነገር በሙሉ ወይም በከፊል የሚያምን መሆኑን የገለፀ እንደሆነ በእምነቱ መሰረት ይገባኛል የሚለው ማናቸውም ዳኝነት እንዲሰጠው አመልካች(ከሳሽ) ሊጠይቅ የሚችል ስለመሆኑ የሰ/መ/ቁ. 109206   የካቲት 3 ቀን 2008 ዓ.ም.   ዲኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ   አመልካች - አቶ ፍስሃ እርቅ ይሁን ተጠሪ - አቶ ኪሮስ ስዩም   መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡  ፍ ር ድ ጉዳዩ የገንዘብ ክርክር ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በተጠሪ ላይ በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ነው ፡፡ የክሱ ይዘት ግራቀኙ በነበረን የንግድ ግንኙነት ጀንፈል ቡና በጋራ ገዝተን አስበጥረን ለማእከላዊ ገበያ አቅርበን በመሸጥ ትርፉን ለመከፋፈል ባደረግነው ስምምነት መሰረት ለጀንፈል ቡና መግዣ ብር 122,000.00 (መቶ ሃያ ሁለት ሺህ) ሰጥቸው ቡናው ተገዝቶ አስበጥረን እና በከሳሽ ፈቃድ ማእከላዊ ገበያ ተልኮ በከሳሽ የቡና ሽያጭ ወኪል በአቶ ዘላለም ጥላሁን አማካኝነት ተሸጦ ገንዘቡ በንግድ ባንክ በኩል የተላከልኝ ሲሆን ይህን ገንዘብ አውጥቼ ትርፉን ተሳስበን እስክንከፋፈል ድረስ ሙሉ ገንዘቡን ለተከሳሽ የሰጠሁት ቢሆንም ሂሳብ ተሳስበን ገንዘባችንን ሳንካፈል በመካከላችን አለመግባባት ስለተፈጠረ በ 10/07/2006 ዓ.ም በሽማግሌ ዋና ገንዘቤንና ትርፉን እንዲሰጠኝ አስጠይቄው ቡና መግዣ ብር 122,000.00 (መቶ ሃያ ሁለት ሺህ) እንደሰጠሁት አምኖ ከዚህ ገንዘብ ብር 41,000.00 (አርባ አንድ ሺህ) የሰጠኝ ሲሆን ቀሪውን ብር 81,000.00 (ሰማንያ አንድ ሺህ) ዛሬ ነገ በማለት ሊሰጠኝ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ዋና ገንዘቤንና ትርፉ ታስቦ እንዲከፍለኝ በማለት ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ የአሁኑ ተጠሪም ለክሱ መልስ ሰጥተዋል፡፡  ...

 • 109383 civil procedure/ jurisdiction/ local jurisdiction

  ፍ/ቤቱ የግዛት ስልጣን የለውም በማለት ለሚቀርብለት መቃወሚያ የሚሰጠው ውሳኔ ፍትህን የሚያጓድል ካልሆነ በቀር ይግባኝ ሊቀርብበት የማይችል ስለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ቁ. 10(2) የሰ/መ/ቁ. 109383 የካቲት 2 ቀን 2008 ዓ.ም     ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ   አመልካች - ሳሊሆም ከፍተኛ ክሊኒክ - ተሾመ ጉታ ቀረቡ ተጠሪ - ዶ/ር ዘመኑ ዮሃንስ  - ቀረቡ፡፡   መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡      ፍ ር ድ በዚህ መዝገብ ለተያዘው ክርክር መነሻ የሆነው የአሁን ተጠሪ በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ ሲሆን አላግባብ ከስራ መሰናበታቸው ህገወጥ ነው ተብሎ ልዩ ልዩ ክፍያ እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል፡፡ አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስ ድርጅቱ የሚገኘው በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ከተማ ቀበሌ 02 በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለውም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ እና በፍሬ ገዳዩም ስንብቱ ህጋዊ ነው እንዲባል የበኩላቸውን መከራከሪያ አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ግራቀኙ ተከራካሪዎች በተለያየ ክልል ነዋሪዎች ስለሆኑ የፌዴራል ፍርድ ቤት ጉዳዩን የማየት ስልጣን አለው በማለት መቃወሚያውን በብይን አልፎ በፍሬ ጉዳዩ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ የስራ ዉሉ በአመልካች የተቋረጠው ከህጉ ውጭ ነው፤ ስለሆነም ለተጠሪ የካሳ፤ የስንብት እና የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ በድምሩ ብር 104,730.00 (አንድ መቶ አራት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ) እንዲሁም በክርክሩ ምክንያት በተጠሪ ላይ ለደረሰው ወጪ እና መጉላላት በቁርጥ ብር 500.00 (አምስት መቶ) እንዲከፍል ወስኗል፡፡ ይህን ውሳኔ በመቃወም አመልካች በይግባኝ ተጠሪ ደግሞ በመስቀለኛ ይግባኝ ቅሬታቸውን ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ክርክራቸውን ሰምቶ የስር ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለማየት ስልጣን አለኝ ማለቱና ስንብቱ ህገወጥ...

 • 109441 evidence law/ circumstantial evidence

  የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃ የአስረጅነት ብቃት ያለው ተአማኒነት ያለው ማስረጃ ተደርጎ እንዲወስድ ሚዛን ላይ ሊቀመጡ ስለሚገባቸው ነገሮች   የሰ/መ/ቁ. 109441 ቀን 17/05/2008 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንደሻው አዳነ ቀንዓ ቂጢታ አመልካች፡- ፈይሳ ማም ማሩ የቀረበ የለም ከተበለ በኃላ አዲስ መሀመድ ቀረቡ   ተጠሪ፡-   የፌዴራል   ዐቃቤ  ህግ  -  የቀረበ   የለምመዝገቡን   መርምረን  የሚከተለውን  ፍርድ ተሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   1. ጉዳዩ የቀረበው የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች የወንጀል ህግ አንቀጽ  540 የተመለከተውን በመተላለፍ ሟች ቁምቢ በዳሳን የመግደል ወንጀል ፈጽሟል በማለት የሰጡት የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በህግ አግባብ የተሰጠነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በሰበር አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ በመጀመሪያ  የተያው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፡፡ ተጠሪ አመልካች በወንጀል ህግ አንቀጽ 540 የተመለከተውን በመተላለፍ ግንቦት 3 ቀን 2003 ዓ/ም ሰዓቱ በውል ተለይቶ በውል ባልታወቀ ጊዜ በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 20/21 ሃያት ኮንደሚኒያም ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ አብሮት ከኦሮሚያ ክልል ሰንደፈ ወረዳ ቀርሳ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ወደ አዲስ አበባ የመጣውን ሟች ቁንቢ በዳሳ ምንነቱ ባልታወቀ ነገር ጭንቅላቱን በመምታት በደርሰበት ጉዳት ህክምና ሲከታተል ቅይቶ ሀምሌ 18 ቀን 2003 ዓ/ም ህወይቱ እንደያልፍ በማድረጉ ተራ የሰው መግደል ወንጅ ፈጽሟል በማለት የወንጀል ክስ አቅርቧል፡፡ 2. አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ ወንጀሉን አልፈጸምኩም ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት ተከራክሯል፡፡ ተጠሪ ክሱን ያስረዳልኛል በማለት የሰውና የጽሁፍ ማስረጃ አቅርቧል፡፡ የተጠሪ የሰው ምስክሮች ቃል በተመለከተ ፤ አንደኛ የተጠሪ ምስክር ሟች አጎቷ መሆኑን ገልጻ ግንቦት 3 ቀን 2003 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት አከባቢ ሟች እና ተከሳሽ ከሰንደፋ ወደ አዲስ አበባ ስሄዱ አግኝቻቸው የት ልትሄድ ብየ ሟችን ስጠየቀው ልጄን...

 • 109497 civil procedure/ conciliation/ procedure for conciliation

  ፍ/ቤት በተዋዋዮች መሃል የተደረገን ውል (የእርቅ ስምምነት) ህጋዊነታቸውን ሳይረጋገጥ ሊያፀድቅበት የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ.1731 የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.277   የሰ/መ/ቁ. 109497 የካቲት 3 ቀን 2008ዓ.ም ዳኞች፡-  ተሻገር ገ/ስላሴ   ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ አመልካች፡- አቶ አግማስ ኡመር እና ወ/ሮ ሰብረና ጌታቸው ጠበቃ ይትባረክ  መኮንን ቀርበዋል ተጠሪ፡- አቶ ኡመር አሳዬ እና ወ/ሮ አሰገድ ሃሰን -ጠበቃ መስፍን እሼቱ ቀርበዋል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡  ፍ ር ድ   በዚህ የሰበር አቤቱታ መዝገብ ክርክር አመልካቾች አቶ አግማስ ኡመር እና ወ/ሮ ስብርና ጌታቸው ጥር 26ቀን 2007ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፌ.ከፍ/ፍ/ቤት በመ.ቁጥር 156998  ታህሳስ 20 ቀን 2007ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ ቅር በመሰኘት የቀረበ ነው፡፡ ቅሬታቸውም የውል ስምምነት በተዋዋዮች መሀከል ሕግ መሆኑ ተደንግጎ እያለ የውል ስምምነት የህግና የሞራል ጥሰት እንዲሁም ሌሎች ህጋዊ ምክንያቶች የተጓደሉበት ሁታዎች የተካተቱበት ሲሆን እና እነዚህ ምክንያቶች ከተዋዋዩ በአንዱ ወገን ላይ የመብት ሆነ የግዴታ ተጽእኖ የበለጠ የሚያበዛበት ሆኖ የተገኘ ከሆነ ተቀባይነት የለውም ሊባል ካልተቻለ በቀር የስር ፍ/ቤት ካለበቂ ምክንያት ስምምነታችንን ውድቅ ማድረጉ ተገቢ ባለመሆኑ ይታረምልን የሚል ነው፡፡   በስር ፍ/ቤት የተደረገው ክርክር በአፈጻጸም የፍ/ባለመብቶች (የአሁን አመልካቾች) በፍ/ባለእዳ (የአሁን ተጠሪዎች) ላይ ብር 480,000 እንዲከፍሉን ተወስኖልናል ሲሉ የአፈጻጸም መዝገብ በፌ.የመ.ደረጃ ፍ/ቤት ይከፍታሉ፡፡ ፍ/ቤቱም የአ.ፍ/ባለእዳዎች በውሳኔው መሰረት   እንዲፈጽሙ ያዛል፡፡ የፍርድ ባለመብቶች (የአሁን አመልካቾች) ከፍ/ባለእዳዎች ጋር ሰኔ 13 ቀን2006ዓ.ም በአፈጻጸም ስምምነት አድርገናል፡፡   በዚሁ ስምምነት መሰረት...

 • 109535 brokerage/ service fee

  የድለላ አበል ክፍያ መጠን ከተሰጠው አገልግሎት ጋር ተመጣጣኝ ሊሆን የሚገባ ስለመሆኑ በድለላ አበል መጠን ላይ በሚደረገው ክርክር እንደ ጉዳዩ ዓይነት እና የተሰጠው አገልግሎት እየተገናዘበ የሚወሰን ስለመሆኑ የን/ሕ/ቁ. 59(3)   የሰ/መ/ቁ.109535 የካቲት 24 ቀን 2008 ዓ/ም መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰትተናል፡፡  ፍ ር ድ ጉዳዩ የደለላ አበል ክፍያ የተመለከተ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ ችሎት የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ በቀረበው ክስ መነሻነት ነው፡፡ የክሱ ይዘትም የአሁነ ተጠሪ ከአመልካች ጋር በነበረው የቆየ የኮሚሸን ስራ ግንኝነት በቃል በደረጉት ስምምነት የአመልካች ንብረት የሆነው አንድ ቪላ መኖርያ ቤት ተከራይ ፈልገው እንዲያካራዩላቸው በተለመደው የኮሚሽን ክፍያ አሰራር መሰረት የአንድ ወር  የኪራይ ገቢ በኮሚሽን መልክ ለተጠሪ እንደሚከፈሉ በዚህም በተደጋጋሚ በተደረገው ጥራት ቤቱ ጰጉሜ 02 ቀን 2005 ዓ/ም የሮያል ኖረዊጂን ኤምበሲ ቤቱን ለጽ/ቤቱ አገልግሎት በወር 20,000 ዶላር ሂሳብ ኪራይ በመስማማት መስከረም 23 ቀን 2006 ዓ/ም የ10 ዓመት ኪራይ ውል ስምምነት በመፈራረም ተከራዩ የአንደኛ ኣመት ቅደመ ክፍያ 4,540,800 ብር ለአመልካች የከፈለ ሲሆን አመልካች ግን በስምምነቱ መሰረት መክፈል የሚጠበቅባቸው የአንድ ወር  ኪራይ ሒሳብ ለመክፈል ፈቃደኛ በለመሆኑ የኮሚሽን ክፍያ 378,400.00 ብር ከመስከረም  2006 ዓ/ም ከሚተሰብ 9% ህጋዊ ወለድ ወጪና ኪሳራ እንዲከፍላቸው ዳኝነት መጠየቃቸው የሚያሰይ ነው፡፡ የአሁኑ አመልካች የመጀመርያ ደረጃ መቃወሚ እና በፍሬ ነገሩ መልስ አቅርበዋል፡፡ የመጀመሪያ መቃወሚያ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ የግዘት ስልጣን እንደሌለው ቤቱም የራሰቸው አለመሆኑን የሚገልጽ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በፍሬ ጉዳዩ ከኖርዋይ ኤምበሲ በተደረገው...

 • 110040 law of succession/ representation

  ተተኪ ወራሽ ለመሆን ሊሟሉ ስለሚገባቸው ሁኔታዎች የፍ/ሕ/ቁ. 842(3) የሰ/መ/ቁ/ 110040   የካቲት 3 ቀን 2008 ዓ/ም       ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- 1. ወ/ሮ እሴተማርያም አክሎግ   2. ወ/ሪት ወይንሸት አክሎግ         የቀረበ የለም   3. አቶ መክብብ አክሎግ ተጠሪ፡- የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ይህ ጉዳይ ውርስ ጥያቄ የመመልከት ነው፡፡ አመልካቾች ለአ.አ.ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት የአያታቸው ወ/ሮ ደብረወርቅ ሀ/ሚካኤል ወራሽነት ይረጋገጥልን  በማለት አቅርበዋ፡፡ የአባታቸው ሻለቃ አክሎግ አድማሱ ወራሽነት ያረጋገጡ ሲሆን የወላጅ አባታቸው እናት ወራሽነት ለማረጋጥ የቀረበ አቤቱታ ነው፡፡ወላጅ አባታቸው በ1981 ዓ/ም ከዚህ አለም በሞት የተለዩ ሲሆን አያታቸው ወ/ሮ ደብረወርቅ ሀብተ ሚካኤል የሞቱት ደግሞ በ1978 ዓ/ም ነው፡፡ በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤቱም አያታቹህ ከአባታቹሁ ቀድመው የሞቱ ስለሆነ ተተኪ ወራሽ ልትሆኑ አትችልም በማለት ብይን ሰጥተዋል፡፡ በዚህ ብይን ባለመስማማት አቤቱታቸውን ለአ.አ.ከተማ ይግባኝ ሰሚና ለሰበር ሰሚ ችሎት ቢያቀርብም ተቀባይነት ሳያገኝ በትእዛዝ ሰርዞውታል፡፡ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው፡፡ የአመልካቾች ተወካይ የካቲት 10 ቀን 2007 ዓ/ም በፃፉት  የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ብይን ተእዛዝ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚሉባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል፡፡ ይዘቱም ባጭሩ ወላጅ አባታችን እናቱ ከሞቱ ጀምሮ እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ በህመም ላይ እንደነበረ ለስር ፍርድ ቤቶች አስረድተን እያለን የአያታችን ወራሽነት አታረጋግጡም መባሉ ከፍተኛ የህግ ስህተት ያለበት ነው፡፡ ወላጅ አባታችን ለ3 አመት የአልጋ ቁራኛ ሆኖ የእናቱ ወራሽነት ሳያረጋግጥ ቢቀርም አመልካቾች ተተኪ ወራሾች የአያታችን ወራሽነት...

 • 110150 civil procedure/ security for cost

    ከሳሽ በተከሳሽ ላይ ለሚደርሰው ኪሳራ ዋስ እንዲያሲዝ የሚጠየቀው ከሳሽ በክሱ ምክንያት በተከሳሽ ላይ የሚደርሰውን ኪሳራ ለመክፈል የሚያስችሉ ሁኔታዎች የሚያጠራጥር ሲሆንና ኪሳራውንም ለመክፈል የሚያስችል ሃብት ወይም ገንዘብ የሌለው በሆነ ጊዜ ስለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 200   የሰ/መ/ቁጥር 110150   የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀንዓ ቂጣታ አመልካች፡- አቶ ገ/መድህን ወ/ሚካኤል - ጠበቃ አብይ ጌታቸው ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1. አቶ ግርማይ ፍትዊ - ጠበቃ ወርቅነሽ መንግስቱ ቀረቡ 2. የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ፅ/ቤት - ነ/ፈጅ ሙሴ ዳዊት ቀረቡ   3. የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት   - ዐቃቤ ሕግ ታደሰ አንዳርጌ ቀረቡ   መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   1. ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የውጭ አገር ዜጋ በመሆናቸው ተከራክረው በለቱ  አንደኛ ተጠሪ ለሚደርስባቸው ኪሳራ ዋስትና የሚሆን ብር 5‚500 /አምስት ሺ አምስት መቶ ብር/ እንዲያስይዙ የተሰጠውን ትዕዛዝ አልፈፀመም በሚል የስር ፍርድ ቤት አመልካች በተከሳሾች ላይ ያቀረበውን ክስና መዝገብ መዝጋቱ የሕግ መሰረት ያለው ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ የክርክሩ መነሻ አመልካች ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ነው፡፡ አመልካች ለስር  ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ይዘትም በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ምክንያት ኤርትራዊያን ከአገር ሲወጡ፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 13 የሚገኘውን ቁጥሩ 3018 የሆነ ቤት ለአንደኛ ተከሳሽ /አንደኛ ተጠሪ/ አከራይቸው ነበር ሁለተኛ ተከሳሽ ይህንን ቤት በአንደኛ  ተከሳሽ ሸጦለታል፡፡ የከሳሽ ዕዳ ነው በሚል ከቤቱ ዋጋ በመቀነስ ለሶስተኛ ተከሳሽ ከከፈለ በኋላ ቀሪውን ገንዘብ በብሔራዊ ባንክ በኩል ሲሳብ በስሜ አስቀምጧል፡፡ ከሳሽ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ በመንግስት ፈቃድ...

 • 110549 Rural land/ Tigray region

  በትግራይ ክልል ገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ መሰረት ባለይዞታ አርሶ አደር ይዞታውን የመሸጥ መብት የሌለውና የኸው ተፈፅሞ ሲገኝ ይህ ውል እንዳይረጋ በማንኛውም ጊዜ ተቃውሞ ሊነሳና ጉዳዩ የቀረበለትም ፍ/ቤትም ውሉ ከጅምሩ ህገወጥ መሆኑን አውቆ ውሉ ህጋዊና ተፈፃሚነት የለውም በማለት ሊወሰን የሚገባ ስለመሆኑ የትግራይ የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 55/1994፣ አዲሱ አዋጅ ቁ. 236/2006 የፍ/ሕ/ቁ. 1678፣1716፣1718፣1195 እና 1196     የሰ/መ/ቁ 110549   የካቲት 16 ቀን 2008 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሀመድ ተኸሊት ይመስል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- ወ/ሮ ደመቀች ንርአ  ጠበቃ ኪሮስ  አቢዲ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ጋለመ ረብሶ                      ተወካይ አለ ረብሶ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የገጠር እርሻ መሬት የሚመለከት ሆኖ በአሁኑ ተጠሪ ከሳሽነት የተጀመረው በአላማጣ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ደግሞ ተከከሽ ነበሩ፡፡ ተጠሪ ባቀረቡት ክስ፡- አዋሳኙ በክስ ማመልከቻቸው የጠቀሱትና በአላማጣ ወረዳ፣ ኩልግዘ ለምለም ጣብያ፣ በጆሃን ጎጥ ውስጥ የሚገኘውንና ስፋቱ 33ሜትር በ50 ሜትር የሆነውን የእርሻ መሬት በሕግ አግባብ ከአያታቸው ከሟች ወ/ሮ ሙሽራ አራርሶ ወርሰው የይዞታ ማረጋገጫ ያወጡበት መሆኑን፣ ይዞታውን ለአመልካች በኪራይ እያከራዩ የነበሩ መሆኑን፣ ቦታው ወደ አላማጣ ከተማ ሲገባ ግን ተጠሪ የታመሙበትን አጋጣሚ በመጠቀም የጎጆ መውጫ የነበረ ቦታ በማስመሰል አመልካች ይዞታውን በስማቸው እንዲሆን ማድረጋቸውን ዘርዝረው አመልካች ቦታውን እንዲያስረክቡ ወይም የአስር አመት አላባ፤ የመሬቱን ቋሚ ማሻሻያ ብር 126,500.00(አንድ መቶ ሃያ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ብር) እንዲከፍሉ ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ የአሁኗ አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስም በይዞታቸው ስር ያለው በተጠሪ ክስ ውስጥ አዋሳኙ የተጠቀሰው...

 • 110681 civil procedure/ execution of judgment

  በአፈጻጸም ወቅት አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት በሐራጅ ተሸጦ ከእዳ መክፈያ /ከግራ ቀኙ/ ይካፈሉ በተባለበት ጊዜ የሐራጅ ማስታወቂያ የፍ/ባለመብትን ጥቅም ላይ በቀጥታ ጉዳት እስካላደረሰ ወይም የሚያደርስ መሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የሐራጅ ማስታወቂያው ተገቢ ለሆነ ቀን በአየር ላይ አልዋለም ወይም በጨረታው ለሚሳተፉ ሰዎች በቂ ጊዜ አልተሰጠም የሚባልበት ሁኔታ አለመኖሩ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. አንቀጽ 445   የሰ/መ/ቁ.114043 የካቲት 18 ቀን 2008 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- የኢትዩጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አቃቤ ሕግ ዐ/ህግ መብት አየሁ ቀረቡ ተጠሪ፡- አባዲ ሞገስ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ እና በአቶ ንጉሴ ገ/ሕይወት ላይ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአውሲረሱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው፡፡ የክሱ ይዘትም፡- ተከሳሾች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1(ሀ) እና(ለ) እንዲሁም የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀጽ 166 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ሆነ ብለው ሕገ ወጥ ጥቅም ለማስገኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ ወይም ማወቅ ሲገባቸው ንብረትነቱ የ2ኛ ተከሳሽ(ንጉሴ ገ/ሕይወት) የሰሌዳ ቁጥር 2-A01474 አ.አ የሆነች የቤት መኪና የቀረጥና ታክስ ስሌቱ ብር 170,958.10(አንድ መቶ ሰባ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስምንት ብር ከአስር ሳንቲም) የሚያወጣ የኮንትሮባንድ እቃ በ2ኛ ተከሳሽ እና በሌሎች ግብረአበሮች አማካኝነት ጭኖ በመያዟ እና 2ኛ ተከሳሽም የመኪናው ባለቤት በመሆኑ እና የኮንትሮባንድ ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታዬ ባለበት ሁኔታ እና ጉዳዩ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲያስገኝ...

 • 111086 criminal law/ retroactive of criminal law

  በቀድሞ ህግ እንደ ወንጀል የሚቆጠር ድርጊት በአዲሱ ህግ የወንጀል ድርጊት መሆኑ ቀሪ ከሆነ ጉዳዩ በወንጀል የሚታይበት አግባብ ስላለመኖሩ በአዲሱ የገቢዎችና ጉምሩክ አዋጅ መሰረት ከቀረጥ በነፃ በገባ እቃ አላግባብ መገልገል የወንጀል ተጠያቂነት ሳይሆን አስተዳደራዊ ተጠያቂነት ብቻ የሚያስከትል ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 5(3) አዋጅ ቁ.622/2001 አንቀፅ 98(1)(ሀ)(ለ) የጉሙሩክ አዋጅ ቁ.859/2006 አንቀፅ 163(1)(ሀ)(ለ)

 • 111216 law of succession/ liquidation of succession/ funeral expenses

  የሟች ንብረት (የውርስ ሃብት) ወደ ወራሾች የሚተላለፈው በመጀመሪያ የሟች እዳ ከተከፈለ ብቻ ስለመሆኑ፤- ሟች ከሞተ በኋላ ለቀብር ማስፈፀሚያ የሚወጡ ወጪዎች ከውርሱ ክፍፍል በፊት መከፈል ያለባቸው ስለመሆኑ፡- የፍ/ሕ/ቁ.1014   የሰ/መ/ቁ.111216 ቀን የከቲት 15/2008 ዓ/ም ዳኞች፡-አልማው ወሌ   ዓሊ መሀመድ   ተኽሊት ይመሰል   እንደሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ   አመልካች፡- ወ/ሮ ኤልሳቤት አህመድ ተወካይ ፀሃይነሽ አህመድ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ማፈኛ አባዩ ቀረቡ መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፈርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   በዚህ ጉዳይ አከራከሪ የሆነው ጭብጥ የውርስ እና የሚስት ግማሽ ድርሻ ንብረት ክፍፍል ከመደረጉ በፊት ሟች ከተቀበሩበት ቀን ጀምሮ እስከ 80 ቀን ድረስ ያለውን ውጪ በእኩል ለመካፈል የተደረገው ስምምነት መሠሰረት ተደርጎ የስር ፍርድ ቤቶች የአሁኗ አመልከች የብር 153,040.00 ግማሽ ይክፈሉ በማለት የሰጡት ትእዛዝ በህጉ አግባብ ነው ወይስ አይደለም? የሚል ነው፡፡   አመልካች ውሉን እንዳልተስማሙበት የተከራከሩ ቢሆንም የስር ፍርድ ቤት የቀረበው ውል ሪፖርት እንደተቀበለ፤ በቀረበው ውል መሠረት ሟቹ ከተቀበሩበት ቀን ጀምሮ እስከ 80 ድረስ ያለው ወጪ ብር 153,540.00 እንደሆነ፤ በፍ/ህ/ቁ. 1014 መሠረት ወጪ ከውርስ ንብረት ክፍፍል በፊት የሚከፈል ስለመሆኑ በደንገጉን የግራ ቀኙ የውል ስምምነትም በዋናው መዝገብ ቁጥር 08093 ላይ ውሳኔ የተሰጠበት እንደሆነ ቤቶቹ የሚከፋፈሉት ከማንኛውም እዳ ነፃ ከሆኑ በኃላ ስለ ሚል፤ ወጪውም ሁለቱም ተከራከሪ ወገኖች እንደሚመለከት፤ የአፈፃፀም ከሳሽ (አመልካች) የወጪውን ግማሽ ብር 76,520.00 ከፍለው እንዲሁም እንደውላቸው የሴንተናል ሆቴል ቤት ግምት አንድ መቶ ሺህ ብር ከፍለው የቤት ቁጥር 1345 የሆነውን እንዲራከቡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡ አመልካች የዲጋ ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 08412 በ21/08/2006...

 • 111498 criminal procedure/ role of court

  በወንጀል ክርክር ሂደት ፍ/ቤት በማስረጃ አቀራረብና አቀባበል ሂደቶች ውስጥ ሊኖረው(ሊያደርገው) ስለሚችለው ሚና የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 136(4)፣137፣138፣143(1)፣145፣194   የሰ/መ/ቁ. 111498   የካቲት 25 ቀን 2008 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አቃቤ ሕግ   -   የቀረበ የለም   ተጠሪ፡- አቶ ሃብታሙ ካርሎ - የቀረበ የለም   መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቶአል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የወንጀል ክርክር ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በሀድያ ዞን የሆሳእና ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ መነሻ ነው፡፡ የክሱም ይዘትም፡- ተጠሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 556(2)(ሐ) ስር በመተላለፍ ተጠሪ በሰው አካል ወይም ጤንነት ላይ ጉዳት ለማድረስ አስቦ በቀን 14/05/2006 ዓ/ም ከቀኑ በግምት 6፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በሆሳዕና ከተማ ሜእእል አምባ ቀበሌ ልዩ ስሙ ውሃዋና ፊት ለፊት ባሉ መጋዘኖች አከባቢ ወ/ሮ ነፃነት አለሙ የተባለችውን ሚስቱን አንገቱን አንቆ በመያዝ አንድ ጊዜ በቀኝ እጁ በጥፊ ፊቷን ሲመታት በአፏና በጥርሷ ላይ ደም ከመፍሰሱም በላይ በግንባሯ ላይ በቦክስ አንድ ጊዜ ሲደግማት ወዲያውኑ መሬት ላይ እንደወደቀች ፖሊሶች ደርሰው ያስጣሉት በመሆኑ በሰው አካል ላይ ቀላል የአካል ጉዳት አድርሷል የሚል ነው፡፡ ተጠሪ ክሱ ድርሶት እንዲረዳው ከተደረገ በኋላ ስለእምነት ክህደት ሲጠየቅ ወንጀሉን አልፈጸምኩም፤ ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት ተከራክሯል፡፡ የሥር ፍርድ ቤት የአመልካችን ሁለት የሰው ምስክሮችን ከሰማና ማስረጃዎቹ የሰጡትን የምስክርነት ቃል ከመረመረ በኃላ በግል ተበዳይ ላይ ተጠሪ በክሱ የተገለፀውን ተግባር ስለመፈፀሙ የተመለከተ ምስክር የሌለ መሆኑ መረጋገጡን ገልጾ   ተጠሪን ከክሱ ምንም መከላከል ሳያስፈልገው...

 • 111778 contract/ suretyship/ validity of contract of surety

  የዋስትና ውል በግልፅ መደረግና ዋሱ ለግዴታው ዋስ የሆነበት የገንዘብ ልክ በዋስትናው ውል መገለጽ ያለበት ስለመሆኑ ለዋስትናው መሠረት የሆነው ዋናው ጉዳይም ሕጋዊና ግራ ቀኙን የተስማሙበትና የሚታወቅ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፡- ፍ/ሕ/ቁ 1928፣1922 አዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2/1/     የሰ/መ/ቁ. 111778 ጥር 16 ቀን 2008 ዓ.ም. አመልካች፡- ወ/ሪት ገንዘብ ስጦታው ቀረቡ ተጠሪ፡- የራያ ቆቦ ወረዳ ፍርድ ቤት የክ/ዐ/ህግ ዘላለም ተስፋዬ ቀረቡ፡፡ መዝገቡንመርምረንተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡  ፍ ር ድ ጉዳዩ ለመንግስት መስሪያ ቤት ለሚፈጸም ቅጥር የተገባውን የዋስትና ውልን መሠረት ያደረገ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞንራያ ቆቦ ወረዳ ፍርድ ቤትየአሁን ተጠሪ ባሁኑ አመልካችና በአቶ ዘመኑ ይላቅ (የሥር 1ኛ ተከሳሽ) ላይ በመሰረተው ክስ መነሻ ነው፡፡ ተጠሪ በመሰረተው ክስ አቶ ዘመኑ ይላቅ በራያ ቆቦ ወረዳ ፍርድ ቤት በግዥና በፋይናንስ የሥራ ሂደት ተቀጥሮ እየሰራ እያለ በተሰጠው ውክልና መሰረት ከልዩ ልዩ ገቢ ደረሰኝ 2617.00 ብርና ከሞዴል 85 ብር 10,070.00 አጠቃላይ ብር 12,687 (አስራ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ ሰባት ብር) ያጎደለ ሲሆን አመልካች በሲቪል ሰርቪስ ሐምሌ 2002 ዓ/ም በወጣው መመሪያ መሰረት ለስር 1ኛ ተከሳሽ አቶ ዘመኑ ይላቅ ዋስትና ስለገቡ የጎደለውን ብር 12,687.00 ከወለድ ጋር በዋስትና ግዴታቸው መሰረት ይክፈሉ ሲል ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስ የፍርድ ቤቱን የሥረ ነገር ስልጣን መሰረት አድርገው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃ ደግሞ የስር 1ኛ ተከሳሽ የተቀጠሩት በግዥ ኦፊሰርነት ሁኖ አመልካች ዋስ የሆኑትም ለዚሁ የስራ መደብ መሆኑን፣ ለክሱ...

 • 112168 contract/ force majuer

  ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ተከስቷል ሊባል የሚችለው በባለእዳው በምንም መልኩ በቅድሚያ ሊያስበው ወይም ሊገምተው የሚያስችል ክስተት ሲፈጠር ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 1792 በየብስ የእቃ ማጓዝ ስራን ለመደንገግ ተሻሽሎ የወጣው አዋጅ ቁ. 547/1999   የሰ/መ/ቁ. 112168   የካቲት 24 ቀን 2008 ዓ.ም   ዳኞች፡-አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡-     የሺ ትራንስፖርት /የሺ ትራንስፖርት የጭነት ማመላለሺያ ባለንብረቶች  ማህበር/ ደምሴ ገበየሁ   ተጠሪ፡-   አቶ እስክንድር ዘርፉ - ዳዊት አባተ   መዝገቡ   የተቀጠረው   መርምሮ  ፍርድ   ለመስጠት   ነው፡፡   በመሆኑም   ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ይህ የሰበር አቤቱታ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 205919 በቀን 13/02/07 ዓ.ም የሰጠውን ፍርድ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 162749 በቀን 09/07/0227 ዓ.ም በማጽናቱ መሠረታዊ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለታቸው ነው፡፡   ጉዳዩ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ጉዳት መድረስን የሚመለከት ነው፡፡ ክርክሩ የጀመረው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጀ ፍ/ቤት ሲሆን ከሳሽ የነበረው የአሁን ተጠሪ ሲሆን አመልካች 2ኛ ተከሳሽ እንዲሁም የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ትራንዚት ሎጀስቲክ አገልግሎት 1ኛ ተከሳሽ ሲሆኑ ጣልቃ ገብ የነበሩት ደግሞ ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ እና አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ ነበሩ፡፡ ተጠሪ በተከሳሾች ላይ አቅርቦት የነበረው ክስ ቶዮታ ያሪስ 998 ሲሲ. የሻንሲ ቁጥር VNKKG96320A001372 የ2005 ምርት ዋጋ ብር 3000 ዩሮ የሆነ ከቤልጂየም ኢንትዊፕ ወደብ ኢትዮጵያ ሞጆ ደረቅ ወደብ ለሟጓጓዝ እና ለማስረከብ በሰነድ ቁጥር  LAU538 ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር ውል የገባ ቢሆንም 1ኛ ተከሳሽ ከተጠሪ ጋር የማጓጓዣ ውል የሌለው ንብረትነቱ የ2ኛ ተከሳሽ /የአሁን አመልካች/ የሆነ የሠሌዳ...

 • 112328 contract/ sale of immovable property/ transfer of title

  አንድን ንብረት የሸጠ ሰው የሸጠውን ንብረት ባለሃብትነት ለገዥው የማዛወር ግዴታ ያለበትና ይህንን ለመፈፀም አስፈላጊ የሆኑ ተግባራቶችን የማከናወን ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ.2273፣2281፣1771(1)፣1757   የሰ/መ/ቁጥር 112328   የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ/ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመለካች፡- ሙገር ሲሚንቶ ኢንተርፕራይ - ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን - ነ/ፈጅ ግርማ ዘለቀ - ቀረቡ   ተጠሪ፡- አቶ ኤፍሬም አሸቱ - የቀረበ የለም   መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የመኪና ሽያጭ ውልን መሰረት ያደረገ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በፌዴራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው፡፡ የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- አመልካች መጋቢት 10 ቀን 2003 ዓ/ም ባወጣው የመኪና ሽያጭ ጨረታ ላይ ተሳትፈው የታርጋ ቁጥር 3-18353 ኢት የሆነውን መኪና በብር 127,915.55 (አንድ መቶ ሃያ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ አስራ አምስት ብር ከሃምሳ አምስት ሳንቲም) የገዙ ቢሆንም ለስም ዝውውሩ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተሸከርካሪውን ማጣሪያ ክሊራንስ እንዲመጣ መጠየቃቸውንና ተጠሪ አመልካችን በዚህ አግባብ እንዲፈፀም ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም አመልካች ለማስጠንቀቂያው በሰጠው ምላሽ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ስም ዝውውሩ እንዲፈጸም ቃል የገባ ቢሆንም አለመፈጸሙን፣ በዚህ መሰረት አመልካች መኪናውን ለገዛው ተጠሪ ስም ለማዛወር የሚረዱ ሰነዶችን ለተጠሪ የማስረከብ ግዴታውን ያልፈፀመ  እና የመኪናው የኪራይ ገቢ ዋጋ በቀን ገቢ ተሰልቶ ብር 205,000.00(ሁለት መቶ አምስት ሺህ) ጥቅም የቀረባቸው መሆኑን ዘርዝረው አመልካች ለተጠሪ መኪናው ከግብርና ታክስ እዳ ነፃ የሆነበትን የክሊራንስ ሰነዶች እንዲያስረክብ፣ በቀን የታጣ ገቢ ብር 205,000.00...

 • 112575 jurisdiction/ adoption/ certificate of inheritance/ Addis Ababa city court

  አዲስ አበባ ከተማ ፍ/ቤት የጉዲፈቻ ስምምነትን ማስረጃን ተመልክቶ የወራሽነት ማስረጃን የመስጠት ስልጣን ያለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 361/1995 አንቀፅ 41(ሸ)   የሰ/መ/ቁ.112575 30/06/2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሠለ አመልካች፡- አቶ አፈወርቅ መኩሪያ - አልቀረቡም   ተጠሪ፡- ወ/ሮ ማዳሊና ፍራንሲኔቲ ጠበቃ ኤልያና ጥላሁን መዝገቡን መርምረን ተከታዮን ፍርድ ሰጥተናል ፡፡  ፍ ር ድ   ጉዳዮ የወራሽነት ማስረጃ እንዲሰረዝ የቀረበ አቤቱታን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ የመጀ/ደ/ፍ/ቤት ነው፡፡ ተጠሪ ቀደም ሲል ከዚህ ፍ/ቤት የወሰዱት የወራሽነት ማስረጃ እንዲሰረዝ አመልካች ያቀረቡት የመቃወሚያ አቤቱታ ይዘት የመቃ/ተጠሪ/የአሁኗ ተጠሪ/ የሟች ወ/ሮ ፈንታዮ መተኪያ ልጅ ሳይሆኑ በተፈጥሮ ሟች እንደወለዱዋቸው ልጅ ነኝ ብለው የወሰድት የወራሽነት ማስረጃ ይሰረዝልኝ የሚል ሲሆን ተጠሪ በበኩላቸው ባቀረቡት የመጀ/ደ/መቃወሚያ ፍ/ቤቱ የልጅነትን ክርክር ጭብጥ ይዞ ለማየት ስልጣን የለውም፣የመቃ/አመልካች የሟች ልጅ /ተወላጅ/ ሳይሆኑ ያቀረቡት መቃወሚያ አቤቱታ ላይ መብት ወይም ጥቅም የላቸውም ፣የመቃ/አመልካች ወላጅ እናት ወ/ሮ አፀደ ንዋይ የሞቱት  ከ 30 ዓመት በፊት ስለሆነ አቤቱታው በይርጋ ቀሪ ነው በማለት መቃወሚያ እና በአማራጭም መልስ ማቅረባቸው ከስር ፍ/ቤት ውሣኔ ላይ ተመልክቷል፡፡   ፍ/ቤቱ የቀረበውን የመጀመሪያ መቃወሚያ መርምሮ የመቃ/አመልካች እንደሚሉት እና በመቃ/ተጠሪም የግራ ቀኙን የልጅነት ክርክርን ፍ/ቤቱ ጭብጥ ይዞ ሲመረምረው በተገቢው ፍ/ቤት አጠናቀው እና ማስረጃ ይዘው እስከ ቀረቡ የወራሽነት ክርክሩ መዝገብ ለጊዜው ተዘግቶ ይቆይ በማለት ብይን ሰጥቷል፡፡ ሌሎች መቃወሚያዎች ላይ መቃወሚያዎቹን ባለመቀበል በብይን አልፋል፡፡  ተጠሪ  በዚህ  ብይን  ላይ ቅሬታቸውን  ለአዲስ  አበባ...

 • 112583 labor dispute/ leave /conversion of leave to payment

  አንድ ሠራተኛ ከአንድ ዓመት በታች አገልግሎት የሰጠ እንደሆነተመጣጣኝ የሆነ የረፍት ጊዜ በአገልግሎት ጊዜው ልክ(proportion to the length of his service) የሚሰጠው ስለመሆኑአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 77(6)   የሰ/መ/ቁ. 112583   ጥቅምት 5 ቀን 2008 ዓ.ም       ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ብርሃኑ አመነው ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መለሰ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጅማ ቅ/የቀረበ የለም ተጠሪ፡- አቶ ብሩክ አበራ- ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   በዚህ መዝገብ የቀረባቸውን ጉዳይ የሥራ ውል መቋረጥ ተከትሎ ሊከፈል የሚገባ ልዩ ልዩ ክፍያ ክርክር የሚመመለከት ነው፡፡   ተጠሪ ከአመልካች ጋር የነበረው የሥራ ውል ማቋረጥ ተከትሎ ልዩ ልዩ ክፍያዎችን የጠየቀ ሲሆን የጅማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ ተጠሪ የሠራበት የእሁድ ቀን ክፍያ የ2006 ዓ.ም የአመት ዕረፍት እና የጥር ወር 2006 ዓ.ም ሙሉ ደመወዝ እንዲከፈለው ወስኗል፡፡   ይግባኙ ለጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአመልካች በኩል የቀረበ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኘም   አመልካች ለኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት አቤቱታ በማቅረቡ ችሎቱም ግራቀኙን ካከራከረ በኃላ የጥር ወር 2006 ዓ.ም ደመወዝ ለተጠሪ የተከፈለ መሆኑ ተረጋግጧል በማለት በዚህ ረገድ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመሻር ፕሮፊደንት ክፍያ ጉዳይ እንዲጣራ ለሥር ፍርድ ቤት በነጥብ እንዲመለስ ሌላው የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ በማፅናት ፍርድ ሰጥቷል ፡፡ ለዚህ ሰበር ችሎት አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ሲሆን የአመልካች የቅሬታ ነጥብ የእሁድ ቀን ሥራ ተጠሪ ሳይሰራ እንዲከፈለው መወሰኑ እና የ2006 ዓ.ም ተጠሪ አገልግሎት (የሥራ ውል) የተቋረጠው ጥር ወር 2006ዓ.ም አገልግሎት እንደሰጠ ተቆጥሮ የዓመት እረፍት ሙሉ ታስቦ እንዲከፈል መወሰኑ አግባብ አይደለም የሚል ነው፡፡   የሰበር ችሎቱ አቤቱታውን ከመረመረ በኃላ የእሁድ...

 • 112725 criminal procedure/ bail/ appeal by prosecutor

  አቃቤ ህግ በዋስትና መለቀቅ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ ፍርድ ቤት የዋስትና መብትን የሚከለከልበቻው ምክንያቶች ከተለየዩ ሁኔታዎች በመመልከት ሊመዝናቸው የሚገባቸው ስለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር67፣75   የሰ/መ/ቁ. 112725 ቀን 22/02/2008 ዓ/ም ዳኞች፡-ተሻገር ገ/ስላሴ   ሙስጠፋ መሐመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ስርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካች፡- አቶ ሀሰን አብዳል ጠበቃ ገበዮህ ይርደው ቀርበዋል   ተጠሪ፡- የፌዴራል ማዕከል ዐቃቤ ህግ የቀረ የለም   መዝገቡ ተመርምሮ ተከተዩ ፍርድ ተሰትቷል    ፍ ር ድ   በዚህ ጉዳይ አመልካች የፀና ንግድ ፈቃድ ሳይኖረው የንግድ ስራ ሰርቷል በሚል በአዋጅ ቁጥር 686/2002 አንቀጽ 2(3) 31(1) እና 60(1) የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት ፈፅሟል በሚል የወንጀል ክስ የቀረበበት ሲሆን ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ እየተመለከተ የነበረው ፍርድ ቤትም የአመልካቾችን ዋስትና መብት በብር 50,000 ወይም ለዚሁ ብቁ የሆነ ዋስትና ከቀረበ በኃላ ከእስር እንዲለቀቅ በሚል የዋስትና መብቱን ጠብቆለታል፡፡ ተጠሪ ቅሬታ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት በማቅረቡ ግራ ቀኙን አስቀርቦ በዋስትና ጉዳይ ላይ እነዲከረከሩ ከዳረገ በኃላ የስር ፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ በመሻር የአመልካችን ዋስትና መብት ጥያቄ ከወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 67(ሀ) አንፃር በመካልከል አመልካች ማረሚያ ቤት ሆኖ ጉዳዩን ይከታተል ስል ወስነዋል፡፡ የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስላወጥ ነው፡፡   የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም በዋስትና መፍቀድ ላይ ዐቃቤ ህግ ይግባኝ ለማለት ስልጣን አለው የሚል አንቀጽ በወ/መ/ስ/ስ/ህጉ ላይም ሳይኖር ፍርድ ቤቱ ይህንኑ ተቀብሎ አከራክሮ ዋስትናውን መሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ሊታረም ይገባል፤ ዐቃቤ ህግ አመልካች በዋስትና ቢወጣ የዋስትና ግዴታውን አክብሮ አይመጣም ለማለት የቀረበው ምክንያት አድራሻ የለውም ቢፈረድበት...

 • 112906 rural land

  አንድ አርሶ አደር የሚጠቀምበት ይዞታ (መሬት) በህግ ስልጣን በተሰጠው አካል የተሰጠው መሆኑን እስካላረጋገጠ ድረስ የመንግስትና የህዝብ መሬትን ለረዥም ዓመት ይዤዋለሁኝ ስለዚህ ይርጋ አይመለከተኝም ብሎ የሚያነሳው ክርክር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ     የሰ/መ/ቁ. 112906 ቀን የካቲት 16 ቀን 2008 ዓ/ም ተጠሪ፡- የማቻካል ወረዳ አካባቢ ጥበቃ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ተወካይ የክልሉ ዓ/ሕግ ቀረቡ መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል ፡፡  ፍ ር ድ ጉዳዩ የመሬት ይዞታ እና የሰብል ግምት ክርክር የሚመለከት ሲሆን ጉዳዩ የተጀመረው በአብኪመ የማቻኮል ወረዳ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪ በዓቃቤ ህግ በኩል በአሁኑ አመልካች ላይ ባቀረበው ክስ መነሻነት ነው፡፡   የአሁኑ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ባጭሩ ፡- አመልካች ከማንም ሕጋዊ መብት ካለው አካል ሳይሰጠው በመቻከል ወረዳ በሸይ ቀበሌ ልዩ ስሙ ገለቦ በተባለው ቦታ በምስራቅ መንገድ በምዕራብ ተምጫ ወንዝ፣ በሰሜን የኔወርቅ ለቀው በደቡብ አሚጋ የሚያዋስነው የህዝብ ግጦሽ መሬት በወርድ 50 ሜትር በቁመት 80 ሜትር የሆነውን የመስኖ መሬት በመያዝ በ2004፣2005 እና 2006 እህል በመዝራት፤ አትክልት በማፍራት ገቢ በማግኘቱ የሰብል ግምት በመክፈል የህዝብና የመንግስት ይዘት ለቆ እንዲያሰረክብ ዳኝነት መጠየቁን የሚያሰይ ነው፡፤   የአሁኑ አመልካች የመከለከያ መልስ ያቀረበ ሲሆን ዋና ፍሬ ነገሩ የሰብል ግምት መቅረብ ያለበት በመሬት ይዞታው ላይ ውሳኔ ከተሰጠ በኃላ መሆን እንዳለበት፤ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን መሬት በ1994 ኣ/ም የቀበሌ አመራር ኮሚቴዎች ለወፍጮ መትክያ የተሰጠው ስለመሆኑ በመግለጽ መልስ አቅርበዋል፡፤   የስር ወረዳ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ የአሁን አመልካች መሬቱ ከ1994 ዓ/ም የያዝኩት ስለሆነ ጉዳዩ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ያቀረበው...

 • 112927 civil procedure/ admission/ procedure when claim admitted

  ከሳሽና ተከሳሽ ያልተካካዱበትና ከሳሽ በክሱ ገልፆ ተከሳሽ ባመነው ነጥብ ላይ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ማስረጃ በመመዘን ሳይሆን ተከሳሹ በሰጠው የእምነት ቃል ወይም መልስ መሰረት መወሰን ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.242 የሰ/መ/ቁ. 112927 ቀን የካቲት 16/2008 ዓ.ም     ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሀመድ ተኽሊት ይመሰል እንደሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- የማርዘነብ ዕቁብ ዳኛ አቶ ባዬ አጥናፉ - ጠበቃ አለጌታ መርሻ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1. አቶ ዋለልኝ ተመስገን - ቀረቡ 2. አቶ አዲሱ ጥሩነህ   መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ 1. ጉዳዩ ላልተከፈለ የዕቁብ ገንዘብ የተሰጠ የዋስትና  ግዴታ የሚመለከት  ነው፡፡ የአመልካች ዕቁብ አባል የሆነ ወርቁ ሚናስ የተባለና የሥር አንደኛ ተከሳሽ የሆነ ሰው የዕቁብ እጣ ደርሶት ብር 465,000 /አራት መቶ ስልሣ አምስት ሺ ብር/ ተቀብሎ ሲወስድ ቀሪውን የዕቁብ እጣ በየጊዜው የሚከፍል ስለመሆኑ፣ አቶ ወርቁ ሚናስ የዕቁብ ገንዘብ መጣሉን ቢያቋርጥ፤ ተጠሪዎች ገንዘቡን የሚከፍሉ ስለመሆኑ ተጠሪዎች የዋስትና ግዴታ ገብተው ፈርመዋል፡፡ አቶ ወርቁ ሚናስ መክፈል የነበረበትን ብር 222,000 /ሁለት መቶ ሃያ ሁለት ሺ ብር/ ሣይከፍል የዕቁብ ገንዘቡን መጣሉን በማቋረጡ አመልካች አንደኛ ተከሳሽ ወርቁ ሚናስና እሱ የዕቁብ ገንዘቡን ሲወስድ ዋስ የሆኑት ተጠሪዎች ገንዘቡን እንዲከፍሉ ውሣኔ ይሰጥልን በማለት ለምሥራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ አቅርቧል፡፡ 2. ተጠሪዎች የዕቁብ አባላትና የዕቁብ ገንዘብ በእጣ ደርሶት የወሰደው አቶ ወርቁ ሚናስ ዋስ እንደሆነ ገልፆም በዕቁብ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የዚህ አይነት የዕቁብ ገንዘብ ለዕቁብተኛ ሲሰጥ የዕቁቡ ኃላፊዎች አራት ዋሶችን አስጠርተው ገንዘቡን መስጠት ነበረባቸው፡፡ የዕቁብ ኃላፊዎች ሁለት ዋሶችን አስጠረተው ገንዘብ መስጠታቸው የዕቁቡን መተዳደሪያ ደንብ...

 • 112956 labor dispute/ severance pay

  አንድ ሠራተኛ ከስራ ከተሰናበተ በኋላ የአገልግሎት ክፍያ ከሚያገኝባቸው ሕጋዊ ምክንያቶች አንዱ በድርጅቱ ከ5 ዓመት በላይ አገልግሎ በገዛ ፈቃዱ ስራ መልቀቁ ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀፅ 2/ሸ/ የሰ/መ/ቁ. 112956   ጥቅምት 22 ቀን 2008 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- ሙስጠፋ ኑር ትዕም ቀረቡ   ተጠሪ፡- የኦሮሚያ መንገዶች ኮንስትራክሽን ኢንተርኘራይዝ ነ/ፈጅ ጋሻው ቡልቶ ቀረቡ መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡  ፍ ር ድ   ጉዳዩ የአሰሪና ሰራተኛ የስራ ቅጥር ውል ማቋረጥን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ በአዳማ ወረዳ ፍ/ቤት በተመሰረተው ክስ መነሻነት ነው፡፡ የክሱ ይዘትም፡- ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ተቀጥሮ በመስራት ላይ እያለ ወደ ኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን ተለውጦ፣ ይህም ድርጅት ወደ ኢንተርኘራይዝ ተቀይሮ ብር 3666.00 በማግኘት ለ28 አመታት የሰራ ቢሆንም ከስራ ሳይቀር፣ ከስራ ለቀረበት ቀንም የሃኪም ማስረጃ አቀርቦ ሳለ ደመወዝም እየተከፈለው በነበረበት ሁኔታ በ18/12/2004 በፅሁፍ ከስራ መሰናበቱ እንደተገለፀለት፤ የተጠሪ ድርጊት ሕገ ወጥ በመሆኑ ወደ ስራ  እንዲመለስ እንዲወሰንለት ዘርዝሮ በአጠቃላይ 89‚328.20 ከወጪና ኪሳራ ከጠበቃ አበል  ጭምር እንዲከፈለው ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው፡፡   ተጠሪ በሰጠው መልስ አመልካች ከስራ የተሰናበተው ከ20/9/2004 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ለአምስት የስራ ቀናት ከስራ የጠፋ ስለሆነ ምክንያቱና ማስረጃውን በወቅቱ ባለማቅረቡ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27/1//ለ/ የስራ ውል ማቋረጥ ሕጋዊ ነው፡፡ የስራ ስንብት ክፍያ አይመለከተውም በአዲሱ ድርጅትም 5 አመት አላገለገለም፡፡ የማስጠንቀቂያ ክፍያም ...

 • 113464 criminal procedure/ criminal law/ participation in crime/ standard of proof

  በወንጀል ጉዳይ ከአንድ በላይ ሰዎች የተከሰሱ እንደሆነ የእያንዳንዱ ተከሳሽ ሚና እና ተሳትፎ ደረጃው በቂና አሳማኝ በሆነ ሁኔታ በከሳሽ ወገን በኩል በሚቀርበው ማስረጃ ነጥሮ ሊወጣ የሚገባ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32፣40 የወ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 141 ተያያዥነት የሌላቸው ፍሬ ነገሮችን መሰረት ተደርጎና የአንድን ነገር መኖር ያለመኖር ሣይረጋገጥ ለአካባቢ ማስረጃ ክብደት መስጠት የማስረጃው አይነት የምዘና መርህን መሰረት ያደረገ ነው ለማለት የሚቻል ስላለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.173(1)   የሰ/መ/ቁጥር 113464   ህዳር 22 ቀን 2008 ዓ/ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ     አመልካች፡- 1. እናት ሁናቸው   2. ባለው እንደወቅቱ   3. ሃብታሙ ሁነኛው       የቀረበ የለም   4. በልስቲ ሁነኛው       ተጠሪ፡- የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አቃቤ ሕግ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡  ፍ ር ድ   ጉዳዩ የወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካቾች እና ስንሻው አለሙ በተባለው ግለሰብ ላይ በመሰረተው ክስ መነሻ ነው፡፡ የክሱም ይዘት፡- ተከሳሾች በ1996 ዓ/ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪፐብሊክ ወንጀል አንቀፅ 32(1(ሀ)) እና 671(2) ስር የተደነገገውን መተላለፍ የማይገባውን ብልጽግና ለማግኘት አስበው ጥቅምት 22 ቀን 2004 ዓ/ም ከምሽቱ በግምት 4፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ጎዛመን ወረዳ ማይ አንገታም ቀበሌ ከአሁኗ 1ኛ አመልካች ሻይ ቤት ውስጥ     አቶ ውባለም ግዛቸው ይባል የነበረውን በአሰቃቂ ሁኔታ ደብድበው ገለው እሬሳውን ከሻይ ቤት ራቅ አድርገው ጥለውት ይዞት የነበደርን ባለሰደፍ ክላሽ ጠመንጃ የወሰዱበት መሆኑን ዘርዝሮ ተከሳሾች ከባድ የውንብድና ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ነው፡፡ የአሁኑ አመልካቾችም ሆነ የሥር 1ኛ ተከሳሽ የነበረው አቶ ስንሻው አለሙ ፍርድ ቤት ቀርበው የአቃቤ ሕግ የክስ ቻርጅ ተነቦላቸው እንዲረዱት ከተደረገ በሁዋላ እምነት ክህደት ቃላቸውን ሲጠየቁ የወንጀል ድርጊቱን...

 • 114043 criminal law/ custom violation/ standard of proof

  በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ መሰረት የጉምሩክ ቁጥጥርን አሰናክለሃል ተብሎ ሊጠየቅ የሚችለው ድርጊቱ ሆነ ተብሎ መፈፀሙን አቃቢ ህግ በበቂ ሁኔታ ሲያስረዳ ስለመሆኑ የጉሙሩክ አዋጅ ቁ. 859/2006 አንቀፅ 166

 • 114669 labor dispute/ termination of contract of employment/ arrest

  አንድ ሠራተኛ በጊዜ ቀጠሮ ከ30 ቀን በላይ መታሰሩ እና ከስራ ገበታው መቅረቱ ከ30 ቀናት የሚበልጥ እስራት እንደተወሰነበት ተቆጥሮ የስራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ ማቋረጥ ተገቢ ስላለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27 /1/በ/   መ/ቁ.114669 ጥቅምት 24 ቀን 2008 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሀመድ ተኸሊት ይመስል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- የኢትዮጲያ መንገዶች ኮንስትራክሽን ኮርፓሬሽን የደብረ ማርቆስ መንገዶች ጥገና ዲስትሪክት ነገረ ፈጅ መሰረት አበራ   ተጠሪ፡- አቶ አስማረ ፈጠነ ቀረበ   መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የአሰሪና ሰራተኛ የስራ ውል ማቋረጥ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ በአ.ብ.ክ.መ.የደብረማርቆስ ወረዳ ፍ/ቤት በአሁኑ አመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻነት ነው፡፡ የክሱ ይዘትም ተጠሪ በአመልካች መስሪያ ቤት ከሚያዚያ 21 ቀን 1984 ዓ/ም ጀምሮ በጠቅላላ 22 ዓመት ሲያገለግሉ እንደቆዩ፤ መስሪያ ቤቱም በየጊዜው እድገት ይሰጣቸው እንደነበር፤ በሹፍርና ሙያ የስራ መደብ እስከ መጋቢት 10 ቀን 2006 ዓ/ም ድረስ ስራቸውን በተገቢው መንገድ እየፈጸሙ በነበሩበት ሁኔታ አመልካች ከመጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ/ም ጀምሮ ምንም ዓይነት ማስጠንቀቂያ ሳይሰጣቸው ክስ እስካቀረቡት ድረስ ከስራ ያገዳቸው በመሆኑ የስራ ውሉ የተቋረጠው በህገ ወጥ መንገድ ነው ተብሎ ወደ ስራ ገብታችሁ እንዲመለሱ፤ ይህ የማይወሰን ከሆነ ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 377/96 የተፈቀዱትን የስራ ስንብት ክፍያ የ6 ወር ደመወዝ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ደመወዝ በወቅቱ ባለመክፈሉ በድምር 60,601.70 /ስልሳ ሺህ ስድስት መቶ አንድ ብር ከሰባ ሳንቲም ከወጪና ኪሳራ ጭምር እንዲከፈል እንዲወሰንላቸው ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ የአሁኑ አመልካች ባቀረበው መልስ የስራ ውሉ የተቋረጠው ተጠሪ...

 • 116002 labor dispute/ backpayment

  ውዝፍ ያልተከፈለ ደሞዝ ከስራ ስለተሰናበተ ሠራተኛ የሚከፈል ሳይሆን ወደ ስራ እንዲመለስ ለተወሰነበት ሰራተኛ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 43(5) የሰ/መ/ቁ. 116002 ቀን 6/3/2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አቶ ተሻገር ገ/ስላሴ   ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ አመልካች፡- የአንቦ የገበሬዎች የህብረት ሥራ ዩንየን አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ ጨመዳ መገርሳ ቀርበዋል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለውን ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   በዚህ የሰበር አቤቱታ መዝገብ ክርክር የአሁኑን አመልካች የአንቦ የገበሬዎች የህብረት ሥራ ዩንየን በቀን 13-11-2007 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የኤሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁጥር 202963 በቀን 29-10-2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም የቀረበ ነው፡፡ ቅሬታውም የስር ፍ/ቤት የ12 ወር ውዝፍ ደሞዝ ለከሳሽ /ለአሁን ተጠሪ/ሊከፍለው ይገባል ብሎ ቢወስን ምንም ነገር ማሳመኛ ምክንያት ሳይጠቅስ ነው፡፡ ከሳሽ / የአሁን ተጠሪ/የአሁን አመልካች ንብረት መጥፋቱን ባልካደበትና የአሁን አመልካች ተጠሪ ወደ ስራ እንዳይመለስ ተከራክሮ እያለ አመልካች የተጠሪን ወደ ስራ መመለስ አልቃወምም ብሏል በማለት ወደ ስራ እንዲመለስ የተሰጠው ውሳኔ ስህተት ነው፡፡፡ ውዝፍ የዓመት ዕረፍት ለተቋረጠ የስራ ውል የሚከፈል እንጂ በህጉ አዋጅ 377/96 አንቀጽ 77/5/ መሠረት ወደ ስራ እንድመለስ ለተወሰነ ሠራተኛ አይደለምና በስር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው፡፡   መዝገቡ ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ አመልካች የወሰደው የስንብት እርምጃ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/3/ መሠረት በይርጋ ይታገዳል በማለት ለተጠሪ የተለያዩ ክፍያ ተከፍሏቸው ወደ ስራ ይመለሱ የመባሉን አግባብነት ከሰበር ውሳኔ...

 • 116209 civil procedure/ appeal/ interlocutory appeal

  በጊዜያዊ ትእዛዝ ላይ በሚሰጥ ብይን ቅር የተሰኘ አካል የስረ ነገሩ ክርክር የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ እስካልተገኘ ድረስ ይግባኝ (የሰበር) አቤቱታ ሊቀርብ የማይችል ስለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.320(3)   የሰ/መ/ቁ. 116209   የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ.ም.       ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ ፈይሳ ወርቁ   አመልካች - የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን  - አልቀረቡም ተጠሪ - ወ/ሮ ምፅላል አብርሃ - አልቀረቡም   መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡      ፍ  ር ድ ጉዳዩ የቀረበው በግራ ቀኙ መካካል ባለው የንብረት ካሳ ክርክር በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በማዕከላዊ ዞን ማዕከላዊ ፍርድ ቤት የአብይ አዲ ምድብ ችሎት በመ/ቁ 02634 ግንቦት 7 ቀን 2007 ዓ.ም ያሳለፈውን ብይን በመቃወም ነው ፡፡ አመልካች ይግባኝ የቀረበበት የገንዘብ መጠን ብር 791,225.00 (ሰባት መቶ ዘጠና አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሃያ አምስት) በመሆኑ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለመወሰን ስልጣን የለዉም፤ እንዲሁም በስር በተደረገ ክርክር ተካፋይ አልነበርኩም የሚሉ መቃወሚያዎችን አቅርቧል፡፡ ፍርድ ቤቱም መቃወሚያዎችን ከመረመረ በኋላ ባሳለፈው ብይን ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትንና ካሳ የሚከፈልበትን ሁኔታ ለመወሰን በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 455/1997 አንቀጽ 11(4) እንዲሁም የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 29(4) ስር እንደተደነገገው ካሳን በተመለከተ በተሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ተከራካሪ ወገን ለሚመለከተው የከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ወይም የከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በሌለበት ለሚመለከተው መደበኛ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሊያቀርብ እንደሚችል ከሚደነግጉ በቀር የተጠቀሱት አዋጆች በካሳዉ ግምት መጠን ወደተለያየ ፍርድ ቤት ይግባኝ እንደሚቀርብ የሚደነግጉ ባለመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን አለው ብሏል፡፡  ሁለተኛውን መቃወሚያ...

 • 116977 law of person/ name/ change of name

  አንድ ሰው በወላጅ አባቴ ስም መጠራቴ ቀርቶ በአሳዳጊዬ ስም እንድጠራ ብሎ የሚያቀርበው የዳኝነት ጥያቄ በሕጉ ስለስም ለውጥ የተጠቀሱትን ድንጋጌዎች የማያሟላ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ.32(1)፣36(1)   የሰ/መ/ቁ 116977   የካቲት 25 ቀን 2008 ዓ/ም   ዳኞች፡-  አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች ፡- ወ/ሪት ሃና ታምራት ጠበቃ አሰፋ ካሳ ቀረቡ ተጠሪ፡- የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ አመልካች ያቀረቡትን አቤቱታ ጉዳዩ በመጀመሪያ ደረጃ የቀረበለት የአዲስ አበባ ከተማ የመ/ደ/ፍርድ ቤት ውድቅ በማድረጉና በየደረጃው ያሉ የከተማው አስተዳደር የበላይ ፍርድ ቤቶችም የመ/ደ/ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማጽናታቸው ነው፡፡   አመልካች ሐምሌ 08 ቀን 2007 ዓ/ም ያቀረቡት አቤቱታ ፍሬ ቃሉ፡- ቀድም ሲል ጸሐይ ብርሃኔ እና ሀና ታምራት እየተባልኩ በሁለት ስም ስለምጠራ ጸሐይ ብርሃኔ መባሌ ቀርቶ ሃና ታምራት ብቻ እየተባልኩ እንድጠራ ውሳኔ ይሰጠኝ በማለት ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ሲሆን የስር ፍርድ ቤትም አመልካች የአቶ ታምራት አመዴ ልጅ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ፍርድ ቤት የልጅነት ውሳኔ ይዘው ሲቀርቡ መዝገቡ ይቅረብ በማለት መዝገቡን የዘጋው ሲሆን በዚህ ትዕዛዝ አመልካች ይግባኛቸውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት፣ የሰበር አቤቱታቸው ለከተማው ሰበር ሰሚ ችሎት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም፡፡   የአሁኑ የሠበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ የአመልካቸ  የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- ሁለት ስም የነበረኝ በመሆኑ የግል ስሜና የወላጅ አባቴ ስም ተቀይሮ በአንዱ የግል ስም እና በአሳዳጊዬ የቤተዘመድ ስም እንድጠራ ያቀረብኩት አቤቱታ ውድቅ መደረጉ ከሕግ ውጪ ነው የሚል ነው፡፡ የጉዳዩ አመጣጥ ከዚህ በላይ የተመለከተው ሲሆን...

 • 117065 criminal law/ tax law

  ማንኛውም እቃ ወይም መጓጓዣ ሊወረስ በሚችል ወንጀል በተከሰሰ ሰው ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ ተጨማሪ ትእዛዝ መስጠት ሳያስፈልግ እቃው ወይም መጓጓዣው እንዲወረስ የሚደረግ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 622/2001 አንቀፅ 104(1)   የሰ/መ/ቁ. 117065 የካተት 30 ቀን 2008ዓ/ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ሙስጠፋ  አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሹ ሺርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዓቃቤ ህግ ምህረቱ ቁምላቸው ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሚፍታ ካሚል ቀርቧል፡፡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ለክርክር መነሻ የሆነው የአሁኑ አመልካች በተጠሪ ላይ ያቀረበው የወንጀል ክስ ነው፡፡ ክሱ የኮንትሮባንድ ወንጀል ሆኖ ክርክሩ የተጀመረው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት አሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፡፡ ተጠሪ ከስር ክስ ሶስት ተከሳሾች ከነበሩት ጋር የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 91/2/ የተደነገገውን በመተላለፍ በቀን 10/10/2006 ዓ.ም ከቀኑ 7፡15 አከባቢ ምንም ዓይነት የጉምሩክ ስነስርአት ያልተፈፀባቸው እና ጠቅላላ ቀረጥና ታክሳቸው ብር 15,425.23 /አስራ አምስት ሺህ አራት መቶ ሃያ አምስት ብር ከሃያ ሶስት ሳንቲም/ ለመንግስት ያልተከፈለባቸው መሆናቸውን እያወቁ ወይም ማወቅ ሲገባቸው የተለያዩ ንብረቶች በ1ኛው ተከሳሽ የአሁኑ ተጠሪ ረዳትነትና የመኪናው ባለቤትነት እና 2ኛ ተከሳሽ አሽከርካሪነት  ከጊዘን ወደ አሶሳ ለመሄድ በኮድ3-00277 ቤጉ በሆነ ሚኒባስ ጭነው በመጓጓዝ ላይ እያሉ ሸርቆሌ ፌዴራል ፖሊስ ካምፕ አካባቢ በፌዴራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር  በማዋላቸው የኮንትሮባንድ ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ክስ ቀርበውበታል፡፡ ከ2ኛ-4ኛ ተከሳሾች ባለመቅረባቸው በሌሉበት ውሳኔ የተሰጠባቸው መሆኑን ከስር መዝገብ መረዳት ይቻላል፡፡  የአሁኑ ተጠሪ የቀረበውን የወንጀል ክስ በመካዱ ፍርድ...

 • 117076 labor dispute/ manager

  አንድ ሠራተኛ የሥራ መሪ ሆኖ የሚቆጠረው እንደ ድርጊቱ የሥራ ፀባይ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንጻር መታየት ያለበት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 377/96 አዋጅ ቁጥር 494/1998 አንቀጽ 3/2/ሐ/ የሰ/መ/ቁ.117076 ጥር 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ዳኞች፡-ተሻገር ገ/ሥላሴ   ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ተብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ   አመልካች፡- በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግስት የቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ  ነ/ፍጅ    ብሩክ ታፈነ ቀረቡ ወክልና አያያዝ   ተጠሪ፡- አቶ ዮሐንስ ብዙነህ   ቀረቡ   መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የስራ ስንብት ክፍያ ጥያቄን አስመልክቶ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት  ሲሆን የተጀመረውም ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከሳሽ በነበረው የአሁኑ አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው፡፡ከሳሽ በ14/02/2007 ዓ.ም. ያቀረቡት ክስ ይዘትም ባጭሩ፡-በተከሳሽ ድርጅት ውስጥ ከ17/08/2005 ዓ.ም. ጀምሮ በወር ብር 4,699 እየተከፈላቸው በሳይት መሀንዲስነት በመስራት ላይ እያሉ ተከሳሽ ድርጅት የስራ ውላቸውን ከሕግ አግባብ ውጪ ያቋጠባቸው መሆኑን የሚገልጽ ሆኖ ሕገ ወጥ የስራ ስንብት እርምጃ የሚያስከትላቸው እና ተዛማጅ ክፍያዎች አግባብነት ባላቸው በአዋጅ ቁጥር  377/1996 ድንጋጌዎች መሰረት በድምሩ ብር 77,219 (ሰባ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ ሺህ) እንዲከፍላቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት የተጠየቀበት ነው፡፡   ተከሳሽ ድርጅት በበኩሉ በ08/03/2007 ዓ.ም. በሰጠው መልስ ከሳሽ የስራ መሪ በመሆናቸው ጉዳዩ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት እና በስራ ክርክር ችሎት ሊስተናገድ የሚገባው አይደለም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ካስቀደመ በኃላ በፍሬ ጉዳዩ ረገድም የስራ ውሉ ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ እና በየሶስት ወሩ የሚታደስ መሆኑን፣እያንዳንዱ ወገን የአንድ ወር ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ማቋረጥ እንደሚችል በውሉ...

 • 117383 criminal procedure/ criminal law/ breach of trust/ bail

  በወ/መ/ህ//አ/ቁ. 676(1) የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል የተከሰሰ ሰው የዋስትና መሰጠት (መፈቀድ) ጥያቄ የሚሰጠው በጉዳዩ ላይ በአግባቡ ተመርምሮ እንጂ ከወዲሁ ስላለመሆኑ አዲሱ የፀረ ሙስና ህግ አዋጅ ቁ. 881/2007 አንቀፅ 31   የሰ/መ/ቁ 117383 ቀን 6/03/2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ሙስጠፍ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸመሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሠለ አመልካች፡- አቶ አዲስ ዋለልኝ በላይ ተጠሪ፡- የፌ/ሥ/ፀ/ሙ/ኮ/ዐ/ሕግ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዮ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ በወንጀል የዋስትና ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የጀመረው በፌ/ከፍ/ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካች አብረዋቸው ከተከሰሱ ሌሎች ተከሳሽ ጋር በመሆን ተከሰንበት የነበረው የወ/ህ/ቁ. 676/1/ በአዲሱ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁ. 881/2007 የተሻረ በመሆኑ እና በዚህ አዋጅ አንቀጽ 31/1/ የተመለከተው ድንጋጌ ዋስትና መብት ስለማይከላከል የዋስትና መብት ይፈቀድልን ብለው ያመለከቱ ሲሆን ተጠሪ በበኩሉ በአዋጅ ቁ. 881/2007 አንቀጽ 37 የመሸጋገሪያ ድንጋጌ ስር ይህ አዋጅ በስራ ላይ ከመዋሉ በፊት የተያዘው የሙስና ወንጀሎች የሚታዮት በወንጀል ሕጉ ድንጋጌ መሠረት ይሆናል ስለሊልና የወ/ህ/አ/676/1/ የዋስትና መብት ስለማያሰጥ ዋስትና ሊፈቀድ አይገባም፡፡ የሚሰጥ ከሆነም የዐ/ሕግ ምስክሮች ከተሰሙ በኃላ ማስረጃ ተመዝኖ መሆን አለበት በማለት ተከራክረዋል፡፡ ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካለው ህግ ጋር መርምሮ የወንጀል ህግ አንቀጽ 6 እና የህገ መንግስቱ አንቀጽ 22 መሠረት ቅጣት ሲወሰን ለተከሳሽ ጠቀሜታ ካለው ሕግ አኳያ ሊታይ ይገባል፡፡ የተከሰሱበት የወ/ህ/ቁ. 676/1/ በአዲሱ አዋጅ ቁ. 881/2007 አንቀጽ 31/1/ ስለሚወድቅ እና ቅጣቱ ከ10 ዓመት...

 • 117390 jurisdiction/ international organizations

  በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ስራቸውን የሚያከናውኑት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ጋር የሚመሰረቱት የሥራ ግንኙነት ስምምነት ያለ እንደሆነ ጉዳዩ የሚዳኘው በዓለም አቀፍ ስምምነቱ መሠረት ስለመሆኑ፡-   የሰ/መ/ቁ.117390 ታህሳስ 21 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- አቶ አለማየሁ መኮነን ጠበቃ ሞላ ዘገየ ቀረቡ   ተጠሪ፡- የምስራቅ አፍሪካ የበርሃ አንበጣ መከላከያ ድርጅት ጠበቃ አድምጠው በለጠ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡  ፍ ር ድ   1. ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ፍርድ  ቤቶች በተጠሪ ላይ ያቀረብኩትን ክስ የማየትና አጣርተው የመወሰን ስልጣን የሌላቸው መሆኑን ገልፆ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሰለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ አመልካች የተጠሪ ሰራተኛ የነበሩ መሆናቸውን ገልፀው ተከሳሽ ሊከፍለኝ ይገባል የሚሏቸውን ክፍያዎች ዘርዝረው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውሳኔ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ ተጠሪ አለም አቀፍ ድርጅት መሆኑን ገልፆ፣ የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በኢትዮጵያ አቆጣጠር ግንቦት 30 ቀን 1969 እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ሰኔ 7 ቀን 1977 ዓ.ም በተዋዋለው ውል መሰረት በፍትሐብሔር ጉዳይ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ያለመክሰስ መብት ያለኝ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለውም የሚል መቃወሚያ አቅርቧል፡፡ 2. የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተጠሪ ዋና  መስሪያ  ቤት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያደረገው ስምምነት ያለመሆኑንና ስምምነቱም እስካሁን ድረስ የፀናና ያልተሻረ መሆኑን ከኢ.ፊ.ዲ.ሪ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በፅሁፍ ያረጋገጠለት መሆኑን ገልፆ፣ ስምምነቱ በይዘቱ የኢትዮጵያ መንግስት...

 • 117517 labor dispute/ unlawful labor practice

  አሰሪው በሰራተኛው ህይወት ላይ አደጋ ሊያደርስ በሚችል አኳኋን እንዲሰራ ማድረግ ህገ ወጥ ተግባር ሲሆን ይህም ሰራተኛው የስራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ ለመቋረጥ በቂ ምክንያት ነው ይህ ከተረጋገጠ ደግሞ ሠራተኛው በአዋጅ መሰረት የተለያዩ ክፍያዎችን የማግኘት መብት  ያለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 14 (1) (ሠ)፣32(1)(ለ) የሰ/መ/ቁ. 117517 ቀን ጥር 30/2008ዓ/ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- ሬድ ፎክስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር - አልቀረበም   ተጠሪ፡- ወ/ት ጀላኔ ጌታቸው - ከጠበቃ መስታውት አሸናፊ ጋር - ቀርበዋል መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡  ፍ ር ድ   ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዳይ በአሰሪና ሰራተኛ የተነሳውን የስራ ክርክር የሚመለከት ነው፡፡ ክርክሩ በፌ/መ/ደረጃ ፍርድ ቤት ሲጀመር ከሳሽ የነበረችው ተጠሪ ናት፡፡ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተው የስራ ውል ከሕግ ውጪ አቋርጠዋል በማለትነው፡፡ በዚህ መሰረትም ልዩ ልዩ ክፍያዎችን እንዲከፈላት ጠይቃለች፡፡   በአመልካች ድርጅት ተመድቤ የምሰራበት ሥራ ከኬሚካል ንኪኪ ያለው በመሆኑ ለሰራተኛው በየጊዜው ምርመራ ይደረጋል፡፡ በመጀመሪያ የተወሰደው የደም ናሙና ውጤቱ የደም ጥራት መጠን በታች በመሆኑ ለሶስት ወር ከኬሚካል ጋር ግንኙነት በሌለበት ሥራ እንዲያዛውር በባለሙያ የተሰጠው አሰተያየት ከአንድ ወር በላይ በመደበቅ ውጤቱ አውቄ ራሴን እንዲጠናቀቅ አልቻልኩም፡፡ ወደ ሌላ ስራ አላዘወረኝም፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ የደም ናሙና ተወስዶ ውጤቱ እንዲያሰውቀኝ ብጠይቅም ምላሽ አልሰጠኝም፡፡ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 32/1/ለ/ መሰረት ከመስከረም 5 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ ስራዬን ለማቋረጥ ተገድጃሎህ፡፡ ስለዚህ ስንብቱ ሕገ ወጥ ተብሎ የተለያዩ...

 • 118252 criminal procedure/ appeal/ stay of exectuion

  በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 188/5/ መሰረት አንድ ፍርድ በተከሳሽ ላይ ከተሰጠ ተከሳሹ ለበላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብሎ ሲቀርብ የበታች ፍርድ ቤትን ውሳኔ የበላይ ፍርድ ቤቱ ማገድ የሚችልበትን አግባብ የሚያሳይ ድንጋጌ ከመሆኑ ውጪ ከሳሽ ወገን በተከሳሽ ነፃ መለቀቅ ላይ ይግባኝ ብሎ ሲሄድ ፍርዱ እንዳይፈፀም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለመስጠት መነሻ የሚያደርገው ስላለመሆኑ   የሰ/መ/ቁ. 118252 ቀን 24/05/2008 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንደሻው አዳነ ቀንዓ ቂጣታ አመልካች፡- ሀብታሙ አያሌው - ጠበቃ አመሃ መኮንን - ቀረቡ   ተጠሪ፡- የፌዴራል ዐቃቤ ህግ - ዐ/ህግ ብርሃኑ ወንድምአገኘሁ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቶአል፡፡  ፍ ር ድ   ጉዳዩ አንድ በሽብር ወንጀል የተከሰሰ ሰው ከክሱ ምንም መከላከል ሳያስፈልገው በነጻ ሲሰነበት በዚሁ ብይን አቃቤ ህግ ይግባኝ ለበላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ የስር ፍርድ ቤት የነጻ መለቀቅ ብይን እንዲታገድለት ሲያመልክት ተቀባይነት የሚያገኝበትን የህግ አግባብ የሚመለከት ነው፡፡   ክርክሩ የጀመረው በፊዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሌሎች ዘጠኝ ግልሰቦች ጋር የተከሰሱበት የጸረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 4 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፈው በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ከሽብር ቡድን ጋር የተለያዩ ግንኙነቶች በመፍጥር የሽብር ቡድኑ በኢትዮጵያ ሊያደርግ ያሰበውን የሽብር እንቅስቃሴ በመምራት በስሩም አባላትን በመመልመል፣ ከሽብር ድርጅቱ አባልና አመራሮች ጋር ግንኙነት በማድረግ፣ የሽብር ቡድኑን ዓላማ፣ ተግባር እና ተልእኮ ለመፈጸም በመንቀሳቀሳቸው በፈጸሙት የሽብርተኝነት ድርጊት ማቀድ፣ መዘጋጅት፣ ማሴር፣ ማነሳሳት እና ሙከራ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ነው፡፡ አመልካቹ የወንጀል ድርጊቱን ክደው በመከራከራቸው አቃቤ ሕግ አሉኝ ያላቸው ማስረጃዎችን አቅርቦ አሰምቶአል፡፡...

 • 118263 labor dispute/ termination of contract of employment/ notice

  አሠሪው ሠራተኛው በሚፈጽመው የሥራ ጥፋት  ማስጠንቀቂያ     በሰጠው ጊዜ የስራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ ማቋረጥ የሚችለው በ30 ቀናት ውስጥ ሲሆን ይህ ቀን ካለፈ በኋላ የሚያደርገው ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ማቋረጥ የሥራ ውል የሚቋረጥባቸውን ሕጋዊ ሥርዓቶች ያላገናዘበ ስለመሆኑ፣   አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 27(3) አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/ሀ/3/፣43/2/   የሰ/መ/ቁ. 118263 ቀን ጥር 18/2008ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመስል እንደሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- ወ/ሮ ሙሪዳ ኑረዲን ቀረቡ   ተጠሪ፡- አቡልኬስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የቀረበ የለም   መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩን ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   በዚህ ጉዳይ በሰበር እንዲታይ የቀረበው መሰረታዊ የክርክር ነጥብ የአሁኑ ተጠሪ የወሰደው ከስራ የማሰናበት እርምጃ በሕጉ አግባብ መሆን ያለመሆኑን ነው፡፡ ጉዳዩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁኗ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ በመ.ቁ. 39053 ባቀረቡት ክስ መነሻነት ነው፡፡ ጉዳዩ በየደረጃው የተመለከቱት የስር ፍ/ቤቶች በአሁኑ ተጠሪ የተወሰደው ከስራ የማሰናበት ተግባር በሕጉ መሰረት ነው በማለታቸው በሰበር እንዲታረም ያቀረበው አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን የቀረበ ነው፡፡   የአሁኗ አመልካች በስር ፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ባጭሩ፡- በተጠሪ ድርጅት በመጋዘን ሃላፊነት ከታህሳስ 06 ቀን 2004ዓ.ም ጀምሮ የስራ ውላቸው እስከተቋረጠበት ግንቦት 21ቀን 2006ዓ.ም ድረስ በወር 3386.32 (ሶስት ሺህ ሶስት መቶ ሰማንያ ስድስት ከሰላሳ ሁለት ሳንቲም) እየተከፈላቸው ስራቸውን ሲሰሩ እንደነበር፤ የአሁኑ ተጠሪ የስራ ውላቸው ከሕግ ውጪ ያቋረጠው በመሆኑ ስንብቱ ሕገወጥ ነው ተብሎ የስራ ስንብት ካሳ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ የግንቦት ወር የ21ቀን ደመወዝ፣ የ4ቀን የዓመት ረፍት ክፍያ እንዲከፈላቸው እንዲወሰንላቸው ዳኝነት መጠየቃቸው የሚያሳይ ነው፡፡ ተጠሪ የመከላከያ መልስ...

 • 119734 labor dispute/ merger / conversion/ termination of contract of employment

  የአንድ ድርጅት ከሌላ ጋር መቀላቀል ወይም  መከፋፈል  ወይም የባለቤትነት መብት ወደ ሌላ መተላለፍ የስራ ውልን የማቋረጥ ውጤት የማይኖረው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/1996 አንቀፅ 23(2) የሰ/መ/ቁ. 119734   የካቲት 30 ቀን 2008 ዓ.ም.   ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ   ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ተብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካች፡- ይርጋ ትሬዲንግ  ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የቀረበ የለም ተጠሪዎች፡- 1.  አቶ ብዙነህ መኮንን 2.  አቶ ሻምበል አሰፋ             ጠበቃ እስጢፋኖስ ተስፋ ቀረቡ 3.  አቶ ረድኤት መሐመድ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ጉዳዩ የስራ ስንብት እርምጃን በመቃወም የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 “ን” መሰረት አድርጎ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት በአዳማ ልዩ ዞን በአዳማ ወረዳ ፍርድ ቤት ከሳሾች የነበሩት የአሁኖቹ ተጠሪዎች በአሁኑ አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው፡፡ ከሳሾቹ በ16/10/2007 ዓ.ም. ያቀረቡት ክስ ይዘትም ባጭሩ፡- ከሳሾቹ በተከሳሽ ድርጅት ውስጥ ከተለያየ ጊዜ ጀምሮ በተለያየ የስራ መደብ የተለያየ መጠን ያለው ደመወዝ እየተከፈላቸው በመስራት ላይ እያሉ የድርጅቱ ባለቤት ተከሳሽ ድርጅትን ሽጠው ተከሳሽ ድርጅት ለከሳሾቹ ሌላ ስራ ሳይሰጥ ወይም ተገቢ ክፍያዎችን ሳይከፍል አላግባብ ከስራ ያሰናበታቸው መሆኑን የሚገልጽ ሆኖ የስንብት እርምጃው ሕገወጥ ነው ተብሎ ሕገወጥ የስራ ስንብት እርምጃ የሚያስከትላቸው እና ተያያዥ ክፍያዎች በአዋጁ መሰረት  ተሰልቶ እንዲከፈላቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት የተጠየቀበት ነው፡፡ተከሳሽ ድርጅት በበኩሉ በ02/11/2007 ዓ.ም. በሰጠው መልስ ከሳሾቹ ከስራ እንዲሰናበቱ የተደረገው ድርጅቱ በመሸጡ እና የሚመደቡበት ሌላ የስራ ቦታ ባለመገኘቱ መሆኑን ገልጾ ክሱ ውድቅ እንዲደረግ ተከራክሯል፡፡ ፍርድ ቤቱም ክሱን እና...

 • 120762 criminal procedure/ prosecution in absentia/ representation by lawyer

  በወንጀል ጉዳይ ተከሳሽ በሌለበት ጠበቃ ብቻውን ሊቀርብ አይችልም የሚለው ጉዳይ ተፈፃሚ የሚሆነው ለተፈጥሮ ሰዎች እንጂ የህግ ሰውነት ላላቸው ሰዎች ስላለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.127   የሰ/መ/ቁ/120762 የካቲት 25 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡-አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ     አመልካች፡-የፌደራል ዐቃቤ ሕግ - ሮዛ በላቸው      ቀረቡ   ተጠሪ፡- 1. ዱባይ አውቶ ጋለሪ-ኤል.ኤል.ሲ             ጠበቃ አበበ አስማረ 2. ወርልድ ኢንተርናሽናል ፍሪዞን ካምፓኒ መዝገቡ የተቀጠረው መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ነው፡፡ በመሆኑም ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ይህ የሰበር አቤቱታ ሊቀርብ የቻለው አመልካቾች ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 155568 ታህሳስ 28 ቀን 2007 ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ላይ የቀረበውን ይግባኝ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 111863 ጥቅምት 1 ቀን 2008 ዓ.ም ይግባኝ የሚባልበት አይደለም በማለት መዝገቡን በመዝጋቱ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለቱ ነው፡፡   ጉዳዩ የሕግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት የወንጀል ክስ በቀረበበት ጊዜ በጠበቃ የመወከል ላይ የተሰጠ ትእዛዝ ይግባኝ ሊቀርብበት የሚገባ መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነው፡፡ በስር ፍ/ቤት ከሳሽ አመልካች ሲሆን ተከሳሾች እነአሽረፋ አወል አብዩ /17 ሰዎች/ ሲሆን ተጠሪዎች 12ኛ እና 13ኛ ተከሳሾች ነበሩ፡፡ አመልካች በተከሳሾች ላይ 6 የተለያዩ ክሶችን ያቀረበ ሲሆን በተጠሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ 3ኛ ክስ የወ/ህ/ቁ 32/1/ /ለ/፣ 34/1/ እና የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 96 የተመለከተውን በመተላለፍ የንግድ ትርፍ ግብር  ባለመክፈል፣ 4ኛ ክስ የወ/ህ/ቁ 32/1/ /ለ/፣ 34/1/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 49 በመተላለፍ ግብይት ባካሄዱባቸው ሥራዎች ተጨማሪ እሴት ታክስ አሳውቆ ባለመክፈል፣...

 • 92991 jurisdiction/ investment

  ካሳ አነሰኝ ወይም ተከለከልሁ ካልሆነ በቀር በኢንቨስትመንት የሚቀርቡ የሕግም ሆነ የፍሬ ነገር ክርክር ይግባኞች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጠው ፍርድ ቤት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 138 አንቀጽ 6/5/     የሰ/መ/ቁ. 92991   ጥቅምት 1 ቀን 2008 ዓ.ም   ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ   ብርሃኑ አመነው ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- አቶ ተፈራ ተሰማ አልቀረቡም፡፡   ተጠሪ፡- የአርሲ ዞን አስተደደር ጽ/ቤት አልቀረቡም፡፡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ወስነናል፡፡  ፍ ር ድ   ጉዳዩ የኢንቨስትመንት ውልን መሠረት አድርጐ ለአመልካች ተሠጥቶ የነበረ የገጠር መሬትን የሚመለከት ሲሆን ተጠሪ ውሉን አፍርሶ መሬቱ እንዲለቀቅ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ለክሱ ምክንያት በማድረግ አመልካች ለአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀጥታ ክስ አቅርበዋል፡፡ ፍ/ቤቱም በተጠሪ የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በመቀበል ጉዳዩ የኢንቨስትመንት ጉዳዩችን አይቶ ውሳኔ ለመስጠት የተቋቋመው የኢንቨስትመንት ኮሚቴ ስልጣን መሆኑን በመጥቀስ መዝገቡን ዘግቷል፡፡   ይግባኝ እና የሰበር አቤቱታ የቀረበላቸው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ችሎቶችም ውሳኔው ጉድለት የለበትም እንዲሁም የህግ ስህተት አልተፈፀመበትም በማለት አሰናብተዋል፡፡   የሰበር አቤቱታው ለዚህ ፍ/ቤት የቀረበው ይህን በመቃወም ነው፡፡ አቤቱታው ተመርምሮ አመልካች በሊዝ የወሰደውን መሬት በማልማት የተለያዩ አትክልት አይነቶች እያመረተ መሆኑን በሚከራከርበት ሁኔታና የአርሲ ዞን አስተዳደር የኢንቨስትመንት ኮሚቴ ከአዋጅ ውጭ መሬቱን የነጠቀው መሆኑን እየተከራከረ የሥር ፍ/ቤቶች ጉዳዩ በዳኝነት አካል የሚታዮ አይደለም በማለት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ የማድረጋቸው አግባብነት የኦሮሚያ ክልል  ኢንቨስትመንት አስተዳደር እንደገና ለመወሰን ከወጣው አዋጅ ቁጥር 115/1998 አንፃር ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡ ግራ ቀኙም ክርክራቸውን በፅሑፍ አቅርበዋል፡፡ በበኩላቸን ቅሬታ...

 • 94913 criminal law/ corporate criminal liability

  አንድ ድርጅት ወንጀል እንዳደረገ የሚቆጠረው ከኃላፊዎች አንዱ ወይም ከሠራተኞች አንዱ ከድርጅቱ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የድርጅቱን ጥቅም በሕገ ወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ ወይም የድርጅቱን ሕጋዊ ግዴታ በመጣስ ወይም በመጠቀም በዋና ወንጀል አድራጊነት ወይም አነሳሽነት ወይም አባሪነት ወንጀል ሲፈጸም ብቻ ስለመሆኑ፣ የወ/ሕግ አንቀጽ 23 እና አንቀጽ 34/1/ ጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 93/1ሀ/ እና 93/2/   የሰ/መ/ቁ.94913 ህዳር 24 ቀን 2008 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማዉ ወሌ ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻዉ አዳነ ቀነዓ ቂጣታ   አመልካች፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት - ዓ/ሕግ አቤል ገ/እግዚአብሔር - ቀረቡ ተጠሪዎች፡-   1. ጆሳምቢን ትሬዲንግ ኃ/የግ/ማህበር       ከጠበቃ አለማየሁ ታደሰ ጋር - ቀረቡ 2. አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ አርጋዉ መዝገቡን መርምረን የሚከተለዉን ፍርድ ሰጥተናል፡፡  ፍ ር ድ ይህ የሰበር ጉዳይ ከጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ጋር በተያያዘ ተፈጸመ የተባለዉን የማጭበርበር ወንጀል የሚመለከት ክርክር መሰረት ያደረገ ነዉ፡፡ የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ፡- የሥር ከሳሽ /የአሁን አመልካች/ በምስራቅ ሻዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረበዉ ክስ ተከሳሾች የጉምሩክ አዋጅ ቁ.622/2001 አንቀጽ 93 /1/ (ሀ) እና 93 /2/ በመፈተላለፍ ቻይና አገር የተመረቱን ዕቃዎች ከዉጭ አገር ለማስገባት የንግድ ፈቃድ አዉጥቶ፣ ዕቃዎቹ ሞጆ ደረቅ ወደብ ገብቶ ሲፈተሽ በዲክላራስዮን ቁጥር C-10951 በ20/12/2012 እ.አ.አ. እና ይህን በሚደግፍ ሰነድ ላይ ያልተሞለዉን መለያ ያለዉ ቬትናም አገር የተመረተ እና የጫማ ሳጥን በማስገባት ቀረጥ እና ታክስ ብር 3,328,524.38 መከፈል ያለበትን ብር 931,799.33 በመክፈል በልዩነት ብር 2,396,725.05 ሳይከፍል ዝቅተኛ ቀረጥና...

 • 95537 civil procedure/ execution of judgment

  የአፈጻጸም ጥያቄ የቀረበለት ፍርድ ቤት ለአፈጻጸሙ ተስማሚ በሆነ መንገድ ፍርድ እንዲፈጸም ትዕዛዝ የሚሰጠው የፍርድ ባለዕዳውን ጠርቶ ከመረመረው በኃላ እንደፍርዱ የማይፈጸምበት ምክንያት አለመኖሩን ካረጋገጠ በኃላ ስለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 207 እና 320(2) መሰረት በተሰጠው ትእዛዝ ላይ ቅሬታ አቅርቦ ነገር ግን ቅሬታው ተቀባይነት ቢያጣ የይግባኝ መብቱን (የይግባኝ ጊዜ ሊሰላበት) ስለሚችልበት አግባብ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 392 (1)   የሰ/መ/ቁ. 95941   ታህሳስ 7 ቀን 2008 ዓ.ም   ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ ፈይሳ ወርቁ     አመልካች፡-   ሔስ ትራቭል ኃ/የተ/የግ/ማህበር - ጠበቃ ረታ አለማየሁ - ቀርበዋል   ተጠሪዎች፡- 1. የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዓ/ህግ ኃይለመለኮት አበበ - ቀርበዋል 2. የኢትዮጵያ ግዮን ሆቴሎች ድርጅት - ነ/ፈ ሙላት ማሞ - ቀርበዋል፡፡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ተሰጥቷል፡፡ ተከታዩን    ፍ ር ድ   በዚህ የሰበር አቤቱታ መዝገብ ክርክር አመልካች ሔስ ትራቭል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ታህሣስ 15 ቀን 2006 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የፌ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 92474፣ ጥቅምት 18 ቀን 2006 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠውን ትዕዛዝ በመቃወም የቀረበ ነው፡፡ ቅሬታውም የአሁን 1ኛ ተጠሪ ሲከራከር የነበረው ለአመልካች የገበሩት ታክስ ቅናሽ እንዲደረግለት ግብሩን ሲያሳውቅ አብሮ ሕጋዊ ደረሰኝ (የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ) ማቅረብ አለበት፡፡ አመልካች ግን ደረሰኝ ብያቀርብም ህጋዊ አይደለም የሚል ሲሆን፤ ከአሁን በፊት የፌ/ከ/ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በጣልቃ ገቢነት የኢትዮጲያ ግዮን ሆቴሎች ድርጅት ገብቶ እንዲከራከር ወስኖ ወደ ፌ/ከ/ፍ/ቤት በመለሰው መሠረት የኢት.ግዮን ሆቴሎች ድርጅት በጣልቃ ገቢነት የሰጠው መልስ በግብር ዘመኑ ገቢ ያደረገ መሆኑን ከአሁን አመልካች ብር...

 • 95922 contract/ commercial code/ contract of carriage/ period of limitation

  የመጓጓዣ ውልን መሰረት ያደረገ የካሳ ጥያቄ ሲቀርብ ጉዳዩ በየትኛው የህግ ማዕቀፍ እንደሚገዛ መለየት የይርጋውንም ሆነ የካሳ ስሌቱን በአግባቡ ለመዳኘት የሚያስችል ስለመሆኑ የን/ሕ/ቁጥር 587፣595 ፣597፣599 እና 603 የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2143፣ 2090   የሰ/መ/ቁ. 95922 መስከረም 26 ቀን 2008 ዓ.ም     ዳኞች፡- አልማው ወሌ ረታ ቶሎሳ ሙስጠፋ አህመድ ቀነዓ ቂጣታ ሌሊሴ ደሳለኝ     አመልካች፡- 1.አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ - ነ/ፈጅ ብሩክ ዘረሁን - ቀረቡ 2. አቶተፈራ ታርቄ - ቀረቡ ተጠሪ፡-    1.ሃምሳ አለቃ ለገሰ ክፍለይ    ጠበቃ አወግቸው መኮንን ቀረቡ 2. ወ/ሮ አክበረት አማረ   መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡      ፍ ር ድ     ጉዳዩ የአጓዥ ተጓዥ ውልን መሰረት ያደረገን የጉዳት ካሳ ይከፈለን ጥያቄ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪዎች በአሁኑ 2ኛአመልካች ላይ በሰሜን ሸዋ መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትግንቦት 28 ቀን 2005 ዓ.ም በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው፡፡የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- ንብረትነቱ የአሁኑ 2ኛአመልካች የሆነ የሰሌዳ ቁጥር ኢት 3-10457 ፣ የጎን ቁጥሩ 1320 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ የተጠሪዎች ልጅ የሆነውን አለም ለገሰ ከአዲስ አበባ ተሳፍሮ ወደ መቐሌ በመጓዝ ላይ እያለ ደብረ ብርሃን ከተማ ቀበሌ 09 ተብሎ  ከሚጠራው ስፍራ ሲደርስ መኪናው ተገልብጦ በዚህ ምክንያት የልጃቸው ህይወት ማለፉንና በህይወትእያለም በግብርና ስራ ላይ ተሰማርቶ ይረዳቸው የነበረ መሆኑን ገልጸው በጠቅላላው ብር 484,000.00( አራት መቶ ሰማንያ አራት ሺ ብር) ካሳ እንዲከፈላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ የአሁኑ 2ኛ አመልካችም ሟች በመኪናቸው ተሳፍረው ሲሄድ መሞቱን ሳይክዱ ግንኙነቱ የመጓጓዣ ውልን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ክሱ ከውል ውጪ ሊቀርብ እንደማይገባ፣ በአጓዥ ግንኙነትም ክሱ መቅረብ የነበረበት በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሁኖ እያለ ከአራት ዓመታት በላይ ቆይቶ መቅረቡ ያላግባብ መሆኑን፣...

 • 95941 criminal law/ tax offense/ turn over tax

  የቲ.ኦቲ /ተርን ኦቨር ታክስ/ ተመዝጋቢ የሆነ ሰው በህግ ፊት እንደ መረጃ /ማስረጃ / ሊያቀርብባቸው የሚገቡ ደረሰኞች ከቫት በተቀበለው የቲ.ኦ.ቲ ደረሰኝ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ /ታክስ የቲ.ኦቲ አዋጅ ቁጥር 285/194 አንቀጽ 21/

 • 96041 contract/ evidence

  በውል የተገባ አንድ ግዴታ መፈጸም ያለመፈጸሙን ለማጣራት የግራ ቀኙ ተዋዋይ ወገኖች የገቡት ግዴታ እና ያላቸው መብት የሚገልጽ የሰነድና የሰው ማስረጃ እንዲሁም የግዴታ ልዩ ባህርይ መሰረት በማድረግ ልምድን መዳሰስ የሚጠይቅ ስለመሆኑ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ 246፣247፣248 እና 249   የሰ/መ/ቁ. 96041   ጥቅምት 26 ቀን 2008 ዓ.ም       ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኸሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ወ/ሮ አልማዝ ግዛው ተወካይ ትዝታ አቡሌ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል    ፍ ር ድ   የጉዳዩ መነሻ በፖስታ ቤት በኩል ወደ ኖርዌይ አገር እንዲላክ አመልከች የተረከበው እቃ አደራረስ ላይ በተነሳው ክርክር የግራቀኙ መብትና ግዴታ ምን እንደነበር ከመወሰን እንፃር የቀረበ ነው ፡፡ በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል ፡፡ ጉዳዩን በየደረጃው የተመለከቱት የሥር ፍ/ቤቶች የአመልካች መከራከሪያ ነጥቦች ውድቅ በማድረግ የዕቃውን ዋጋ እንዲከፍል በመወሰናቸው ምክንያት መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልከች ያቀረበው አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን የቀረበ ነው፡፡   የክሱ ይዘትም፡- አመልካች ወደ ኖርዌይ አገር ዕቃውን ለማድረስ ውል የገባ ቢሆንም ዕቃውን በውሉ መስረት ወደ ተባለው አገር ባለማድረሱ ነው የዕቃው ግምትና የማጓዣ ክፍያ በድምር ብር 9374.38 /ዘጠኝ ሺህሦስት መቶ ሰባ አራት 38/100) እንዲከፍላት ተጠሪ ዳኝነት መጠየቋን የሚያሳይ ነው ፡፡ የአሁኑ አመልካች በሰጠው መልስም በግራቀኙ ስምምነት መስረት ዕቃው ወደ ኖርዌይ ተልኮ ተቀባይ ካላገኘ እንደሚመጣ መፈረማቸው ዕቃው ወደ ተባለው አገር ተልኮ ተቀባይ ያጣ በመሆኑ ወደ ሀገር ቤት እንደተመለሰ ፤የተጠሪ ክስ ውድቅ ሊደረግ ይገባል ሲል ተከራክረዋል፡፡   የሥር ፍርድ ቤትም የግራቀኙ ክርክር ከመረመረ በኃላ አመልካች...

 • 96548 extracontractual liability/ professional liability

  በወሊድ ወቅት በህክምና ተቋሙና በሙያው ባለቤት ዘርፉ የሚጠይቀውን ጥንቃቄ ሳይደረግ በሚወለደው ህፃን ላይ የአካል ጉዳት ከደረሰ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1790፣2028፣2031፣2647 /2/ እና 2651   የሰ/መ/ቁ. 96548   መስከረም 24 ቀን 2008 ዓ.ም.   ዳኞች፡-አልማው ወሌ   ረታ ቶሎሳ ሙስጠፋ አህመድ ቀነዓ ቂጣታ ሌሊሴ ደሳለኝ   አመልካች፡- የሐያት ሆስፒታል ባለቤት አቶ ኢብራሂም ናውድ ጠበቃ ፍቅሬ ሞያ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን /የህፃን ሐምራዊ ቀለሙ ሞግዚት - ጠበቃ አሰፋ አሊ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ ር ድ   ይህ ጉዳይ በወሊድ ወቅት በተጠሪ ሕፃን ላይ የደረሰውን የአካል ጉዳት በተመለከተ የጉዳት ካሳ ለማስከፈል የቀረበ  ክስን  መነሻ  ያደረገ  ክርክር  ነው፡፡ የጉዳዩ አመጣጥ  ሲታይ፡-  የስር ከሳሽ /የአሁን ተጠሪ/ በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረበችው ክስ ከሳሽ በ1ኛ ተከሳሽ ሆስፒታል የነፍሰጡር ምርመራ ክትትል ሳደርግ ቆይቼ፣ መጋቢት 4 ቀን 1992 ዓ/ም በ2ኛ ተከሳሽ ዶ/ር ይልማ አስረስ/ አዋላጅ ሀኪም አማካኝነት የወለድኩ ሲሆን የህፃን ሐምራዊ ቀለሙ እናት ከወሊድ በፊት በጥሩ ጤንነት ላይ የነበርኩኝ፤ በወሊድ ወቅት አዋላጅ ሐኪም በትክክለኛ የማዋለድ ሥርዓት የሙያ ግዴታቸውን መፈጸም ሲገባቸው ባለማድረጋቸው በቸልተኝነት ጉዳት የደረሰባት ልጅ እንድትወለድ አድርገዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ሕፃን ሐምራዊ ቀለሙ የጡንቻዎች መስነፍ፣ የብራካ መስለል፣ የቀኝ እጅ መስነፍ እና መዘርጋት ችግር አጋጥሟታል፣ ሕፃን ሐምራዊ ቀለሙ ላይ በወሊድ ወቅት የደረሰባት ከፍተኛ የጤና ጉዳት ችግር ለወደፊት የትምህርት እና እንቅስቃሴ ቀጣይ ሕይወቷ ላይ ቋሚ የሆነ ከፍተኛ ጉዳት እና ተፅዕኖ የሚያሳድር ነው፡፡ ስለዚህ ሕፃን ሐምራዊ ቀለሙ ወደ ውጭ አገር ሄዳ ቀዶ ጥገና ሕክምና ማድረግ እንዳለባት በባለሙያ ስለተረጋገጠ ለውጭ አገር ሕክምና እና ለልዩ ልዩ ወጪ...

 • 97760 contract/ commercial law/ contract of carriage

  በአጓዥ ጥፋት በደረሰ አደጋ ምክንያት በተጓዡ(መንገደኛው) ላይ ለደረሰው ጉዳት ካሳ ለመወሰን ልንከተላቸው ስለሚገቡ የካሳ አከፋፈል መርሆች የን/ሕ/ቁ. 599፣ የፍ/ሕ/ቁ. 2091 እና 2092     የሰ/መ/ቁ.97760 ታህሳስ 19 ቀን 2008 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- ወ/ሮ ንግስቲ አትክልቲ  -ጠበቃ ሙሉዓለም ፈጠነ ቀረቡ፡፡ ተጠሪ፡- አቶ አበባው ሽፈራው                    -የቀረበ የለም፡፡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ  ር ድ   ጉዳዩ የአካል ጉዳት ካሳ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኗ አመልካች እና አቶ በረከት ተስፋዬ ላይ በመሰረቱት ክስ ነው፡፡ የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡ ንብረትነቱ የአመልካች በሆነውና በስር 2ኛ ተከሳሽ በነበሩት በአቶ በረከት ተስፋዬ ይሽከረከር በነበረው ኮድ 3- 58098 አ.አ ተሸከርካሪ ከአለታ ወንዶ ከተማ ወደ ሐዋሳ ከተማ ብር 22.00 ከፍለው በመጓጓዝ ላይ እንዳሉ መኪናው በከፍተኛ ፍጥነት ይሸከረከርና ሹፌሩም ሞይባል ያናገር ስለነበር ከተራራው ጋር ተጋጭተው በአካላቸው ላይ  50% የአካል ጉዳት  የደረሰባቸው መሆኑን፣በዚህም ምክንያት  ገቢ ያጡና ለሕክምና ወጪ ያወጡ መሆኑንና ሹፌሩም በወንጀል የተቀጡ መሆኑን ዘርዝረው  በድምሩ ብር 497,105.97(አራት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ አንድ መቶ አምስት ብር  ከዘጠና ሳንቲም) ባልተነጣጠለ ኃላፊነት የመኪናው ባለቤትና ሹፌሩ እንዲከፍሉ ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስም ጉዳቱ የጥቅም ግንኙነት በሌለው ሁኔታ ስለመሆኑ፣ ተጠሪ በጉዳቱ ምክንያት የተቋረጠባቸው ገቢ ወይም ጥቅም የሌለ መሆኑንና የጉዳት ካሳ መጠኑም የተጋነነ መሆኑን ዘርዝረው ክሱ ውድቅ ሊሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡ የሥር 2ኛ ተከሳሽ የነበሩት ግለሰብ ባለመቅረባቸው ጉዳዩ በሌሉበት እንዲታይ ተደርጎአል፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ...

 • 97797 contract/ contract of sale/

  አንድ የሽያጭ ውል የእጅ በእጅ ሽያጭ ውል ነው ለማለት ስለሚቻልበት አግባብ የፍ/ብ/ሕ/ አንቀጽ 2278(1) የሰ/መ/ቁ.97797 መስከረም 28/2008 ዓ/ም ዳኞች፡-ተገኔ ጌታነህ   ተሻገር ገ/ስለሴ ብርሃኑ አመነው ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካች፡- ናሽናል ስሚንቶ አ/ማህበር አልቀረቡም   ተጠሪ፡- አቶ ብርሃኑ ግደይ   ጠበቃ አቶ በላቸው ዘመድኩን ቀረቡ   መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ  ር ድ   በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ የሽያጭ ውል አፈፃፀም የተመለከተ ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት ከሳሽ የአሁን ተጠሪ ነው፡፡ የክሱም ይዘት ከአመልካች ጋር መጋቢት 30 ቀን 2003 ዓ/ም በተደረገ የሽያጭ ውል ስምንት ሺህ ኩንታል (8000) ስሚንቶ የአንዱ ኩንታል ብር 255.41 ሂሣብ ቫት እና ታርንኦቫር ታክስ ጨምሮ ነው 2,360,000 (ሁለት ሚሊዮን ሦስት መቶ ስልሣ ሺህ) መክፈሉን እና አመልካች (ሸጭ) 7272 ኩንታል ሲምንቶ ካሰረከበ በኃላ 723 ኩንታል ስሚንቶ ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ይህንኑ ቀሪ ስሚንቶ ተገዶ እንዲያሰረክብ አለያም ዋጋውን ብር 214. 760 እንዲከፍል እንዲወሰን ጠይቋል በአመልካች በኩል የቀረበው ክርክር የዋጋ ለውጥ ሊደረግ እንደሚቻል አስቀድሞ መስማማታቸው በዚሁም መሠረት በየጊዜው የዋጋ ለውጥ ሲደረግ እንደነበርና ተጠሪም ይህንኑ አውቆ ሲረከብ እንደነበረ ገልጾ አጠቃላይ እስከ አሁን የተረከበው በየጊዜው ከነበረው ዋጋ ለውጥ አንፃር ተሰልቶ ቀሪ ብር 120 (አንድ መቶ ሃያ ብር) ብቻ መሆኑን ጠቅሶ ክሱ ውድቅ እንድደረግ ጠይቋል፡፡   ጉዳዩ በመጀመሪያ የዳኝነት ሥልጣን ያከራከረው የፌዴራል የመ/ደረጃ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ከመረመረ በኃላ የስሚንቶ ዋጋ ለውጥ ወይም ጭማሪ መደረጉን የተጠሪ (የከሳሽ) ወኪል ያውቃል እንዲሁም ለተጠሪም አሳውቋል ዋጋ ጭማሪ የተደረገውም በስምምነታቸው    መሠረት ነው በማለት ተጠሪ...

 • 98348 contract/ performance bond

  ለመልካም ሥራ አፈጻጸም ለዋስትና የተያዘ ገንዘብ ውሉ እንደውሉ ሳይፈጸም ሲቀር ዋስትና አስያዡ የተያዘውን ገንዘብ በውል ለተጎዳው ወገን መክፈል የሚገባው ስለመሆኑ ለመልካም ስራ አፈፃፀም የሚሰጥ ዋስትና ዓይነተኛ ዓላማው በተሰራው ነገር ጉዳት የደረሰበት ተዋዋይ ወገን በገንዘቡ ረገድ ለመካስ ስለመሆኑ ፍ/ሕ/ቁ. 1815   ys¼m¼q$¼98348 ¬HúS 18 qN 2008 ›¼M   xmLµÓCÝ.1ኛ አቶ ዘሪሁን የኔነህ ቀረቡ 2ኛ የአቶ የኔነህ ጨርቆሴ ህጋዊ ወረሾች 1.  አቶ ታረቀኝ የኔነህ 2.   ,,  የኃላሸት የኔነህ አልቀረቡም 3.   ,,  ዘሪሁን የኔነህ t-¶Ý( ሀዋሣ ዩኒቨርሲቲ ነገረ ፈጅ እንግዳወርቅ ጌታቸው ቀረቡ mZgb#N mRMrN tk¬†N FRD s_tÂLÝÝ F R D ጉዳዩ የመልከም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን አመልከቾች ባሁኑ ተጠሪ እና በዚህ መዝገብ የክርክሩ ተከፋይ ባልሆኑ 1ኛ ወ/ት ንሰሐ ወርቅህ 2ኛ ዳሽን ባንክ ላይ ባቀረቡት ክስ መነሻነት ነው፡፡ የክሱ ይዘትም በዚህ መዝገብ የክርክሩ ተከፋይ ያልሆነችው ወ/ሪት ንሰሐ ወርቅነህ ከአሁኑ ተጠሪ ሀዋሣ ዩኒቨርሰቲ ጋር በተፈራረሙት የበሰለ ምግም አቅርቦት ውል 1ኛ ተከሳሽ የነበረቸው ወ/ት ንሰሐ ቀርቅነህ ለመልከም አፈፃፀም ዋስትና 3ኛ ተከሳሽ ከነበረው የዳሽን ባንክ እንዲሰጣት ጠይቃ፤ 3ኛ ተከሳሽም ለዋሰትና የሚበቃ ንብራት እንድታቀርብ በመጠየቁ የአሁኑ 1ኛ አመልከች በስሙ ተመዝግቦ የሚገኝ የመኖሪያ ቤትና የሰሌዳ ቁጥር 3-42314 አይሱዙ የጭነት መኪና እንዲሁም 2ኛ አመልከች የመኖሪያ ቤት በመያዣ እንዲያዝ በመፍቀዳቸው ሦስቱም ንብረቶች በብር 658,568.00 ተገምተው ህዳር 15 ቀን 2007 ዓ/ም እ/ኤ/አ/ በተፈረመ የመያዣ ውል ለ3ኛ ተከሳሽ ሰጥቷል፡፡ 2ኛ ተከሳሽ (የአሁኑ ተጠሪ) አቅርቦቱ የጥራት ደረጃውን አልጠበቀም...

 • 98583 contract/ authentication of date/

  የአንድን የውል ሰነድ እርግጠኛ ቀን የሚባለው ሰነዱን የፃፈው ወይም የተቀበለው እንደ ሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ፅ/ቤትን የመሰለ የመንግስት መስሪያ ቤት ሲሆን የፃፈበት ወይም የተቀበለበት ቀን ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ.2015(ሀ) የሰ/መ/ቁ.98583 መስከረም 27 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ   ተሻገር ገ/ሥላሴ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካቾች፡- 1ኛ/ ወ/ሮ ኤደን ሲሳይ         ጠበቃ አቶ በላይነህ ማሞ ቀረበ 2ኛ/ ወ/ሮ አስቴር ደምሴ ተጠሪ፡- አቶ ሰይፈ ዓለሙ - የህፃን ናትናኤል ሰይፋ እና የህፃን ዮናታን ሰይፋ ሞግዚት ጠበቃ አለማየሁ አበበ   መዝገቡን መርምረን ተከታዮን ወስነናል ፡፡    ፍ ር ድ   ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዳዩ የውል ይፍረስልኝ የዳኝነት ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ጉዳዩ የጀመረው በፌ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ነው ፡፡ የአሁን ተጠሪ ከሳሽ ፤የአሁን አመልካቾች ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ፡፡   ከሥር ፍ/ቤቾች የውሳኔ ግልባጮች መረዳት እንደሚቻለው ከሳሽ ባቀረቡት የክስ አቤቱታ የሟች ወ/ሮ ፈትለወርቅ ተረፈ በህይወት በነበሩበት ወቅት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ቀበሌ 09/14 የቤት ቁጥር 750 የሆነ የድርጅት ቤት የነበራቸው ሲሆን ይህን ቤት 1ኛ ተከሳሽ ከሟች ውክልና ተሠጥቶኛል በሚል ሟች በከፍተኛ ህመም በነበሩበት ጥቅምት 25/2002 ዓ.ም ተደረገ በተባለ ውል ለ 2ኛ ተከሳሽ የሸጡ በመሆኑና ውሉንም አደረግን የሚሉት በውል አዋዋይ ፊት ሟች ከሞቱ ከዘጠኝ ቀን በኃላ በመሆኑ ፤ውክልናው በሞት ምክንያት ቀሪ ከተደረገ በኃላ የተደረገ በመሆኑና ፤ቤቱም በሚሊዮን የሚቆጠር ዋጋ የሚያወጣ ሆኖ እያለ ሞግዚት የሆንኩላቸውን ተተኪ ወራሾች ለመጉዳት በብር 250,000.00 ተሸጠ መባሉ ተገቢ ባለመሆኑ ውሉ እንዲፈርስ እንዲወሰን በማለት ጠይቀዋል ፡፡ ተከሳሾችም በየራሳቸው በሠጡት መልስ ሟች ቤቱን ሚያዝያ 1/2001 ዓ.ም በተደረገ የመንደር ውል...

 • 98961 contract/ agency/ conflict of interest/ period of limitation

  ተወካይ የውክልና ስልጣኑን መሠረት በማድረግ ከሶስተኛ ወገን ጋር የሚያደርገው ውል ከወካይ ጋር የጥቅም ግጭት ተፈጠሯል ብሎ ወካይ ካወቀ ይህንን ለመቃወም /ለመስፈረስ/የሚችለው ወካይ ይህንን ሁኔታ መፈጠሩን ካወቀበት እስከ ሁለት ዓመት ጊዜ ድረስ ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 2187(1)(2 የሰ/መ/ቁ.98961 መስከረም 24 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ረታ ቶሎሣ ሙስጠፋ አህመድ ቀነዓ ቂጣታ ሌሊሴ ደሣለኝ አመልካቾች፡- 1. አቶ ኡመር መሐመድ                              ከጠበቃ ገናነው ተሾመ 2. ወ/ሮ ነፍሳ ሲራጅ            ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- ሻ/ባሻ ከድር ቬህ አብዱላሂ - አልቀረበም፡፡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡    ፍ ር ድ   ይህ ጉዳይ ከውክልና /እንደራሴነት/ ህግ አፈፃፀም ጋር ተያይዞ የቀረበን ክርክር የሚመከለት ሆኖ ክርክሩም የጀመረው የአሁኑ ተጠሪ በባሌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በአመልካቾች ላይ በመሰረተው ክስ መነሻነት ነው፡፡ ተጠሪ ግንቦት 10 ቀን 2003 ዓ.ም በተጻፈ ለስር ፍ/ቤት ያቀረበው የክሱ ይዘት ባጭሩ፡- ተጠሪ በጊኒር ከተማ 02 ቀበሌ ውስጥ በስማቸው የተመዘገበ ቤት ያላቸው መሆኑን፣ ይህንኑ ቤትና ቦታ 1ኛ አመልካች በአደራ እንዲጠብቁና እንዲያስተዳድሩ የሚል በ4/9/1985 ዓ.ም በውልና ማስረጃ ጽ/ቤት የተመዘገበ የውክልና ስልጣን ተሰጥቷቸው የነበረ መሆኑን፣ ሆኖም ግን አንደኛ አመልካች ከተሰጠው ውክልና ስልጣን ውጭ በመውጣት ባለቤታቸው ለሆኑት ለሁለተኛ አመልካች በዝቅተኛ ዋጋ በብር 2500 የሸጡ መሆኑን፣ በዚሁ መነሻነት ለ1ኛ አመልካች ተሰጥቶ የነበረው የውክልና ስልጣን በተጠሪ መሻሩን፣ ይህንኑን ተከትሎም አንደኛ አመልካች ቤቱን ለማስረከብ ፍላጎት ስላልነበረው በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ-05861 በሆነው ላይ ክስ ቀርቦ እንደነበረና ፍ/ቤቱም በበኩሉ አንደኛ አመልካች በቤቱ ላይ የፈፀመው የሽያጭ ውል የተጠሪን መብት የሚጋፋ ከሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ-2187 መሠረት ውሉ እንዲፈርስ የመጠየቅ መብቱን ጠብቆ ወስኖ...

 • 99082 intellectual property/ moral damage

  በቅጂና ተዛማጅ መብቶች መጣስ /ለሚደርስ ለጉዳት ካሳ/ ወይም የሞራል ካሳ ዋጋው በተዋዋዮች ወገን ካልተቆረጠ የወቅቱን ዋጋ አጣርቶ መወሰን የሚገባ ስለመሆኑ፣ የሞራል ካሳ አከፋፈል ከፍ/ብ/ሕ/ቁ ውጪ መወሰን የሌለበት ስለመሆኑ የቅጂና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ ቁ 410/96 አንቀጽ 7፣8፣37 የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2102   የሰ/መ/ቁ. 99082   ጥቅምት 23 ቀን 2008 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ   አመልካች፡- ወ/ሮ ፍሬ ህይወት ደመቀ (የመካኒኩ ፊልም ኘሬዲውሰር)- ጠበቃ ሙሉጌታ ዘመነ ቀረቡ፡፡   ተጠሪ፡- ወ/ት ቤሩት ዳዊት - ጠበቃ መንግስቴ ቀረቡ፡፡   መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቶአል፡፡    ፍ         ር         ድ   ጉዳዩ የቅጅና ተዛማጅ መብት ጥያቄ ጋር የተያያዘ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኗ አመልካች ላይ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው፡፡   የተጠሪ የክስ ይዘትም፡- ዕውቀታቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ ጊዜያቸውን በመሰዋት በነጠላ ዜማ የለቀቁትን “በትዝታ አቅርቤ” የተሰኘውን የዘፈን ሥራቸውን ያለፈቃዳቸውና ያለ ስምምነታቸው የአሁኗ አመልካች ኘሮዲውስ ላደረጉት "መካኒኩ" ለተባለው ፊልም በማጀቢያነት (ሳውንድትራክ) በመጠቀም ያለአግባብ ቁሳዊ ጥቅም ያገኙበት መሆኑን፣በአመልካች አድራጎትም 164,000.00 የሚገመት የኢኮኖሚ ጥቅም ማጣታቸውንና የብር 100,000.00 የሞራል ጉዳት እንደደረሰባቸው ጠቅሰው በድምሩ ብር 264,000.00 (ሁለት መቶ ስልሳ አራት ሺህ ብር) ከነወለድ ወጪና ኪሣራ ጨምረው እንዲከፍሏቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡   የአሁኗ አመልካች ለተጠሪ ክስ በሰጡት መልስም፡- የተጠሪ የሙዚቃ ሥራ ለመካኒኩ ፊልም ማጀቢያነት የተጠቀሙት መሆኑን ሳይክዱ የሙዚቃው ሥራ ለፊልሙ መጠቀም ይችሉ እንደሆነ በአቶ  ዮናስ  ብርሃነ  መዋ  በኩል  ተጠሪን  ጠይቀውና  ተገናኝተንው  የተጠሪን        ስራ...

 • 99124 contract/ sale of immovable property/ form

  ተዋዋዮች የማይንቀሳቀስ ንብረት በሽያጭ ሲተላለፍ በህጉ በተደነገገው መሰረት ውል ለመዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርቦ የማስመዝገብ ግዴታን ስምምነታቸው ላይ ካካተቱና ነገር ግን ይህንን ተፈፃሚ ማድረግ ካልተቻለ የተዘጋጀው ስምምነት ረቂቅ እንጂ ከጅምሩ ውል ነው ተብሎ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሊነሱ የሚገባቸውን ጉዳዮች ማንሳት ሰህተት ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ.1723፣1810፣1885(1)   የሰ/መ/ቁ. 99124   የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ/ም       ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ   ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ     አመልካቾች ፡- 1ኛ  ወ/ሮ ስብለ ማሞ            ጠበቃ እሌኒ አስራት ቀረቡ 2ኛ አቶ ዳዊት ግርማ ተጠሪዎች፡- 1ኛ የ፲ አለቃ  ተስፋየ  በዛብህ ወራሾች 1. ወ/ሮ      ትግስት        ተስፋየ   - ቀርቧል 2. ወ/ሮ  አስራት  ተስፋየ -ቀርቧል   2ኛ ወ/ሮ ጥሩነሽ ሀይሉ -ወኪል ወ/ሮ ትግስት ተስፋዬ ቀርቧል፡፡ መዝገቡን መርምረን የሚከተውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡  ፍ ር ድ   ይህ ጉዳዩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን በዚሁ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካቾች ከሰሾች፤ የአሁኑ ተጠሪዎች ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የስር ከሳሾች የካቲት 22 ቀን 2005ዓ/ም በተፃፈ አቤቱታ ያቀረቡት ክስ መሰረታዊ ይዘቱ በግራ ቀኙ ጥቅምት 30/2005ዓ/ም በተደረገው የሽያጭ ውል በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/07 በተከሳሾች ስም ተመዝግቦ የሚገኘው የቦታው የስፋት መጠን 105ካ/ሜ ካርታ ቁጥር ኮ/ቀ/የማ/ን/መ/154/12199/00 የሆነውን ቤት በ800,000/ስምንት መቶ ሺ ብር /ሊሸጡልን የተዋዋልን ሲሆን በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሰነዶች ማረጋገጫ እና መዝገብ ጽ/ቤት እስከሚረጋገጥ ድረስ በቅድሚያ 50,000/ሀምሳ ሺ ብር/ በምስክር ፊት ቆጥረን ሰጠናል፡፡ ሆኖም ተከሳሾች ከዛሬ ነገ ሲሉ እሰከ ሶስት ወር ውል ያልፈፀሙ ሲሆን እንዲያውም አንደኛ ተከሳሽ የአእምሮ በሽተኛ እንደሆነ እና ውሉን በምናደርግበት ሰዓት ሁለተኛ ተከሳሽ  ይህኑን  ያልነገሩን  ሲሆን  በዚሁም  ምክንያት  ውሉ  ተፈፃሚ  መሆን...

 • 99447 contract/ contract of carriage/ damage

  በማጓጓዝ ውል ግንኙነት በደረሰ የሕይወት ሕልፈት የሚከፈል ካሣ በንግድ ህጉ መሰረት ስለመሆኑ   የሰ/መ/ቁ.99447 .ጥቅምት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.   ዳኞች:- አልማው ወሌ   ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች:- አቶ ተፈራ ጣሰው - የቀረበ የለም ተጠሪ:- ወ/ሮ ፈንታዬ በንቲ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል፡፡    ፍ  ር ድ   ጉዳዩ በተሸከርካሪ መገልበጥ ምክንያት ከደረሰ የሞት አደጋ ጋር ተያይዞ የተነሳ የጉዳት ካሳ ክፍያ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት የምዕራብ ሸዋ ዞን ከ/ፍ/ቤት ከሳሽ በመሆን ክሱን የመሰረቱት ተጠሪ ናቸው፡፡ ተጠሪ ክስ የመሰረቱት በአሁኑ አመልካችና አቶ አስማማው ደረጀ በተባሉ ግለሰብ ሲሆን ክሱም በ15/03/2003 ዓ.ም. አዘጋጅተው ያቀረቡት ነው፡፡ የክሱ ይዘት ባጭሩ፡- ንብረትነቱ የተከሳሾች የሆነና የሰሌዳ ቁጥሩ 3-30038 አ.አ. የሆነ አይሱዚ ተሽከርካሪ በ04/05/2002 ዓ.ም. በደረሰ አደጋ በመገልበጡ ከጌዶ ወደ አዲስ አበባ ተሳፍረው ሲጓዙ በነበሩት የከሳሽ ባለቤት አቶ እንዳሉ ባይሳ ላይ የሞት አደጋ እንደደረሰ፣ ባለቤታቸው በንግድ ስራ ያገኙት ከነበረው ገቢ ከሳሽን እንዲሁም የ 4 እና የ 2 ዓመት ዕድሜ ያላቸውን ሁለት ልጆቹን ያስተዳድር እንደነበረ እና በሞቱ ምክንያት በመተዳደሪያ ረገድ ጉዳት እንደደረሰባቸውና በጉዳቱ ጊዜ ደግሞ ወጪ ያወጡ መሆኑን የሚገልጽ ሆኖ በድምሩ ብር 349,192.61(ሶስት መቶ አርባ ዘጠኝ ሺህ አንድ መቶ ዘጠና ሁለት ብር ከስልሳ አንድ ሳንቲም)፣ የጠበቃ አበል 10% እና ለክሱ የወጣውን ወጪና ኪሳራ ተከሳሾች እንዲከፍሉ  ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት የተጠየቀበት ነው፡፡ 2ኛ ከሳሽ የነበረውን ግለሰብ ከተጠሪ ጋር በእርቅ በመጨረሳቸው ምክንያት ከክሱ ውጪ የሆኑ ሲሆን የአሁኑ አመልካች ግን ወደ ክርክሩ ተጠርተው በሰጡት መልስ ጉዳዩ ከስር 2ኛ...

 • 99667 contract/ part of contract

  የተዋዋዮች የውል ግንኙነት መሰረት ያደረገው ፕርፎርማን ሳይሆን ፕሮፎርማን ተከትሎ በፅሑፍ የተደረገን ውል በሆነ ጊዜ በፕሮፎርማው ላይ ተጠቅሶ ነገር ግን ተዋዋዮቹ የውላቸው አካል አድርገው ያልተሰማሙበት ጉዳይ በፕሮፎርማ ላይ የተጠቀሰ በመሆኑ ብቻ እንደውሉ አካል ተቆጥሮ በተዋዋዮቹ (ከተዋዋዮቹ) በአንዱ ላይ አስገዳጅነት እንዳለው አድርጎ መውሰድ ተገቢ ስላለመሆኑ የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2287-2300 ተፈፃሚነት የሚኖራቸው በተሸጠው እቃ ላይ የተገኘው ጉድለት መኖሩ በገዥው የታወቀው ከርክክቡ በኋላ በሆነ ጊዜ ስለመሆኑ የሰ/መ/ቁ. 99667   መስከረም 27 ቀን 2008 ዓ.ም.   ዳኞች፡-አልማው ወሌ   ረታ ቶሎሳ ሙስጠፋ አህመድ ቀነዓ ቂጣታ ለሊሴ ደሳለኝ   አመልካች፡- ቻኩ ቢዝነስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር -- የቀረበ የለም   ተጠሪ፡- ናሽናል ሞተርስ ኮርፖሬሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር  -ጠበቃ ነስቡ ሜኮ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል፡፡  ፍ ር ድ   ጉዳዩ የሽያጭ ውል አፈጻጸምን የሚመለከት ክርክር ሲሆን የተጀመረውም ከሳሽ የነበረው የአሁኑ ተጠሪ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ በነበረው የአሁኑ አመልካች ላይ ባቀረበው ክስ ነው፡፡ ከሳሽ በ26/07/2004 ዓ.ም. አዘጋጅቶ ያቀረበው ክስ ይዘትም ባጭሩ፡- ከሳሽ እና ተከሳሽ በ06/04/1998 ዓ.ም. ባደረጉት የሽያጭ ውል ከሳሽ ብዛታቸው 13 የሆነ ሬኖ ክራክስ ተሽርካሪዎችን/ሻሲዎችን/ የተጨማሪ እሴት እና የስም ማዛወሪያ ወጪዎችን ጨምሮ እያንዳንዳቸውን በብር 1,051,346 በጠቅላላው ደግሞ በብር 13,667,498 ለመሸጥ በመስማማት ተሽከርካሪዎቹን ከ29/02/2000 ዓ.ም. በፊት ለተከሳሽ ያስረከበ መሆኑን፣ተከሳሽ ከሽያጩ ገንዘብ ውስጥ ብር 9,434,248.80 በባንክ በኩል የከፈለ መሆኑን፣ከቀሪው ብር 4,233,249.80 ውስጥ ከሳሽ ብር 2,183,125 በውሉ አንቀጽ...

 • 99900 commercial law/ partnership

  በውል መሰረት ከተቋቋመ የሽርክና ማህበር ውስጥ አንድ የማህበር አባል ከማህበሩ ሊወጣበት ስለሚችልበት አግባብ   የሰ/መ/ቁ. 99900   መስከረም 25 ቀን 2008 ዓ.ም   ዳኞች፡- አልማው ወሌ   ረታ ቶሎሣ ሙስጠፋ አህመድ ቀነዓ ቂጣታ ሌሊሴ ደሣለኝ   አመልካች፡- አቶ ኃይሉ መንግስቱ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡-      1. አቶ ሬገን መሐመድ - አልቀረቡም 2. አቶ ጌታሁን ገሰሰ አልቀረቡም፡፡   መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡    ፍ  ር ድ   ጉዳዩ የሽርክና ማህበር በማቋቋም የተዋጣው ገንዘብ ይመለስልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩም የጀመረው የአሁኑ አመልካች በአፋር ክልል ገቢረሱ ከፍተኛ ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ በመሰረተው ክስ መነሻነት ነው፡፡ የክሱ ፍሬ ነገርም በአጭሩ ከተጠሪዎች ጋር በነበራቸው የሽርክና ውል መሰረት የእርሻ ስራ መጀመራቸውን ገልፆ በመካከሉ ግን አመልካች ከማህበሩ መውጣት መፈለጉን ተከትሎ ያዋጣው ገንዘብ ብር 38,900 አመልካች እንዲመለስለት በጠየቀው መሰረት ተጠሪዎች ገንዘቡን በሁለት ዙር ክፍያ ሊከፍሉ ከተስማሙ በኃላ ያለመከፈላቸውን ጠቅሶ በውሉ መሰረት ሊከፍሉ የተስማሙበትን ብር 38,900ና ብሩ ተከፍሎ እስኪያልቅ ድረስ  ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዲሁም በውሉ መሰረት ባለመፈፀማቸው ቅጣት/ ገደብ ብር 5000 እና ወጪና ኪሳራን ጨምሮ እንዲከፈልኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ሲሆን የስር 1ኛ ተከሳሽ የሆነው የአሁኑ 1ኛ ተጠሪም በበኩሉ ቀርቦ ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስ ፡- ከአመልካች ጋር በሽርክና በጋራ ስራ ለመስራት ገንዘብ ማዋጣቸውን አምኖ ሆኖም ግን አመልካች የዋጣውን ገንዘብ ለመመለስ አለመስማማቱን ወይም ውል አለመፈረሙንና አመልካች የውል ስምምነት ነው ብሎ ያቀረበው ሰነድም 2ኛ ተጠሪን ብቻ በሽማግሌዎች አማካኝነት    በመደለልና አታሎ ያስፈረመው ውል እንጂ እኔን ጭምር ያካተተ ባለመሆኑ ውሉ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጾ ይልቁንም በሽርክና ውላችን መሰረት የከዚህ ቀደሙን...